የላማናዊው ሳሙኤል ለኔፋውያን የሰጠው ትንቢት።
ምዕራፍ ፲፫ እስከ ፲፭ አጠቃሎ የያዘ።
ምዕራፍ ፲፫
ላማናዊው ሳሙኤል ኔፋውያን ንስሃ ካልገቡ በቀር እንደሚጠፉ ተነበየ—እነርሱ እና ሀብታቸው የተረገሙ ናቸው—ነቢያትን አልተቀበሉአቸውም እናም በድንጋይ ወገሩአቸው፤ እነርሱም በአጋንንት ተከበቡ፣ እናም ክፋትን በመፈፀም ደስታን ፈለጉ። በ፮ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም እንግዲህ እንዲህ ሆነ በሰማንያ ስድስተኛው ዓመት ላማናውያን በሙሴ ህግ መሰረት የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ለመጠበቅ ጠንቃቆች በሆኑበት ጊዜ፣ ኔፋውያን በክፋታቸው፣ አዎን በታላቅ ክፋት ነበሩ።
፪ እናም እንዲህ ሆነ በዚህ ዓመት፣ ሳሙኤል የሚባል አንድ ላማናዊ ሰው ነበር፣ እርሱም ወደ ዛራሔምላ ምድር መጣና ለህዝቡ መስበክ ጀመረ። እናም እንዲህ ሆነ ለብዙ ቀናትም ህዝቡን ስለንስሃ ሰበከ፣ እናም እነርሱ ግን አስወገዱትና፣ እርሱ ወደራሱ ምድር ለመመለስ ተቃርቦ ነበር።
፫ ነገር ግን እነሆ፣ እንደገና እንዲመለስ ዘንድ፣ እናም ወደ ልቡ የመጡትን ነገሮች ለህዝቡ መተንበይ እንዳለበት የጌታ ድምፅ ወደእርሱ መጣ።
፬ እናም እንዲህ ሆነ እነርሱም ወደ ከተማው እንዲገባ አልፈቀዱለትም ነበር፤ ስለዚህ ሄደ እናም በግንብ ላይ ቆመና፣ እጁን ዘረጋ፣ እናም በኃይል ጮኸና፣ ጌታ በልቡ ያመጣለትን ማናቸውንም ነገሮች ተነበየ።
፭ እናም እንዲህ አላቸው፥ እነሆ፤ እኔ ላማናዊው ሳሙኤል፣ ጌታ በልቤ ያስቀመጣቸውን ቃላት እናገራለሁ፤ እናም እነሆ ለዚህም ህዝብ የፍትህ ጎራዴ በዚህ ህዝብ ላይ ትሆናለች እንድልም በልቤ አስቀመጠ፤ እናም የፍትህ ጎራዴ በዚህ ህዝብ ላይ ካልሆነች በስተቀር አራት መቶ ዓመታት አያልፉም።
፮ አዎን፣ ይህን ህዝብ ኃያል የሆነው ጥፋት ይጠብቀዋል፤ በእርግጥም በዚህ ህዝብ ላይ ይመጣል፣ እናም ንስሃና፣ በእርግጥ ወደዚህ ዓለም በሚመጣውና፣ በብዙ ነገሮች ለሚሰቃየው፣ እንዲሁም ለህዝቡም በሚሞተው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ካልሆነ በቀር ይህን ህዝብ ምንም ሊያድን አይችልም።
፯ እናም እነሆ፣ የጌታ መልአክ ለእኔ ይህን ነገረኝና፣ ለነፍሴም መልካም የምስራች አመጣልኝ። እናም እነሆ መልካሙ የምስራች ይኖራችሁ ዘንድ ለእናንተ እንድገልፅ ተልኬ ነበር፤ ነገር ግን እነሆ እኔን አልተቀበላችሁኝም።
፰ ስለዚህ፣ ጌታም እንዲህ ይላል፥ የኔፊ ሰዎች ልብ በመጠጠሩ፣ ንስሃ ካልገቡ ቃሌን ከእነርሱ እወስዳለሁ፣ መንፈሴንም ከእነርሱ አርቃለሁ፣ እናም ከዚህ ወዲያ አልታገስም፣ የወንድሞቻቸውን ልብ በእነርሱ ላይ አዞራለሁም።
፱ እናም እንዲመቱ ከማድረጌም በፊት አራት መቶኛው ዓመት አያልፍም፤ አዎን፣ በጦርነትና በረሃብ፣ እናም በቸነፈር እጎበኛቸዋለሁ።
