ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ
ዮሴፍ ስሚዝ ላይ የፈሰሱት ራዕዮች ነብይ እንደነበር ያረጋግጣሉ ።
የመጀመሪያው ራዕይ
ወጣት ልጅ መፅሐፍ ቅዱስን አነበበ፣ እናም አይኖቹ በአንድ የጽሐፍ ቅዱስ አንቀጽ ላይ አርፈው ቆዩ። ይህም አልምን የሚቀይር ቅፅበት ነው።
የትኛው ቤተክርስቲያን ወደ እውነት እና ደህንነት እንደሚያመራው ለማወቅ ጓጓ።ቢያንስ ሁሉንም ነገሮች ሞክሮ ነበር፣ እናም አሁን ወደ መፅሐፍ ቅዱስ ተመልሶ እነዚህን ቃላት አነበበ፥ “ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል።”1
በእነዚህ ነገሮች ላይ ደጋግሞ አሰላሰለ። የመጀመሪያዋ የብርሀንብልጭታ ጨለማውን ሰነጠቀች። ይህ ከመምታታት እና ከጨለማ መውጫ መንገድ መልስ ነውን? እንደዚህ ቀላል ሊሆን ይችላልን? እግዚአብሔርን ጠይቅ እና መልስ ይሰጣልን? በመጨረሻም እግዚአብሔርን መጠየቅ ወይም በጨለማ እና በመምታታት መቆየት እንዳለበት ወሰነ።
እና ምንም ቢጓጓም፣ ወደ አንድ ፀጥ ወዳለ ጥግ ሄዶ የፍጥነት ጸሎት አላደረገም። ገና 14 አመቱ ነው፣ ነገር ግን በፍጥነት ለማወቅ ፈጣን ነገሮችን አላደረገም። ይህ እንደ ማንም አይነት ጸሎትመሆን የለበትም። የት መሄድ እና ጥረቱን መቼ ማድረግ እንዳለበት ወሰነ። ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ተዘጋጀ።
ከዚያም ቀኑ ደረሰ። ይህም በቆንጆ የ1820 (እ.አ.አ) የጸደይ ጠዋት ነው።ብቻውን በአቅራቢያው ወደሚገኘው ፀጥ ወዳለው ጫካ ከእርሱ በላይ በቆሙት ዛፎቹ ስር ሄደ።2 ከዚህ በፊት ለመሄድ ወደወሰነበት ቦታ ደረሰ። ተንበረከከ እና የልቡን ፍላጎት በጸሎት አቀረበ።
ከዛ በኋላየተከሰተውን ሲገልፅ፣ እንዲህ አለ፥
“የብርሀን አምድ በራሴ ትክክል ላይ አየሁ፣ ከፀኃይ ብርሀን የበለጠ፣ በላዬ ላይ እስያርፍ ድረስ በዝግታ ወረደ።
“ብርሀኑም በእኔ ላይ ባረፈ ጊዜ ብርህነታቸውና ክብራቸው ቃላት ከሚገልጸው በላይ የሆኑ ሁለት ግለሰቦችን በአየር ላይ ከበላዬ ቆመው አየሁ። አንዱም በስሜ በመጥራት እና ወደሌላውም በመጠቆም እንዲህ ሲል ተናገረኝ---[ጆሴፍ] ይህ የምወደው ልጄ ነው፣ እርሱን ስማው።”3
ከ24 አመት በኋላ ብቻ፣ ጆሴፍ ስሚዝ እና ወንድሙ ሀይረም በዚህ ቦታ በተጀመረው ምክንያት ይሞታሉ።
ተቃውሞ
ዮሴፍ አስራ ሰባት አመት ሲሞላው፣ መልአክ “ስምህ በመልካም እና በክፉ በሀገሮች፣ ...በህዝቦች መካከል ይገኛል” ብሎ እንደተናገረው ተናገረ።4 የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአለም ዙሪያ በምትስፋፋበት ጊዜ ይህ ትንቢት መሟላቱን እየቀጠለ ነው።
ተቃውሞ፣ ወቀሳ፣ እና ጥላቻ ለእውነት ጓደኞች ናቸው። ስለሰው አላማ እና እጣ ፈንታ እውነት በሚገለጽበት ጊዜ፣ የሚቃወመው ሀይል ይኖራል። በገነት ውስጥ ከአዳም እና ሔዋን ጀምሮ፣ እስከ ክርስቶስ አገልግሎት ድረስ፣ እናም እስከ ጊዜአችን ድረስ፣ የህይወት እቅድን የሚያታልል፣ የሚያጠፋ፣ የሚቃወም፣ እና የሚያቆም ጥረቶች ሁልጊዜም አሉ።
ትልቁን የአዋራ ደመና ከሁሉም አፈሮች በላይ ተቃውሞ ባገኘው፣ በተፈተነው፣ እና በተወገደው፣ በተወገረው፣ በተተወው፣ እና በተሰቀለው፣ ከሁሉም ነገሮች በታች ዝቅ ባለው ላይ የተበተነውን ተመልከቱ። እና እዛ እውነትን ታገኛላችሁ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የሁሉም ሰው ዘሮች አዳኝ። ለምንድን ነው ለብቻው ያልተዉት?
