ቅዱሳት መጻህፍት
ኤተር ፬


ምዕራፍ ፬

ሞሮኒ የያሬድን ወንድም ጽሑፎች እንዲያሽጋቸው ታዘዘ—ጽሑፎቹም ሰዎች እንደያሬድ ወንድም እምነት እስከሚኖራቸው አይገለፁም—ክርስቶስም ሰዎች ቃሉን እናም የደቀመዛሙርቱን ቃላት እንዲያምኑ አዘዛቸው—ሰዎች ንሰሃ እንዲገቡ፣ ወንጌልን እንዲያምኑ፣ እና እንዲድኑ ታዘዋል።

እናም ጌታም የያሬድን ወንድም ጌታ ካለበት ተራራ ወርዶ እንዲመጣ፣ እናም ያያቸውን ነገሮች እንዲፅፍ አዘዘው፤ እርሱም በመስቀል ላይ እስከሚሰቀል ወደ ሰው ልጆች እንዳይመጡ ተከልክለዋል፤ እናም በዚህም የተነሳ ክርስቶስ ለህዝቡ እራሱን እስኪገልፅ ወደ ዓለም መምጣት ስለሌለባቸው ንጉስ ሞዛያ ጠበቃቸው።

እናም ክርስቶስም በእውነት እራሱን ለህዝቡ ከገለፀ በኋላ ጽሑፎቹ እንዲገለጡ አዘዘ።

እናም፣ እንግዲህ፣ ከዚያን በኋላ፣ ሁሉም እምነት አጥተው መነመኑ፤ እናም ከላማናውያን በስተቀር ማንም አልነበረም፣ እናም እነርሱም የክርስቶስን ወንጌል አስወግደዋል፤ ስለዚህ እኔ በድጋሚ ጽሑፎችን በመሬት ውስጥ እንድደብቅ ታዘዝኩ።

እነሆ፣ በእነዚህ ሰሌዳዎች ላይ የያሬድ ወንድም የተመለከታቸውን ነገሮችን ፅፌአለሁ፤ እናም ለያሬድ ወንድም ከተገለፀው በላይ የተገለፁ ታላቅ የሆኑ ነገሮች በጭራሽ አልነበሩም።

ስለዚህ ጌታም እንድፅፋቸው አዞኛል፤ እናም ፅፌአቸዋለሁ። እናም እንዳሽጋቸው አዞኛል፤ እናም ደግሞ ትርጉሙን እንዳሽግ አዞኛል፤ እናም በጌታም ትዕዛዝ በመመራት ተርጓሚዎቹን አሸግኋቸው።

ጌታም እንዲህ ብሎኛልና፥ አህዛብ ለክፋቶቻቸው ንሰሃ እስከሚገቡበት ቀን እናም በጌታም ፊት ንፁህ እስከሚሆኑ ድረስ ወደ እነርሱ አይሄዱም።

እናም ጌታም እንዲህ አለ፥ በእኔ እንዲነጹ ዘንድ፣ በዚያን ቀንም የያሬድ ወንድም እንዳደረገው በእኔ ታማኝ ይሁኑ፤ ከዚያም በኋላ እኔም የያሬድ ወንድም የተመለከታቸውን ነገሮች፣ እንዲሁም ራዕዮቼን በሙሉ እገልፅላቸዋለሁ ይላል የሰማይና የምድር አባት፣ እናም በእነርሱ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ነገሮች የፈጠረ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ።

እናም ከጌታ ቃል ጋር የሚከራከር፣ የተረገመ ይሁን፤ እናም እነዚህን ነገሮች የሚክድ፣ የተረገመ ይሁን፤ ምንም ታላቅ ነገሮችን ለእነርሱ አላሳያቸውም፣ ይላል ኢየሱስ ክርስቶስ፤ የምናገራችሁም እኔ ነኝና።

እናም በእኔ ትዕዛዝ ሰማያት ይከፈታሉ እንዲሁም ይዘጋሉ፤ በቃሌም ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ እናም በትዕዛዜ ነዋሪዎችዋ በእሳትም እንኳን ቢሆን ይጠፋሉ።