፲ አዎን፣ በኃያሉ ቁጣዬም እጎበኛቸዋለሁ፣ እናም የእናንተን ፍፁም ጥፋት የሚመለከቱ አራተኛ ትውልድ የሆኑት ጠላቶቻችሁ በህይወት ይኖራሉ፤ እናም ንስሃ ካልገባችሁ በእርግጥ ይህ ይሆናል ይላል ጌታ፤ እናም የአራተኛውም ትውልድ ጥፋታችሁን ይጎበኛሉ።
፲፩ ነገር ግን ንስሃ የምትገቡ እናም ወደ ጌታ አምላካችሁ የምትመለሱ ከሆነ፣ እኔም ቁጣዬን ከእናንተ አርቃለሁ ይላል ጌታ፤ አዎን ጌታም እንዲህ ይላል፣ ንስሃ የሚገቡና ወደ እኔ የሚመለሱ የተባረኩ ናቸው፣ ነገር ግን ንስሃ ለማይገቡት ወዮላቸው።
፲፪ አዎን፣ ለዚህች ለታላቋ የዛራሔምላ ከተማ ወዮላት፤ እነሆም ፃድቃን በሆኑት ምክንያት ነው የዳነችው፤ አዎን፣ ለዚህች ታላቅ ከተማ ወዮላት ይላል ጌታ፤ ብዙዎች፣ አዎን፣ የዚህች የታላቋ ከተማ አብዛኛው ክፍል የሚሆኑት በእኔ ላይ ልባቸውን እንደሚያጠጥሩ አስተውላለሁ፣ ይላል ጌታ።
፲፫ ነገር ግን ንስሃ የሚገቡት የተባረኩ ናቸው፤ ምክንያቱም እነርሱን አድናቸዋለሁና። ነገር ግን እነሆ፣ በዚህች ታላቅ ከተማ ስላሉት ስለ ፃድቃኖች ባይሆን ኖሮ፤ እነሆ፣ እሳት ከሰማይ እንዲወርድ እናም እንዲያጠፋቸው ባደረግሁ ነበር።
፲፬ ነገር ግን እነሆ፣ ስለ ፃድቃን ሲባል ነው የዳነው። ነገር ግን እነሆ ፃድቃኖችን ከመካከላችሁ የምትወረውሩበት ጊዜ ይመጣል፣ ከዚያም ለጥፋት የበሰላችሁ ትሆናላችሁ ይላል ጌታ፤ አዎን በውስጧ ባሉት ክፋትና ርኩሰት የተነሳ ለዚህች ከተማ ወዮላት።
፲፭ አዎን፤ እናም የጌዴዎን ከተማ በውስጧ ስላለው ክፋትና እርኩሰት ወዮላት።
፲፮ አዎን፣ እናም በኔፋውያን በተያዙት ከተሞችና በዙሪያቸው ላሉት ሁሉ በክፋታቸው እንዲሁም በርኩሰታቸው የተነሳ ወዮላቸው።
፲፯ እናም እነሆ፣ በምድሪቱ ላይ ባሉት በሰዎቹ ድርጊትም፣ አዎን፣ በክፋታቸውና በእርኩስነታቸው የተነሳ እርግማን በምድሪቱ ላይ ይመጣል ይላል የሰራዊት ጌታ።
፲፰ እናም እንዲህ ይሆናል ይላል የሰራዊት ጌታ፤ አዎን፣ ታላቁና እውነተኛው አምላካችን፣ በምድሪቱም ታላቅ እርግማን በመሆኑ በምድር ውስጥ ሀብት የቀበረ ፃድቅ ካልሆነና የደበቀው ለጌታ ካልሆነ መልሶ አያገኘውም።
፲፱ ሀብታቸውን ወደ እኔ እንዲደብቁት እፈልጋለሁና፣ አለ ጌታ፤ እናም ሀብታቸውን ለእኔ ለማይደብቁት እርግማን ይሆንባቸዋል፤ ፃድቃኖች ካልሆኑ በቀር ንብረታቸውን ወደ እኔ አይደብቁምና፤ እናም ወደ እኔ ንብረቱንም የማይደብቅ፣ እርሱና፣ ደግሞ ንብረቱ፣ የተረገመ ነው፤ እናም ምድሪቱ በመረገሟ ማንንም አያድነውም።
፳ እናም ልባቸውን በሀብታቸው ላይ በማድረጋቸው ንብረታቸውን የሚደብቁበት ቀን ይመጣል፤ እናም ልባቸውን በሀብታቸው ላይ በማድረጋቸውና ከጠላቶቻቸው ሲሸሹ ንብረታቸውን ስለሚደብቁ፤ ወደ እኔም ስለማይደብቋቸው፣ እነርሱም ሆኑ ንብረቶቻቸው የተረገሙ ይሁኑ፤ በዚያም ቀን ይመታሉ ይላል ጌታ።
