ሴት ልጆች በቃል ኪዳን ውስጥ
ወደ ሰማይ አባታችን የምንጓዝበት … መንገድ ከእግዚአብሔር ጋር በምንገባቸው ቃል ኪዳናት ምልክት የተለየ ነው።
በዚህ ምሽት በመንፈስ ሀይል አማካኝነት ተምረናል። እነዚህ በታላቅ የእህት መሪዎች የተናገሯቸው ቃላት በእኔ እንዳደረጉት በልባችን እንዲገቡ ጸሎቴ ነው።
ይህ ታሪካዊ ስብሰባ ነው። የስምንት አመት እና ከዚያ በላይ እድሜ ያላቸው የቤተክርስቲያኗ ሴቶች በዚህ ምሽት ከእኛ ጋር እንዲሆኑ ተጋብዘዋል። ብዙዎቻችን መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር እንዲገኝ ጸልየናል። እነዚህ እህቶች ሲናገሩ እና የሚያነሳሱ መዝሙሮችን ስንሰማ ያም በረከት ተሰጥቷል። የማበረታቻ ቃላትን ሳቀርብ እና ከሰማናቸው በተጨማሪ ምስክርነቴን ስሰጥ መንፈስ ከእኛ ጋር መገኘቱን እንዲቀጥል እጸልያለሁ።
ወደ ሰማይ አባታችን በምንጓዝበት ጊዜ ስለምንሄድበት መንገድ በዚህ ምሽት እናገራለሁ። ያም መንገድ ከእግዚአብሔር ጋር የምንገባቸው ቃል ኪዳናት ምልክት የተለየ ነው። ስለ እነዛን ቃል-ኪዳኖች በመግባትና በመጠበቅ ስለሚመጣው ድስታ እናገራችኋለው።
ብዙዎቻችሁ በቅርብ የተጠመቃችሁ እና መንፈስ ቅዱስን እጅ በመጫን የተቀበላችሁ ናችሁ። ለእናንተ ያ ትዝታ አዲስ ነው። ሌሎቻችሁ የተጠመቃችሁት ከብዙ ጊዜ በፊት ነበር፣ ስለዚህ የዛ የቃል-ኪዳን ልምድ ስሜት ትውስታ ምናልባት ያነሰ ግልፅ ይሆናል፣ ነገር ግን የቅዱስ ቁርባንን ጸሎት በምትሰሙበት ጊዜ እነዛ ስሜቶች ተመልሰው ይመጣሉ።
ያን የጥምቀት ካል ኪዳን ስንገባ እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ስንቀበል ስለነበረበት ቀን ማንም ሰው አንድ አይነት ትዝታ አይኖረውም። ነገር ግን እያንዳንዳችንም የእግዚአብሔርን ተቀባይነት ተሰምቶናል።እናም ይቅርታ የማድረግና ይቅርታን የመቀበል ፍላጎት እናም ትክክለኛ ለማድረግ ተጨማሪ የልብ ውሳኔ ነበሩን።
እነዚያ ስሜቶች ምን ያክል በልባቹ ውስጥ ዘልቀው መግባታቸው በታላቅ የሚወሰነው በአፍቃሪ ሰዎች ምን ያክል በመዘጋጀታችሁ ነበር። በቅርብ ወደ መንግስቱ የመጣችሁት ከእናታችሁ አጠገብ በመቀመጣችሁ እየተባረካችሁ መሆኑን ተስፋ አደርጋለው።፡ከሆናችሁ፣አሁኑኑ የአመሰግናለው ፈገግታ መላክ ትችላላችሁ። በፊለዶልፊያ፣ ፔንስልቫኒያ ከጥምቀቴ በኋላ በመኪናው ውስጥ ከእናቴ ኋላ ተቀምጬ የነበረኝን የደስታና የምስጋና ስሜት አስታውሳለሁ።
