ለእምነት በእውነት መኖር
እያንዳንዳችን ቅድመ አባቶቻችን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን እንዲቀላቀሉ ያደረጋቸውን የእምነት እና የመስዋት ታሪክ ካወቅን በትልቅ እንባረካለን።
የቤተክርስቲያንን ታሪክ በጣም እወዳለሁ። በእርግጥ ልክ እንደ አብዛኞቻችሁ ወንጌልን ተቀብለው ለእምነታቸው በእውነት ስለኖሩት ስለ አስገራሚ ቅድመ አያቶቻችን ጥረት ስማር የራሴ እምነት ጠነከረ።
ከወር በፊት፣ ከጊልበርት አሪዞና ቤተመቅደስ አውራጃ 12 ሺህ አስገራሚ ወጣቶች ባለቀው አዲሱ ቤተመቅደሳቸው በዳንስ እና በትያትር አከበሩ፣ ፅድቅን ለመኖር ፍላጎታቸውን በማሳየት። የድግሱ መርህ ቃል “ለእምነት በእውነት መኖር” ነበር።
ልክ እነኛ ታማኝ የአሪዞና ወጣቶች እንዳረጉት፣ እያንዳንዱ የኋለኛው ቀን ቅዱስ “ለእምነቱ በእውነት ለመኖር” ቃል መግባት አለበት።
የመዝሙሩ ቃላቶች እንዲህ ይላሉ “ወላጆቻችን ለተንከባከቡት እምነት በእውነት መኖር” (ለእምነት በእውነት መኖር” መዝሙር ቁጥር 254)።
እኛ መጨመር እንችላለን “ቅድመ ወላጆቻችን ለተንከባከቡት እምነት በእውነት መኖር”
እነኛ የተነሳሱ የአሪዞና ወጣቶች እያንዳንዳቸው የራሳቸውን የቤተክርስቲያ ታሪክ ይወቁ አይወቁ አላቅም-- ቤተሰባቸው እንዴት የቤተክርስቲያን አባል እንደሆኑ ያለውን ታሪክ ካወቁ፤ ሁሉም የኋለኛው ቀን ቅዱስ የቅድመ አያቶቻቸውን ወደ ወንጌል እንዴት እንደተለወጡ ያለውን ታሪኮችን ቢያቁ በጣም ድንቅ ነው።
የመስራቾች ተዋረድ ሆናችሁም አልሆናችሁም፣ የሞርሞን መስራች ቅርስ አምነት እና መስዋት የእናንተ ቅርስ ነው። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የሚያኮራ ቅርስ ነው።
በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የሆነው አንዱ ምዕራፍ የተፈጠራው ውልፎርድ ውድሩፍ፣ የጌታ ሐዋርያ፣ 1840 ቤተክርስቲያኗ ከተቋቋመች አስር ዓመት በኋላ የተመለሰውን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በመላው ታላቅ ብርቴን እያስተማረ ሳለ ነበር።
ውልፎርድ ውድሩፍ እና ሌሎች ሐዋርያቶች ትኩረታቸውን ያደረጉት ሊቨርፑል እና ፕርስተን በሚባል የእንግሊዝ ግዛት ውስጥ ነበር፣ ብዙ ውጤትም ነበራቸው። የቤተክርስቲያ ሽማግሌ ውድሩፍ፣ በኋላ ላይ የቤተክርስቲያ ፕሬሰዳንት መሆን የቻለው፣ ጠቃሚ በሆነው ስራው ላይ እግዚያብሄር እንዲመራው በተከታታይ ይፀልይ ነበር። የሱ ፀሎት ወደ ሌላ ቦታ ሄዶ ወንጌልን እንዲያስተምር አነሳሳው።
