ቅዱሳት መጻህፍት
አልማ ፷፪


ምዕራፍ ፷፪

ሞሮኒ ፓሆራንን ለመርዳት ወደ ጌዴዎን ምድር ዘመተ—ሀገራቸውን ለመከላከል የተቃወሙት የንጉስ ሰዎች ተገድለዋል—ፓሆራን እናም ሞሮኒ ኔፋውያንን በድጋሚ ያዙ—ብዙ ላማናውያን ከአሞንን ሰዎች ጋር ተቀላቀሉ—ቴአንኩም አሞሮንን ገደለው እናም ቀጥሎም እራሱ ተገደለ—ላማናውያን ከምድሪቱ ተባረሩ፣ እናም ሰላም ሠፈነ—ሔለማን ወደ አገልግሎቱ ተመለሰ፣ እናም ቤተክርስቲያኗን አሳደገ። ከ፷፪–፶፯ ም.ዓ. ገደማ።

እናም እንግዲህ እንዲህ ሆነ ሞሮኒ ይህንን ደብዳቤ በተቀበለ ጊዜ ስሜቱ ተነሳስቶ ነበር፣ እናም በፓሆራን ታማኝነት፣ ደግሞም ለሀገሩ ነፃነት ከሀዲ ስላልነበረ በታላቅ ደስታ ተሞልቶ ነበር።

ነገር ግን ፓሆራንን ከፍርድ ወንበር ባባረሩት ኃጢያትም ደግሞ እጅግ አዝኖ ነበር፤ አዎን፣ በአጠቃላይ በሀገራቸው ላይ እናም ደግሞ በአምላካቸው ላይ ባመፁት አዝኖ ነበር።

እናም እንዲህ ሆነ እንደ ፓሆራን ፍላጎት ሞሮኒ ጥቂት ሰዎችን ወሰደ፤ እናም ለሌሂና፣ ቴአንኩም በቀሪዎቹ ወታደሮች ላይ አዛዥ አደረጋቸው፤ ጉዞውንም ወደ ጌዴዎን ምድር አደረገ።

እናም በደረሰበት ስፍራ ሁሉ የነፃነት አርማውን አነሳ፣ እናም ወደ ጌዴዎን ምድር በዘመተበት ሁሉ የሚችለውን ኃይል አገኘ።

እናም እንዲህ ሆነ በሺህ የሚቆጠሩ ወደ አርማው በአንድነት ተሰበሰቡ፣ እናም በባርነት ስር እንዳይወድቁ ለነፃነታቸው ለመታገል ጎራዴያቸውን አነሱ።

እናም ሞሮኒ የሚችለውን ሁሉ ሰው በአንድነት በሰበሰበ ጊዜ፣ ወደ ጌዴዎን ምድር መጣ፤ እናም ጠንካራ ከሆኑት ከፓሆራን ወታደሮችም ጋር ቀላቀላቸው፣ እነርሱም ከዛራሔምላ ምድር ነፃ የሆኑትን ሰዎች ካስወጡት ከተቃዋሚዎች ንጉስ፣ እናም ምድሪቱን ከወሰደው ከፓኩስ የበለጠ ጠንካሮች ሆኑ።

እናም እንዲህ ሆነ ሞሮኒና ፓሆራን ከወታደሮቻቸው ጋር ወደ ዛራሔምላ ምድር ሄዱ፣ እናም ከተማዋን አጠቁና፣ ለውጊያም የፓኩስን ሰዎች አገኙአቸው።

እናም እነሆ፣ ፓኩስ ተገደለና የእርሱም ሰዎች እስረኞች ሆነው ተወሰዱ፣ እናም ፓሆራን ወደ ፍርድ ወንበሩ ተመለሰ።

እናም በህጉ መሰረት የፓኩስ ሰዎች፣ እናም ደግሞ በምርኮ ተወስደው ወህኒ ቤት የተጣሉት የንጉስ ሰዎች በህጉ መሰረት ተገደሉ፤ አዎን፣ ሀገራቸውን ለመከላከል የጦር መሳሪያ ያልያዙት ሁሉ፣ ነገር ግን ይህንን በመቃወም የተዋጉት፣ አዎን፣ የፓኩስና የንጉስ ሰዎች፣ እንዲገደሉ ተደረገ።