ያንን ቃል ኪዳን እንድገባና ከዛ በኋላ ለሚከተሉት ሁሉ እንድዘጋጅ ያደረገችው እናቴ ነበረች። ለዚህ ከጌታ የመጣ ሀላፊነት ታማኝ ነበረች፥
“እና ደግሞ፣ ወላጆች በፅዮን፣ ወይም በተደራጁት ካስማዎቿ፣ ውስጥ ልጆች እስካሏቸው ድረስ፣ ስለ ንስሀ፣ ስለ በህያው እግዚአብሔር ልጅ በክርስቶስ እምነት፣ እናም ስለ ጥምቀት እና ስለ እጆችን በመጫን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ስለመቀበል ትምህርትን ባያስተምሯቸው፣ስምንት አመት ሲሞላቸው ኃጢአቱ በወላጆቹ ራስ ላይ ይሆናል።
“ይህም ለፅዮን ፣ወይም በማንኛውም በተደራጁት ካስማዎቿ፣ ኗሪዎች ህግ ይሆናልና።
“እናም ልጆቻቸውም ለኃጢአቶቻቸው ስርየት በስምንት አመታቸው ይጠመቁ፣ እናም መንፈስ ቅዱስንም ይቀበሉ።”1
እናቴም የራሱዋን ድርሻ ተወታለች። በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ እንደተፃፈው በእንደ አልማ አይነት ቃላቶች ልጆቿን አዘጋጅታለች፥
“እናም እንዲህ ሆነ እንዲህም አላቸው፥ እነሆ፣ የሞርሞን ውሃ ይህ ነው፣ (ለዚህም ነበር የተጠሩት) እናም አሁን፣ እናንተ ወደ እግዚአብሔር በአንድ አላማ ለመምጣት እንደፈለጋችሁ፣እናም ህዝቡ ትባሉ ዘንድ፣ እናም አንዳችሁ የአንዳችሁን ሸክም ለመሸከም ፈቃደኞች በመሆን እንዲቀላችሁ ታደርጉ ዘንድ፤
አዎን፣ እናም ከሚያዝኑት ጋር ለማዘን ፈቃደኞች ትሆኑ ዘንድ፤እናም መፅናናትን ለሚፈልጉ ካፅናናችኋቸው፤ እናም በሁሉም ጊዜ በሁሉም ነገር የእግዚአብሔር ምስክር በመሆን ትቆሙ ዘንድ፣ በጌታ ትድኑ ዘንድ እስከ ሞትም ድረስ እንኳን በሁሉም ቦታ ትኖሩ ዘንድ እናም የፊተኛውን ትንሳኤ ከሚያገኙት ጋር ትቆጠራላችሁ ---
“አሁን እላችኋለሁ፣ ይህ የልባችሁ ፍላጎት ከሆነ፣ እርሱን እንደምታገለግሉ እናም ትዕዛዛቱን እንደምትጠብቁ፣ እርሱም በእናንተ ላይ መንፈሱን በብዛት ያፈስባችሁ ዘንድ በፊቱ እንደምስክርነት ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት በጌታ ስም ለመጠመቅ የሚያስቸግራችሁ ምንድን ነው?