ከሰማይ ነገርን እንድናደርግ ግፊት ሲሰማን ወዲያው እንድናደርገው ፕሬሰዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን አስተምሮናል---- አናራዝምም። ውልፎርድ ውድሩፍ ያረገውም ልክ እንደዛ ነው። ወደ ደቡብ እንዲሄድ ከመንፈስ ቁዱስ በተቀበለው ግልፅ ምሬት መሰረት፣ የቤተክርስቲያ ሽማግሌ ውድሩፍ ወዲያው ያለበትን ቦታ ትቶ በደቡብ እንግሊዝ የእርሻ ሀገር ወደ ሆነው ሄርፎርድሻየር ወደምትባል የእንግሊዝ ክፍል ተጓዘ። አዛ “በደስታ ልብ እና በታላቅ ምስጋና አቅራቢነት “እንኳን ደህና መጣህ” የሚባልበትን ቦታ ጆን ቤንቦው በሚባል በሀብታም ገበሬ ቤት አገኘ (ውልፎርድ ውድሩፍ፣ በመታየስ ኤፍ ካውሊ፣ Wilford Woodruff: History of His Life and Labors as Recorded in His Daily Journals ውስጥ [1909]፣ 117)።
600 ያለው የሰው ቡድን፣ የተባበሩት ወንድማማቾች ብለው ራሳቸውን የሚጠሩት “ብርሃን እና እውነትን ለማግኘት ፀልየው” ነበር (ውልፎርድ ውድሩፍ፣ በ Teachings of Presidents of the Church: Wilford Woodruff ውስጥ [2004]፣ 91)። ለጸሎታቸው መልስ ይሆን ዘንድ ጌታ ውልፎርድ ውድሩፍ ላከው።
የቤተክርስቲያ ሽማግሌ ውድሩፍ ትምህርት ወዲያው ፍሬን አፈራ፣ አናም ብዙ ተጠምቀው ነበር። በሄርፎርድሻየር ብረገም ያንግ እና ዊልያም ሪቻርድስ ተቀላቀሉ፣አናም እነኚ ሶስት ሐዋርያቶች አስገራሚ ውጤት ነበራቸው።
በትንሽ ዋራት ውስጥ ብቻ፣ ቤተክርስቲያንን ለተቀላቀሉ 541 አባሎች33 ቅርንጫፎችን አቋቋሙ። የእነሱ አስገራሚ ስራቸው ቀጠለ፣ ቀስበቀስ የተባበሩት ወንድማማቶች አባል ሁሉም በሚባል ሁኔታ ወደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የእአሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተጠመቁ።
የሴት ቅም ቅም አያቴ ሃና ማርያ ሐሪስ የውልፎርድ ውድሩፍን ትምህርት ከሰሙት የመጀመርያዋ አንዷ ነበልች። የእግዚአብሔርን ቃል አንደ ሰማች እና ለመጠመቅ እንደፈለገች ለባሏ፣ ሮበርት ሐሪስ ጀአር አሳወቀችው። ሮበርት የሚስቱን ዘገባ ስሰማ አልተደሰተም ነበር። ቀጥሎ በሚሰጠው የሞርሞን ሚስዮኖች ስብከት ላይ አብሯት እንደሚሄድ፣ እና ከዚያ የሚያስተምረውን ትምህርት እንደሚያርመው ነገራት።
ከተሰብሳቢዎቹ ፊት ለፊት ቅርብ በመቀመጥ፣ በስብከቱ ላለመሳብ ባለ ጥብቅ ፍላጎት፣ እንደውም ጎብኚ አስተማሪውን በጫጫታ ግራ ለማጋባት፣ ልክ ሚስቱ እንደሆነችው ሮበርት በተመሳሳይ መንገድ በመንፈስ ቅዱስ ተነካ።
የእነሱ የእምነት ታሪክ እናፍቅር ከሌሎች ሺዎች ጋር ተመሳሳይ ነው፤ የወንጌልን መልክት ሲሰሙ፣ እውነት እንደሆነ አወቁ።
ቅዱስ መፅሐፍ እንደሚለው “በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል” (ዮሐንስ 10፥27)።
የእረኛውን ድምፅ በመስማት፣ ወንጌልን ለመኖር የጌታን ነቢይ ምሬት ለመከተል ህይወታችውን ሙሉ ሰጡ። “ወደ ፅዮን ተሰብሰቡ” የሚለውን ጥሪ በመስማት እንግሊዝ ያለውን ቤታቸውን ወደ ኋላ ጥለው በመሄድ፣ አትላንቲክን በማቋረጥ፣ አና ናቩ ውስጥ ከቅዱሳን ጋር ተቀላቀሉ።
ወንጌልን በሙሉ ልባቸው ተቀበሉ፣ በአዲሱ ምድር ላይ ለመቋቋም አየጣሩ ሳሉ በአስራታቸው እና በጉልበት ስራ የናቩ ቤተመቅደስ ግንባታ ላይ አግዘዋል። በቤተመቅደስ ግንባታ ላይ በየአስር ቀኑ በመስራት።
