ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦችን መጠቀም


ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፣”ን መጠቀም ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 ( እ.አ.አ)]

ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፣”ን መጠቀም ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦችና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2021 (እ.አ.አ)ን መጠቀም

ይህ ጽሁፍ ለማን ነው?

ይህ ጽሁፍ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ላለ ለእያንዳንዱ ግለሰብ እና ቤተሰብ ነው። በግልዎም ሆነ ከቤተሰብዎ ጋር፣ ወንጌልን እንዲማሩ ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ከዚህ በፊት ወንጌልን ዘወትር የማያጠኑ ከሆነ፣ ይህ ጽሁፍ እንዲጀምሩ ይረዳዎታል። ቀድሞውኑ በወንጌል ጥናት ጥሩ ልማድ ካለዎት፣ ይህ ጽሁፍ የበለጠ ትርጉም ያለው ተሞክሮ እንዲኖርዎት ይረዳል።

ይህንን ጽሁፍ እንዴት መጠቀም ይኖርብኛል?

ይህንን ጽሁፍ ለእርስዎ በሚረዳ በማንኛውም መንገድ ተጠቀሙበት። ለግል እና ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እንደ መመሪያ ወይም እንደ እርዳታ ያግዝዎታል። ለቤተሰብ የቤት ምሽትም ይህን ለመጠቀም ይችላሉ። ይዘቶቹ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኙትን ጠቃሚ መርሆዎች ያደምቃሉ፣ የግለሰቦችን እና ቤተሰቦችን የጥናት ሀሳቦችን እና እንቅስቃሴዎችን ይጠቁማሉ፣ እንዲሁም ግንዛቤአችሁን የምትመዘግቡባቸው ቦታዎችን ያቀርባሉ።

ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች ከሚያደርጓቸው ሌሎች መልካም ነገሮች ጋር የሚወዳደር ወይም እነሱን የሚተካ አይደለም። የእራስዎን የእግዚአብሔርን ቃል ጥናት እንዴት መከወን እንደሚችሉ ለመወሰን የመንፈስ ቅዱስን መመሪያ ይከተሉ።

ምስል
ጥንዶች ቅዱስ መጽሃፍን በቤት ውስጥ ሲያጠኑ

ይህ ጽሁፍ በቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚሆነው ጋር የሚዛመደው እንዴት ነው?

በዚህ መገልገያ ውስጥ ያሉት ይዘቶች በሳምንት የንባብ መርሃግብር መሠረት የተደራጁ ናቸው። የ ኑ፣ ተከተሉኝ ግብዓቶች ለመጀመሪያ ክፍልለሰንበት ትምህርት ቤት፣ እና ለአሮናዊ ክህነት ቡድኖች እና ለወጣት ሴቶች ክፍሎች ተመሳሳይ መርሃግብርን ይከተላሉ። በቤት ውስጥ ወንጌልን ለመማር እና ለመኖር ያደረጋችሁትን ጥረቶች ለመደገፍ፣ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ያሉ አስተማሪዎችዎ በቤትዎ ውስጥ ስላጠኑት የቅዱሳን መጻህፍት ምንባቦች ልምድዎን፣ ሀሳብዎን እና ጥያቄዎን ለማጋራት እድሎችን ይሰጡዎታል።

የሰንበት ትምህርት በወር ሁለት ጊዜ ብቻ ስለሚቀርብ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መምህራን ሳምንታዊ መርሃግብሩን ለመከታተል ይዘቶቹን ለመዝለል ወይም ለማዋሃድ መምረጥ ይችላሉ። በካስማ ስብሰባ ወይም በሌሎች ምክንያቶች የተነሳ መደበኛ የቤተክርስቲያን ስብሰባዎች በማይካሄዱባቸው ሳምንቶችም፣ (ለሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል እና ለመጀመሪያ ክፍል ለሁለቱም) ይህ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። በእነዚህ ሳምንታት ውስጥ ብሉይ ኪዳንን በቤትዎ ውስጥ ማጥናት እንዲቀጥሉ ይጋበዛሉ።

መርሃግብሩን መከተል አለብኝን?

መርሃግብሩ እስከ አመቱ መጨረሻ ከብሉይ ኪዳን እና ከታላቁ ዋጋ ዕንቁ የተመረጡትን እንዲያነቡ ይረዳዎታል። በተጨማሪም፣ እንደሌሎች ተመሳሳይ መርሃግብርን መከተል በቤት፣ በቤተክርስቲያን፣ እና በሁሉም ቦታዎች ትርጉም ወዳለው ልምዶች ይመራል። ነገር ግን መርሃግብሩን በመከተል እንደተወሰኑ ወይም እያንዳንዱን ጥቅስ ለማንበብ እንደተገደዱ አይሰማዎት፤ መርሃግብሩ በራስዎ ፍጥነት እንዲከተሉ የሚያግዛችሁ መመሪያ ነው። አስፈላጊው ነገር በግል እና በቤተሰብ ውስጥ ወንጌልን መማራችሁ ነው።

ስለብሉይ ኪዳን የንባብ መርሃግብር ማስታወሻ

የተጠቆሙት የ2022 (እ.አ.አ) የ ኑ፣ ተከተሉኝ የንባብ መርሃግብር እያንዳንዱን የብሉይ ኪዳን ምዕራፍ አያጠቃልሉም። ብሉይ ኪዳን ከሌሎች የቅዱስ መጽሐፍት ይዘቶች ረጅም በመሆኑ ምክንያት፣ የንባብ መርሃግብሩን ለእናንተ እና ለቤተሰባችሁ የበለጠ የሚመችለማድረግ የተወሰኑ ምዕራፎች እና መጽሐፎች ተቀንሰዋል።

ድግግሞሽን ለማስወገድ እና ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሚመሰክሩ፣ በትምህርት የካበቱ እና በተለይ ለዘመችን ተዛማች በሆኑ ገፆች ላይ ለማተኮር ምዕራፎችና መጽሐፎች ተመርጠዋል። ለምሳሌ የተጠቆመው የንባብ መርሃግብር 1ኛእና 2ኛ ዜና መዋዕልን አያጠቃልልም ምክንያቱም የእነዛ መጽሐፎች አብዛኛው ይዘት በ 1ኛእና 2ኛ ነገሥትውስጥ የሚገኙ ቅጂዎች ስለሆኑ ነው። መርሃግብሩ በተጨማሪም የሰለሞንን መዝሙር አያጠቃልልም ምክንያቱም ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ በመንፈስ የተነሳሳ ቅዱስ መጽሐፍ እንዳልሆነ አስተምሯል (የቅዱሳት መጽሐፍቶች መመሪያ፣ “የሰለሞን መዝሙርን፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.orgይመልቱ)። ይሁን እንጂ፣ ይህ የተጠቆመ የጥናት መርሃግብር ብቻ እንደሆነ አስታውሱ። የግለሰብ እና የቤተሰብ የቅዱስ ጽሁፍ ጥናታችሁ በግላዊ ራዕይ መመራት አለበት።

አትም