ምዕራፍ ፰
በመንግስቱም ላይ ጥል እና ፀብ ሆነ—አኪሽ ንጉሱን ለመግደል በመሀላ የተሳሰረ ሚስጢራዊው ሴራ ሰራ—ሚስጢራዊው ሴራዎች የዲያብሎስ ናቸው እናም ሀገሪቱንም የማጥፋት ውጤት አላቸው—የዘመኑ አህዛቦችም የምድሮችን፣ የህዝቦችን፣ እና የሃገሮችን ሁሉ ነፃነት ለመገልበጥ ወደሚፈልገው ሚስጢራዊ ሴራ እንዳይገቡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶአቸዋል።
፩ እናም እንዲህ ሆነ እርሱም ኦመርን ወለደ፤ ኦመርም በእርሱ ምትክ ነገሰ። እናም ኦመር ያሬድን ወለደ፤ እናም ያሬድ ወንድ እና ሴት ልጆችን ወለደ።
፪ እናም ያሬድ በአባቱ ላይ አመፀ፣ እናም ሔደ እናም በሔት ምድር ኖረ። እናም እንዲህ ሆነ የመንግስቱን ግማሽ እስከሚያገኝ ድረስ በአጭበርባሪ ቃላቶቹ ብዙ ሰዎችን ሸነገላቸው።
፫ እናም የመንግስቱን ግማሽ ባገኘ ጊዜ ከአባቱ ጋር ተዋጋ፣ እናም አባቱን በምርኮ ወሰደው፣ እናም በምርኮም እንዲያገለግል አደረገው፤
፬ እናም እንግዲህ፣ ኦመር በነገሰበት ጊዜ ዘመኑን አጋማሽ በምርኮ ላይ ነበር። እናም እንዲህ ሆነ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ፤ ከእነርሱ መካከልም ኤስረምና ቆሪያንተመር ነበሩ፤
፭ እናም በወንድማቸው በያሬድ ሥራዎች እጅግ ተቆጥተው ነበር፤ በዚህም የተነሳ ወታደሮችን አዘጋጁ እናም ከያሬድ ጋር ተዋጉ። እናም እንዲህ ሆነ ከእርሱም ጋር በምሽት ተዋጉ።
፮ እናም እንዲህ ሆነ የያሬድን ወታደሮች በገደሉአቸው ጊዜ እርሱንም ለመግደል ተቃርበው ነበር፤ እናም እርሱም እንዳይገድሉት፣ እናም መንግስቱንም ትቶ ለአባቱ እንደሚሰጥ ተማፀናቸው። እናም እንዲህ ሆነ እነርሱም ህይወቱ እንዲተርፍ አደረጉ።
፯ እናም እንግዲህ ያሬድም መንግስቱን ስላጣ እጅግ አዘነ፣ ምክንያቱም እርሱ ልቡን በመንግስቱ ላይ እናም በዓለም ክብር ላይ አድርጎ ነበርና።
፰ እንግዲህ የያሬድ ሴት ልጅ ብልጥ ነበረች፣ እናም የአባቷን ሃዘንም ተመልክታ የአባቷን መንግስት ማዳን የምትችልበትን ዕቅድ ለመቀየስ አሰበች።
፱ እንግዲህ የያሬድ ሴት ልጅም እጅግ መልከ መልካም ነበረች። እናም እንዲህ ሆነ ለአባቷም እንዲህ ስትል ተናገረችው፥ በምን ምክንያት ነው አባቴ በኃይል ያዘነው? አባቶቻችን ታላቁን ጥልቅ አቋርጠው ያመጧቸውን መዛግብት አላነበባቸውምን? እነሆ፣ በሚስጢራዊው ዕቅዳቸው መንግስታቸውን እናም ታላቁን ክብራቸውን እንዳገኙ የሚናገር የጥንቶቹን በተመለከተ ታሪክ የለምን?