እናም ይህን ህግ ለሀገራቸው ደህንነት ሲባል በጥብቅ መከተሉ እንደዚህ አስፈላጊ ሆነ፤ አዎን፣ እናም ነፃነታቸውን ሲክድ የተገኘ ማንኛውም በህጉ መሰረት በፍጥነት ይገደል ነበር።

፲፩ እናም እንደዚህ በኔፊ ህዝብ ላይ የመሣፍንቱ ሰላሳኛ የንግስ ዘመን ተፈፀመ፤ ሞሮኒ እናም ፓሆራን በዛራሔምላ ምድር በህዝባቸው መካከል ለነፃነታቸው ምክንያት ታማኝ ባልሆኑት ላይ ሁሉ የሞት ፍርድ በመፍረድ ሰላምን መሠረቱ።

፲፪ እናም እንዲህ ሆነ በኔፊ ህዝብ ላይ በመሣፍንቱ ሰላሳ አንደኛ የንግስና ዘመን መጀምሪያ ላይ፣ ሞሮኒ ምግብ በፍጥነት እንዲላክ፣ እናም ደግሞ ስድስት ሺህ ወታደሮች ሔለማንን ምድሪቱን ለመጠበቅ እንዲረዱት ዘንድ እንዲላኩ አዘዘ።

፲፫ እናም ደግሞ ስድስት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ከበቂ ምግብ ጋር ወደ ሌሂና ቴአንኩም ወታደሮች እንዲላኩ አደረገ። እናም እንዲህ ሆነ ይህም የተደረገው ምድሪቱን ከላማናውያን ለመጠበቅ ነበር።

፲፬ እናም እንዲህ ሆነ ሞሮኒና ፓሆራን በዛራሔምላ ምድር ብዙ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች በመተው፣ ላማናውያንን በዚያች ከተማ ለማሸነፍ በመቁረጥ ወደ ኔፋውያን ምድር ጉዞአቸውን አደረጉ።

፲፭ እናም እንዲህ ሆነ ወደ ምድሪቱ በዘመቱ ጊዜ ከላማናውያን በርካታ ሰዎችን ያዙና፣ ብዙዎቹን ገደሉ፣ እናም ስንቃቸውንና የጦር መሳሪያዎቻቸውን ወሰዱባቸው።

፲፮ እናም እንዲህ ሆነ ሞሮኒ፣ እነርሱን ከወሰዱ በኋላ፣ በኔፋውያን ላይ በድጋሚ የጦር መሳሪያዎቻቸውን እንዳያነሱ ቃል ኪዳን እንዲገቡ አደረጉአቸው።

፲፯ እናም ይህንን ቃል ኪዳን በገቡም ጊዜ ከአሞን ህዝብ ጋር እንዲኖሩ ላኩአቸው፤ እናም ያልሞቱት ቁጥር ወደ አራት ሺህ ይጠጋ ነበር።

፲፰ እናም እንዲህ ሆነ ላማናውያንን በላኩአቸው ጊዜ ጉዞአቸውን ወደ ኔፊአያህ ምድር ቀጠሉ። እናም እንዲህ ሆነ ወደ ኒፋአያህ ከተማ በመጡ ጊዜም፣ በኒፋአያህ ከተማ አጠገብ በሜዳው ላይ ድንኳናቸውን ተከሉ።

፲፱ እንግዲህ ሞሮኒ በሜዳው ላይ ላማናውያን መጥተው እንዲዋጉ ፈልጎ ነበር፤ ነገር ግን ላማናውያን ያላቸውን ታላቅ ድፍረት በማወቃቸው፣ እናም በቁጥር እጅግ ብዙ መሆናቸውን ተመለከቱ፣ ስለዚህ በእነርሱ ላይ ለመምጣት አልደፈሩም፤ ስለዚህ በዚያን ቀን ለውጊያ አልመጡም ነበር።

እናም ምሽቱ በመጣም ጊዜ፣ ሞሮኒ በምሽት ጨለማ ሄደ፣ እናም በግንቡ ጫፍ ላይ ላማናውያን ከወታደሮቻቸው ጋር የጦር ምሽግ ያደረጉበትን ከተማ በስለላ ለማየት ሄደ።

