2010–2019 (እ.አ.አ)
መከታተል
ሚያዝያ 2014


16:2

መከታተል

ፍራቻችንን በትክክለኛ እምነት በመተካት ቀጣይነት ባለው የሚስዮን ስራ የበለጠ መካፈል እንችላለን።

በዚህ ክረምት ከስልሳ አራት አመታት በፊት በእንግሊዝ ከነበረው ሚስዮን አገልግሎቴ ተመለስኩ። ከተመለስኩኝ ከሶስት ቀናት በኋላ ከጓደኛዬ ጋር የሔሎ ደይ ዳንስ በዩታህ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተካፈልኩ። እኔ ማግኘት እንዳለብኝ ያሰባትን ዩለተኛ አመት ተማሪ የሆነች ባርባራ ስለምትባል ቆንጆ ነገረኝ። ወደ እኔ አመጣት እና አስተዋወቀን፣ እና መደነስ ጀመርን።

መጥፎ አጋጣሚ ሆኖ፣ ይሄ “የመለያ ዳንስ” ብለን የምንጠራው ነበር፣ ይህም ማለት ከአንድ ሴት ጋር የደነሰው ሌላ ሰው ለይቶ እስኪያስወጣ ድረስ ብቻ ነበር። ባርባራ ንቁ እና ታዋቂ ነበረች፣ ስለዚህም፣ ሌላ ወጣት ወንድ መቶ እስከሚለየየኝ ከእንድ ደቂቃ በታች ብቻ ነው ከሷ ጋር የደነስኩት።

ያለእኔ ተቀባይነት አልነበረውም። የመከታተልን አስፈላነት ከሚስዮኔ በመማሬ፣ ስልክ ቁጥሯን ተቀበልኩ እና ቀጠሮ ለመያዝ በሚቀትለው ቀን ደወልኩላት፣ ገር ግን በትምህርት እና ማህበራዊ ተግባራት ተወጥራ ነበር። ለሚስዮኔ ምስጋና ይድረስና ብርታት በማጣት ውስጥም ጽናትን አስተምሮኛል፣ እና ከጊዜ በኁዋላ ቀጠሮ ማስያዝ ቻልኩኝ። ያም ቀጠሮ ወደ ሌላ ቀጠሮዎች አመራ። እንደምንም በእነዚያ ቀጠሮዎች ወቅት እሷን እስከሚመለከታትም ቢሆን፣ ብቸኛው እውነተኛ እና ነዋሪ የሚስዮን ተመላሽ መሆኔን አሳመንኳት። አሁን ከ64 አመታት በኋላ፣ ምንም ያል መልእክታችሁ አስፈላጊ ቢሆን፣ ያለ የማያቋርጥ ጽኑ መከታተል መልእክቱን ማድረስ እንደማይቻል ያሉን ሰባት ልጆች፣ ብዙ የልጅ ልጆች እና የልጅ ልጅ ልጆች ምስክሮች ናቸው።

ባለፉት ሁለት አጠቃላይ ጉባኤ ንግግሮችን ዛሬ እንድከታተል የተሰማኝ ንጹህ መነሳሳት ለዚህ ይሆናል።

በጥቅምት 2011 ጉባኤ፣ የእነዚህን አስፈላጊ ዬታ ቃላት እንድናስታውስ ግፊት አቅርቤ ነበር፣ “ለዚህም ነው በኋለኛው ቀን ቤተክርስቲያ እንደዚህ ብሎ መጠራት ያለበት፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን።”1

በነኚህ ቃላቶች ፣ ይሄ ተገቢ እርስ ብቻ ሳይሆን ቤተክርስያኑ መጠራት ያለበትም ስም እንደሆነ ጌታ ግልጽ አድረጎታል። የእርሱ ግልጽ አዋጅ እንዳለ ሆኖ፣ ቤተክርስያኑን በሌላ መጠሪያዎች መወከል የለብንም፣ እንደ “የሞርሞን ቤክርሰቲያን” ወይም “የኤልዲኤስ ቤተክርስቲያን” በሚሉት።

ሞርሞን የሚለው ቃል የቤተክርስቲያን አባላትን በሚጠቅሱ ተገቢ ቦታዎች መጠቀም ይቻላል፣ እንደ የሞርሞን መስራቾች፣ ወይም እንደ የሞርሞን ተበርናክል ኳየር ያሉ ማህበሮች። የቤተክርስቲያን አባላት በስፋት ሞርሞን ተብለው ይታወቃሉ፣ በእኛ እምነት ካልሆኑ ጋር ባለው መስተጋብር፣ እራሳችን ሞርሞን ብለን ልንወክል እንችላለን፣ በዚህም ከቤተክርስያኑ ሙሉ ስም ጋር በማጣመር።

