2022 (እ.አ.አ)
ሃምሌ 1847(እ.አ.አ)፦ መስራቾች ወደሶልት ሌክ ሸለቆ ደረሱ።
ሰኔ 2022 (እ.አ.አ)


በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ውስጥ በዚህ ወር የተከሰተ

ሃምሌ 1847(እ.አ.አ)፦ መስራቾች ወደሶልት ሌክ ሸለቆ ደረሱ።

ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ በሰማዕትነት በተገደለበት ወቅት፣ ቅዱሳኑ በደህና ለመኖር የሚችሉበትን ቦታ በመፈለግ እና ቤተክርስቲያኗ ከመላው አለም የመጡ አባላትን መቀበል ትችል ዘንድ፣ የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን ፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ (1801–1877) የኋለኛው ቀን ቅዱሳንን በዩናይትድ ስቴትስ አቋርጠው ወደ ምድረበዳ በሚጓዙ ኩባንያዎች አደራጅተው ነበር። ብሪገም የሚፈልጉትን ቦታ ያውቁ ነበር። በራእይ አይተውት ነበር እና ወዴት እንደሚሄዱ ሲጠየቁም፣ “ወደ እሱ በመጣን ጊዜ አሳያችኋለሁ። አይቼዋለሁ፣ በራእይ አይቼዋለሁ፣ እና የተፈጥሮ ዓይኖቼ ባዩት ጊዜ አውቀዋለሁ።”1

በሐምሌ 24 ቀን፣ 1847 (እ.አ.አ)፣ ብሪገም ያንግ ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆ ለመጀመሪያ ጊዜ ተመለከቱ። ከአንድ ሺህ ማይል በላይ በሜዳ፣ በበረሃ እና በሸለቆዎች ውስጥ ከተጓዙ በኋላ፣ እይታው አስደናቂ ነበር። ይህ ቅዱሳን የሚሰፍሩበት እና ሌላ የፅዮንን ካስማ የሚመሰርቱበት ቦታ ነበር። ቤቶችን መገንባት፣ የፍራፍሬ እርሻዎችንና የአትክልት ቦታዎችን ማልማት እንዲሁም የአምላክን ሕዝቦች ከዓለም ዙሪያ መሰብሰብ ይችላሉ። እና ብዙም ሳይቆይ፣ ልክ ኢሳይያስ በትንቢት እንደተናገረው፣ የጌታ ቤት በተራሮች ላይ ይመሰረታል እና ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ይላል።2 ሸለቆውን ማዶ በመመልከትም፣ ብሪገም ለብዙ ደቂቃዎች ሸለቆውን አጠኑ፣ እናም እንዲህ አሉ “በቃ። ይህ ትክክለኛው ቦታ ነው፣ ይንዱ።”3

ልክ እንደ መጀመሪያዎቹ ቅዱሳን፣ የአለም ዙሪያ ሰዎች እንደ ዘመናዊ አቅኚዎች ከኋለኛው ቀን ቅዱሳን ጋር ለመቀላቀል፣ ሃይማኖታዊ ባህሎቻቸውን ተዉ እናም አንዳንዶቹ ቤተሰቦቻቸውን እና ቤታቸውን ትተው ሄዱ።

ሽማግሌ ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ እንዳሉት፦

“በአሥራ ዘጠነኛው መቶ ዘመን በነበሩት አቅኚዎች መካከል ቅድመ አያቶች የሉኝም። ነገር ግን፣ ከቤተክርስቲያኔ አባልነት የመጀመሪያዎቹ ቀናት ጀምሮ፣ ሜዳውን ከተሻገሩት ቀደምት አቅኚዎች ጋር የቅርብ ዝምድና ይሰማኛል። ብሔር፣ ቋንቋ እና ባህል ሳይገድባቸው፣ ለእያንዳንዱ የቤተክርስቲያኗ አባል እንደሚሆኑት፣ ለእኔም መንፈሳዊ ዘሮቼ ናቸው።”4

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት እንደመሆናችን መጠን እምነታችን የጠነከረው በመጀመሪያዎቹ እና በዘመናችን አቅኚዎች በተመዘገቡት ዘገባዎች ነው። የእነርሱ የእምነት እና የድፍረት ታሪክ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በረከት ያስታውሰናል እናም በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ እንድንቀጥል ያበረታቱናል።

ማስታወሻዎች

  1. ዴቪድ ደብልዩ. ኢቫንስ፣ “በሽማግሌ ኢራስተስ ስኖው የቀረበ ንግግር፣” ዴዘረት ኒውስ፣ ጥቅምት 22/1873፣ 4።

  2. ቅዱሳን የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ታሪክ፣ ቅጽ 2፣ No UnhallowedHand 1846-1893 [2020]፣ 67።

  3. ቅዱሳን፣ ቅጽ 2፣ 65።

  4. ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ የቀዳሚ አመራር ሁለተኛ አማካሪ፣ “የነብያትን ድምፅ ማድመጥ፣” ኢንዛይን፣ ሐምሌ 2008 (እ.አ.አ)፣ 5።