2022 (እ.አ.አ)
የጾምን ህግ መኖር
ሰኔ 2022 (እ.አ.አ)


የአካባቢ መሪ መልዕክት

የጾምን ህግ መኖር

በእምነት፣ በጾም እና በጸሎት አማካኝነት ተዓምራቶቻችንን አይተናል።

በ2020 (እ.አ.አ)፣ ባለቤቴ እና እኔ ሁለቱን ልጆቻችንን አሮንን እና ሙሴን ወደሃገር ቤት ለማምጣት ገንዘብ ፈልገን ነበር። በባንጋሎር(ህንድ)ሲከታተሉ የነበሩትን ትህርታቸውን ገና መጨረሳቸው ነበር፤ ሆኖም እነርሱን ለማምጣት ገንዘብ ለማሰባበሰብ ያደረግነው ጥረት ፍሬያማ አልነበረም። ስለዚህ ይህንን ጉዳይ ለጌታችን አሳልፈን ለመስጠት ወሰንን።

በዚያው ዓመት ውስጥ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በባንጋሎር ተስፋፍቶ የነበረ ሲሆን የመዛመት ፍጥነቱም እየጨመረ ነበር። ስለሁለቱ ልጆቻችን በጣም ተጨንቀን ነበር።

አንድ ዕሮብ ምሽት ጸሎት ካደረግኩኝ በኋላ ጾም አንዳደርግ የሚገፋፋ ስሜት ተሰማኝ፤ እየጾምኩኝ በነበረበት ሰዓትም ሁለቱ ልጆቼ በጸሎት እንዲተጉ ጠየቅኳቸው። እንዲህ አልኳቸው፣ “ልጆቼ፣ ዛሬ ማታ ልክ ፈርዖን እስራኤላውያን በቀይ ባህር በደረቅ መሬት ሲሻገሩ ሲያይ እንዳፈረው ጠላትን የሚያሳፍር ተዓምር እንዲደረግልን እንጠይቃለን። እኩለ ሌሊት ላይ እንነሳለን፣ እንዘጋጃለን ከዚያም ጸሎት እንጀምራለን።” የምሠራው ሥራ እንዳለኝ ሰበብ ፈጥሬ ባለቤቴ ከለሊቱ 11፡00 ሰዓት እንዲቀሰቅሰኝ ነገርኩት። በዚያው ምሽት ቅዱሳት መጻህፍትን አነበብኩ፣ ነፍሴን በብዙ ጸሎት አፈሰስኩ እንዲሁም የሰማይ አባታችንን ድንቅ ነገሮች አሰላስልኩ። በቀጣዩ ቀን ጌታ መሬታችንን የሚገዛን ሰው በመላክ ጥያቄያችንን መለሰልን።ለልጆቻችን መጓጓዣ ገንዘብ ለማሰባሰብ ላለፉት አስራ ሁለት ወራት ገዥ እየፈለግን ነበር። ተዓምራችን ተፈጽሞ ነበር!

ሽማግሌ ጆሴፍ ቢ.ወርዝሊን (1917–2008) እንዲህ አስተምረዋል: “ጾም ያለጸሎት ሙሉ አይደለም፤ በቀላሉ፣ መራብ ብቻ ነው የሚሆነው። ጾማችን በባዶ ሆድ ከመሆን የዘለለ እንዲሆን ልባችንን፣ አእምሯችንን እና ድምፃችንን በማንሳት ከሰማይ አባታችን ጋር መተባበር አለብን። ጾም ከታላቅ ጸሎት ጋር ሲጣመር ጉልበት አለው። በመንፈሱ መገለጥ አዕምሯችንን ሊሞላ ይችላል። በፈተና ጊዜ ሊያጠነክረን ይችላል።”1

የሞዛያ ልጆች የሚስዮን አገልግሎት አመርቂ ነበር፤ ምክንያቱም ራሳቸውን በብዙ ጸሎት እና ጾም ስላተጉ ነበር (አልማ 17፥3)።

ኢሳይያስ ዛሬ እንዴት መጾም እንዳለብን ይነግረናል፣ “እኔስ የመረጥኩት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?” (ኢሳይያስ 58፥6)።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደጾመኛ ለሰዎች እንዳንታይ ይመክረናል (ማቴዎስ 6፥18)። ለኔፋውያንም “እንደግብዞች አትሁኑ፤ ምክንያቱም ለሰዎች እንደጾመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠወልጋሉና። እውነት እላችኋለሁ፣ ዋጋቸውን ተቀብለዋል” ብሏቸው ነበር” (3 ኔፊ 13፥16)።

ኢየሱስ ክርስቶስ ህያው እንደሆነ አውቃለሁ። እርሱ ቤዛችን እና አዳኛችን ነው። ዛሬ በህይወት ባለው ነቢዩ በራስል ኤም. ኔልሰን አማካኝነት ቤተክርስቲያኑን ይመራል። እግዚያብሄር በህይወታችን እንዲያሸንፍ ስንመርጥ እግዚያብሄር “የተዓምራት አምላክ” እንደሆነ እናውቃለን።2

እህት ዴልፊን ማሬ ቢትሪስ ማዋንግ ሉኮ ሙዛማ የተወለደችው በኪክዊት(ባንዱንዱ፣ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ)ነው።እርስዋ እና ባለቤትዋ የአራት ልጆች ወላጆች ሲሆኑ የአካባቢ ድርጅት አማካሪ ሆና የተጠራችውም በሃምሌ 2021 (እ.አ.አ) ነው።

ማስታወሻዎች

  1. “የጾም ህግ፣” አጠቃላይ ጉባኤ፣ ሚያዝያ 2021(እ.አ.አ)።

  2. ራስልኤም. ኔልሰን፣ አጠቃላይ ጉባዔ፣ጥቅምት 2020(እ.አ.አ)።

አትም