ለምን? ምክንያቱም እርሱ እውነት ነው፣ እናም እውነት ሁልጊዜም ተቃውሞ ያጋጥማታል።
ከዚያም የኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ ምስክርና ሌሎች ቅዱሳት መጽሐፍት ያመጣን፣ የወንጌል ሙሉነትና የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ወደ ምድር በዳግም እንዲመለሱ መሳሪያ የሆነውን ተመልከቱ፤ እርሱንም ተመልከቱ እና አዋራውን ሲበር ለማግኘት ጠብቁ። ለምን ለብቻውን አይተዉትም?
ለምን? ምክንያቱም እውነትን ስላስተመረ፣ እናም እውነት ሁልጊዜም ተቃውሞ ያጋጥማታል።
የራዕይ ጎርፍ
ወደ ዮሴፍ ስሚዝ የመጡት ራዕዮች እርሱ የእግዚአብሔር ነቢይ እንደነበረ ማረጋገጫ ይሰጣሉ። የተወሰኑትን እንይ፣ በእርሱ በኩል የተገለጹት ብርሀንና እውነቶችን በእርሱ እና በእኛ ቀናት ከሚታመኑት ጋር በሚነፃፀሩበት ጊዜ እንዴት እንደሚያንጸባርቁ እንይ።
-
እግዚአብሔር አካል ያለው፣ የከበረ ፍጥረት፣ የዘለአለም አባት ነው። እርሱም አባታችን ነው።
-
አብ እግዚአብሔር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እና መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ ፍጥሮች ናቸው።5
-
ሰዎች ከመሆን በላይ ናችሁ። የዘላለም አባት የእግዚአብሔር ልጅ ናችሁ እናም በልጁ እምነት ካላችሁ፣ ንስሀ ከገባችሁ፣6 መንፈስ ቅዱስን በመቀበል እና እስከመጨረሻው በመፅናት ስነ-ሰርዕቶችን ከተቀበላችሁ6 እንደእርሱ መሆን ትችላላችሁ።7
-
የዛሬው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በሟች ምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት ያቋቋመው ተመሳሳይ የሆነ ቤተክርስቲያን ነው። ነበያቶችና ሐዋርያቶች፣ የመልከፀዴቅና ሌዊያዊ የክህነት ስልጣኖች፣ ሽማግሌዎች፣ ከፍተኛ ካህኖች፣ ዲያቆኖች፣ አስተማሪዎች፣ ኤጲስ ቆጶሶች እና ሰባዎች ሁሉም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተገለፀው።
-
ከአዳኙና ከሐዋርያቶቹ ሞት በኋላ የክህነት ስልጣን ከምድር ተወስዶ ነበር እናም በድጋሚ በእኛ ዘመን ተቋቋመ።
-
ራዕይ አላቆመም፣ እናም ሰማያትም አልተዘጉም። እግዚአብሔር ለነቢያት ዛሬም ይናገራል፣ እናም ለእናንተና ለእኔም እንዲሁ ይናገራል።8
-
ከዚህ ህይወት በኋላ ከሰማይና ከገሀነም ሌላ ተጨማሪም አለ። የክብር ደረጃዎች አሉ፣ ሶስት የግርማ ደረጃዎች አሉ፣ እናም በዚህ ህይወት ውስጥ የምናደርጋቸው ነገሮች ትልቅ ትርጉም አላቸው።9
-
በክርስቶስ ዝምብለን ከማመን ባሻገር “በሁሉም አስተሳሰባችን [እርሱን] መመልከት፣”10 “የምናደርጋቸውን ነገሮች በሙሉ በወልድ ስም ማድርግ፣”11 “ሁልጊዜ እርሱን እንድናስታውና የእርሱ ትእዛዛት እንድንጠብቅ ... የእርሱ መንፈስ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር እንዲኖር” ማድረግ አለብን።12
-
