ቅዱሳት መጻህፍት
፫ ኔፊ ፳፱


ምዕራፍ ፳፱

የመፅሐፈ ሞርሞን መምጣት ጌታ እስራኤልን የሚሰበስብበት እንዲሁም ቃል ኪዳኑን ለመፈጸም የሚጀምርበት ምልክት ነው—የኋለኛው ቀን ራዕዮችን እንዲሁም ስጦታዎችን የማይቀበሉ የተረገሙ ይሆናሉ። ከ፴፬–፴፭ ዓ.ም. ገደማ።

እናም እንግዲህ እነሆ፣ እንዲህ እላችኋለሁ፤ እነዚህ ነገሮች በቃሉ መሰረት ወደ አህዛብ መምጣታቸው በጥበቡ ጌታ ተገቢ መሆናቸውን በሚመለከትበት ጊዜ፣ አብም ከእስራኤል ልጆች ጋር በድጋሚ ወደ ትውልድ ምድራቸው ለመመለስ ቃል ኪዳን የገባውን መፈፀም እንደጀመረ ታውቃላችሁ።

እናም በቅዱሳን ነቢያት የተነገሩት የጌታ ቃልም በሙሉ እንደሚፈፀሙ ታውቃላችሁ፤ እናም ጌታ ወደ እስራኤል ልጆች የሚመጣበት ጊዜውን አዘገየ ማለት አያስፈልጋችሁም።

እናም የተነገሩት ቃላትም ከንቱ ናቸው ብላችሁ በልባችሁ አትገምቱ፣ ምክንያቱም እነሆ ጌታ ለእስራኤል ቤት ለህዝቡ የገባውን ቃል ኪዳን ያስታውሳልና።

እናም እነዚህ የተባሉት በመካከላችሁ ሲመጡ በምትመለከቱበት ጊዜ፣ ከዚያም የጌታን ስራ ልትወቅሱ አይገባችሁም፣ ምክንያቱም የፍትህ ጎራዴ በቀኝ እጁ ናትና፤ እናም እነሆ፣ በዚያን ቀን ስራውን የምትወቅሱ ከሆነ በቅርቡይህችም እንድታሸንፋችሁ ያደርጋል።

የጌታን ስራ የሚወቅስ ወዮለት፣ አዎን፣ ክርስቶስን እና ስራዎቹን ለሚክድ ወዮለት!

አዎን፣ የጌታን ራዕይ ለሚክድ፣ እናም ጌታ ከእንግዲህ በራዕይ፣ ወይንም በትንቢት፣ ወይም በስጦታ፣ ወይም በልሳን ወይም በፈውስ፣ ወይንም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አይሰራም ለሚል ወዮለት!

አዎን፣ እናም በዚያን ቀን ጥቅምን ለማግኘት፣ በኢየሱስ ክርስቶስም ከእንግዲህ ድንቅ ነገር አይሰራም ለሚል ወዮለት፤ ይህንን የሚያደርግ እንደጥፋት ልጅ ይሆናልና፣ ለእርሱም በክርቶስ ቃል መሰረት ምህረት አይኖረውምና!

አዎን፣ እናም ከእንግዲህ ልታጉረመርሙ፣ እንዲሁም ልትወቅሱአይሁዶችንም ሆነ፣ የእስራኤል ቤት ቅሪት በሆኑት ላይ ትቀልዱም ዘንድ አይገባችሁም፤ እነሆም ጌታ ለእነርሱ የገባውን ቃል ኪዳን ያስታውሳል፣ እናም በመሃላ እንደገባውም ይፈጽምላቸዋል።

ስለዚህ ጌታም ለእስራኤል ቤት የገባውን ቃል ኪዳን ለማሟላት ፍትሁን ለመፈጸም እንዳይችል ቀኝ እጁን ወደግራው ለመመለስ ይቻለናል በማለት መገመት የለባችሁም።