እናም ቃላቴን የማያምን ደቀመዛሙርቶቼንም አያምንም፤ እናም ይህን የማልናገር ከሆነ እናንተ ፍረዱ፤ ምክንያቱም በመጨረሻው ቀን እኔ እንደምናገር ታውቃላችሁና።

፲፩ ነገር ግን እኔ የተናገርኳቸውን እነዚህን ነገሮች የሚያምን በመንፈሴ መገለጥ እጎበኘዋለሁ፤ እናም እርሱ ያውቃል እናም ይመሰክራል። ምክንያቱም በመንፈሴ እነዚህ ነገሮች እውን መሆናቸውን ያውቃል፤ ሰዎች መልካም እንዲሰሩም ይገፋፋቸዋልና።

፲፪ እናም ሰዎች መልካምን ነገር እንዲሰሩ የሚገፋፋ ከእኔ የሆነ ነው፤ ከእኔ ካልሆነ በቀር መልካም የሆነ ከማንም አይመጣምና። እኔ ሰዎችን መልካም ወደሆነው ሁሉ የምመራ ነኝ፤ ቃሌን የማያምን በእኔ አያምንም—እኔም እንደሆንኩኝ አያምንም፣ እናም በእኔ የማያምን በላከኝ በአብ አያምንም። እነሆም፣ እኔ አባት ነኝ፤ የዓለምም ብርሃን፣ ህይወትም፣ እውነትም ነኝ።

፲፫ አህዛብ ሆይ ወደ እኔ ፣ እናም ታላቅ የሆኑትን ነገሮች፣ ባለማመንም የተደበቁትን እውቀቶች እንድታውቁ አሳያችኋለሁ።

፲፬ እናንት የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ወደ እኔ ኑ፤ እናም አብ ከዓለም መፈጠር ጀምሮ ምን ያህል ታላቅ ነገሮችን እንዳዘጋጀላችሁ ይገለፅላችኋል፤ እናም እናንተ ባለማመናችሁ ምክንያት ሊደርሱ አልቻሉም።

፲፭ እነሆ፣ በክፋታችሁ በአሰቃቂ ሁኔታ እንድትቀሩ እናም በልባችሁ ጠጣርነት እናም በአእምሮአችሁ መታወር እንድትቀሩ የሚያደርጋችሁን የአለማመን መጋረጃ ስትቀዱት፣ ከዓለም መፈጠር ጀምሮ ታላቁ እና አስደናቂው ነገር ከእናንተ የተደበቀው—አዎን፣ በተሰበረ ልብ እና በተዋረደ መንፈስ፣ አብን በስሜ ስትጠሩት፣ አብ ለአባቶቻችሁ፣ አቤቱ ለእስራኤል ቤት፣ የገባውን ቃል ኪዳን እንደሚያስታውስ ታውቃላችሁ።

፲፮ እናም በአገልጋዬ በዮሐንስ እንዲፃፉ ያደረግኋቸው ራዕዮቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ይከፈታሉ። እነዚህን ነገሮች በምትመለከቱበት ጊዜ በእርግጥ ስራ የሚገለጡበት ጊዜ መቃረቡን ማወቃችሁን አስታውሱ።

፲፯ ስለዚህ፣ ይህንን መዝገብ በምትቀበሉበት ጊዜ የአብ ሥራ በምድር ላይ መጀመሩን ታውቃላችሁ።

፲፰ ስለዚህ፣ እስከምድር ዳርቻ ያላችሁ ሁሉ ንሰሃ ግቡ፣ እናም ወደ እኔም ኑ፣ እናም ወንጌሌን እመኑ፣ እናም በስሜ ተጠመቁ፤ ያመነ እናም የተጠመቀ ይድናልና፤ ያላመነ ግን ይኮነናል፤ እናም በስሜ የሚያምኑትን ምልክቶች ይከተሏቸዋል።

፲፱ እናም በመጨረሻው ቀን ለስሜ ታማኝ ሆኖ የሚገኝ የተባረከ ነው፤ ምክንያቱም ከዓለም መፈጠር ጀምሮ ለእርሱ በተዘጋጀለት መንግስት ለመኖር እርሱ ከፍ ይላልና። እናም እነሆ ይህን የምናገረው እኔ ነኝ። አሜን።