የሚወዱትን ነቢይ ጆሴፍ ስሚዝ እና የወንድሙን ሃይረም ሞት ዜና ሲሰሙ በጣም ልባቸው ተሰብሮ ነበር። ነገር ግን ቀጠሉ! ለእምነታቸው እውነት በመሆን ቆዩ።
ቅዱሳን ተቃውሞ ሲደርስባቸውና ከናቩ ሲባረሩ፣ የሚሲሲፒን ወንዝ ከመሻገራቸው እና ወደ ምዕራብ ከመሄዳቸው በፊት ሮበርት እና ማርያ በቤተምቅደስ ውስጥ ቡራኬያቸውን ሲቀበሉ በታላቁ እንደተባረኩ ተሰማቸው፣ ከፊታቸው እንደሚያጋጥማቸው እንግጠኛ ባይሆኑም ስለ እምነታቸው እና ምስክርነታቸው እርግጠኛ ነበሩ።
ከስድስት ልጆቻቸው ጋር፣ ወደ ምዕራብ ለመሄድ አይዋን ሲሻገሩ በአስቸጋሪ ሁለታ በጭቃ ውስጥ ተግዋዙ። በሙዙሪ ወንዝ በኩል በመጨረሻም ዊንተር ክዋርተር ተብሎ ወደ ታወቀው ቦታ ለራሳቸው ጊዜያዊ መጠለያን ገነቡ።
እነዚህ ፍራቻ የሌለባቸው ቡድን፣ መስራቾች እንዴት እና መቼ ወደ ምዕራብ ጠልቀው እንደሚሄዱ ሐዋርያዊ የሆነ መልክት እየጠበቁ ነበር። የአስራ ሁለቱ አባል ፕሬሰዳንት ብሬገም ያንግ አሁን የሞርሞን ጦርነት ተብሎ ወደሚታወቀው ዩናይትድ ስቴት እራሳቸውን እንደ ወታደር ፍቃደኛ እንዲያደርጉ ለወንዶች ጥሪን ሲሰጡ፣ የእያንዳንዱ እቅድ ተቀየረ።
ለብሬገም ያንግ ጥሪ ከመለሱት 500 በላይ ከሆኑ የሞርሞን መስራች ወንዶች መካከል ሮበርት ሐሪስ አንዱ ነበር። እርጉዝ ሚስቱን እና ስድስት ልጆቹን ወደ ኋላ ትቶ መሄድ ማለት ቢሆንም ወደ ሞርሞን ውጊያ ሄደ።
እሱና ሌሎቹ ሰዎች እንዲ አይነት ነገርለምን ያደርጋሉ?
መልሱ በቅም ቅም አያቴ በራሷ ቃላቶች ሊሰጥ ይችላል። የሻለቃ ጦርነቱ በሳንታ ፌ አካባቢ እንዳለቀ ለሚስቱ ደብዳቤ ፃፈላት። እንዲህ ፃፈ “ እምነቴ በጣም ከበፊቱ በላይ ጠንካራ ነው [እና ፕሬዘዳንት ብሪገም ያንግ የነገረንን ነገሮች ሳስብ]፣ ታላቁ እግዚአብሔር የነገረን ያህል ነው የማምነው።
በአጭሩ፣ የእግዚአብሔርን ነቢይ እየሰማ እንደነበረ ያውቃል፣ ሌሎቹን እንደዛው ነው ያወቁት። ለዛ ነው ያደረጉት! በእግዚአብሔር ነቢይ እየተመሩ እንደሆነ ያውቁ ነበር።
በዛው ደብዳቤ ላይ፣ ለሚስቱ እና ለልጆቹ መልካም የሆነ ስሜት ገለፀላቸው እናም እሷ እና ልጆቹ እንዲባረኩ የማያቅዋርጥ ፀሎቱ ይናገራል።
ከዝያ በደብዳቤው ላይ የሚያስገርም አርፍተ ነገር ተናገረ: “በጌታ ቤተመቅደስ እኔ እና አንቺ ያየነውን እና የሰማነውን ልምድ መርሳት የለብንም”።
ቀደም ብሎ ከሰጠው ምስክርነት ጋር “በእግዚአብሔር ነቢይ እንመራለን” አለ እነኚ ሁለት ቅዱስ ንግግሮች ለእኔ እንደ እግዚአብሔር ቃል ሆነዋል።
ለአስራ ስምንት ወር የሻለቃ ጦርነቱ ጉዞ በኋላ፣ ሮበርት ሐሪስ በሰላም ከሚወዳት ማርያ ጋር ተመለሰ። በሕይወታቸው ሙሉ ለተመለሰው ወንጌል እውነተኛ እና ታማኝ ሆነው ቆዩ። 15 ልጆች ነበራቸው፣ ከነሱ ውስጥ13ቱ በጉልምስና እድሜ ነበሩ። የሴት አያቴ ፋንይ ዎከር የሬይመንድ፣ አልበርት፣ ካናዳ፣ የእነሱ የልጅ ልጆች ከነበሩት 136 የልጅ ልጆች አንዷ ነበረች።