ያለወንጌሉ እና ለደህንነት አስፈላጊ የሆኑትን ስርዓቶች ሳይፈጽሙ የኖሩትና የሞቱት ብዙ ቢልዮኖች አይጠፉም። በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት፣ሁሉም የሰው ዘሮች ለህያው እና ለሙታን በሚከናወነው፣13 “በወንጌሉ ህግጋት እና ስርዓቶች ታዛዥ በመሆን መዳን ይችላሉ።”14
-
ሁሉም ነገሮች በውልደት የጀመረ አይደለም። ከዚህ በፊት በእግዚአብሔር ፊት እንደ እርሱ ወንድና ሴት ልጆች ኖራችኋል እና ለዚህ ምድራዊ ህይወት ተዘጋጅታችኋል። 15
-
ጋብቻ እና ቤተሰብ ሞት እስከሚለየን ድረስ ብቻ የሚደረጉ የሰዎች ስምምነቶች አይደሉም። ከእግዚአብሔር ጋር በምናደርገው ቃል-ኪዳኖች አማካኝነት ዘላለማዊ እንዲሆኑ ነው የታቀዱት። ቤተሰብ የሰማይ ንድፍ ነው።16
ይህ ለዮሴፍ ስሚዝ ከተጨመሩለት የራዕይ ጎርፎች መካከል አንዱ ክፍል ብቻ ነው። ለጨለማ ብርሀንን፣ ለመጠራጠር ግልፅነትን የሰጡት፣ እንዲሁም ሚሊዮን ህዝቦችን ያነሳሱና ያሻሻሉ እነዚህ ራዕዮች ከየት የመጡ ናቸው? የጥኛው ነው የበለጠ የሚሆነው፣ ሁሉንም በራሱ ያለመው ሰው ወይም የሰማይኝ እርዳታ ያገኘው ሰው? እርሱ ያፈራቸው ቅዱሳት መፀጽሐፍቶች የስው ቃላቶች ወይም የእግዚአብሔር ቃሎች ይመስላሉን?
መደምደሚያ
ዮሴፍ ስሚዝ ስላከናወናቸው ነገሮች ምንም ክርክር የለም፣ ክርክር ያለው ዮሴፍ ስሚዝ ባከናወናቸው ነገሮች ላይ ሳይሆን ያደረጋቸውን ነገሮች እንዴት እንዳደረጋቸውና ለምን እንዳደረጋቸው ላይ ነው። እናም ብዙ ምርጫዎች የሉም። እርሱ አስመሳይ ወይም ነቢይ ነበር ማለት ነው። ያደረገውንነገር ለብቻው ነበር ያደረገው ወይም የሰማይ እርዳታ ነበረው ማለት ነው። መረጃውን ተመልከቱ፣ ግን ሁሉንም መረጃዎች ተመልከቱ፣ የህይወቱን ነጠላ ድርጊት ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የህይወቱን ዝርዝሮች ተመልከቱ። ከሁሉም በላይ፣ ወጣቱ ዮሴፍ እንዳደረገው አድርጉ፣ እናም “ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን [ለምኑ]፣ እናም ሁሉም [ይሰጣችኋል]”17 ይህም እንዴት ስለመፅሐፈ ሞርሞን እና ዮሴፍ ስሚዝ እውነታ የምትማሩበት መንገድ ብቻ አይደለም፣ እንዲሁም የሁሉንም ነገሮች እውነታ ለማወቅ የሚረዳ ንድፍ ነው።18
ዮሴፍ ስሚዝ፣ በዚህ ጊዜ ቶማስ ኤስ ሞንሰን እንደሆኑት፣ የእግዚአብሔር ነቢይ ነበር። በዮሴፍ ስሚዝ አማካኝነት፣ የእግዚአብሔር መንግስት ቁልፎች እንደገና “በምድር ላይ ለሰው ተሰጠ፣ እናም… ወንጌሉ ወደ ፊት ይንከባለላል… እጅም ሳይነካው ከተራራው ተፈንቅሎ ምድርን እስከሚሞላ ድረስ እንደሚንከባለለውም ድንጋይ፣ ወደ ምድር ዳርቻም ይገፋል።” 19
እግዚአብሔር የዘለአለም አባታችን ነው፣ እናም ኢየሱስም ክርስቶስ ነው። እናመልካቸዋለን። ከእነርሱ ፍጥረቶች፣ ከደህንነት እቅድ፣ እና ከእግዚአብሔር ጥቦት የሃጢያት ክፍያ መስዋዕትነት ጋር የሚወዳደር ምንም የለም። በዚህ ዘመን፣ የአብ እቅድን የምናሟላው እናም የኃጢያት ክፍያ ፍሬን የምንካፈለው በዮሴፍ ስሚዝ አማካኝነት በዳግም የተመለሱትን ህግጋት እና ስርዓቶችን በማክበር ብቻ ነው። ስለእነርሱም፣ ስለእግዚአብሔር የዘለአለም አባት፣ ስለአለም አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም እንደዚህ አደርጋለው፣ አሜን።