ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
መለወጥ ግባችን ነው


“መለወጥ ግባችን ነው፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“መለወጥ ግባችን ነው፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ሴት ቅዱሳን መጽሐፍትን በቤት ስታጠና

መለወጥ ግባችን ነው

ሁሉም የወንጌል መማር ማስተማር አላማ በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ በጥልቅ እንድንለወጥ እና እነርሱን እንድንመስል እኛን መርዳት ነው። በዚህ ምክንያት፣ ወንጌልን በምናጠናበት ጊዜ፣ እኛ አዲስ መረጃን ብቻ የምንፈልግ ሳይሆን “አዲስ ፍጡር” ለመሆንም እንፈልጋለን(2ኛ ቆሮንቶስ 5፥17)። ይህም ልባችንን፣ አመለካከታችንን፣ ድርጊቶቻችንን እና ተፈጥሮአችንን ለመለወጥ ይረዳ ዘንድ በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ መታመን ማለት ነው።

ነገር ግን እምነታችንን የሚያጠናክር እና ወደ ለውጥ ተዓምር የሚመራው አይነት የወንጌል ትምህርት በሙሉ በአንድ ጊዜ አይከሰትም። ከመማሪያ ክፍል በላይ ወደ ልባችን እና ቤታችን ይሰፋል። ወንጌልን መረዳት እና መኖር የማይቋረጥ የእለትተለት ጥረትን ይጠይቃል። ወደ ትክክለኛ መለወጥ የሚመራ የወንጌል ትምህርት የመንፈስ ቅዱስን ተፅዕኖ ይፈልጋል።

መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ይመራናል እናም ስለዚያ እውነት ይመሰክራል ( ዮሐንስ 16፥13ን ይመልከቱ)። እርሱ አዕምሯችንን ያበራል፣ ግንዛቤያችንን ያፋጥናል እናም የእውነት ሁሉ ምንጭ በሆነው በእግዚአብሔር ራዕይ ልባችንን ይነካል። መንፈስ ቅዱስ ልባችንን ያነጻል። በእውነት የመኖር ፍላጎትን በውስጣችን ያነቃቃል፣ እንዲሁም ይህን የምናደርግባቸውን መንገዶች በጸጥታ ይነግረናል። በእውነትም፣ “መንፈስ ቅዱስ … ሁሉንም ያስተምረናል” (ዮሐንስ 14፥26)።

በእነዚህ ምክንያቶች፣ ወንጌልን ለመኖር፣ ለመማር፣ እና ለማስተማር በምናደርገው ጥረት፣ በመጀመሪያ እና ከሁሉም በላይ የመንፈሱን አብሮ መሆን መፈለግ አለብን። ይህ ግብ ምርጫዎቻችንን መምራት እና ሀሳባችንን እና ድርጊቶቻችንን መምራት ይገባዋል። የመንፈስን ተጽዕኖ የሚጋብዘውን ማንኛውንም ነገር ሁሉ መፈለግ እና የእሱን ተጽዕኖ ከሚያርቁ ነገሮች መራቅ አለብን—እኛ ለመንፈስ ቅዱስ መገኘት ብቁዎች ለመሆን ከቻልን፣ እንዲሁ ከሰማያዊ አባት እና ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረን ለመኖር ብቁ ለመሆንም እንደምንችል እናውቃለንና።

አትም