2022 (እ.አ.አ)
ስለ መልከጸዴቅ ክህነት ተማሩ
ሰኔ 2022 (እ.አ.አ)


የቃል ኪዳን ጉዞዬ

ስለ መልከጸዴቅ ክህነት ተማሩ

“የዛሬው ማንነቴ በሕይወቴ ውስጥ ባለው በዚህ ድንቅ የተመለሰ ወንጌል ምክንያት ነው።”

“እናም ይህም ታላቅ ክህነት ወንጌሉን ያስተዳድራል እናም የመንግስቱን ሚስጥር ቁልፎች እንዲሁም የእግዚአብሔርን እውቀት ቁልፎችን ይዟል።” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥19)።

“የዛሬው ማንነቴ በሕይወቴ ውስጥ ባለው በዚህ ድንቅ በዳግም የተመለሰ ወንጌል ምክንያት ነው።” የፃኬን አጥቢያ አባሏ እህት ኮሲ ንድሎቩ ክህነት እንዴት ሕይወቷን እንደባረከው ስታስብ ትደሰታለች። እንዲህ ብላ ቀጠለች፣ “በመልከ ጸዴቅ ክህነት ኃይል አማካኝነት ይህ በዳግም የተመለሰ ወንጌል፣ ትምህርቶች፣ ነብዩ የተቀበለው ማስጠንቀቂያዎች እና ራዕዮች አባቴ እንድሆን እንደሚፈልገው እንድሆን እኔን እስተካክሎኛል እንዲሁም ማስተካከሉን ቀጥሏል።”

በመልከ ጸዴቅ ክህነት አማካኝነት እያንንዱ የቤተክርሰቲያን አባል የክህነት ስርዓቶችን መቀበል ይችላሉ። እነዚህ ስርዓቶችን ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳኖችን እንድንገባ ያስችሉናል።

የመልከ ጸዴቅ ክህነት ተሸካሚዎች የመፅናናት በረከቶችን ሊሰጡ እንዲሁም የታመሙትን ሊባርኩ ይችላሉ። እነዚህ በረከቶች ሲያስፈልጉ ታላቅ እፎይታን እና መፅናናትን መስጠት ይችላሉ።

ሴቶች እና ወንዶች በመልከ ጸዴቅ ክህነት ኃይል ስር በቤተክርስቲያን ውስጥ ሲያገለግሉ፣ ብቁ ወጣት ወንዶች ለመልከ ጸዴቅ ክህነት ይሾማሉ እናም በክህነት ስርዓቶች ውስጥ ያገለግላሉ።

ፕሬዝደንት ዳለን ኤች. ኦክስ እንዲህ አሉ፣ “ክህነት ማለት ለእግዚአብሔር ስራ ለሁሉም ልጆቹ ጥቅም ሲባል በታማኝነት የተያዘ መለኮታዊ ኃይል እና ስልጣን ነው። የክህነት በረከቶች፣ እንዲሁም እንደ የወንጌል ሙላት እና እንደ ጥምቀት፣ ማረጋገጫና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ፣ የቤተመቅደስ ቡራኬ እና የዘላለም ጋብቻ አይነት ስርዓቶች፣ ለወንዶች እና ለእህቶች በእኩል ደረጃ ተደራሽ ናቸው።”1

እህት ኮሲ እንዲህ አለች፣ “በዚህ ቀን እና ጊዜ፣ በዚህ ትርምስ በተሞላ ዓለም ውስጥ አባታችን እንድንሆን እንደሚፈልገው እንሆን ዘንድ እኛን ከፍ ለማድረግ፣ ለማሻሻል እና ለመርዳት ዋና ኃላፊነታቸው የሆነ ወንድሞች አሉን። ያ ደስታን እና መፅናናትን እንዴት እንደሚሰጠኝ። በመልከ ጸዴክ ክህነት አማካኝነት የሴለስቲያል መንግስት በሮች ለሁሉም እንደተከፈቱ ስለማውቅ ደስተኛ ነኝ።”

ማስታወሻዎች

  1. ዳለን ኤች ኦክስ፣ አጠቃላይ ጉባኤ በሚያዚያ 4 ቀን 2020 (እ.አ.አ)።

አትም