፲ እናም እንግዲህ፣ ስለዚህ አባቴም አኪሽ የቂምኖርን ልጅ ይጥራ፤ እናም እነሆ፤ እኔ ቆንጆ ነኝ፣ እናም በፊቱም እወዛወዛለሁ፣ እናም አስደስተዋለሁ፣ ስለዚህ ለሚስትነት ይፈልገኛል፤ ስለዚህ እኔን ለሚስትነት እንድትሰጠው ይፈልግሀል፣ ከዚያም እንዲህ በለው፥ የንጉሱን የአባቴን ራስ የምታመጣልኝ ከሆነ እርሷን እሰጥሃለሁ።
፲፩ እናም እንግዲህ ኦመር ለአኪሽ ወዳጅ ነበር፤ ስለዚህ ያሬድ አኪሽን በጠራው ጊዜ የያሬድ ሴት ልጅ በፊቱ ተወዛወዘች እናም አስደሰተችው፣ በዚህም የተነሳ ለሚስትነት ፈለጋት። እናም እንዲህ ሆነ ለያሬድም እንዲህ አለው፥ እርሷን ለሚስትነት ስጠኝ።
፲፪ እናም ያሬድ እንዲህ አለው፥ የንጉሱን የአባቴን ራስ የምታመጣልኝ ከሆነ እርሷን እሰጥሃለሁ።
፲፫ እናም እንዲህ ሆነ አኪሽ በያሬድ ቤት ዘመዶቹን በሙሉ ሰበሰባቸው፤ እናም እንዲህ ሲል ተናገራቸው፥ እኔ በምፈልግባችሁ ነገር ለእኔ ታማኝ ለመሆን ትምሉልኛላችሁን?
፲፬ እናም እንዲህ ሆነ አኪሽ ከፈለገው እርዳታ የተለየን የሚፈልግ ራሱን እንዲያጣ፣ እነርሱ ሁሉም በሰማይ አምላክ፣ እናም ደግሞ በሰማያት፣ እናም ደግሞ በምድር እናም በህይወታቸው መሃላን አደረጉ፤ እናም አኪሽ ለእነርሱ ያሳወቀውን ማንኛውን ነገር የሚገልፅ እርሱም ህይወቱን ያጣል።
፲፭ እናም እንዲህ ሆነ እነርሱም ከአኪሽ ጋር ተስማምተው ነበር። እናም አኪሽ በጥንት ጊዜ ሥልጣንን ይፈልጉ በነበሩት የተሰጣቸውን ከመጀመሪያው ገዳይ በነበረው በቃየን የተላለፈውን መሃላ እንዲገቡ አደረጋቸው።
፲፮ እናም እነርሱም ይህንን መሃላ ለህዝባቸው ለመስጠት፤ እነርሱንም በጨለማ ለማቆየት፤ ሥልጣንን ለማግኘት የሚፈልጉትን ለመርዳት፤ እናም ለመግደል፣ እናም ለመዝረፍ፣ እናም ለመዋሸት፣ እናም ሁሉንም ዓይነት ክፋቶችን እና ዝሙት ለመፈፀም በዲያብሎስ ሃይል ተጠብቀው ነበር።
፲፯ እናም የጥንት የሆኑትን ነገሮች በሙሉ እንዲፈልግ ያደረገችው የያሬድ ሴት ልጅ ነበረች፤ እናም ያሬድ በአኪሽ ልብ ውስጥ ይህንን አስቀመጠ፤ ስለዚህ፣ አኪሽም ለነገዶቹ እናም ጓደኞቹም የፈለገውን ነገር እንዲያደርጉለት መልካም በሆነ በተስፋ ቃል በመምራት መሃላን አስገባቸው።
፲፰ እናም እንዲህ ሆነ እነርሱም በጥንት ጊዜ እንደነበሩት ሚስጢራዊ ሴራን አቋቋሙ፤ ህብረቱም በእግዚአብሔር ፊት ከሁሉም በላይ የከፋና የረከሰ ነው።
፲፱ ጌታም በሚስጢራዊ ሴራዎች አይሰራም፣ ወይም ሰዎችም ደም እንዲያፈሱ አይፈቅድም፣ ነገር ግን ከሰው መፈጠር ጀምሮ ይህንን ተግባር ከልክሏል።