የሴት አያቴ አያቷ በሞርሞን ጦርነት ላይ ስላገለገለ ትኮራ ነበር፣ የልጅ ልጆችዋ ሁሉ እንዲያውቁት ፈለገች። አሁን እኔ አያት ስለሆንኩ፣ ለእሷ በጣም ጠቃሚ እንደነበር ተረዳሁኝ። የልጆች ልብ ወደ አባታቶች እንዲመለስ ፈለገች። የልጅ ልጆችዋ ፃድቅ የሆነውን ውርሳችውን እንዲያውቁ ፈለገች--- ምክንያቱም ህይወታቸውን እንደሚባርክ አውቃለች።
ፅድቅወደ ሆኑት ቅድመአባቶቻችን ጋይ የበለጠ የተገናኘን ያህል ሲሰማን ጥበብ የተሞላበት እና ፃድቅ የሆነ ምርጫ ን የመምረጥ እድላችን ይሰፋል።
እናም እውነት ነው። እያንዳንዳችን ቅድመ አባቶቻችን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን እንዲቀላቀሉ ያደረጋቸውን የእምነት እና የመስዋት ታሪክ ካወቅን በትልቅ እንባረካለን።
ሮበርት እና ማርያ መጀመሪያ ውልፎርድ ውድሩፍ ስለተመለሰው ወንጌል ሲያስተምር እና ሲመሰክር ሲሰሙ፣ ሮበርት እና ማርያ ወንጌሉ እውነት እንደሆነ አወቁ።
ምንም ፈተና እና መከራ ወደ እነሱ ቢመጣም ለእምነታቸው በእውነት በመቆየት እንደሚባረኩ አውቀዋልም። የዛሬ የእኛን ነቢይ ቃላቶች የሰሙ ነው ሚመስለው ፣ እንዲህ ያለው። የትኛውም መሰዋዕት በጣም ትልቅ አይደለም ...የቤተመቅደስን በረከት ለመቀበል” (ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “The Holy Temple—a Beacon to the World,” Ensign orLiahona, May 2011, 92)።
በዩናይትድ ኪንግደም ሁለት ፓውንድ ላይ እንደተፃፈው፣ “በታላቆቹ ትከሻ ላይ መቆም “ስለ ታላቅ መስራች ቅድመአባቶቻችን ሳስብ ፣ ሁላችንም በታላቆች ትከሻ ላይ እንደቆምን ይሰማኛል።”
ምንም ምክሩ ከሮበርት ሐርስ ደብዳቤ ቢመጣም፣ ብዙ ቅድመአባቶች ለልጆቻቸው እና ለልጅ ልጆቻቸው ተመሳሳይ መልክት እንደሚልኩ አምናለሁ። እናም ቃል ለመግባት እና በቤተመቅደስ ምክንያት የሚመጡትን በርከቶች መርሳት የለብንም።። በሁለተኛ ደረጃ፣ በእግዚአብሔር ነቢይ እንደምንመራ መርሳት የለብንም።
በእግዚአብሔር ነቢይ እንደምንመራ እመሰክራለሁ። በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት ጌታ የሱን ቤተክርስቲያን በኋለኛ ቀን መልሷል፣ ባልተሰበር ሰንሰለት በእግዚአብሔር ነብዮች እንደተመራን መርሳት የለብንም ከጆሴፍ ስሚዝ እስከ ብሬገም እና በተከታታይ እስከ አሁን ያለ የቤተክርስቲያን ነቢይ ድረስ--- ቶማስ ኤስ. ሞንሰን አቀዋለሁ እናም እወደዋለሁ ዛሬ በምድር ላይ ያለ የእግዚያብሔር ነቢይ እንደሆነ አውቃለሁ።
የእኛን ቅድመአባቶቻችህንን ፃድቅ ቅርስ እናከብር ዘንድ ከልጆቼ እና ከልጅ ልጆቼ ጋር የልቤ ፍላጎት ነው፣ እኛ ታማኝ በነበሩ የሞርሞን መስራቾች መሰውያው ላይ ለአምላካቸው እና ለእምነታቸው ሁሉንም ለማስቀመጥ ፍቃደኛ ነበሩ። እያንዳንዳችን ወላጆቻችን ለተንከባከቡት እምነት በእውነት መኖርእንድንኖር ፀሎቴ ነው። በቅዱስ እና በተቀደሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።