፳፩ እናም እንዲህ ሆነ በመግቢያው በኩል በስተምስራቅ ነበሩ፣ እናም ሁሉም ተኝተው ነበር። እናም አሁን ሞሮኒ ወደ ወታደሮቹ ተመለሰና፣ ከግንቡ ጫፍ ወደ ውስጥ እንዲሆኑም ለማድረግ በፍጥነት ጠንካራ ገመድ እንዲሁም መሰላል እንዲያዘጋጁ አደረገ።

፳፪ እናም እንዲህ ሆነ ሞሮኒ የእርሱ የሆኑት ሰዎች እንዲሄዱ፣ እናም በግንቡ ጫፍ እንዲመጡ፣ እንዲሁም ወደ ከተማዋ፣ አዎን፣ በስተምዕራብ በኩልም እንኳን ላማናውያን ከወታደሮቻቸው ጋር ወዳልሰፈሩበትም እንዲወርዱ አደረገ።

፳፫ እናም እንዲህ ሆነ በጠንካራው ገመድና፣ መሰላል አማካኝነት በምሽት ሁሉም ወደ ከተማዋ ገቡ፤ ጠዋት በሆነም ጊዜ ሁሉም በከተማዋ ግንብ ውስጥ ነበሩ።

፳፬ እናም እንግዲህ፣ ላማናውያን በተነሱ ጊዜና የሞሮኒ ወታደሮች በግንቡ ውስጥ መሆናቸውን በተመለከቱ ጊዜ በበሩም ሸሽተው እስከሚወጡ ድረስ እጅግ ፈርተው ነበር።

፳፭ እናም አሁን ሞሮኒ ከፊቱ መሸሻቸውን በተመለከተ ጊዜ፣ የእርሱ ሰዎች በእነርሱ ላይ እንዲዘምቱ አደረገና፣ ብዙዎችን ገደሉ፣ እናም ሌሎች ብዙዎችን ከበቡአቸው፣ እናም በእስረኛነት ወሰዱአቸው፤ እናም የተቀሩት በባህሩ ዳርቻ ወደነበረው ወደ ሞሮኒ ምድር ሸሹ።

፳፮ ሞሮኒ፣ እናም ፓሆራን አንድም ነፍስ ሳይጠፋባቸው የኒፋአያህን ከተማ እንዲህ ወሰዱ፤ እናም የተገደሉ ብዙ ላማናውያን ነበሩ።

፳፯ እንግዲህ እንዲህ ሆነ እስረኞች የነበሩ ብዙ ላማናውያን ከአሞን ሰዎች ጋር ለመገናኘት፣ እናም ነፃ ሰው ለመሆን ፈለጉ።

፳፰ እናም እንዲህ ሆነ ብዙዎች እንደፍላጎታቸው ተደርጎላቸዋል።

፳፱ ስለዚህ የላማናውያን እስረኞች በሙሉ የአሞን ህዝቦች አባል ሆኑ፣ እናም ተግተው መስራት፣ መሬት ማረስ፣ ሁሉንም ዓይነት እህል መዝራትና፣ ሁሉንም ዓይነት ከብቶችና፣ መንጋዎች ማርባት ጀመሩ፤ እናም እንደዚህ ኔፋውያን ከታላቁ ሸክማቸው አረፉ፤ አዎን ከላማናውያን እስረኞች በሙሉ ተላቀቁ።

እንግዲህ እንዲህ ሆነ፣ ሞሮኒ የኒፋአያህን ከተማ ካገኘ በኋላ፣ የላማናውያን ወታደሮችን የቀነሱአቸውን ብዙ እስረኞችንም ከወሰደ በኋላ፣ እናም እስረኞች ተደርገው የተወሰዱትን ኔፋውያንን ብዙዎችን በድጋሚ ስላገኙ የሞሮኒን ወታደሮች ተጠናከሩ፤ ስለዚህ ሞሮኒ ከኒፋአያህ ከተማ ወደ ሌሂ ምድር ሄደ።

፴፩ እናም እንዲህ ሆነ ላማናውያን ሞሮኒ በእነርሱ ላይ መምጣቱን በተመለከቱ ጊዜ፣ በድጋሚ ፈሩ፣ እናም ከሞሮኒ ወታደሮች ፊት ሸሹ።

