ምን አይነት ሰዎች?
መሆን ያለብን አይነት ሰዎች ለመሆን ምን አይነት ለውጦች የጠበቅብናል?
ይህን አለማቀፋዊ ጉባኤ ስናጤን፣ የትም ቢሆን ከእነዚህ መሰባሰብ የሚነጻጸር እንደሌለ እናስተውላለለን። የክህነት ክፍለ ጊዜ አላማ የክህነት ስልጣን ተሸካሚዎችን ምን አይነት ሰዎች መሆን እንደሚገን ለማስተማር ነው (3ኛ ኔፊ 27፣27 ተመልከቱ) እና ያንን ስኬት ላይ ለመድረስ እንድንነሳሳ ነው።
ከግማሽ ምእተ አመት በፊት በሐዋይ እንደ አሮናዊ ካህንነቴ እና በእንግሊዝ እንደ ሚስኦናዊነቴ፣ በስብሰባ ቤቶች ተሰብስበን እና(በጽኑ ጥረት) የክህነት ስልጣን ክፍለ ጊዜን በሞባይል ግንኙነት ተጠቅመን እናዳምጥ ነበር። በቀጣዮቹ አመታት፣ ዝግጅቶቹን በማዳመጥም በምስልም በሳተላይት በተመረጡ የቤተክርስቲያን ቦታዎች በእነዚያ ታላላቅ ዲሽ መቀበያዎች ማሰራጨት አስቻሉ። በዚያ ቴክኖሎጂ ተገርመን ነበር! ጥቂቶች የዛሬውን አለም ማሰብ ችለዋል፣ ኢንተርኔት ግንኙነት ያለው ማንም ሰው በዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ስልክ እና ኮምፒውተር የዚህን ስብሰባ መልእክቶች ማግኘት ይችላል።
ነገር ግን፣ ይህ ሰፊ የጌታን አገልጋዮች ድምጽ የማግኘት እድገት፣ ከራሱ ከጌታ ድምጽ አንድ የሆኑት (ት እና ቃ 1፣38 ተመልከቱ)፣ ቃሉን ለመቀበል (ት እና ቃ11፣21 ተመልከቱ) እና ለመከተል ፍቃደኛ ካልሆንን ትንሽ ዋጋ ብቻ ነው ያለው። በቀላሉ ለማስቀመጥ፣ የአጠቃላዩ ጉባኤ እንዲሁም የእዚህ የክህነት ስልጣን ክፍለ ጊዜ አላማ የሚሳካው ለመተግበር ፍቃደኞች ከሆንን፣ ለመለወጥ ፍቃደኞች ከሆንን ብቻ ነው።’
ከጥቂት አስርተ አመታት በፊት እንደ ኤጲስቆጶስ እያገለገልኩ ነበር። ከቆይታ በኋላ በአጥቢያችን በብዙ አመት የእኔ የበላይ የነበረ ሰውን ተገናኘሁ። ይሄ ሰው ከሚስቱ ጋር አስቸጋሪ ግንኙነት ነበረው እና ከልጆቻቸው ተነጥሎ ነበር። በስራው ላይ ለመቆየት ይታገል ነበር፣ የቅርብ ጓደኞች አልነበሩትም፣ ከአጥቢያው አባላት ጋር ለመቀራረብ በጣም ተቸግሮ በስተመጨረሻ በቤተክርሰቲያን ውስጥ ለማገልገል ፍቃደኛ አልነበረም። ስለ ህይወቱ ውጣውረድ በነበረ አንድ ጠልቅ ውይይት ላይ፣ ወደ እኔ ደገፍ ብሎ፣ ለብዙው ንግግራችን እንደ ማጠቃለያው፣ እንዲህ አለ፣ “ኤጲስቆጶስ፣ መጥፎ ንዴት አለኝ፣ እና በቃ እኔ እንደዚህ ነኝ!”
