ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
የግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናትዎን ለማሻሻል ሀሳቦች


“የግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናትዎን ለማሻሻል ሀሳቦች” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021(እ.አ.አ)]

“የግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናትዎን ለማሻሻል ሀሳቦች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
አንድ ሴት ቅዱሳን መጻህፍትን በቤት ስታጠና

የግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናትዎን ለማሻሻል ሀሳቦች

በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ የሚገኘውን የእግዚአብሔር ቃል ጥናትዎን የሚያሳድጉ አንዳንድ ቀላል መንገዶች እነሆ።

ስለኢየሱስ ክርስቶስ እውነቶችን ይፈልጉ

ቅዱሳን መጻህፍት ሁሉም ነገሮች ስለክርስቶስ እንደሚመሰክሩ ያስተምሩናል ( 2 ኔፊ 11፥4ሙሴ 6፥63፣ ይመልከቱ)፣ ስለዚህ ስለአዳኝ እና እርሱን እንዴት መከተል እንደሚቻል በሚያስተምሩት ጥቅሶች ላይ ትኩረት መስጠትን ወይም ምልክት ማድረግን አስቡ።

የሚያነሳሱ ቃላትን እና ሃረጎችን ይፈልጉ

በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ የተወሰኑ ቃላቶች እና ሀረጎች በተለይ ለእርስዎ እንደተጻፉ ሆነው ሊሰሟችሁ ይችላሉ። እነሱ ለግላችሁ ተገቢ እንደሆኑ ይሰማዎታል እናም ያነሳሱዎታል እንዲሁም ያነቃቁዎታል ። እነዚህንም በቅዱሳን መጻህፍትዎ ላይ ምልክት ማድረግን ወይም በጥናት ደብተርዎ ውስጥ መፃፍን ያስቡ።

የወንጌል እውነቶችን ይፈልጉ

አንዳንድ ጊዜ የወንጌል እውነቶች (ብዙውን ጊዜ ትምህርት ወይም መርሆዎች ተብለው ይጠራሉ) በቀጥታ ይገለጻሉ፣ እናም አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በምሳሌ ወይም በታሪክ አማካይነት ይገለጻሉ። እራሳችሁን ጠይቁ፣ “እነዚህ ጥቅሶች ምን ዘለዓለማዊ እውነቶችን ያስተምራሉ?”

መንፈስን ስሙ

ከምታነቡት ጋር የማይዛመዱ ቢሆኑም፣ ለሀሳብዎ እና ለስሜትዎ ትኩረት ስጡ። እነዚያ ግንዛቤዎች የሰማይ አባትዎ እንዲማሩ የሚፈልጋቸው ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ።

ቅዱሳን መጻህፍትን ከሕይወትዎ ጋር አመሳስሉ

የምታነቧቸው ታሪኮች እና ትምህርቶች በሕይወትዎ ውስጥ እንዴት እንደሚሠሩ ልብ ይበሉ። ለምሳሌ፣ “እኔ ከማነበው ጋር የሚመሳሰሉ ምን ልምዶች አግኝቻለሁ?” ወይም “በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ ያለውን የዚህን ሰው ምሳሌ መከተል የምችለው እንዴት ነው?” ብለው መጠየቅ ይችላሉ።

በሚያጠኑበት ጊዜ ጥያቄዎችን ጠይቁ

ቅዱሳን መጻህፍትን ሲያጠኑ፣ ጥያቄዎች ወደ አዕምሮዎ ሊመጡ ይችላሉ። እነዚህ ጥያቄዎች ከምታነቡት ጋር ወይም በአጠቃላይ ከሕይወትዎ ጋር ሊዛመዱ ይችላሉ። እነዚህን ጥያቄዎች አሰላስሉ እና ቅዱሳን መጻህፍትን ማጥናትን ስትቀጥሉ መልሶቹን ፈልጉ።