አባላት ቤተክርስቲያኑን ትክክለኛ ስም “ሞርሞን” ከሚለው ቃል ጋር መጠቀምን ከተማሩ፣ ክርስቲያን መሆናችንን፣ እና ቤተክርስቲያን አባላት መሆናችንን ትኩረት ያሳጣል።

ወንድሞች እና እህቶች፣ እንከታተል እና እኛ የኋለኛ ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ጋር እንደምንካተት ሁሌ ግልጽ የማድረግን ልምድ እናዳብር።

መከታተል አለብን ብዬ የሚሰማኝ ለተኛው መልእክት ልክ ካለፈው ጉባኤ አባላት ከገና በፊት የተመለሰውን ወንጌል ለመጋበዝ ወደ አንድ ሰው እንኳን እንዲመሩ መጸለይ እንዳለባቸው ያበረታታሁት ነው። ብዙ የቤተክርስቲያን አባላት ለሚስዮን እድል በመጠየቃቸው ያጋጠማቸውን ልዩ ተሞክሮዎች አካፍለውኛል።

አንድ ከሚስዮን የተመለሰ፣ ለምሳሌ፣ መድረስ ወደሚችለው ወደ “አንዱ” እንዲመራ ጸለየ። የቀድሞ የኮሌጅ የክፍል ጓደኛው ስም ወደ አዕምሮው መጣ። በፌስቡክ አገኛት፣ እና በህይወቷ ስለ አላማ እና ትርጉም ስትጸልይ እንደነበረ አወቀ። ልክ እውነትን ፍለጋ ላይ በነበረችበት ወቅት ተከታተለ፣ እና ታህሳስ ውሰጥ ተጠመቀች።

ብዙ ተማሳሳይ ግብዣ መጃዎች ደርሰውኛል፣ ግን ዬ ወንድም እንደተከታተለው ያለ ጥቂት ብቻ ነበር።

መከታተል በሚለው ጽንሰ ሀሳብ ታላቅ አማኝ ነኝ። ወንጌሌን ማወጅ በሚለው የሚስዮን መምሪያ ላይ እንደሚለው፣ “መከታተል የሌለው ግብዣ የማይጨረስ ጉዞ እንደመጀመር ወይም ወደ ቲያትር ለማይኬደው ነገር መግቢያ እንደመቁረጥ ነው። ያለ መፈጸሚያ ድርጊት፣ ለስራው መሰጠት ንቱ ነው።”2

መጋበዝ ብቻ ሳይሆን መከታተልንም ወንጌሌን አውጁ የሚለው ሁሉንም ያስተምራል። የሚስዮን ስራ አላማ እንደዚህ ትርጉም ተሶቶታል፣ “ ሌሎች ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በሀጢያት ክፍያ እምነት፣ ንስሀ፣ ጥምቀት፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እና እስከመጨረሻው በመጽናት የተመለሰውን ወንጌል እንዲቀበሉ በመርዳት” መጋበዝ ነው።3

በእርግጥ መጋበዝ የሂደቱ ክፍል ነው። ነገር ግን የአባላት የሚስዮን ስራ ለሰዎች ሚስዮኖችን እንዲሰሙ ከመጋበዝ በላይ መሆኑን አስተውሉ። እምነትን በማጎልበቱ ለንስሀ በመበረታታት ቃልኪዳን ለመፈጸም በመዘጋጀት እና በመጽናት ውስጥ፣ ከሚስዮኖች ጋር መከታተልን ያካትታል።

የሚቀጥለው መሰረታዊ መርሆ በሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ ውስጥ በምሳሌ ተሰጥቷል፥

“ጴጥሮስ እና ዮሀነስም ወደ ቤተመቅደስ ይወጡ ነበር …

“ወደ መቅደስም ከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ፣ ሰዎች ተሸክመውት መልካም በሚሏት በመቅደስ ደጅ በየቀኑ ያስቀምጡት የነበሩ ከእናቱ ማህጽን ጀምሮ አንካሳ የሆነ አንድ ሰው ነበረ።

“እርሱም ጴጥሮስ እና ዮሀነስ ወደ መቅደስ ሊገቡ ባየ ጊዜ፣ ምጽዋትን ለመናቸው።

“ጴትሮስም ከሀነስ ጋር ትኩር ብሎ ወደ እርሱ ተመልክቶ፣ ወደ እኛ ተመልከት አለው።

“እርሱም አንድ ነገር ከእነርሱ እንዲቀበል ሲጠብቅ ወደ እነርሱ ተመለከተ።

“ጴጥሮስ ግን ብርና ወርቅ የለኝም፣ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሀለሁ፣ በናዝሬቱ በኤየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሳና ተመላለስ አለው።”

