1. የሰሜን ምስራቅ ዩናይትድ ስቴትስ
-
ቶፕስፊልድ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ቀዳማዊ የተወለዱበት ቦታ፣ በ ሐምሌ ፲፪፣ ፲፯፻፸፩ (እ.አ.አ.) ተወለዱ።
-
ጊልሰም ሉሲ ማክ የተወለዱበት ቦታ፣ በሐምሌ ፰፣ ፲፯፻፸፭ (እ.አ.አ.) ተወለዱ።
-
ተርንብሪጅ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ቀዳማዊ እና ሉሲ ማክ በዚህ ተጋቡ፣ ጥር ፳፬፣ ፲፯፻፺፮ (እ.አ.አ.)።
-
ዊትንግሀም ብሪገም ያንግ የተወለዱበት ቦታ፣ በሰኔ ፩፣ ፲፰፻፩ (እ.አ.አ.) ተወለዱ።
-
ሀርመኒ ኤማ ሄል በሀርመኒ ከተማ ተወልዳ ነበር፣ ሰኔ ፲፣ ፲፰፻፬ (እ.አ.አ.)።
-
ሼረን ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ በእዚህ ቦታ ተወለደ፣ ታህሳስ ፳፫፣ ፲፰፻፭ (እ.አ.አ.) (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፫ን ተመልከቱ)።
-
ለበኖን የስሚዝ ቤተሰብ በለበኖን ከተማ ውስጥ ከ፲፰፻፲፩ እስከ ፲፰፻፲፫ (እ.አ.አ.) ድረስ ኖሩ፣ በዚህም ጊዜ ጆሴፍ ስሚዝ የተከታተሉ የእግር ቀዶ ጥገና ነበረው።
-
ኖርዊች የስሚዝ ቤተሰብ ከፓልማይራ ከመውጣታቸው በፊት ከ፲፰፻፲፬ እስከ ፲፰፲፮ (እ.አ.አ.) ድረስ በእዚህ ቦታ ኖሩ።
-
ፓልማይራ የስሚዝ ቤተሰብ በ፲፰፻፲፮ (እ.አ.አ.) ወደ እዚህ ከተማ መጡ (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፫)።