ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
የቤተሰባችሁን የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ለማሻሻል ሀሳቦች


“የቤተሰባችሁን የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ለማሻሻል ሀሳቦች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“የቤተሰባችሁን የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ለማሻሻል ሀሳቦች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ልጅ እና እናት ቅዱሳን መጻህፍትን በቤት ሲያጠኑ

የቤተሰባችሁን የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ለማሻሻል ሀሳቦች

መደበኛ የቤተሰብ የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ቤተሰባችሁ ወንጌልን እንዲማሩ ለመርዳት ሀይለኛ መንገድ ነው። እንደቤተሰብ የሚያነቡት ነገር ብዛት እና የሚያነቡበት ጊዜ ርዝመት ያላሰለሰ ጥረት የማድረጋችሁን ያህል አስፈላጊ አይደሉም። የቅዱሳን መጻህፍት ጥናትን የቤተሰባችሁ ህይወት አስፈላጊ ክፍል ስታደርጉት፣ የቤተሰባችሁ አባሎች ወደ ሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲቀርቡ እና በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ምስክርነታቸውን እንዲገነቡ ትረዷቸዋላችሁ።

የሚቀጥሉትን ጥያቄዎች አስቡባቸው፦

  • የቤተሰብ አባላትን በራሳቸው ቅዱሳን መጻህፍትን እንዲያጠኑ እንዴት ማበረታታት ይችላሉ?

  • የቤተሰብ አባላት የሚማሩትን እንዲያጋሩ ለማበረታታት ምን ማድረግ ይችላሉ?

  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚማሩትን መሰረታዊ መርሆዎች በእለት ተለት ትምህርቶች ጊዜ እንዴት ማጉላት ይችላሉ?

ቤት ለወንጌል ትምህርት አመቺ ስፍራ መሆኑን አስታውሱ። በቤተክርስቲያን ክፍል ውስጥ በማይቻል መንገድ ወንጌልን በቤታችሁ ውስጥ መማር እና ማስተማር ይችላሉ። ቤተሰባችሁ ከቅዱሳን መጻህፍት እንዲማሩ ለመርዳት መንገዶችን መፍጠርን አስቡ። የቤተሰባችሁን የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ለማጉላት የሚከተሉትን ሀሳቦች ይመልከቱ።

ሙዚቃን ይጠቀሙ

በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ የተማራችሁትን መሰረታዊ መርሆዎች የሚያጠናክሩ መዝሙሮች ይዘምሩ። የተመረጡ መዝሙሮች ወይም የህጻናት መዝሙሮች በእያንዳንዱ ሳምንታዊ ማውጫ ውስጥ ተዘርዝረዋል። በግጥሞቹ ውስጥ ስላሉት ቃላት ወይም ሐረጎች የቤተሰብ አባሎችን ጥያቄዎች መጠየቅ ይችላሉ። ከመዘመር በተጨማሪ ቤተሰባችሁ ከመዝሙሮቹ ጋር የሚሄዱ ተግባሮችን ማከናወን ወይም ሌሎች ተግባሮችን በሚያከናውኑበት ጊዜ መዝሙሮቹን እንደ የበስተጀርባ ሙዚቃ ማዳመጥ ይችላሉ። ለበለጠ ሃሳቦች በዚህ ፅሁፍ ውስጥ “ቅዱስ መዝሙርን በወንጌል ትምህርትዎ ውስጥ ማካተት”የሚለውን ይመልከቱ።

ትርጉም ያላቸው የቅዱሳን መጻህፍት ጥቅሶችን ያጋሩ።

የቤተሰብ አባላት በግል ጥናታቸው ያገኟቸውን ለእነሱ ትርጉም የሰጧቸውን የቅዱሳን መጻህፍት ምንባቦች እንዲያካፍሉ ጊዜ ይስጧቸው።

የራስዎን ቃላት ይጠቀሙ

ከምታጠኗቸው ቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ ምን እንደተማሩ በገዛ ቃላቸው እዲያብራሩ የቤተሰብ አባሎቻችሁን ይጋብዟቸው።

ወጣት ትንሽ ልጅን ቅዱሳን መጽሐፍትን ለማንበብ ሲረዳ

ቅዱሳን መጻህፍት በሕይወታችሁ እንዲሰሩ ያድርጉ

የቅዱሳን መጻህፍትን ምንባብ ካነበባችሁ በኋላ የቤተሰብ አባላት መልዕክቱ በህይወታቸው እንዴት ሊሰራ እንደሚችል እንዲያካፍሉ ይጠይቋቸው።

