ቅዱሳት መጻህፍት
ኤተር ፪


ምዕራፍ ፪

ያሬዳውያን ወደ ቃል ኪዳን ምድር ለመጓዝ ተዘጋጁ—ይህችም ሰዎች ክርስቶስን ማገልገል ያለባቸው የተመረጠች ምድር ናት አለበለዚያም ይወገዳሉ—ጌታም ለያሬድ ወንድም ለሦስት ሰዓታት ያህል ተናገረው—ያሬዳውያን ጀልባዎችን ሰሩ—ጌታም የያሬድ ወንድም እንዴት ጀልባዎቹ ብርሃን ማግኘት እንደሚችሉ ሃሳቡን እንዲያቀርብ ጠየቀው።

እናም እንዲህ ሆነ ሴት እናም ወንድ ከሆኑት ከሁሉም ዓይነት በአንድ ላይ ከሰበሰቧቸው ከመንጋዎቻቸው ጋር ያሬድ እና ወንድሙ፣ እናም ቤተሰቦቻቸው፣ እናም ደግሞ የያሬድ ወዳጆች፣ እናም ወንድሞቹ እና የእርሱ ቤተሰቦች፣ በሸለቆው በስተሰሜን በኩል ሄዱ፤ (እና ሸለቆውም በኃያሉ አዳኝ ስም ናምሩድ ተብሎ ይጠራ ነበር)።

እናም ደግሞ ወጥመድ ዘረጉ እናም የሰማይ አዕዋፋትን ያዙ፤ እናም መንጠቆአቸውን ደግሞ አዘጋጁ፣ በእነዚህም የውሀዎችን ዓሣ ተሸከሙ።

እናም እነርሱ ደግሞ በትርጉም የንብ ቀፎ የሚባለውን ደዘረት ተሸክመው ነበር፤ እናም የንብ መንጋዎችን እናም በምድር ላይ ያሉትን ነገሮች ሁሉ፣ የሁሉም አይነት ዘሮችን እንደዚህ ተሸክመው ነበር።

እናም እንዲህ ሆነ ወደ ናምሩድ ሸለቆ በወረዱ ጊዜ ጌታ መጣ እናም ከያሬድ ወንድም ጋር ተነጋገረ፤ እናም እርሱ በደመና ውስጥ ነበር፣ እናም የያሬድ ወንድምም አላየውም።

እናም እንዲህ ሆነ ጌታም ከዚህ በፊት ማንም ሰው ሰፍሮበት ወዳልነበረበት ሥፍራ ወደ ምድረበዳው እንዲሄዱ አዘዛቸው፤ እናም እንዲህ ሆነ ጌታም መራቸው፤ እናም በደመና ውስጥ ቆሞ አነጋገራቸው፣ እናም ወዴት መሔድ እንዳለባቸውም አቅጣጫውን አሳያቸው።

እናም እንዲህ ሆነ በምድረበዳው ውስጥ ተጓዙ፣ እናም ያለማቋረጥም በጌታ እጅ በመመራት፣ ብዙ ውሀዎችን ያቋረጡበትን ጀልባ ሰሩ።

እናም ጌታ ከባህሩ ባሻገር ወዳለው ምድረበዳ እንዲቆሙ አልፈቀደላቸውም፣ ነገር ግን ወደ ቃል ኪዳን ምድር እንዲመጡ ይፈልግ ነበር፤ ምድሪቷም ከሌሎች ቦታዎች በላይ የተመረጠች ነበረች፤ ጌታ አምላክም ፃድቅ ለሆኑ ሰዎች ያስቀመጣት ነበረች።

እናም ይህችን የቃል ኪዳን ምድር የራሱ ያደረገ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከዘለዓለም እውነተኛ እናም አንድ የሆነውን አምላክ ማገልገል እንዳለበት ለያሬድ ወንድም በቁጣው ማለለት፤ አለበለዚያ የቁጣው ሙላት በደረሰ ጊዜ እነርሱ ይወገዳሉ

እናም እንግዲህ፣ ይህችን ምድር በተመለከተ የቃል ኪዳን ምድር ስለመሆንዋ የእግዚአብሔርን ድንጋጌ ለመመልከት ይቻለናል፤ እናም ማንም ይህችን ምድር የራሱ ያደረገ ሀገር እግዚአብሔርን ያገለግላል፣ አለበለዚያ የቁጣው ሙላት በእነርሱ ላይ በሆነ ጊዜ ይወገዳሉ። እናም በክፋት በተሞሉ ጊዜም የቁጣው መዓት በእነርሱ ላይ ይሆናል።