ያ ከጌታ አገልጋይ የመጣ ሀይለኛ ግብዣ ነው፣ አይደል? ጴጥሮስ ግን በመጋበዝ አላቆመም። ቀጣዩ የጥቅሱ ቅጥያ እንደሚነግረን፤ “ቀኝ እጁን ይዞ እና አነሳው፣ እናም ወዲያው መረጋገጫዎቹ እና የጉልበት አጥንቶቹ ጥንካሬን ተቀበሉ’

“ወደላይ ዘሎም ቆመ፣ ይምላለስም ጀመረ፣ እየተመላለሰም እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደ መቅደስ, ገባ።”4

በሌላ አነጋገር፣ ጴጥሮስ የክስነት ስልጣኑን በቀላሉ አልነበረም የተጠቀመው እና እንዲነሳ እና እንዲሄድ ሰውየውን የጋበዘው። ወደ ሰውየው በመድረስም ግብዣውን ተከታትሏል። በቀኝ እጁ በመውሰድ፣ ከፍ በማድረግ፣ እና ከዚያም ወደ ቤተመቅደስ አብሮት በመጓዝ።

በጴጥሮስ ምሳሌ መንፈስ ውስጥ፣ ፍራቻችንን በትክክለኛ እምነት በመተካት ቀጣይነት ባለው የሚስዮን ስራ የበለጠ መካፈል እንደምንችል ሀሳብ ሰጣለሁ፣ በእየእሩብ አመቱ፣ በየአመቱ አራቴ፣ አንድ ሰው እንኳ በመጋበዝ- በሙሉ ጊዜ አገልጋይ ሚስዮኖች እንዲማሩ። በትሁት መንፈስ እና ከጌታ ልብ በሚመካ መነሳሳት ለማስተማር ተዘጋጅተዋል። በጋራ ግብዣችንን መከታተል እና ወደ ቤተመቅደስ በሚወስደው የመንፈስዊ ጉዞዋቸው አብሯቸው በመጓዝ።

በዚህ ሂደት እንዲረዳችሁ፣ ሁሉንም አባላት እጋብዛለሁ፣ በምንም አይነት ጥሪ ላይ ቢሆን ወይም የቤተክርስቲያን የተሳትፎ ደረጃችሁ፣ ወንጌሌን አውጅ የሚለው መጽሀፍ ቅጂ እንድታገኙ። በማከፋፈያ ማእከሎቻችን ወይም በማይከፈልበት ኢንተርኔት ላይ ይገኛል። ለሚስዮን ስራ መምሪያ መጽሀፍ ነው፣ ይህም ማለት ለሁላችንም መምሪያ መጽሀፍ ነው። አንብቡት፣ አጥኑት፣ እና ከዛ በመጋበዝ እና በመከታተል ነብስ ወደ ክርስቶስ እንዴት ማምጣት እነደሚቻል እንዲገባችሁ የረዳችሁ ዘንድ የተማራችሁትን ተግብሩ። ፕሬዘዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንዳሉት፣ “አባላት እና ሚስዮኖች አንድ የመሆናቸው ጊዜ አሁን ነው፣ አብሮ ለመስራት፣ ነፍሳትን ወደ እርሱ ለማምጣት በጌታ የወይን እርሻ ላይ ለመስራት ጊዜው አሁን ነው።”5

ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን እንዲህ አስተማረ፤

“መከሩስ ብዙ ነው፣ ሰራተኞች ግን ጥቂት ናቸው፤

“እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሰራተኞች እንዲልክ ለምኑ።”6

በአለም ታሪክ ታላቅ ቁጥር ባላቸው የሙሉ ጊዜ ሚስዮኖች በእኛ ጊዜ ጌታ ያንን ጸሎት መልሷል። በዚህ የታማን አገልጋዮች አዲስ እንቅስቃሴ፣ በዚያ ታላቅ የነብሳት መከር ውስጥ እሱን እንድናግዝ ጌታ ሌላ እድል ሰጥቶናል።

ተግባራዊ መንገዶች አሉ አባላት ድንቅ ሚስዮኖቻችንን እንዲረዱ እና እንዲያግዙ የሚያስችሉ። ለምሳሌ፣ ወንጌሌን አውጁ የሚለውን መመሪያ እያነበባችሁ እንደሆነ ለሚስዮኖች መንገር ትችላላችሁ እና እነሱ በጥናታቸው የተማሩት መጠየቅ ትችላላችሁ። እርስ በእርስ ስትረዳዱ፣ በአባላት እና ሚስዮኖች መካከል መተማመን በእርግጥም ይጨምራል፣ ልክ ጌታ እንዳዘዘው፤