“እናም አሁን ህዝቡ ይህንን አባባሉን በሰሙ ጊዜ፣ በደስታ አጨበጨቡ፣ እናም በደስታ ይህ የልባችን ፍላጎት ነው ብለው ጮኹ።”2
ያን የጥምቀት ቃል ኪዳን ስትሰሙ እጆቻችሁን አላጨበጨባችሁም ይሆናል፣ ነገር ግን በእርግጥም የአዳኝን ፍቅር እና ለእርሱ ሌሎችን ለመንከባከብ ታላቅ ውሳኔ ተሰምቷችኋል። እኔም “በእርግጠኝነት” ይህ ስሜት በሁሉም የሰማይ አባት ሴት ልጆች ልብ ውስጥ በጥልቅ ስለሚገኝ ነው ማለት እችላለው። ያም ከእርሱ ያገኛችሁ መለኮታዊ የውርሳችሁ ክፍል ነው።
ወደዚህ ህይወት ከመምጣታችሁ በፊት በእርሱ ሰልጥናችሁ ነበር። ለእናንተ በደንብ የተመረጡ ፈተናዎች እና እድሎች እንደሚኖሯችሁ እንድትረዱና እድትቀበሉ እረድቷችኋል። የሰማይ አባታችን በእነዚህ ፈተናዎች በደህንነት እንድታልፉ እና ሌሎችን በራሳቸው ፈተናበደህንነት እንዲያልፉ የምትረዱበት የደስታ እቅድ እንደነበረው ተምራችኋል። ይህም እቅድ ከእግዚአብሔር ጋር በምንገባው ቃል ኪዳን የተለየ ነው።
እነዚያን ቃል ኪዳኖች መግባት እና መጠበቅ የራሳችን ምርጫ ነው። በዚህ ህይወት ውስጥ ስለቃል ኪዳኖቹ እንኳል ለመማር እድል ያላቸው የሴት ልጆቹ ቁጥር ትንሽ ነው። እናንተ ከተመረጡት ጥቂቶች አንዶች ናችሁ። እናንተ፣ ውድ እህቶች፣ እያንዳንዳችሁ በቃል ኪዳን ውስጥ ያላችሁ ሴት ልጆች ናችሁ።
የሰማይ አባት ከመውለዳችሁ በፊት ስለሚኖራችሁ ልምዶች ከእርሱ ተለይታችሁና ወደ ምድር ስትመጡ አስተምሯኋል። ወደ እርሱ ቤት የምትመለሱበት መንገድ ቀላል እንደማይሆን ተምራችኋል። ያለእርዳታ ጉዞውን ለማድረግ በጣም ከባድ እንደሚሁንባችሁ ያውቃል።
በዚህ ህይወት ውስጥ እነዚያን ቃል ኪዳኖች ለመግባት መንገድ እንድታገኙ ብቻ ሳይሆን እንደ እናንተ የሰማይ አባት የቃል ኪዳን ሴት ልጆች በሆኑ ሌሎች እንድትከበቡም በረከት ሰጥቷችኋል።
በዚህ ምሽት ሁላችሁም እናንተን ለመርዳት እና ለመምራት ቃል ኪዳንበገቡት በእግዚአብሔር ሴት ልጆች መካከል በመገኘታችሁ በረከቶች ተሰምቷችኋል።የቃል-ኪዳን እህቶች ለማፅናናትና ለመርዳት ያን ውሳኔ እንደሚጠብቁት እና በፈገግታ እደሚሰሩት ያያችሁትን እኔም አይቻለው።
የእህት ሩቢ ሄይትን ፈገግታ አስታውሳለው። እርሳቸውም የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ቡድን አባል የነበሩት የሽማግሌ ዴቪድ ቢ. ሄይት ባለቤት ነበሩ። በወጣትነታቸው በፓሎ አልቶ፣ ካሊፎርኒያ እንደ ካስማ ፕሬዘደንትነት አገልግለው ነበር። በዎርዳቸው ውስጥ ስለሚገኙት በሚያ ሜድ ክፍል ውስጥ ስለሚገኙት ልጃገረዶች ይጸልዩ እና ይጨነቁ ነበር።
ስለዚህ ፕሬዘደንት ሄይት ሩቢ ሄይት እነዛን ልጃገረዶች እንዲያስተምሩ እንዲጠሩ ኤጲስ ቆጶስን ጠየቁ። በዛ ክፍል ውስጥ ያሉትን ልጃገረዶች ከፍ የሚያደርጉ፣ የሚያፅናኑ፣ እና የሚያፈቅሩ የእግዚአብሔር ምስክር እንደሚሆኑ ያውቁ ነበር።