እነሆም፣ ይህች ምድር ከሌሎች ምድሮች ሁሉ በላይ የተመረጠች ናት፤ ስለዚህ የያዛት ሁሉ እግዚአብሔርን ያገለግላል አለበለዚያ ይወገዳል፤ ምክንያቱም ይህ ዘለዓለማዊ የሆነ የእግዚአብሔር ድንጋጌ ነውና። እናም ምድሪቱ በሰው ልጆች መካከል በክፋት በተሞላች ጊዜ ነው የሚወገዱት

፲፩ እናም አህዛብ ሆይ ፍፃሜው እስከሚደርስ ንሰሃ እንድትገቡ እናም ክፋታችሁን ታቆሙ ዘንድ፤ ስለዚህ የምድሪቱ ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት የእግዚአብሔር ቁጣ ሙሉንት በራሳችሁ ላይ እንዳይመጣ የእግዚአብሔርን ድንጋጌ ታውቁ ዘንድ ይህ ለእናንተ ይመጣል—

፲፪ እነሆ፣ ይህች የተመረጠች ምድር ናት፣ እናም በጻፍናቸው ነገሮች የተገለፀውን የምድሪቷን አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስን ካገለገሉ፣ ምድሪቷን የያዘ ማንኛውም ሀገር ከባርነት እናም ከምርኮ፣ እናም ከሰማይ በታች ካሉት ሌሎች ሀገሮች ነፃ ይሆናል።

፲፫ እናም እንግዲህ ታሪኬን እቀጥላለሁ፤ እነሆም፣ እንዲህ ሆነ ጌታም ያሬድን፣ እና ወንድሙን ምድሪቷን ወደ ከፈለው ወደ ታላቁ ባሕር አመጣቸው። እናም ወደ ባሕሩም በመጡ ጊዜ ድንኳናቸውን ተከሉ፤ እናም የቦታውን ሥም ሞሪያንኩመር ብለው ጠሩት፤ እናም በድንኳኑ ኖሩ፣ እናም ለአራት ዓመታት ያህልም በባህሩ ዳርቻ በድንኳን ኖሩ።

፲፬ እናም እንዲህ ሆነ በአራተኛው ዓመት መጨረሻ ጌታ በድጋሚ ወደ ያሬድ ወንድም መጣ፣ እናም በዳመናው ውስጥ ቆሞ ከእርሱ ጋር ተነጋገረ። እናም ጌታም ለሦስት ሰዓታት ያህል ከያሬድ ወንድም ጋር ተነጋገረ፣ እናም የጌታን ሥም ለመጥራት ባለማስታወሱ ገሰፀው

፲፭ እናም የያሬድ ወንድም ለሰራው ክፋት ንሰሃ ገባ፤ እናም ከእርሱ ጋር ለነበሩት ወንድሞቹ ሲል የጌታን ሥም ጠራ። እናም ጌታ እንዲህ አለው፥ አንተን እናም ወንድሞችህን ስለኃጢአታቸው ይቅር እላቸዋለሁ፤ ነገር ግን ከእንግዲህ ኃጢያት አትስራ፤ መንፈሴ ሁል ጊዜ ከሰዎች ጋር እንደማይሆንም አስታውስ፤ ስለዚህ እስከምትበስል ኃጢያት ከሰራህ ከጌታ ፊት ተለይተህ ትጠፋለህ። እናም ውርስ በምሰጥህ ምድር ላይ ያሉኝ ሀሳቦች እነዚህ ናቸው፤ ምክንያቱም ይህች ከሌሎች ምድሮች ሁሉ በላይ የተመረጠች ምድር ናትና።

፲፮ እናም ጌታ እንዲህ አለ፥ ሂድ እናም ከዚህ በፊት እንደሰራኸው አይነት ጀልባን ሥራ። እናም እንዲህ ሆነ የያሬድ ወንድም እናም ደግሞ ወንድሞቹ ወደሥራቸው ሔዱ፣ እናም ጌታ እንዳዘዛቸው ቀደም ሲል እንደሰሩት አድርገው ጀልባዎችን ሰሩ። እናም ትንንሽ ነበሩ፣ እናም ወፍ በውሃ ላይ እንደሚቀለው ያህል እነርሱም በውሃ ላይ ቀላል ነበሩ።