“ነገር ግን ማንም ሰው በጌታ በእግዚአብሔር ስም ሊናገር ይችላል፣ በአለም አዳኝም ስም ቢሆን።”7

እና፣ ስለሆነም፣ ለሰዎች እንድትመሰክሩ እና እንድታስጠነቅቁ ልኬአችኋለሁ እና የሰማም ሁሉ ጎቤቱን እንዲያስተነቅቅ ይሆናል።8

ወንድሞች እና እህቶች፣ ቤተሰቦች እና ጓደኞች ለሙሉ ጊዜ ሚስዮኖች በሚጽፉት ደብዳቤ እና ኢሜል ከወንጌን አውጅ መምሪያ ውስጥ በግላዊ ጥናታቸው የተማሩትን ቢያካትቱ ተጽእኖውን መገመት ትችላላችሁ? በሚስዮናቸው ልጆቻቸው የሚያጠኑትን እና የሚያስተምሩትን ቢያውቁ እና በይበልጥ ቢረዱ ለቤተሰቦች የሚያመጣውን በረከት ሊታያችሁ ይችላል? የእና የሚሆነውን ሚያስደንቅ የተትረፈረፈ የቤዛነት ክፍያ ለመመዘን እንኳን ትችላላችሁ፣ እንደ አዳኙ ቃልኪዳን ነብሳት ወደ እሱ እንዲመጡ በመጋበዝ ሄደት ምስክርነት ለሚያካፍሉ ሁሉ- እና ከዛ በእነዚያ ግብዣዎች ላይ ክትትል ለሚያደርጉ።

“የተባረካችሁ ናችሁ።” አለ ጌታ በዮሴፍ ስሚዝ አማካኝነት፣ “ያካፈላችሁት ምስክርነት መለእክት እንዲመለከቱት በሰማይ ተመዝግቧል፣ እና በእናንተ ይደሰታል፣ እና ሀጢያታችሁም የቅር ተብሏል።”9

“በዚህ ትእዛዝ የእናንተን ሀጢያት እኔ ይቅር እላለሁ- ጠንክራችሁ እንድትቀጥሉ… ስለተነገራችሁ ነገሮች ለአለም ሁሉ ምስክርነታችሁን በማካፈል።”10

ተከትለን ወደላይ ከሄድን፣ ጌታ እንድንወድቅ አያደርግም። በምስክርነት በተጣመረው መጋበዝ እና የእምነት ክትትል በቤተክርስቲያን አባላት በአለም ዙሪያ ስለሚያመጣው ሊነገር የማይችል ደስታ አይቻለሁ። በቅርቡ አርጀንቲና ውስጥ፣ ከዚህ አጠቃላይ ጉባኤ በፊት ወደ ቤተክርስቲያን አንድ ሰው እንዲጋብዙ አባላትን አበረታታሁ። ጆሽዋ የሚባል ስምንት አመት ልጅ አዳመጠ እና ምርጥ ጓደኛውን እና ቤተሰቡን በቦነስ አይረስ በሚገነው አትቢያ ዝግጅት ላይ ጋበዛቸው። የጆሽዋን ግብዣ እና የእምነት ክትትሉን ሚያብራራውን ከደረሰኝ ደብዳቤ ላንብብላችሁ፤

“መምጣታቸውን ለማትበየት ጥቂት ደቂቃዎች ወደ መግቢያ ጆሽዋ ይሮጣል። እንደሚመጡ ማወቁን ተናግሯል።

ምሽቱ ገፋ እና የጆሽዋ ጓደኛ አልመጣም፣ ጆሽዋ ግን ተስፋ አልቆረጠም። በእምነት በየጥቂት ደቂቃው የመግቢያውን በር ይመለከታል። ነገሮችን መቋቻ ጊዜ ሲጀምር ነብር ጆሽዋ ወደ እላይ እና ታች በመዝለል “መጥተዋል! መጥተዋ!” ብሎ አሳወቀ፣ ስመለከት ሙሉው ቤተሰብ ወደ ቤተክርስቲያን እየቀረቡ ነበር። ጆሽዋ እነሱን ለመቀበል ሮጦ ወጣ እና ጓደኛውን አቀፈ። ሁሉም ወደ ውስጥ ገቡ እና ዝግጅቱን የወደዱት የመስሉ ነበር። ጥቂት በራሪ ወረቀት ወስዱ እና አዲስ ጓደኞች በመግባባት ብዙ ጊዜ አሳለፉ። የዚህን ትንሽ ልጅ እምነት እና ህጻናትም ሚስዮኖች መሆን እንደሚችሉ ማየቴ በጣም አስደሰተኝ።”11

የእኛን ፈንታ ለማድረግ ስንጥር፣ አንዱን በመፈለግ፣ መጋበዝ እና እንደ ጆሽዋ በእምነት መከታተል፣ ከእኛ ጋር የኋለናው ቀን ቅዱሳን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲን ለመቀላቀል በመቶዎች እና ሺዎች የሚቆጠሩ እግዚአብሔርን ልጆች እናገኛለን። ስራውን በማፍጠኑ ጥረታችን ጌታ ሁላችንንም ይባርከን፣ በትህትና እጽልያለሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።