፳ እናም እንግዲህ፣ እኔ ሞሮኒ፣ የመሃላውን አይነትም እንዲሁም ህብረቱን አልፅፍም፣ ምክንያቱም እነርሱ በህዝቡ ሁሉ የነበሩ መሆናቸውን እንዳውቅ ተደርጌአለሁና፣ እናም በላማናውያንም መካከል አሉ።
፳፩ እናም አሁን እኔ ለምናገርላቸው ሰዎች እናም ደግሞ ለኔፊ ሕዝብ ጥፋት ምክንያት ሆነዋል።
፳፪ እናም በሁሉም ሀገር እስከሚሰራጩ ድረስ፣ ሥልጣንን እናም ጥቅምን ለማግኘት እንደዚህ አይነቱን ሚስጢራዊ ሴራዎች የሚደግፍ ማንኛውም ሀገር፣ እነሆ ይጠፋል፤ ምክንያቱም ደማቸው በእነርሱ የፈሰሰባቸው ቅዱሳንን በእነርሱ ላይ ለበቀል ሁልጊዜም ከምድር እንዲጮኹ እናም ተመልሶም እንዳይበቀላቸው ጌታ አይፈቅድምና።
፳፫ ስለሆነም፣ አህዛብ ሆይ፣ ስለዚህ ለኃጢአቶቻችሁ ንሰሃ ትገቡ ዘንድ፣ እናም ሥልጣንን እና ጥቅምን ለማግኘት የተሰሩት እነዚህ የግድያ ህብረቶችም ከእናንተ በላይ እንዲሆኑ እንዳትፈቅዱላቸው እነዚህ ነገሮች ለእናንተ መታየታቸው ለእግዚአብሔር ጥበብ ነው—እናም አዎን፣ እነዚህ ነገሮች እንዲሆኑም ከፈቀዳችሁ ሥራው አዎን፣ የጥፋት ሥራም በእናንተ ላይ ይሆናል፣ አዎን፣ የዘለዓለማዊው አምላክ የፍርድ ጎራዴ እናንተን ለመፈንቀል እና ለማጥፋት በላያችሁ ላይ ይወድቃል።
፳፬ ስለሆነም፣ በዚህ በእናንተ መካከል በመጣው ሚስጢራዊው ሴራ የተነሳ እነዚህን ነገሮች በእናንተ ላይ መምጣታቸውን በምትመለከቱበት ጊዜ፣ ስለአሰቃቂ ሁኔታችሁ ስሜታችሁን እንድታነቁ ዘንድ ጌታ ያዛችኋል፤ ወይም በተገደሉት ደማቸውም መፍሰስም የተነሳ ወዮላቸው፤ ምክንያቱም በዚህ ላይ እናም ደግሞ ይህን ባቋቋሙት ላይ ለበቀል ከመሬት ይጮሃሉና።
፳፭ እናም እንዲህ ይሆናል ሚስጢራዊውን ህብረት የመሰረተ የምድርን፣ የሀገሪቷን እና የህዝቡን ነፃነት ለመጣል ይፈልጋል፤ እናም የሀሰት አባት በሆነው፣ እንዲሁም የመጀመሪያ ወላጆቻችንን ያታለለው፣ አዎን፣ ይኸው ሀሰተኛ በሆነው የሰውን ልጅ ከመጀመሪያ ጀምሮ ባሳሳተው፣ ከመጀመሪያ ጀምሮ የሰዎችንም ልብ ነቢያትን እንዲገድሉአቸው፣ በድንጋይ እንዲወግሩአቸው፣ እናም እንዲጥሏቸው ባጠጠረው በሀሰት አባት በዲያብሎስ የተገነባ ስለሆነ፣ ይህም የህዝብን ሁሉ ጥፋት ያመጣል።
፳፮ ስለዚህ፣ ክፉ ነገርም ይወገድ ዘንድ፣ እናም ሰይጣንም በሰው ልጆች ልብ ላይ ኃይል የማያገኝበት፣ ነገር ግን ያለማቋረጥ መልካም ነገርን ለመስራት የሚገፋፋበት፣ ወደ ሁሉም ፅድቁ ምንጭ መጥተው የሚድኑበት ጊዜ ይመጣ ዘንድ እኔ ሞሮኒ እነዚህን ነገሮች እንድፅፍ ታዘዝኩ።