እህት ሄይት ከሚያስተምሯቸው ሴቶች በ30 አመት እድሜ የሚበልጡ ነበር። ነገር ግንእነርሱን ካስተማሯቸው ከ40 አመታት በኋላ፣በእርሳቸው ክፍል ውስጥ ከነበሩት ልጃገረዶች ውስጥ አንዷ የነበረችውን ባለቤቴን በሚያገኙበት በእያንዳነዱ ጊዜ፣ እጃቸውን ዘርግተው፣ በፈገግታ፣ ለካቲ እንዲህ ይሉ ነበር፣ “የእኔ ማያሜድ።” ከፈገግታቸው በላይ ተመለከትኩኝ። እስካሁን ድረስ ልክ እንደራሳቸው ልጅ አድርገው ስለሚንከባከቧት አንድ እህት ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር ሰማው። የእርሳቸው ፈገግታና ደማቁ ሰላምታ የመጣው አንድን እህት እና የእግዚአብሔር ሴት ልጅ ወደ ቤት ወደሚያመራው የቃል ኪዳን መንገድ ላይ መሆኗን በማየታቸው ነው።
የሰማይ አባት እናንተ ሴት ልጁን ወደ ዘለአለም ሕይወት ወደሚያመራው የቃል-ኪዳን መንገድ ላይ እንድትጓዝ ስትረዱ በእናንተ ፈገግ ይላል። እናም ትክክለኛውን ለመምረጥ በምትጥሩበት በእያንዳንዱ ጊዜም ይደሰታል። እናንተ ማን እንደሆናችሁ ብቻ ሳይሆን ማን መሆን እንደምትችሉ ያያል።
መሆን ከምትችሉበት በላይ የተሻለ መሆን እንደምትችሉ የሚያስቡ የምድር ወላጆች ሊኖራችሁ ይችል ይሆናል። እኔ እንደዚህ አይነት እናት ነበረኝ።
በወጣትነቴ ሳላውቀው የቀረሁት ነገር ቢኖር የሰማይ አባቴ፣ የእናንተ የሰማይ አባት፣እኛ ወይም የምድር ወላጆቻችን እኛ ላይ ከሚያዩት በላይ ታላቅ ችሎታዎችንበልጆቹ ያያል። ወደ ችሎታችሁ በዛ መንገድ ላይ ወደ ላይ ስትገፉ፣ደስታን ያመጣለታል። የእርሱንም ተቀባይነት ሊሰማችሁ ይችላል።
ያን ግርማዊ ችሎታ የትም በሚገኙ በሴቶች ልጆቹ ይመለከታል። አሁን፣ ያ በእያንዳንዳችሁ ላይ ታላቅ ሀላፊነት ይጥላል። መንኛውንም የምታገኙትን ሰው እንደ እግዚአብሔር ልጅ እንድትንከባከቡ የጠብቅባችኋል። በዚህም ምክንያት ነው ጎረቤቶቻችንንእራሳችንን እንደምንወደው እንድንወዳቸውና ይቅር እንድንላቸው ያዘዘን። ለሌሎች ያላችሁ ደግነት እና ምህርት ከእርሱ እና ከሴት ልጆቹ እንደ መለኮታዊ ውርሳችሁ ይመጣሉ። የምትገናኟቸው እያንዳንዱ ሰዎች የሚወደዱ የመንፈስ ልጆቹ ናቸው።
ያ ታላቅ እህትነት ሲሰማችሁ፣የሚከፋፍሉን የሚመስሉን ይወድቃሉ። ለምሳሌ፣ ወጣትና ጎልማሳ እህቶች ስሜታቸውን ሰው እንደሚረዳቸውና እንደሚቀበላቸው በመገመት ያካፍላሉ። እንደ እግዚአብሔር ሴት ልጆች ከልዩነታችሁ በላይ አንድ ናችሁ።
በዛ አስተያየት፣ ወጣት ሴቶች የእነርሱን ወደ ሴቶች መረዳጃ መቀላቀል ሊያውቋቸው ሊያደንቋቸው እና ሊወዷቸው ከሚችሉት ሰዎች የእነርሱን የእህቶች ቀለበት ለማሳደግ እድሎችን መፈለግ።