ከጥቂት አስርተ አመታት በፊት እንደ ኤጲስቆጶስ እያገለገልኩ ነበር። ከቆይታ በኋላ በአጥቢያችን በብዙ አመት የእኔ የበላይ የነበረ ሰውን ተገናኘሁ። ይሄ ሰው ከሚስቱ ጋር አስቸጋሪ ግንኙነት ነበረው እና ከልጆቻቸው ተነጥሎ ነበር። በስራው ላይ ለመቆየት ይታገል ነበር፣ የቅርብ ጓደኞች አልነበሩትም፣ ከአጥቢያው አባላት ጋር ለመቀራረብ በጣም ተቸግሮ በስተመጨረሻ በቤተክርሰቲያን ውስጥ ለማገልገል ፍቃደኛ አልነበረም። ስለ ህይወቱ ውጣውረድ በነበረ አንድ ጠልቅ ውይይት ላይ፣ ወደ እኔ ደገፍ ብሎ፣ ለብዙው ንግግራችን እንደ ማጠቃለያው፣ እንዲህ አለ፣ “ ኤጲስቆጶስ፣ መጥፎ ንዴት አለኝ፣ እና በቃ እኔ እንደዚህ ነኝ!”
ሆኖም፣ በዚህ የክህነት ስብሰባ የምንገናኝበት ምክንያት አሁን የሆነው ወደፊት መሆን የምንችለውን ስላልሆነ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ዛሬ ምሽት ተሰብስበናል። የተሰበሰብነው የእሱ የሀጢያት ክፍያ ለሁላችንም፣ ምንም ደካማ፣ አጥፊ እና ሱሰኛ ብንሆን እንኳ፣ ለመለወጥ ብቃት እንደሚሰጠን በመተማመን ነው። የተሰበሰብነው የወደፊታችን፣ ማንም አይነት ታሪክ ቢኖረን፣ መሻሻል እንደምንችል በተስፋ ነው።
“በሙሉ ልብ” (ሞሮኒ 10፣4) በዚህ ስብሰባ ለመለወጥ ስንሳተፍ፣ መንፈስ ቅዱስ ከልባችን እና አእምሯችን ጋር ሙሉ ግንኙነት አለው። ጌታ ለዮሴፍ ስሚዝ እንደገለጠው፣ “እናም እንዲህ ይሆናል፣ በእኔ እምነትን እስከተገበሩ ድረስ” እምነት የሀይል እና ተግባር መርህ መሆኑን አስታውሱ፣ “እራሳቸው በአንድ ላይ በተሰበሰቡ ቀን መንፈሴን በእነርሱ ላይ አፈሳለሁ።”(ት እና ቃ 44፣2) ያ ማለት ዛሬ ምሽት ነው!
ውጣውረዳችን ማለቂያ የለውም ብላችሁ ካሰባችሁ፣ በትንሽ መንደር በሐይደርባድ ህንድ በ2006 ስላገኘሁት ሰው ልንገራችሁ ይህ ሰው የመለወጥ ፍላጎት ምሳሌ ነው። አፓ ራኦ ኑሉ በህንድ ገጠር ነው የተወለደው። ሶስት አመት ሲሞላው፣ የፖልዮ በሽታ ተጠናወተው እና አካል ጉዳተኛ ሆነ። የእሱ ማህበረሰብ አቅሙ በጣም የተገደበ እንደሆነ አስተማሩት። ቢሆንም፣ እንደ ወጣት ጎልማሳ፣ የእኛ ሚስኦናውያን አገኛቸው። ስለታላቅ አቅም አስተማሩት፣ በዚህ ህይወትም እና ለዘለአለም የሚሆን። እንደ ቤተክርስቲያን አባል ተጠመቀ እና ማረጋገጫም ተሰጠው። ጉልህ በሆነ የራእይ መነሳት፣ የመልከጻዲቅ የክህነት ስልጣን ለመቀበል እና ሚስኦን ለማገልገል አቀደ። መራመድ ቀላል አልነበረም። ዘንግ በሁለቱም እጁ በመያዝ የተቻለውን አደረገ እና አንዳንዴም ወደቀ፣ ነገርግን ጥረቱን ማቆም ምርጫ አልነበረም። በክብር እና በመሰጠት ሚስኦኑን ለማገልገል ወሰነ፣ አደረገውም።