፳፩ እነሆ እናንተ፣ የዚህች ታላቅ ከተማ የሆናችሁ ሰዎች፣ እናም ቃሌን አድምጡ፤ አዎን፣ ጌታ የተናገራቸውንም ቃላት አድምጡ፤ እነሆም እንዲህም አለ፥ በሀብታችሁም የተረገማችሁ ናችሁ፤ እናም ደግሞ በእነርሱ ላይ ልባችሁን ስላደረጋችሁና ለእናንተ እነዚህን የሰጣችሁንም የእርሱን ቃላት ስላላዳመጣችሁ ሀብታችሁ ተረግመዋል።
፳፪ ጌታ አምላካችሁን በተባረካችሁበትም ሁኔታ አታስታውሱትም፤ ነገር ግን ጌታ አምላካችሁን ባታመሰግኑበትም ሁልጊዜ ሀብታችሁን ታስታውሳላችሁ፤ አዎን ልባችሁ ወደጌታ አልተወሰደም፣ ነገር ግን ለጉራና ለመወጣጠር፣ ለቅናቶች፣ ለፀብ፣ ለተንኮል፣ ለስደትና፣ ለግድያ፣ እናም ለሁሉም ዓይነት ክፋት በኩራት ያብጣል።
፳፫ በዚህም የተነሳ ጌታ እግዚአብሔር በምድሪቱ ላይ፣ እናም ደግሞ በሀብታችሁ ላይ እርግማን እንዲመጣ ያደርጋል፣ እናም ይህ የሆነው በክፋታችሁ ነው።
፳፬ አዎን፣ በደረሰው በዚህ ጊዜ፣ ነቢያቱን በማባረራቸውና፣ በመሳለቃቸው፣ እናም በድንጋይ በመውገራቸውና፣ በመግደላቸው፣ እንዲሁም እንደጥንት ጊዜውም እንዳደረጉት ሁሉንም ዓይነት ክፋት በማድረጋቸው ለዚህ ህዝብ ወዮለት።
፳፭ እናም እንግዲህ በምትናገሩ ጊዜም እንዲህ ብላችኋል፥ ጊዜአችን እንደ ጥንቱ እንደ አባቶቻችን ጊዜ እንኳን ቢሆን ነቢያቶቹን አንገድላቸውም ነበር፤ በድንጋይም አንወግራቸውም ነበር፣ እናም አንወረውራቸውም ነበር።
፳፮ እነሆ እናንተ ከእነርሱ የከፋችሁ ናችሁ፤ ምክንያቱም ጌታ ህያው እንደሆነ ስለኃጢአታችሁ እንዲሁም ስለክፋታችሁ ለመመስከር የጌታን ቃል ለእናንተ ለመናገር በመካከላችሁ ነቢይ ከመጣ፣ በእርሱ ትቆጣላችሁም፣ ታባርሩታላችሁም፣ እናም እርሱን ለማጥፋት ሁሉንም ዓይነት መንገድ ትሻላችሁ፤ አዎን፣ ስራችሁ መጥፎ መሆኑን በመመስከሩ እርሱ ሀሰተኛ ነቢይና፣ ኃጢአተኛ፣ እንዲሁም የዲያብሎስ ነው ትላላችሁ።
፳፯ ነገር ግን እነሆ፣ አንድ ሰው ከመካከላችሁ ከመጣና ይህንን አድርጉ፣ ኃጢኣት አይደለም፣ አድርጉትና አትሰቃዩም ካላችሁ፣ አዎን እንዲህም ይላል፥ በልባችሁ ኩራትም ተመሩ፤ አዎን፣ በዐይኖቻችሁ ኩራትም ተመሩ፤ እናም ልባችሁ እንደፈቀደም አድርጉ—እናም አንድ ሰው በመካከላችሁ ከመጣና እንዲህ ቢላችሁ፥ እርሱን ትቀበሉታላችሁ፣ ነቢይ ነውም ትሉታላችሁ።
፳፰ አዎን፣ እርሱን ታወድሱታላችሁ፣ እናም ለእርሱም ካላችሁ ቁሳቁሶች ትሰጡታላችሁ፣ ከወርቃችሁና ከብራችሁም ትሰጡታላችሁ፣ እንዲሁም ውድ የሆኑ ልብሶችም ታለብሱታላችሁ፤ እናም ሸንጋይ የሆኑ ቃላት ለእናንተ በመናገሩና፣ ሁሉም መልካም ነው በማለቱ፣ በእርሱ ዘንድ ስህተት አታገኙም።
፳፱ አቤቱ እናንተ ኃጢአተኛና ጠማማ ትውልዶች፣ እናንተ ጠጣሮችና አንገተ ደንዳና የሆናችሁ ሰዎች፣ ጌታ ምን ያህል ጊዜ ይታገሰናል ብላችሁ ትገምታላችሁን? አዎን፣ በሞኝ እናም በእውር መሪስ ለምን ያህል ጊዜ እንድትመሩ ትፈቅዳላችሁን? አዎን፣ ለምን ያህል ጊዜስ ነው ከብርሃን ይልቅ ጨለማን የምትመርጡት?
