ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ወጣት ልጆችን ማስተማር


“ወጣት ልጆችን ማስተማር፣” ኑ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ወጣት ልጆችን ማስተማር፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ወላጆች እና ወጣት ልጅ ወደ መጸሐፍ ሲመለከቱ

ወጣት ልጆችን ማስተማር

በቤተሰባችሁ ውስጥ ወጣት ልጆች ካሉ ለመማር የሚረዷቸው አንዳንድ ተግባራት እነሆ፦

  • ዘምሩ።ልጆች የመዝሙር መጽሐፍ ውስጥ ያሉ መዝሙሮች እና ሙዚቃዎች ትምህርትን በኃይል ያስተምራሉ። ከምታስተምሯቸው የወንጌል መሰረታዊ መርሆዎች ጋር የሚዛመዱ መዝሙሮችን የርዕሶች ማውጫንልጆች የመዝሙር መጽሐፍ በስተጀርባ በማግኘት ተጠቀሙ። ልጆቻችሁ የመዝሙሮቹን መልእክቶች በሕይወታቸው ላይ እንዲያዛምዱ እርዷቸው። (“ቅዱስ መዝሙርን በወንጌል መማር ላይ ስለመጨመር” አስመልክቶ በዚህ ግብዓት ውስጥ ይመልከቱ።)

  • አንድን ታሪክ አዳምጡ ወይም ተውኑ ወጣት ልጆች ከቅዱሳን መጽሃፍት፣ ከህይወታችሁ፣ ከቤተሰባችሁ ታሪክ፣ ወይም ከቤተክርስቲያን መጽሔቶች ውስጥ የሚመጡ ታሪኮችን ይወዳሉ። በትረካው ውስጥ እነርሱን ለማሳተፍ መንገዶችን ፈልጉ። እነርሱ ስዕሎችን ወይም ዕቃዎችን መያዝ፣ የሚሰሙትን በስዕል መልክ መሳል፣ ታሪኩን መተወን፣ ወይም ታሪኩን በመናገር መርዳት ይችላሉ። በምታጋሯቸው ታሪኮች ውስጥ ልጆቻችሁ የወንጌል እውነቶችን እንዲገነዘቡ እርዷቸው።

  • ቅዱሳን መጻህፍትን አንብቡ ወጣት ልጆች በጣም ብዙ ማንበብ አይችሉም ይሆናል፣ ነገር ግን ከቅዱሳን መጻህፍት በመማር እነርሱ እንዲሳተፉ ለማድረግ ይችላሉ። በአንድ ጥቅስ፣ ቁልፍ ሐረግ ወይም ቃል ላይ ማተኮር ያስፈልጋችሁ ይሆናል። ልጆች ከቅዱሳን መፃህፍት ውስጥ አጫጭር ሃረጎችን የተወሰነ ጊዜ ከደጋገሙ ለመሸምደድ ይችላሉ። የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰሙ፣ መንፈስ ቅዱስ ይሰማቸዋል።

  • ፎቶግራፍ ወይም ቪዲዮ ይመልከቱ ለልጆቻችሁ ከወንጌል መርሆ ወይም የመጽሐፍ ታሪካ ጋር የሚዛመድ ምስል ወይም ቪዲዮ ስታሳዪአቸው፣ እየተመለከቱት ካለው ነገር እንዲማሩ የሚረዷቸውን ጥያቄዎች ጠይቋቸው። ለምሳሌ፣ እንደዚህ ብላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ፣ “በዚህ ሥዕል ወይም ቪዲዮ ውስጥ ምን እየሆነ ነው? ምን ስሜት ይሰጣችኋል?” ስዕሎችን እና ቪዲዮዎችን ለመፈለግ፣ የወንጌል ሚዲያ፣ MediaLibrary.ChurchofJesusChrist.org፣ እና children.ChurchofJesusChrist.org ጥሩ ቦታዎች ናቸው።

  • ፍጠሩ። ልጆች ከሚማሩት ታሪክ ወይም መሠረታዊ መርሆ ጋር የሚዛመድ አንድ ነገር መገንባት፣ መሳል ወይም ቀለም መቀባት ይችላሉ።

  • በምሳሌአዊ እቃዎችትምህርቶች ውስጥ መሳተፍ ቀለል ያለ የእቃ ምሳሌአዊ ትምህርት ልጆቻችሁ ለመረዳት አስቸጋሪ የሆነውን የወንጌል መርህ እንዲገነዘቡ ሊረዳቸው ይችላል። የእቃ ምሳሌአዊ ትምህርቶችን በምትጠቀሙበት ጊዜ፣ ልጆቻችሁ እንዲሳተፉበት የሚያስችሏቸውን መንገዶች ፈልጉ። እነሱ በመመልከት ብቻ ሳይሆን በተሳትፎ ተሞክሮ የበለጠ ይማራሉ።

  • ትወና ልጆች በእውነተኛ ህይወት ውስጥ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉትን ሁኔታዎች በሚና ትወና ሲጫወቱ የወንጌል መሰረታዊ መርሆች በህይወታቸው እንዴት እንደሚሠራ የበለጠ ለመረዳት ይችላሉ።

  • ተግባሮችን ደጋግሙ ወጣት ልጆች ፅንሰ ሀሳቦችን ለመረዳት ደጋግመው መስማት ያስፈልጋቸው ይሆናል። ታሪኮችን ወይም እንቅስቃሴዎችን አዘውትራችሁ ለመድገም አትፍሩ። ለምሳሌ፣ አንድን የቅዱስ ጽሁፍ ታሪክ፣ ከቅዱሳን መጻህፍት በማንበብ፣ በራሳችሁ ቃላት በማሳጠር፣ ቪዲዮን በማሳየት፣ ልጆች ታሪኩን ለመናገር እንዲረዷችሁ በመፍቀድ፣ ታሪኩን እንዲተውኑ በመጋበዝ እና በመሳሰሉ ነገሮች፣ በተለያዩ መንገዶች ደጋግመው ማካፈል ይችላሉ።

አትም