“ተጨማሪ የጥናት ምንጮች፣” ኑ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]
“ተጨማሪ የጥናት ምንጮች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)
ተጨማሪ የጥናት ምንጮች
አብዛኛዎቹ እነዚህ የጥናት ምንጮች በወንጌል ቤተ-መጽሐፍት መተግበሪያ ውስጥ እና በ ChurchofJesusChrist.orgላይ ይገኛሉ።
መዝሙር እና የልጆች መዝሙር መጽሐፍ
የተቀደሰ ሙዚቃ መንፈስን ይጋብዛል እናም ትምህርትን በማይረሳ መንገድ ያስተምራል። የታተሙ መዝሙሮችን እና የልጆች ሙዚቃዎችንከመጠቀም በተጨማሪም፣ የብዙ መዝሙሮች እና የልጆች ሙዚቃዎችን የድምፅ እና የቪዲዮ ቅጂዎችን በ music.ChurchofJesusChrist.org እና በቅዱስ መዝሙር እና የወንጌል ሚዲያ ፕሮግራሞች ላይ ማግኘት ይችላሉ።
የመንፈሳዊ ትምህርት ቤት እና የኢንስቲቱት መመሪያ መጽሐፎች
የመንፈሳዊ ትምህርት ቤት እናየኢንስቲቱት መመሪያ መጽሐፎች በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ ለሚገኙት መሰረታዊ መርሆዎች እና ታሪኮች ታሪካዊ መግለጫ እና የመሠረተ ትምህርት አስተያየትን ያቀርባሉ።
የቤተክርስቲያን መጽሔቶች
የ ፍሬንድ, ለወጣቶች ጥንካሬ, እና የ ሊያሆና መጽሔቶች ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦችን ሲያስተምሩ መሰረታዊ መርሆዎቹን የሚደግፉ ታሪኮችን እና ተግባሮችን ይዘዋል።
የወንጌል ርዕሶች
በ የወንጌል ርዕሶች (topics.ChurchofJesusChrist.org) ውስጥ ስለወንጌል ርዕሰ ጉዳዮች፣ እንዲሁም ከእነዚህ ጋር የሚገናኙ እንደ የአጠቃላይ ጉባኤ መልእክቶች፣ መጣጥፎች፣ ጥቅሶች፣ እና ቪዲዮዎች ያሉ የተለያዩ መሰረታዊ መረጃዎች ጠቃሚ አገናኞችን ለማግኘት ይችላሉ። እንዲሁም ለትምህርታዊ እና ታሪካዊ ጉዳዮች ጥልቅ መረጃ የሚሰጡ የወንጌል ርዕሶች ጽሁፎችለማግኘት ይችላሉ።
የብሉይ ኪዳን ታሪኮች
የብሉይ ኪዳን ታሪኮች በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኙ ትምህርት እና ታሪኮችን ልጆች እንዲማሩ ሊረዳ ይችላል። እንዲሁም የእነዚህን ታሪኮች ቪዲዮዎች በወንጌል ቤተመጻሕፍት መተግበሪያ ውስጥ እና በ MediaLibrary.ChurchofJesusChrist.orgማግኘት ይችላሉ።
የቅዱሳን ፅሁፎች ታሪኮች ማቅለሚያ መጽሐፍ፦ ብሉይ ኪዳን
ይህ የጥናት ምንጭ ልጆች ከብሉይ ኪዳን የሚማሩትን ትምህርት ለማሳደግ የተነደፉ አዝናኝ ቀለም የመቀባት ተግባራዊ ገጾችን ያካትታል።
ቪዲዮዎች እና ስነ ስእል
የስዕል ስራ፣ ቪዲዮች፣ እና ሌሎች ሚዲያዎች ቤተሰቦቻችሁ ከቅዱሳን መጻህፍት ጋር የተዛመዱትን ትምህርቶችን እንዲገነዘቡ እና ታሪኮችን በአይነ ህሊና እንዲመለከቱ ይረዷቸዋል። የቤተክርስቲያኗን የሚዲያ የጥናት ምንጮችን ክምችት ለማሰስ የወንጌል ሚዲያን በ MediaLibrary.ChurchofJesusChrist.org ውስጥ ይጎብኙ። የወንጌል ሚዲያ የሞባይል መተግበሪያም ይገኛል። ብዙ መጠቀም የሚችሏቸው ምስሎችም በ ወንጌል ስነጥበብ መጽሐፍውስጥ ይገኛሉ።
በአዳኙ መንገድ ማስተማር
በአዳኙ መንገድ ማስተማር ስለክርስቶስ መሰል የማስተማሪያ ዘዴ መርሆችን ለመማር እና ተግባራዊ ለማድረግ ሊረዳዎት ይችላል።