፴፪ እናም እንዲህ ሆነ ሞሮኒና ሠራዊቱ ከሌሂና ከቴአንኩም ጋር እስከሚያገኙአቸው ድረስ ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላኛው ተከተሉአቸው፤ እናም ላማናውያን ከሌሂና ከቴአንኩም በባህሩ ዳርቻ ወደ ሞሮኒ ምድር እስከሚመጡ ድረስ ሸሹ።

፴፫ እናም የላማናውያን ሠራዊቶች በሞሮኒ ምድር አንድ እስከሚሆኑ ድረስ ሁሉም በአንድነት ተሰበሰቡ። አሁን አሞሮን፣ የላማናውያን ንጉስም ደግሞ ከእነርሱ ጋር ነበር።

፴፬ እናም እንዲህ ሆነ ላማናውያን በምድረበዳው በስተደቡብና፣ በምድረበዳው በስተምስራቅ እስከሚከበቡ ድረስ፣ ሞሮኒና፣ ሌሂ፣ እናም ቴአንኩም በሞሮኒ ምድር ዳርቻ ዙሪያ ከወታደሮቻቸው ጋር ሰፈሩ።

፴፭ እናም በምሽት እንደዚህ ሰፈሩ። እነሆም፣ ኔፋውያንና፣ ደግሞ ላማናውያን በጉዞው ታላቅነት ምክንያት ደክሞአቸው ነበር፤ ስለዚህ ከቴአንኩም በስተቀር በምሽት ምንም ዓይነት የጦር ስልት አልወሰኑም ነበር፤ ምክንያቱም እርሱ በአሞሮን እጅግ ተቆጥቶ ነበር፤ ምክንያቱም አሞሮንና ወንድሙ አማሊቅያ ይህ ታላቅና፣ መጨረሻ የሌለው ጦርነት በእነርሱና በላማናውያን መካከል ለተደረገው፣ ለረጅሙ ጦርነትና፣ ደም መፋሰስ አዎን እናም ለከፋ ረሃብ መንስኤ መሆናቸውን ስላሰበ ነበር።

፴፮ እናም እንዲህ ሆነ ቴአንኩም በቁጣ ወደ ላማናውያን የጦር ሰፈር ሄደ፤ በከተማዋ ግንብ ውስጥም ገባ። እናም ከቦታ ቦታ በገመድ ሄዶ ንጉሱን አገኘው፤ በእርሱም ላይ ጦር ወረወረበት፣ እርሱም በልቡ አጠገብ ወጋው። ነገር ግን እነሆ ንጉሱ ከመሞቱ በፊት አገልጋዮቹን ቀሰቀሳቸው፣ እነርሱም ቴአንኩምን ተከተሉት፣ እናም ገደሉት።

፴፯ እንግዲህ እንዲህ ሆነ ሌሂና ሞሮኒ ቴአንኩም መሞቱን ባወቁ ጊዜ እጅግ አዝነው ነበር፤ እነሆ እርሱ ለሀገሩ በጥንካሬ የተዋጋ፣ አዎን፣ ለነፃነት እውነተኛ ጓደኛ የሆነ ሰው ነበር፤ እናም በብዙ አሰቃቂ ስቃይ እጅግ ተሰቃይቶ ነበር። ነገር ግን እነሆ ሞተ፣ እናም ምድር ሁሉ ወደሚሄዱበት ሄዷል።

፴፰ እንግዲህ እንዲህ ሆነ ሞሮኒ በሚቀጥለው ቀን ዘመተና፣ በታላቅ ሁኔታ እስከሚገድሏቸው ድረስ ወደ ላማናውያን መጡ፤ እናም ከምድሪቱ አባረሩአቸው፤ እናም ሸሹ፣ እንዲሁም በዚያን ጊዜ በኔፋውያን ላይ አልተመለሱም።

፴፱ እናም በኔፊ ህዝብ ላይ የመሣፍንቱ ሰላሳ አንደኛ የንግሥና ዘመን ተፈፀመ፤ እናም ለብዙ አመታት ጦርነትና፣ ደም መፋሰስ፣ እናም ረሃብና፣ ስቃይ ነበራቸው።