ምስል
ወጣቶች ቅዱሳን መጽሐፍትን በቤት ሲያጠኑ

የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት መርጃን ይጠቀሙ

በምታነቡት አንቀጾች ላይ ግንዛቤ ለማግኘት የግርጌ ማስታዎሻዎቹን፣ የአርዕስት መምሪያን፣ የመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ-ቃላትን፣ እና የቅዱሳን መጻህፍት መመሪያ (scriptures.ChurchofJesusChrist.org)፣ እንዲሁም ሌሎች የጥናት እርዳታዎችን ይጠቀሙ።

የቅዱሳን መጻህፍትን አገባብ ከግምት ውስጥ ያስገቡ

የቅዱስ ጽሑፍን አገባብ ማለትም ፅሁፉ የተከናወነበትን ሁኔታ እንዲሁም ጊዜ እና ቦታ ከግምት ውስጥ ካስገቡ ትርጉም ያላቸውን ግንዛቤዎችን ማግኘት ይችላሉ። ለምሳሌ፣ ነብይ ያነጋግራቸውን ሰዎች ያለፈ ታሪክ እና እምነቶች ማወቁ የቃላቱን ዓላማ በተሻለ ለመረዳት ይረዳዎታል።

ሀሳብዎን እና ስሜትዎን መዝግቡ

በሚያጠኑበት ጊዜ የሚመጡትን ግንዛቤዎች ለመመዝገብ ብዙ መንገዶች አሉ። ለምሳሌ፣ ትርጉም ያለው ቃል ወይም ሐረግ ላይ ምልክት ሊያደርጉ እንዲሁም ሀሳብዎን በቅዱሳን መጻህፍቶችዎ ውስጥ እንደ ማስታወሻ ሊፅፉ ይችላሉ። እንዲሁም የሚቀበሉትን ግንዛቤዎች፣ ስሜቶች፣ እና ሃሳቦች ማስታወሻ ደብተርዎ ላይ መያዝ ይችላሉ።

የኋለኛው ቀን ነቢያትን እና ሐዋርያትን ቃል ያጥኑ

በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ ስለሚያገኟቸው መርሆዎች የኋለኛው ቀን ነቢያት እና ሐዋርያት ምን እንዳስተማሩ ያንብቡ (ለምሳሌ፣ conference.ChurchofJesusChrist.org እና የቤተክርስቲያን መጸሔቶችን ይመልከቱ።)

ግንዛቤዎችን ያጋሩ

ከግል ጥናትዎ ያገኙትን ግንዛቤዎች መወያየት ሌሎች ሰዎችን ለማስተማር ጥሩ የሆነ መንገድ ብቻ ሳይሆንያነበቧቸውን በተመለከተ ያሎትን ግንዛቤ ለማጠናከርም ይረዳል።

በተማሩት ይኑሩ

የቅዱሳን መጻሕፍት ጥናት ማነቃቃት ብቻ ሳይሆን አኗኗራችንን እንድንቀይር ሊያደርጉን ይገባል። በሚያነቡበት ጊዜ መንፈስ እንዲያደርጉ የሚገፋፋዎትን ያድምጡ፣ ከዚያም በእነዚያ ማነሳሻዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ይወስኑ።

ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር እንዲህ አሉ፦ “እኛም ታማኝ ደቀመዛሙርት ለመሆን እና እስከመጨረሻ በጥንካሬ ለመፅናት የሚያስፈልጉንን ቤተክርስቲያኗ እንደተቋም እንድታስተምረን ወይንም እንድትነግረን መጠበቅ አይገባንም ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥29ይመልከቱ።) ይልቁንም፣ የግል ሀላፊነታችን መማር ያለብንን ለመማር፣ መኖር እንዳለብን በምናውቀው መልኩ ለመኖር፣ እናም መምህር እንድንሆን የሚፈልገንን ለመሆን ነው። ቤታችንም ለመማር፣ ለመኖር፣ እና ለመሆን ዋነኛ አመቺ ስፍራ ነው” (“ማንኛውንም አስፈላጊ ነገር ለማግኘት ተዘጋጁ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 102)።

አትም