ወንድም ኑሉን ስናገኘው፣ ከሚስኦኑ 20 አመት በኋላ፣ መንገዱ ማብቂያ ላይ በደስታ ሰላምታ ሰጠን እና ሙሉ ወዳልሆነው አፈራማ መንገድ ላይ ከሚስቱ እና ከሶስት ልጆቹ ጋር ወደሚኖርበት ሁለት ክፍል ቤት መራን። በጣም ሞቃት እና የማይመች ቀን ነበር። አሁንም በከባድ ሁኔታ ነው ሚራመደው፣ ስለራሱ ግን አያዝንም። በግሉ ትጋት፣ መምህር ሆኗል፣ ለመንደሩ ልጆች ትምህርትን ያደርሳል። ወደ ትሁት ቤቱ ስንደርስ፣ ወዲያው ወደ ጥግ ወሰደኝ እና በጣም አስፈላጊ ንብረቶቹን የያዘውን ሳጥን ጎትቶ አወጣ። ነጠላ ወረቀት እንዳይ ነበር የፈለገው። እንዲህ ይላል፣ “ለቤተክርስቲያን ሽማግሌ ኑሉ መልካም በመመኘት እና በመባረክ፣ ብርቱ እና ደስተኛ ሚስኦን፣ (ቀኑም) ሰኔ 25፣ 1987፤ (ተፈርሟል) ቦይድ ኬ ፓከር” በዚያ ወቅት፣ ከዛም የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ፓከር ህንድን ሲጎበኙ እና የሚስኦን አገልጋዮችን ሲያናግሩ፣ ለሽማግሌ ኑሉ በ2006 በዚያ ቀን እያለኝ የነበረው ወንጌል በቋሚነት እንደቀየረው ነው!
በዚህ የኑሉ ቤት ጉብኝት ወቅት፣ የሚስኦን ፕሬዘዳንቱ አብሮን ነበር። በዚያ የነበውም ወንድም ኑሉ፣ ሚስቱ እና ልጆቹን ቃለመጠይቅ ለማድረግ ነበረ፣ ወላጆቹ ቡራኬን እንዲያገኙ እናም እንዲታተሙ እና ልጆቹም ከወላጆቻቸው ጋር እንዲታተሙ ነበር። ለዚህ የቤተመቅደስ ስርአትም ቤተሰቡ ወደ ሆንግኮንግ ቻይና እንዲጓዙ ሁኔታዎችን አመቻቸን። ብዙ የጠበኩት ህልም ሊሳካ በመሆኑ በደስታ አነቡ።
የእግዚአብሔርን ክህነት ከተሸከመ ሰው ምን ይጠበቃል? መሆን እንዳለብን አይነት ሰው ለመሆን ምን ለውት ያስፈልጋል? ሶስት ሀሳቦችን አቀርባለሁ።
-
የክህነት ሰው መሆን አለብን! አሮናዊ ክህነት ዬዘን ወጣትም ሆንን ዌም መልከጻዲቅ ክህነትን የተሸከምን ወንዶች፣ የክህነት ሰው ሞን አለብን፣ ቃል ኪዳንን በመፈጸማችን መንፈሳው ንቃትን በማሳየት። ጳውሎስ እንዳለው “ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፣ እንደ ልጅ እረዳ ነበር፣ እንደ ልጅም አስብ ነበር፣ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሸሬአለሁ”(1ኛ ቆሮንጦስ 13፣11)። የክህነት ተሸካሚ በመሆናችን የተለየን መሆን አለብን- ልቅነት ወይም ኩራተኛ ወይም እራስ ወዳድ ሳይሆን፣ ነገር ግን ትሁት እና መማር የምንችል እና የዋህ መሆን አለብን። ክህነትን እና የተለያዩ ክፍሎቹን መቀበል ለእኛ ትርጉም ሊሰጠን የይገባል። በተወሰነ ዘመን በራሱ የዋህ “የባህል መተላለፊያ” መሆን የለበትም፣ ነገር ግን ታስቦ የሚደረግ ቃልኪዳን ጥልቅ ተግባር ነው። ድርጊታችን ሁሉ ይህን ስለሚያሳይ የተባክን መሆናችን ሊሰማን እና አመስጋኞች ሞን አለብን። ስለ ክህነት አንዳንዴ ብቻም እንኳን ብናስብ፣ መለወጥ ያስፈልገናል።
