2022 (እ.አ.አ)
ቤተክርስቲያኗ በኢትዮጵያ የሚገኙ 2,500 የተራቡ ሰዎችን መገበች።
ታህሳስ 2022 (እ.አ.አ)


የሰብአዊነት ዜና

ቤተክርስቲያኗ በኢትዮጵያ የሚገኙ 2,500 የተራቡ ሰዎችን መገበች።

በመገናኛ ለሚኖሩ ከ500 በላይ ለሚሆኑ ቤተሰቦች የታሸጉ ምግቦች ተሰራጭቷል።

በአዲስ አበባ መገናኛ የሚኖሩ በአጠቃላይ ወደ2,500 የሚሆኑ የተራቡ ሰዎችን የሚይዙ ወደ550 የሚገመቱ በድህነት የተጠቁ ቤተሰቦች ከኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ላለፉት በርካታ ወራት የምግብ ድጋፍ ሲያገኙ ቆይተዋል።

የጎዳና ተዳዳሪዎች እና የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው ብዙ ሰዎች ያሉበት የመገናኛ ወረዳ 5 የአካባቢ የመንግስት ባለስልጣናት ምግብ የሚሰጣቸውን ቤተሰቦች ለመለየት ከቤተክርስቲያኗ ጋር እየሰሩ ነው። የታሸጉ ምግቦቹ ሪል ሂዩማኒታሪያን በተሰኘ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት አማካኝነት ይሰራጫሉ።

ቤተክርስቲያኗ ሀምሌ 16, 2022 (እ.አ.አ)፣ ኢኒሼቲቩን ለማስጀመር በተደረገው የምግብ ዘመቻ ላይ ተሳትፋለች። በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ሚሲዮን ሚሲዮናዊ የሆነው ሽማግሌ ጆሴፍ ኔልሰን፣ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚገኙ ስራ ፈላጊዎችን ወይም በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎችን ለመርዳት እድል የፈጠረ እንደበር ተናግሯል።

ከነዚህ ሰዎች አንዷ ትግስት ንጉስ ኪሮስ ነች። “በአካባቢያችን በተከሰተው ጦርነት ሳቢያ ቤተሰቦቼ ችግር ውስጥ ወድቀው ስለነበር ወደአዲስ አበባ የመጣሁት ብቻዬን ነበር” ስትል ተናግራለች ወይዘሪት ትዕግስት። “ይህን ምግብ በማግኘቴ ወደዚህ በመምጣት ከጦርነቱ ለመዳን ይችሉ ዘንድ ከእኔ ጋር እንዲሆኑ ለቤተሰቤ የምልከው ብዙ ገንዘብ መቆጠብ እችላለሁ።”

ሌላዋ ድጋፍ የተደረገላት ሰላም ማቲዮስ አየለ ስትሆን እሽግ ምግቡ ለቤተሰባቸው ተስፋ ሰጪ መሆኑን ተናግራለች። “በኢትዮጵያ ጊዜው በጣም አስቸጋሪ ከመሆኑ የተነሳ ስራ እና ምግብ ማግኘት አስቸጋሪ ነው” ብላለች ወይዘሪት ትዕግስት። “ይህ ምግብ ቤተሰቤን እንደሚመግብ እና ይህን የዝናብ ወቅት ማሳለፍ እንደሚያስችለን ተስፋ አደርጋለሁ”

በዝግጅቱ ላይ፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የአካባቢ መሪ የሆነው ብርሀኑ ሞላ ቤተክርስቲያኗ ልገሳውን የሰጠችው የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርቶች ለመከተል በምታደርገው ጥረት እንደሆነ ለመገናኛ ብዙኃን፣ ለማህበረሰቡ አባላት እና ለመሪዎች ተናግሯል።

አቶ ብርሃኑ “እኛ ሁላችን በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠርን እንደመሆናችን መጠን ለወገኖቻችን መልካም ማድረግ እና ያለንን ለተቸገሩት ማካፈል ይኖርብናል” ሲል ተናግሯል።

“በሀገራችን ሰላምና ብልፅግና እንዲመጣ የበኩላችንን ሚና መወጣት አለብን። ቤተ ክርስቲያኗ የተቸገሩትን መርዳቷን ትቀጥላለች።”

በዝግጅቱ ታድሞ የነበረው የቤተክርስቲያኗ ሚስዮናዊ ሽማግሌ ካሌብ ፎላው ስለነበረው ልምድ ስሜቱን አካፍሏል።

“ይህ በችግር ውስጥ ያሉትን ሰዎች ፍላጎት ለማሟላት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በጋራ ለመስራት የተከፈተው እድል እንደ አዳኙ በማገልገል ረገድ ለውጥ ለማምጣት አስችሎናል” ብሏል። እያንዳንዳችንን ከምንገምተው በላይ ይወደናል።

አትም