ጥያቄ ይጠይቁ

የቤተሰብ አባላት የወንጌል ጥያቄ እንዲጠይቁ ይጋብዙ፣ እናም ከዚያ ለጥያቄው መልስ ሊያግዙ የሚችሉ ጥቅሶችን በመፈለግ ጊዜአችሁን ያሳልፉ።

የቅዱሳን መጻህፍት ጥቅስን ያሳዩ

ያገኙትን ትርጉም ያለው ጥቅስ ይምረጡ፣ እና የቤተሰብ አባላት ብዙውን ጊዜ በሚያዩበት ቦታ ላይ ያስቀምጡት። ሌሎች የቤተሰብ አባላት አንድ የቅዱስ ፅሁፍ ጥቅስ ለማሳየት በየተራ እንዲመርጡ ይጋብዙ።

የቅዱሳን ፅሁፎች ዝርዝር ያዘጋጁ

በሚመጣው ሳምንት እንደ ቤተሰብ በጥልቀት ለመወያየት የምትፈልጓቸውን የተለያዩ ጥቅሶች ይምረጡ።

ቅዱሳን ፅሁፎችን በቃልዎ ያጥኑ

ለቤተሰብዎ ትርጉም ያለው የቅዱስ ፅሁፍ ምንባብ ይምረጡ፣ እና የቤተሰብ አባላቱ በየዕለቱ በመድገም ወይም የማስታወሻ ጨዋታ በመጫወት በአዕምሮአቸው በመያዝ እንዲያስታውሱ ይጋብዙአቸው።

ሰዎች በጋራ በቤት ሲዘምሩ

የምሳሌያዊ ነገረ ትምህርቶችን ያጋሩ

እንደ ቤተሰብ ከምታነቧቸው ምዕራፎች እና ጥቅሶች ጋር የሚዛመዱ ቁስ ነገሮችን ይፈልጉ። እያንዳንዱ ነገር በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ ካሉት ትምህርቶች ጋር እንዴት እንደሚዛመድ እንዲናገሩ የቤተሰብ አባላትን ይጋብዙ።

ርዕስ ይምረጡ

ቤተሰቡ አብሮ የሚያጠናውን ርዕስ የቤተሰብ አባላት ተራ በተራ እንዲመርጡ ያድርጉ። በቅዱሳን መጻህፍት ምንባብ ውስጥ ስለርዕሶች መረዳጃ ለማግኘት፣ የርዕስ መመሪያን፣ የመፅሐፍ ቅዱስ መዝገብ ቃላትን፣ ወይም የቅዱሳን መጻህፍት መመሪያን (scriptures.ChurchofJesusChrist.org) ይጠቀሙ።

ስዕል ይሳሉ

እንደቤተሰብ ጥቂት ጥቅሶችን አንድ ላይ ያንብቡ፣ ከዚያ የቤተሰብ አባላቶች ካነበቡት ነገር ጋር የሚዛመድ አንድ ነገር እንዲስሉ ጊዜ ይስጧቸው። አንዳችሁ በሌላውን ስዕሎች ላይ ለመወያየት ጊዜ ይመድቡ።

ታሪኩን ይተውኑ

አንድ ታሪክ ካነበባችሁ በኋላ የቤተሰብ አባላት እንዲተውኑት ይጋብዙ። ከዚያ በኋላ፣ ታሪኩ በግል እና በቤተሰባችሁ ውስጥ ከሚገኙ ነገሮች ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ይነጋገሩ።

ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳሉት፥ “ቤታችሁን እንደ ወንጌል መማሪያ ክፍል ለመለወጥ በትጋት ስትሰሩ፣ ከጊዜ በኋላ የ የናንተ ሰንበት ቀኖች በደስታ የተሞሉ ይሆናሉ። ልጆቻችሁ የአዳኝን ትምህርት በመማር እና በመኖር ይደሰታሉ፣ እናም ጠላት በህይወታችሁ እና በቤታችሁ ውስጥ ያለው ተፅዕኖ ይቀንሳል። በቤተሰባችሁ ውስጥ ያለው ለውጥ ታላቅ እና የሚቀጥል ይሆናል” (“ምሳሌያዊ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን መሆን፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 113)።