ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ቅዱስ መዝሙርን በወንጌል ትምህርትዎ ውስጥ ማካተት


“ቅዱስ መዝሙርን በወንጌል ትምህርትዎ ውስጥ ማካተት፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“ቅዱስ መዝሙርን በወንጌል ትምህርትዎ ውስጥ ማካተት፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ቅዱስ መዝሙርን በወንጌል ትምህርትዎ ውስጥ ማካተት

የመጀመሪያ ክፍል ሙዚቃዎችን እና መዝሙሮችን መዘመር እናንተን እና ቤተሰባችሁን በብዙ መንገድ ሊባርክ ይችላል። እነዚህ ሃሳቦች ወንጌልን ለመማር እና ለመኖር ስትጥሩ ቅዱስ ሙዚቃን እንድትጠቀሙ ሊረዱ ይችላሉ።

  • የአስተህምሮ መርሆዎችን ይማሩ። በምትዘምሩት ወይም በምታዳምጡት መዝሙር ውስጥ የሚገለፁትን እውነታዎች ይመልከቱ። ይህ ቀኑን ሙሉ ስለእነዚህ እውነታዎች ወደ ወንጌል ውይይቶች ሊመራ ይችላል። ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለወንጌሉ የሚያስተምሩ የመጀመሪያ ክፍል ሙዚቃዎችን ወይም መዝሙሮችን ዘምሩ ወይም አድምጡ። ስለአዳኙ እና ስለትምህርቶቹ መንፈስ ቅዱስ በሚመሰክርባቸው መንገዶች ላይ አትኩሮት ስጡ።

  • የመዝሙርን ኃይል ተገንዘቡ። የመጀመሪያ ክፍል ሙዚቃዎችን እና መዝሙሮችን መዘመር ወይም ማዳመጥ በአስፈላጊ ጊዜዎች በረከት ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፣ መዝሙርን መዘመር ህፃንን በእንቅልፍ ሰዓት ሊያረጋጋ፣ ቤተሰባችሁ በጋራ ሲሰሩ ደስታን ለመፍጠር፣ የታመመን ጎረቤት ከፍ ለማድረግ ወይም ጭንቀት የሚሰማውን ሰው ለማፅናናት ይችላል።

  • ተሞክሮዎችን አካፍሉ። ከመዝሙሮቹ መልዕክቶች ጋር የሚዛመዱ ግላዊ እና የቤተሰብ ልምዶችን አካፍሉ። የሚዛመዱ የቅዱስ ጽሁፍ ታሪኮችን እራሱ ማካፈል ይችላሉ።

  • ቤተሰባችሁን አሳትፉ። በንቃት የሚሳተፉ ከሆነ ቤተሰባችሁ ከመዝሙሮቹ የበለጠ ይማራሉ። የቤተሰብ አባሎችን ለማሳተፍ፣ ታላቅ ልጅ ለታናናሾቹ መዝሙርን በማስተማር እንዲረዳ መጋበዝ ይችላሉ ወይም ልጆች በመጀመሪያ ከፍል ውስጥ የተማሩትን መዝሙር ቤተሰባችሁን እንዲያስተምሩ ይጋብዙ። የቤተሰብ አባሎች መዝሙር በየተራ እንዲመሩ መፍቀድም ይችላሉ።

  • አዲስ ነገር ፈጣሪ ሁኑ። ቅዱስ መዝሙሮችን ለመማር እንደቤተሰብ የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀሙ። ለምሳሌ፣ ከመዝሙሩ ቃላት እና ሀረጎች ጋር አብረው የሚሄዱ ምልክቶችን መጠቀም ይችላሉ። ወይም የመዝሙሩን ክፍሎች በመተወን ሌሎች የቤተሰብ አባሎች ደግሞ መዝሙሩ ምን እንደሆነ በየተራ እንዲገምቱ ማድረግ ይችላሉ። ቤተሰባችሁ መዝሙሮችን በተለያዩ ፍጥነቶች ወይም ቅላፄ በመዘመር ሊደሰቱ ይችላሉ። የወንጌል ቤተመጽሐፍት እና የወንጌል ለህፃናት መተግበሪያዎች መዝሙሮችን ለመማር የሚረዱ የድምፅ ቅጂዎችን እና ቪድዮዎችን ይዘዋል። የተቀደሱ መዝሙሮችን ለማዳመጥ የመጫወቻ ዝርዝሮችን መስራትም ይችላሉ።

ለበለጠ ሃሳቦች በ “ትምህርትን ለማስተማር መዝሙርን መጠቀም” እና “ልጆች የመጀመሪያ ክፍል ሙዚቃዎችን እና መዝሙሮችን እንዲማሩ እና እንዲያስታውሱ መርዳት፣” የሚሉትን “በመዝሙር ጊዜ መመሪያዎች እና የልጆች ቅዱስ ቁርባን መዝሙር አቅርቦት” በ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍሎችውስጥ የሚገኙ ክፍሎችን ይመልከቱ