ያ ምን መሆን እንደምንችል ለማየት የሚያስችለን በቤተሰቦች እና በመጀመሪያ ክፍል ውስጥ እያደገ ነው። በቤተሰብ ምሽት እና በመጀመሪያ ክፍል ፕሮግራሞች ውስጥ እየተከሰተ ነው። ትንንሽ ልጆች አዳኙ ከትንሳኤው በኋላ ሲያስተምራቸው አንደበታቸውን በፈታበት ጊዜ እንደነበረው አይነት ታላቅ እና አስደናቂ ነገሮችን ለመናገር እየተነሳሱ ነው።3
ምናልባት ሰይጣን እህቶችን በመጀመሪያው እድሜዎቻቸው እያጠቃቸው ሲሆን፣ ጌታ ግን እህቶችን ከፍ ከፍ ወዳለ መንፈሳዊነት እያሳደጋቸው ነው። ለምሳሌ፣ ወጣት ሴቶች እናቶቻቸውን ቅድመ አያቶቻቸውን ለማግኘትና ለማዳን እንዴት የቤተሰብ ምርመራ መጠቀም እንደሚችሉ ያስተምሯቸዋል። የማውቃቸው አንዳንድ ወጣት እህቶች ከኤልያስ መንፈስ በላይ ካለ ምንም መገፋፋት በጠዋት ተነስተው በምትክነት በቤተ-መቅደስ ውስጥ ለመጠመቅ ይመርጣሉ።
በምድር ውስጥ በሚገኙ ሚስዮኖች፣ እህቶች እንደ መሪዎች እንዲያገለግሉ እየተጠሩ ነው። ጌታ የሴቶችን ልብ እንዲያገለግሉ በብዙ ቁጥር በመንካት የእነርሱን የአገልግሎት አስፈላጊነት ፈጠረ። ከትንሽ በላይ የሚሆኑ የሚስዮን ፕሬዘደንቶች እህት ሚስዮኖች በጣም ሲበዛ ሀይለኛ ሰባኪዎች እና መሪዎች ሲሆኑ አይተዋል።
እንደ ሙሉ ጊዜ ሚስዮኖች ብታገለግሉም ወይም ባታገለግሉም፣የታላቅ ሴቶችን ምሳሌ በመከተል ጋብቻችሁን የሚያበለጽግ እና ልዑል ልጆችን ለማሳደግ የሚያስችላችሁን ተመሳሳይ ችሎታ ለማግኘት ትችላላችሁ።
የሰው ዘር እናት የሆነችውን ሔዋን አስቧት።ሽማግሌ ራስል ኤም ኔልሰን ስለሔዋን እንዲህ አሉ፣ “እኛ እና የሰው ዘር በሙሉ በሔዋን ታላቅ ጉብዝና እና ጥበብ ለዘለአለም የተባረክን ነን። የመጀመሪያውን ፍሬ በመብላት፣ መደረግ የሚገባውን አደረገች። አዳም ይህን ለማድረግም ጥበበኛ ነበረ።”4
ሔዋን ወደ ቤተሰቧ ማምጣት የቻለችውን በረከት እያንዳንዷ የሔዋን ሴት ልጅ ወደ ቤተሰቧ ለማምጣት ብቃቱ አላት። በቤተሰቦችን በመመስረት ረገድ እርሷ በጣም አስፈላጊ ነበረች ስለሆነም ሰለ እርሷ ፍጥረት ይህኛው ገለፃ አለን፣ “እና አማልክቱም እንዲህ አሉ፥ ለሰውየው እረዳት እንፍጠርለት፣ ሰውየው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለምና፣ ስለዚህ ለአርሱ እረዳት እንፈጥርለታለን።”5
ሔዋን ለአዳም እና ለቤተሰቧ ምን ያህል እርዳታ እንደነበረች አናውቅም። ነገር ግን ስለሰጠችው አንድ ታላቅ ስጦታ እናውቃለን፣ ይህም እያንዳንዳችሁም መስጠት የምትችሉት ነገር፥ ከፊት ያለው መንገድ ከባድ በመሰለበት ሰአት፣ ወደ ቤት የሚያመራውን መንገድ እንዲያዩ እረዳቻቸው። “እና ሚስቱ ሔዋንም እነዚህን ነገሮች በሙሉ ሰማች እና ደስተኛ ነበረች፣ እንዲህ አለች፥ ባናጠፋ ኖሮ ዘርም አይኖረንም ነበር፣ እና መልካምና ክፉን፣ እናም የመዳንን ደስታ፣ በመተላለፋችን ምክንያት ባይሆን ኖሮ ዘር አይኖረንም ነበር እናም መልካምና መጥፎ አናውቅም ነበር የመዳናችንን ደስታ እና እግዚአአብሔር ለታዛዦች ሁሉ የሰጠውን የዘላለም ሕይወት ባላወቅን ነበር ።”6