-
ማገልገል አለብን! ክህነትን የመሸከም ጥልቅ ምንነት ሌሎችን በማገልገል “ጥሪያችንን ማጉላት”(ት እና ቃ 84፣33 ተመልከቱ) ነው። ሚስቶቻችንን እና ልጆቻችንን የማገልገል አስፈላጊ ሀላፊነታችንን ማስወገድ፣ በቤተክርሰቴያን ውስጥ ጥሪን በቸልታ መፈጸም እና አለመቀበል፣ ካልተመቸን በስተቀር ለሌሎች አለማሰብ፣ እኛ መሆን ያለብን እንደዚህ አይደለም። አዳኙ አወጀ፣ “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ”((ማቴዎስ 22፣37) እና በኋላም ጨምሮ አለ፣ “የምትወደኝ ከሆነ ታገለግለኛለህ” ((ት እና ቃ 42፣ 29)። እራስ ወዳድነት ብቁ ያልሆነ የክህነት ሀላፊነት ነው፣ እና የባህሪያችን መገለጫ ከሆነ፣ መለወጥ አለብን።
-
ብቁ መሆን አለብን! ሲያደርግ ለ “ወደፊታችሁ ግቡ… አፍንጫ ለአፍንጫ፣ በቂ በሆነ እሳት…ቅንድባችሁን እንዲለበልባችሁ”(“We Are All Enlisted,” Ensign orLiahona,, Nov. 2011, 45)፣ ነገር ግን፣ ውድ ወንድሞች፣ የክህነት ሀይላችንን የሚያንቁ በልምድ ተቀባይነት ያገኙ ድርጊቶች ላይ ነቃ ማለት አለብን። በራቁት ምስል ወይም ፊልም መቀለድ እነኳ እንችላለን ብለን ብናስብ፣ ወይም ንጽህና ጥሰት ወይም በምንም መልኩ አለመታመን፣ እኛንም ሆነ ቤተሰባችን ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አያመጡብንም ብለን ካሰብን፣ ተታለናል። ሞሮኒ እንደገለጸው፣ “ሁሉንም ነገሮች ስታደርጉ በተገቢው ማድረጋችሁን ተመልከቱ”(ሞሮኒ 9፣29)። ጌታ በሀይል ምሬት ሲሰጥ፣ “አሁን እኔ ትእዛዝ እሰጣለሁ ስለራሳችሁ እንድታውቁ፣ ዘለአለማዊ ህይወት ቃላትን በትጋት እንድታደምጡ” (ት እና ቃ 84፣43)። ብቁነታችንን የሚያስወግዱ ያልተወገዱ ሀጢያቶች ካሉ፣ መለወጥ አለብን።
ኢየሱስ ክርስቶስ ላነሳው ጥያቄ፣ “ምን አይነት ሰው ነው መሆን ያለባችሁ?” ላለው ብቸኛ ሙሉ መልስ የሚሆነው እሱ ግልጽና ጥልቅ በሆነ ሁኔታ የሰጠው ነው፤ “እንደ እኔ ሁኑ” (3ኛ ኔፊ 27፣27)። “ወደ ክርስቶስ ኑ እና በሱ ፍጹማን ሁኑ” (ሞሮኒ 10፣ 32) የሚለው ግብዣ መለወጥን ይጠይቃል እና የጠብቃልም። በምህረት፣ እርሱ ብቻችንን አልተወንም። “ሰዎች ወደ እኔ ቢመጡ ድክመታቸውን አሳያቸዋለሁ…. እናም ደካማ ነገሮችን ጠንካራ አደርጋለሁ” (ኤተር 12፣ 27)። በአዳኛችን የሀጢያት ክፍያ ላይ ተመርኩዘን መለወጥ እንችላለን። በዚህ እርግጠኛ ነኝ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።