እናም በኔፊ ሰዎች መካከል ግድያና፣ ፀብና፣ መከፋፈል፣ እንዲሁምም ሁሉም ዓይነት ክፋት ነበር፤ ይሁን እንጂ ለፃድቃኖች ሲባል፣ አዎን፣ በፃድቃኖች ፀሎትም ምክንያት እነርሱ ድነዋል።

፵፩ ነገር ግን እነሆ፣ በኔፋውያንና በላማናውያን መካከል በነበረው ታላቅ ጦርነት እርዝማኔና ጦርነቱ እጅግ ረጅም በመሆኑ ብዙዎች ጠጣሮች ሆኑ፤ እናም ብዙዎች በስቃያቸው የተነሳ በእግዚአብሔር ፊት እራሳቸውን እስከሚያዋርዱ፣ በጥልቅ ትህትናም ዝቅ እስከሚሉ ለስላሶች ነበሩ።

፵፪ እናም እንዲህ ሆነ ለላማናውያን ይበልጥ የተጋለጠውን ምድር በብቁ ጠንካራ እስኪሆኑ ድረስ ሞሮኒ ምሽግ ካደረገ በኋላ፣ ወደ ዛራሔምላ ምድር ተመለሰ፤ እናም ደግሞ ሔለማን ወደ ትውልድ ስፍራው ተመለሰ፤ እናም በኔፊ ህዝብ መካከል እንግዲህ ሰላም ተመሰረተ።

፵፫ እናም ሞሮኒ ሞሮኒሀ ተብሎ ለሚጠራው ልጁ የሠራዊቱን መሪነት አሳልፎ ሠጠ፤ እናም ቀሪውን ጊዜውን በሰላም ያሳልፍ ዘንድ በቤቱ ተቀመጠ።

፵፬ እናም ፓሆራን ወደፍርድ ወንበሩ ተመለሰ፤ እናም ሔለማን ለህዝቡ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስበክ ሀላፊነትን ተቀበለ፤ ብዙ ጦርነቶችና ፀብ ስለነበሩ በቤተክርስቲያኗ በድጋሚ ደንብ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ነበር።

፵፭ ስለዚህ፣ ሔለማንና ወንድሞቹ ሄዱና፣ የእግዚአብሔርን ቃል ብዙ ኃጢአተኞችን ለማሳመን ተናገሩ፤ ብዙዎችንም ለኃጢአታቸው ንስሃ እንዲገቡ፣ እናም በጌታ በአምላካቸው እንዲጠመቁ አደረጓቸው።

፵፮ እናም እንዲህ ሆነ በምድሪቱ ሁሉ በድጋሚ የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን አቋቋሙ።

፵፯ አዎን፣ እናም ህጉን በተመለከተ ደንብ ወጣ። እናም ዳኞቻቸውንና፣ ዋና ዳኞቻቸውን ተመረጡ።

፵፰ እናም የኔፊ ህዝብ በምድሪቱ ላይ በድጋሚ መበልፀግ ጀመሩና፣ በድጋሚ በምድሪቱ ተባዙና እጅግ ጨመሩ። እናም እጅግ ሀብታም መሆን ጀመሩ።

፵፱ ነገር ግን ሀብታም እንዲሁም ጠንካሮች፣ እናም የበለፀጉ ቢሆኑም በኩራት ከፍ ብለው አልታዩም፤ ወይም ጌታ አምላካቸውንም ለማስታወስ አልዘገዩም፤ ነገር ግን በፊቱ እራሳቸውን እጅግ አዋርደው ነበር።

አዎን፣ ጌታ ታላላቅ ነገሮችን እንዴት እንዳደረገላቸው፣ ከሞትና፣ ከባርነት፣ እናም ከእስርና፣ ከሁሉም ዓይነት ስቃይ እንዳዳናቸው፣ እናም ከጠላቶቻቸው እጅም እንዴት እንዳስለቀቃቸው ያስታውሱ ነበር።

፶፩ እናም እንደቃሉ ጌታ እስከሚባርካቸው ወደ ጌታ አምላካቸው ሳያቋርጡ ይፀልዩ ነበር፣ ስለዚህ በምድሪቱ ላይ በረቱም በለፀጉም።

፶፪ እናም እንዲህ ሆነ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ተፈፀሙ። እናም ሔለማን በኔፊ ህዝብ ላይ በመሣፍንቱ ሰላሳ አምስተኛ የንግስ ዘመን ሞተ።