፴ አዎን፣ እነሆ የጌታ ቁጣ በእናንተ ላይ ነዷል፤ እነሆ፣ ምድሪቱንም በክፋታችሁ የተነሳ ረግሟታል።
፴፩ እናም እነሆ፣ ሀብታችሁን መያዝ እንዳትችሉ ከእጃችሁ እንዲያመልጥ የሚረግምበት ጊዜ ይመጣል፤ እናም በድህነታችሁም ወቅት መልሳችሁ አታገኙትም።
፴፪ እናም በድህነታችሁም ቀን ወደ ጌታ ትጮኻላችሁ፤ የመውደሚያችሁ ጊዜ ስለደረሰባችሁና ጥፋታችሁም እርግጥ በመሆኑ በከንቱ ትጮኻላችሁም፤ እናም በዚያን ቀን ታለቅሳላችሁና ትጮኻላችሁ አለ የሰራዊት ጌታ። ታለቅሳላችሁም፣ እንዲህም ትላላችሁ፥
፴፫ አቤቱ ንስሃ ብገባና፣ ነቢያቱንም ባልገድል፣ እናም በድንጋይ ባልወግርና፣ ባልወረውራቸው እመኝ ነበር። አዎን፣ በዚያን ቀን እንዲህ ትላላችሁ፥ አቤቱ ሀብታችንን በሰጠን ቀን ጌታ አምላካችንን ብናስታውስ ኖሮ፣ እናም እንዳናጣቸው ከእጃችን አያመልጡም ነበር፤ እነሆ ሀብታችን ከእኛ ሸሽቷልና።
፴፬ እነሆ እዚህ መሳሪያ አስቀምጠናል፣ እናም በሚቀጥለው ቀን የለም፤ እናም እነሆ፣ ለጦርነት ጎራዴዎቻችንንም በፈለግናቸው ጊዜ ከእኛ ተወስደዋል።
፴፭ አዎን ንብረቶቻችንን ደብቀናል፣ እናም ምድሪቱም በመረገሟ ጠፍተውብናል።
፴፮ የጌታ ቃል ወደ እኛ በመጣ ጊዜ ንስሃ በገባን ኖሮ፤ ምክንያቱም እነሆ፣ ምድሪቱ ተረግማለች፣ እናም ሁሉም ነገር ከእጅ አምላጭ ሆነዋል፣ እኛም ልንይዛቸው አልቻልንም።
፴፯ እነሆ፣ እኛ በጋኔን ተከበናል፤ አዎን፣ ነፍሳችንን ለማጥፋት በፈለገው መላዕክትም ተከበናል። እነሆ ኃጢአቶቻችን ታላቅ ናቸው። አቤቱ ጌታ፣ ቁጣህን ከእኛ መመለስ አትችልምን? እናም በእነዚያ ቀን የእናንተ ቋንቋ እነዚህ ይሆናሉ።
፴፰ ነገር ግን እነሆ፣ የሙከራ ቀናት አልፈዋል፤ እስከዘለዓለም ድረስ እስከሚዘገይ እናም መጥፊያችሁ እርግጥ እስከሚሆን ድረስ የመዳኛ ቀናችሁን አዘገያችሁ፤ አዎን፣ የህይወት ዘመናችሁን በሙሉ ልታገኙት በማትችሉት ተመኝታችኋል፤ እናም ታላቅና ዘለዓለማዊው ራስ በሆነው ውስጥ ባለው የፅድቅ ተፈጥሮ ተቃራኒ በሆነው ነገር ክፋትን በመስራት ደስታን ተመኝታችኋል።
፴፱ የዚህች ምድር የሆናችሁ ሰዎች፣ አቤቱ ቃሌን እንድታደምጡ እፈልጋለሁ! እናም ንስሃ እንድትገቡና እንድትድኑ ዘንድ፣ እናም የጌታ ቁጣ ከእናንተ እንዲመለስ ዘንድ እፀልያለሁ።