2022 (እ.አ.አ)
የኤፍኤስዋይ ጉባኤ መክፈቻ በአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ
ታህሳስ 2022 (እ.አ.አ)


የአካባቢ ዜናዎች

የኤፍኤስዋይ ጉባኤ መክፈቻ በአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ

በናይሮቢ፣ ኬንያ ወደ 700 ወጣቶች እና 80 ወጣት ያላገቡ ጎልማሶች ለአምስት ቀናት በተደረጉ ክፍሎች፣ ትምህርቶች እና እንቅስቃሴዎች ተደሰቱ።

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ በታሪኩ የመጀመሪያው የሆነውን የለወጣቶች ጥንካሬ (ኤፍኤስዋይ) ጉባኤ ከሀምሌ 4 እስከ 8 አካሄደ። ይህ የመክፈቻ ጉባኤ በአካባቢው ውስጥ እንዲፈጸሙ ቀጠሮ ከተያዘላቸው የኤፍኤስዋይ ጉባኤዎች ውስጥ የመጀመሪያው ነው።የጉባኤው ጭብጥ በምሳሌ 3፡5–6 ላይ እንደሚገኘው “በጌታ ታመኑ” የሚል ነበር።

ጉባኤውን የታደሙት 695 ወጣቶች፣ 77 ወጣት ያላገቡ ጎልማሶች እና ሶስት ሎጂስቲክሱን እና ክፍለ ጊዜውን የሚቆጣጠሩ ጥንዶች ነበሩ። ወጣቶችን በሚነኩ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ንግግር ለመስጠት የተደረደሩ ተናጋሪዎች ነበሩ።

የኤፍኤስዋይ ጉባኤዎች፤ እንቅስቃሴዎችን፣ አምልኮዎችን፣ እና ወጣቶች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት እንዲያጠነክሩ እና በመንፈሳዊ፣ በማህበራዊ፣በአካላዊ፣ እና በአዕምሯዊ መልኩ እንዲያድጉ እድሎችን የሚሰጡአቸውን ክፍሎች የሚያጠቃልሉ የአምስት ቀናት ዝግጅቶች ናቸው። የኤፍኤስዋይ ጉባኤዎች ለብዙ አመታት በስፋት ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከካናዳ ውጪ ሲካሄድ ነበር እናም ብሪግሀም ያንግ ዩኒቨርሲቲ በሚያዘጋጀው በተለይ ለወጣቶች በተሰኘው ጉባኤ (ኢኤፍዋይ) ላይ ተመስርቶ የተቀረጸ ነው። በአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ የናይሮቢ ኬንያ ወጣቶች ይህንን በኮቪድ-19 ምክንያት ተሰርዞ የነበረውን አስገራሚ ዝግጅት ለመሳተፍ እድል አግኝተው ነበር። በዛ አካባቢ ያሉ ሌሎች ሀገሮች በቅርቡ የራሳቸውን ያደርጋሉ።

የኤፍኤስዋይ መሪ ጥንድ የነበሩት ክፍለጊዜውን የሚመሩት ጥንዶች ወንድም እና እህት ሙካሳ የጉባኤውን አላማ አብራርተዋል፤ በጭብጡ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። እንዲሁም ወጣቶቹ ከሰዎች ጋር እንዲግባቡ፣ እንዲደሰቱ፣ እናም ከሁሉም በላይ በመንፈሳዊ እንዲታነጹ ጋብዘዋል።

“ወጣቶቹ በኤፍኤስዋይ ውስጥ ሲያልፉ በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነታቸውን እንዲያጠነክሩ እና በእርግጠኝነት በጌታ ላይ ሊተማመኑ እንደሚችሉ እንዲያውቁ ተስፋ እናደርጋለን” ብላለች እህት ኢውኒስ ሙካሳ።

ተሳታፊዎቹ በወንድም ሂላሪ ኦኮት እና በእህት ሲንቲያ ትሪኒቲ አመራር ስር ወንድም እና እህት ባዱን፣ ወንድም ካርሎስን እና እህት ሀርሌን፣ ወንድም እና እህት ሙካሳን፣ 695 ወጣቶችን፣ እንዲሁም 77 አማካሪዎችን ያካትት ነበር።የተጋበዙ ተናጋሪዎች እህት ኤማ ምቢቲ፣ እህት ሊሊያን ኦዲየሮ፣ ወንድም እና እህት አንዲካ እና ወንድም ኤሪክ ኦንያንጎ ነበሩ። ከቤተሰብ መፈለጊያ ስፍራ ሽማግሌ እና እህት ስፓክማን፣ ሽማግሌ እና እህት ስታፍለር እና ወንድም ሮበርት ኦፕዮ ከእኛ ጋር ነበሩ።

የጉባኤው ትልቁ ክፍል በሽማግሌ እና በእህት ሲታቲ የተሰጠው የተለየ አምልኮ ነበር። እህት ሲታቲ እንደወጣት በመታዘዝ እና ትእዛዛቱን በመጠበቅ በመጠንከር ፈተናን ያሸነፈችበትን ልምድ አካፍላለች፤ ብዙ ጊዜ በቤተሰቦችዋ ስትላክ እንዴት ከ3 ኪ.ሜ በላይ ትሮጥ እንደነበር እና ልክ እንደ ኔፊ እንዳላጉረመረመች አካፍላለች። ወጣቶቹን የንጽህና ህግን እንዲጠብቁ፣ ጀግና እንዲሆኑ እና በንጽህና ህግ ላይ በማተኮር የእግዚአብሄርን ትእዛዛት በመጠበቅ ታዛዥ እንዲሆኑ ጋብዛለች።

ሽማግሌ ሲታቲ ነጻ ምርጫችንን ትክክለኛውን ለመምረጥ የመጠቀማችንን አስፈላጊነት አበክረው ተናግረዋል፤ ይኸውም ለነፍሳችን ደህንነትን ስለሚያመጣ ነው። “ሁሉም የእግዚአብሄር ትእዛዛት በምድር ላይ ሰላም ማግኘትን የሚያጠቃልለውን፤ ዘላለማዊ ደስታችሁን የሚያረጋግጡ ናቸው፣ እግዚአብሄር ምርጫ ሰጥቷችኋል፣ እንዳትታለሉ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን፣ መሪዎችን፣ ነብዩን፣ ቤተሰቦችን ተከተሉ፣ እናም ስህተትን ወደመስራት ወይም የንጽህና ህግን ወደመጣስ አትመሩም።” ማጭበርበርን እንዲሸሹ፣ የንጽህና ህግን ለመጠበቅ ጠንካራ እና ደፋር እንዲሆኑ ወጣቶቹን በመማጸን ንግግራቸውን ዘግተዋል።

“ነጻ ምርጫ የመምረጥ ሀይል ነው፣ ሞሮኒ 7:12–17 መልካም የሆኑ ነገሮች በሙሉ ከእግዚአብሄር እንደሚመጡ ያስተምራል።እባካችሁ ይህን ጥቅስ አስታውሱ እና ያለመጠራጠር ሂዱበት።”

አትም