የምትከተሉት የእርሷ ምሳሌ አላችሁ።
በራዕይ፣ ሔዋን ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚመራውን መንገድ አስታወሰች። የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ የዘለአለም ህይወትን በቤተሰቦች ውስጥ እውን እንዲሆን እንደሚያደርግ አወቀች።ከሰማይ አባቷ ጋር የገባችውን ቃል-ኪዳኖቸ በጠበቀችበት ሰአት፣ አዳኙና መንፈስ ቅዱሱ እሷንና ቤተሰቧን ምንም አይነት ሀዘንኖችና መከፋቶች ቢመጡ ሲወጡት እንዳዩአቸው፣ እርሷ እርግጠኛ እንደነበረች እናንተም መሆን ትችላላችሁ። በእነርሱ ማመን እንደምትችልም ታውቅ ነበር።
“በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤
በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።”7
ሔዋን ሀዘን እና ተስፋ መቁረጥ እንዳጋጠማት አውቃለሁ፣ ነገር ግን እርሷ እና ቤተሰቧ ከእግዚአብሔር ጋር አብረው ለመኖር መመለስ እንደሚችሉ በማወቋ ደስታ እንዳገኘች አውቃለሁ። እዚህ ያላችሁ ብዙዎቻችሁ ሀዘን እና ተስፋ መቁረጥ እንደሚያጋጥማችሁ አውቃለሁ። እንደ ሔዋንወደ ኋላ ስትመለሱ እርሷ የተሰማትን ያንን ተመሳሳይ ደስታ እንዲሰማችሁ በረከቴን እተውላችኋለሁ።
አብ እግዚአብሔር እናንተን በፍቅር እንደሚጠብቅ እርግጠኛ ምስክርነት አለኝ።፡ይህን የማውቀው እናንተን እንደሚወዳችሁ ስለማውቅ ነው። እያንዳንዳችሁን ይወዳል። እናንተ በቃል-ኪዳን ውስጥ ያላችሁ የእርሱ ሴት ልጆች ናችሁ። ስለሚወዳችሁ፣ ራሳችሁን እና ሌሎችን ወደ እርሱ መገኛ መመለሻ መንገድ ላይ ወደ ላይ ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልጋችሁን እርዳታ ያዘጋጃል።
አዳኝ ለኃጢያቶቻችን በሙሉ ዋጋ እንደከፈለ እና መንፈስ ቅዱስ ስለእውነት እንደሚመሰክር አውቃለሁ። በዚህ ስብሰባ ውስጥ ያንን መፅናናት ተሰምቷችኋል። ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን የሚያስሩ ቁልፎች በዳግም እንደተመለሱ ምስክርነት አለኝ። በሕይወት ባለው ነብያችን በፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን ዛሬ ተይዘዋል አንዲሁም አገልግሎት ላይ ውለዋል። እነዚህን የማፅናኛ እና የተስፋ ቃሎች ለእናንተ በእርሱ ለተወደዳችሁ የቃል ኪዳን ሴት ልጆቹ እተውላችኋለው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።