2022 (እ.አ.አ)
ራስን የመቻል ታላቅ መርህ
ሰኔ 2022 (እ.አ.አ)


የአባላት ድምጽ

ራስን የመቻል ታላቅ መርህ

ራስን የመቻልን መርህ በተግባር ላይ ለማዋል የምናደርገው ነገር ዛሬ እና ነገ እኛን እና ቤተሰቦቻችንን ይባርካል።

የአስራሁለቱ ሃዋርያት ሸንጎ አባል የሆኑት ሽማግሌ ቤድናር “ተግባራዊ እርምጃ መውሰድ የእምነት ልምምድ ነው”።1 ብለዋል።ራስን የመቻል እጅግ አስፈላጊው እርምጃ መጀመር ነው። በኮቪድ-19 አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነንም እንኳን አንድ ነገር መስራት እንችላለን! ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን በሚያዝያ 2020(እ.አ.አ) አጠቃይ ጉባኤ ላይ “ጌታ ጥረትን ይወዳል”2 ብለዋል። እናም ለዚያ የተገባው ቃልም “ጌታ የእኛን ትንሽ ነገር ግን የማያቋርጥ ጥረታችንን ያጎላል” የሚል ነው።”3

አሁን የሚወሰዱ ትናንሽ ራስን የመቻል እርምጃዎች በኋላ ላይ የትልቅ እርምጃዎችን ውጤት ሊያመጡ ይችላሉ።

በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኪንሻሳ የምትኖረው እህት ፑአቲ. ቲ ኦዲሌ ይህ መርህ በህይወቷ ውስጥ ሲተገበር አይታለች።ራስን የመቻልን ትምህርት ከጨረሰች በኋላ “የኮንጎ ሬስቶራንቴን የማስፋፋት ሀሳብ ነበረኝ” ብላለች። የምግብ አዘገጃጀት ስልጠና ለመውሰድ ወሰነች። “ስለምግብና ባህል ወይም ጋስትሮኖሚ ያለኝን እውቀቴን አሳደኩኝ። እናም ስለዓለም አቀፍ ምግብ አዘገጃጀት የበለጠ ተማርኩ። አሁን የእስያ፣ የአሜሪካ፣ የአውሮፓ እና የአፍሪካ ምግቦችን ማቅረብ እችላለሁኝ” ትላለች እህት ኦዲሌ።

“ተጨማሪ ገንዘብ ማግኘት ስለምንችል ትምህርቱ ረድቶናል።” በአሁኑ ጊዜ፣ “ራሳችንን የቻልን ነን፤ ምንም አይጎድለንም። አስራታችንን እና የጾም በኩራታችንን እንከፍላለን እንዲሁም ቤተሰቦቻችንን እንረዳለን” ትላለች። ወንድም ብርሃነ በላይ ወንድም ነጻ ዘርን በሚያቀርብ ፕሮግራም አማካኝነት መሬት አዘጋጀቶ፣ ተክሎ እና ተንከባከቦ ለቤተሰቦቹ የሚሆን እህል እንዳመረተ ያጋራል። ለቤተሰቡ የሚያስፈልገውን የተመጣጠነ ምግብ ለማግኘት ነበር ያዘጋጀው።

ከኪንሻሳ ዲአርሲ የመጣችው እህት ማርሴሊን ኩካሉኪላ ኩናንጊካ የኪንሻሳ ካስማ ፓትርያርክ የሆኑት የሲሞን ሌንዶ ቫንዳም ዋማንዴ ሚስት ነች።ቤተሰቧ ከጌታ የተቀደሰ የፓትርያርክ ጥሪ ለመቀበል ታማኝ ለመሆን፣ ለመዘጋጀት እና ብቁ ለመሆን ምን እንዳደረጉ ስትጠየቅ፣ “ሁልጊዜ ጌታን በህይወታችን ውስጥ ቁጥር አንድ ቦታ ላይ እናስቀምጠው ነበር“ ብላለች።ጌታ የሚሰጠውን ማንኛውንም ጥሪ እንቀበል ነበር፤ አንዲሁም ያንን ጥሪ በቻልነው በማንኛውም መንገድ እናጎላው ነበር።ምንም ይሁን ምን ቤተሰባችን የወንጌል መርሆችን እንዲኖሩ እና አንዳቸው ለሌላው እንዲሁም ለህብረተሰቡ የብቁነት ምሳሌ እንዲሆኑ አስተምረናል”ብላለች። ስለዚህ ጥሪው ሲመጣ ቤተሰቡ በመንፈሳዊ ራስን መቻልን ገንብተው ነበር፣ ተዘጋጅተው ነበር።

ምንም እንኳን ብዙ ሀብት ከሌላቸው ቤተሰብ የተገኘች ብትሆንም፣ ከካናንጋ፣ ዲአር ሲ የመጣችው እህት ፓቲየን ንጋሉላ ጋዜጠኛ ለመሆን ብርቱ ፍላጎት ነበራት።የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን አጠናቀቀች ከዚያም በራዲዮ/ቴሌቪዥን ጣቢያ ያለ ክፍያ በበጎ ፈቃደኝነት ሰራች።

እህት ኤሊሴ ቡዛንጉ እና ባለቤቷ ዣን ክላውድ የሚኖሩት ኪንሻሳ ውስጥ ነው። ሁለቱም ተመላሽ ሚስዮናውያን ናቸው፤በትዳር ህይወታቸው መጀመሪያ አካባቢ በገንዘብ ለመዘጋጀት ለመጀመር ወሰኑ። በትዳር ውስጥ ለ20 ዓመታት ስንቆይ ልጆቻችን ትምህርት እንዲያገኙ እንዲሁም በሚስዮን ማገልገል ይችሉ ዘንድ ብዙ መስዋዕትነት ከፍለናል። “የስጋዊ እና የመንፈሳዊ በረከቶቻችን ሚስጥር ሁልጊዜ አስራት መክፈል እና ጠንክሮ መስራት ነው።”

እነዚህ ቅዱሳን እንደሰጡት ምስክርነት ዛሬ የምናደርገው ትልቅም ይሁን ትንሽ ጥረት ይህንን አስደናቂ ራስን የመቻል መርህ ስንታዘዝ ሁላችንም መጪውን ጊዜ በደስታ እንድንመለከት ይረዳናል።

ማስታወሻዎች

  1. ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ Exercise Faith in Christ፣ (ቪዲዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org.

  2. ጆይ ዲ. ጆንስ፣ “An Especially Noble Calling፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020, 16.

  3. ክሪስቶፈር ደብልዩ. ዋድል፣ “There Was Bread፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020, 44.