2022 (እ.አ.አ)
የገና ትምህርቶች
ታህሳስ 2022 (እ.አ.አ)


የአካባቢ መሪ መልእክት

የገና ትምህርቶች

በዚህ ገና ለናንተ እና ለቤተሰባችሁ ያለውን አስፈላጊነት በማሰብ የእየሱስ ክርስቶስ ውልደትን ተአምር ክፈቱ።

የታህሳስ ወር ቀርቧል፤ ምን ያህል አስደሳች የበአል ወቅት ነው። ልጆች ትልቅ ፈገግታ ያላቸው ይመስላል እንዲሁም የመልካም ፍቃድ ሙላት አየሩን ሞልቶታል። የእውነት ‘የመደሰቻ ወቅት‘ ነው። እህት አርደርን እና እኔ እንደእናንተ ገናን እና ወቅቱ የሚያመጣውን ደስታ እንወደዋለን። በቆንጆ ሁኔታ ያጌጡ የሚታዩ የገና ዛፎች አሉ፣ የሚያብለጨልጩ ማጋጌጫ ወረቀቶች ሱቆችን አስጊጠዋል፣ ብርሀኖች ያብረቀርቃሉ እንዲሁም የቡድን የገና መዝሙሮች ቤታችንን፣ ልባችንን፣ ገበያዎቻችንን እና የገበያ ማእከሎቻችንን ሞልተዋል። በማዕከላዊ አፍሪካ ውስጥ ቤተሰቦች ለማክበር ሲሰበሰቡ ምን አይነት ምግብ እንደሚበሉ ለማወቅ ብዙ አልቆየሁም ነገር ግን አስደሳች እንደሚሆን አውቃለሁ።

ነገር ግን ቆይ! በገና ጊዜ ክርስቶስስ? የእውነተኛው የገና ትርጉም የመሰረት ድንጋይ አዳኛችን እና የእርሱ መሲሃዊ ተልእኮ ናቸው። ስለዚህም በብልጭልጭ ወረቀቶቻችን እና አብረቅራቂ መብራቶች እሱ አለመሸፈኑን ማረጋገጥ አለብን። ‘ለወቅቱ ክርስቶስ ምክንያቱ’ እንደሆነ ለማስታወስ ተጨማሪ ምን ማድረግ እንደምንችል አስቤያለሁ። እነዚህ ሊረዷችሁ የሚችሉ አምስት ቀላል ሃሳቦች ናቸው።

  1. በገና እለት ትልቁን የድሎት ምግብ ከመመገባችሁ በፊት፣ በሉቃስ ሁለተኛ ምእራፍ ላይ የተገለጸውን የገና ታሪክ ለመመገብ ቤተሰባችሁን እንድትሰበስቡ ሀሳቤን አቀርባለሁ። ቀላል የሆኑ ግን የከበሩ ስጦታዎች ከመፈታታቸው በፊት የኢየሱስ ክርስቶስ ውልደት ተአምር ለእናንተ እና ለቤተሰባችሁ ያለውን አስፈላጊነት በማንበብ እና በማሰላሰል ፍቱ።

  2. የክርስቶስ ህይወት ሌሎችን የማገልግል ህይወት እንደነበር አስታውሱ። ይሕ የገና ወቅት እሱ ፍቅሩን ለእኛ እንዳሳየው ፍቅራችንን ለሌሎች በሚያሳይ መልኩ የምናገለግልበት ምቹ ጊዜ ነው። አንድ ህጻን ለጓደኞችና ጎረቤቶች የሚስጥር የገና አባት ሲሆን የሚፈጠረውን ጉጉት እና የሚማረውን ትምህርቶች አስቡት። ፍቅር በሚያስፈልገው ሰው በር ላይ ትንሽ ልጆቼ ኩኪስ፣ ፍራፍሬ ወይም ቤት የተሰራ ካርድ በማስቀመጥ የሚስጥራዊ አገልግሎት ሲያሳዩ የነበራቸው የደስታ ጩኸት አሁንም ይሰማኛል።

  3. ጥሩ ዘማሪ አይደለሁም ነገር ግን በደንብ የተጻፈ ግጥም እወዳለሁ።የገና መዝሙሮች ለሙዚቃ የተቀመጡ ግጥሞች ናቸው፣ ስለዚህ መዘመር ካልቻላችሁ በግጥሙ ተደሰቱ። እንዲሁም ቤተሰቦች፣ ቅርንጫፎች፣ እና አጥቢያዎች ተሰብስበው የክርስቶስ የምስጋና እና የአክብሮት መዝሙሮችን ሲዘምሩ የምንማራቸው ጠቃሚ የገና ትምህርቶች አሉ። ጥሩ ዘማሪ ባትሆኑም መዘመር ጥሩ ነው።

  4. ትንሽ ዛፍን ስታስጌጡ ወይም ምናልባት በቤታችሁ ውስጥ አንድ ክፍልን ስታስጌጡ የምትማሩትን የገና ትምህርቶች ችላ አትበሉ።ኮከብዋ ጠቢቦቹን የመራችው የአዲሷ ኮከብ ምሳሌ ናት (ማቲዎስ 2፡2 ይመልከቱ)፣ ቀላል የሆኑት መብራቶች ክርስቶስ ትክክለኛው ብርሀን እንደሆነ ያስታዉሱናል (ዮሀንስ 1፡9 ይመልከቱ) እናም በእርግጥ አዳኙ እንደሚወለድ ያበሰረው መልአክ አለ (ሉቃስ 1፡26 ይመልከቱ)።

  5. ሌላኛው የገና ትምህርት የመስጠት ስጦታ ነው። ክርስቶስ ለኛ የሰጠን ታላቁ ስጦታ፤ በጌቴሰማኒ በጀመረው፣ በቀራኒዮ በመስቀሉ ላይ በቀጠለው እና እኛ የሱ መንፈሳዊ ወንድሞች እና እህቶች ትንሳኤ እንድናገኝና በድጋሚ እንኖር ዘንድ በፍቃደኝነት ህይወቱን በመስጠት እና በትንሳኤ በተደመደመው፣ የማያልቅ ቤዛነት አማካኝነት ሊኖር የቻለው የዘላለማዊ ህይወት እድል ነው።

በዚህ የገና ወቅት የገና ትምህርቶችን ማስተማር እና መማር በደንብ ይከናወን።

መልካም ገና ለእያንዳንዳችሁ።

አትም