፲፯ እናም እነዚህም በጣም ጥብቅ ሆነው ተሰርተዋል፣ እንዲሁም ልክ እንደ ሣህን ውሃ ለመያዝ ይችሉ ነበር፤ እናም ሥራቸውም ልክ እንደሳህን የጠበቀ ነበር፤ እናም ጎኖቹም እንደሳህን የጠበቁ ነበሩ፤ እናም ጫፎቹም የሾሉ ነበሩ፤ እናም ላዩ እንደሳህን የጠበቀ ነበር፤ እናም እርዝመቱም የዛፍ እርዝማኔን ያክል ነበር፤ እናም መዝጊያው በሚዘጋበት ጊዜም እንደሳህን የጠበቀ ነበር።

፲፰ እናም እንዲህ ሆነ የያሬድ ወንድም ወደ ጌታ እንዲህ ሲል ጮኸ፥ ጌታ ሆይ ያዘዝከኝን ሥራዎች አከናውኛለሁ፤ እናም እንደመራኸኝም አድርጌ ጀልባዎችን ሠርቻለሁ።

፲፱ እናም እነሆ፣ አቤቱ ጌታ፣ በውስጣቸው ብርሃን የለም፤ ወዴት እንቅዘፍ? እናም ደግሞ በውስጣቸው ካለው አየር በስተቀር ለመተንፈስ ስለማንችል ልንሞት እንችላለን፤ ስለዚህ እንሞታለን።

እናም ጌታ ለያሬድ ወንድም እንዲህ ሲል ተናገረው፥ እነሆ፣ ከላይና ከታች ቀዳዳ ታበጃለህ፤ እናም አየር በምታጣ ጊዜም ቀዳዳውን ከፍተህ አየር ታገኛለህ። እናም ውሃው ወደ አንተ ከመጣብህ፣ እነሆ፣ በጥፋት ውሀ እንዳትጠፋ ቀዳዳውን ትደፍነዋለህ።

፳፩ እናም እንዲህ ሆነ የያሬድ ወንድም ጌታ ባዘዘው መሰረት አደረገ።

፳፪ እናም በድጋሚ ወደ ጌታ እንዲህ በማለት ጮኸ፥ አቤቱ ጌታዬ እነሆ ያዘዝከኝን አድርጌአለሁ፤ ለህዝቤም ጀልባዎችን አዘጋጅቻለሁ፣ እናም እነሆ በውስጣቸውም ብርሃን የለም። እነሆ አቤቱ ጌታዬ ይህንን ታላቅ ውሃ በጨለማው እንድናቋርጥ ትፈቅዳለህን?

፳፫ እናም ጌታ ለያሬድ ወንድም እንዲህ ሲል ተናገረው፥ በጀልባው ውስጥ ብርሃን እንዲኖር ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ? እነሆም፣ መስኮት ሊኖረው አይችልም፣ ምክንያቱም ትሰባበራላችሁና፤ በእሳት ብርሃን መሄድ ስለሌለባችሁ እሳትም ለመያዝ አትችሉም።

፳፬ እነሆ፣ በባሕሩ መሃል እንደአሳ ነባሪ ትሆናላችሁ፤ እንደተራራ ከፍ የሚለውም ማዕበል ያጋጫችኋል። ይሁን እንጂ በድጋሚ ከባህሩ ውስጥ አወጣችኋለሁ፤ ምክንያቱም ነፋሱ ከአፌ የሚመጣ ነውና፣ እናም ደግሞ ዝናቡንና ጎርፉን እኔ ልኬዋለሁና።

፳፭ እናም እነሆ፣ ከእነዚህ ነገሮች እንድትጠበቁ አዘጋጃችኋለሁ፤ ለባህሩ ማዕበል፣ እናም የሚመጣውን ነፋስ፣ እናም የሚመጣባችሁን የጥፋት ውሀ እኔ ካላዘጋጀኋችሁ በቀር ይህንን ጥልቅ ባህር ልታቋርጡት አትችሉም። ስለዚህ በባህሩ ጥልቅ ስትሰጥሙ ብርሃን ታገኙ ዘንድ ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?