6. የቤተክርስቲያኗ ወደ ምዕራብ ጉዞ
-
ፈየት በጥር ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ከፈየት ወደ ከርትላንድ ኦሀዮ ሄደ። እንዲሰበሰቡ ጌታ ባዘዘው መሰረት የኒው ዮርክ ሶስቱ ቅርንጫፎች (ፈየት፣ ኮልስቪል፣ እና ማንቸስተር) ከሚያዝያ እስከ ግንቦት ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) ድረስ እርሱን ተከተሉ (ት. እና ቃ. ፴፯–፴፰ን ተመልከቱ)።
-
ከርትላንድ ከ፲፰፻፴፩ እስከ ፲፰፻፴፰ (እ.አ.አ.) ድረስ ዋናው የቤተክርስቲያኗ ጠቅላይ መምሪያ በከርትላንድ ውስጥ ነበር።
-
ኢንዲፔንደንስ ጌታ ኢንዲፔንደንስን (ጃክሰን ክፍለ አገር ምዙሪ) እንደ ፅዮን ዋና ቦታ በሐምሌ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) ጠቆማት (ት. እና ቃ. ፶፯፥፫ን ተመልከቱ)። በአመፅ የተነሱ ሰዎች ቅዱሳንን ከጃክሰን ክፍለ አገር በህዳር ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) በግድ አስወጧቸው።
-
ልብርቲ የጃክሰን ክፍለ አገር ቅዱሳን ከ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) ቅዱስን እንደገና እንዲወጡ እስከተደረገበት እስከ ፲፰፻፴፮ (እ.አ.አ.) ድረስ በክሌይ ክፍለ አገር ተሰበሰቡ። ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ከአምስት ሌሎች ጋር በማይገባ ሁኔታ ከታህሳስ ፲፰፻፴፩ እስከ ሚያዝያ ፲፰፻፴፱ (እ.አ.አ.) ድረስ በእዚህ ቦታ ታሰሩ።
-
ፋር ዌስት ከ፲፰፻፴፮–፲፰፻፴፰ (እ.አ.አ.) ድረስ በእዚህ ቦታ መሸሸጊያ ተመስርቶ ነበር። በ፲፰፻፴፰ (እ.አ.አ.) የቤተክርስቲያኗ ጠቅላይ መምሪያ ነበር። በ፲፻፴፰–፲፰፻፴፱ (እ.አ.አ.) ቅዱሳን ከኢለኖይ እንዲሸሹ ተገደዱ።
-
ናቩ ከ፲፰፻፴፱–፲፰፻፵፮ (እ.አ.አ.) ድረስ የቤተክርስቲያኗ ጠቅላይ መምሪያ ነበር። ከነቢዩ እና ከወንድሙ ሀይረም ሰማዕት በኋላ፣ ቅዱሳን ወደ ምዕራብ ሄዱ።
-
ካውንስል ብላፍስ ፈር ቀዳጆች በሰኔ ፲፰፻፵፮ (እ.አ.አ.) በእዚህ ቦታ ላይ ደረሱ። የሞርሞን የሻለቃ ጦር አባላት በሐምሌ ፳፩፣ ፲፰፻፵፮ (እ.አ.አ.)፣ በጄምስ አለን አመራር ስር ከእዚህ ቦታ ሄዱ።
-
ዊንተር ኮርተርስ ከ፲፰፻፵፮–፲፰፻፵፮ (እ.አ.አ.) ድረስ ጊዜአዊ መስፈሪያ የሆነ ቦታ ነበር። የመጀመሪያው ቡድን በፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ አመራር ስር ወደ ምዕራብ በሚያዝያ ፲፰፻፵፯ (እ.አ.አ.) መሄድ ጀመሩ።
-
ፎርት ሌቭንዎርዝ የሞርሞን የሻለቃ ጦር በነሀሴ ፲፰፻፵፮ (እ.አ.አ.) ወደ ምዕራብ ጉዞአቸውን ከመጀመራቸው በፊት በእዚህ ቦታ ታጥቀው ነበር።
-
ሳንታ ፌ በጥቅምት ፲፱፣ ፲፰፻፵፮ (እ.አ.አ.) የሞርሞን የሻለቃ ጦርን ከእዚህ ሲጓዙ ፊሊፕ ኮክ ይመራቸው ነበር።
-
ፑዌብሎ ሶስት የታመሙ የተገነጠሉ የሞርሞን የሻለቃ ጦር አባላት እስከሚሻላቸው ድረስ ወደ ፑዌብሎ እንዲሄዱ ታዝዘው ነበር፣ በእዚህ፣ ከ፲፰፻፵፮–፲፰፻፵፯ (እ.አ.አ.) ድረስ ከምስስፒ ከመጡት ቅዱሳን ጋር ቆዩ። እነዚህ ቡድኖች ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆ በሐምሌ ፲፰፻፵፯ (እ.አ.አ.) ገቡ።
-
ሳን ዲያጎ የሞርሞን የሻለቃ ጦር ወደ እዚህ ቦታ ያደረጉትን የ፫ ሺህ ፪፻ ኪሎ ሜትር ጉዞአቸውን በጥር ፳፱፣ ፲፰፻፵፯ (እ.አ.አ.) ፈጸሙ።
-
ሎስ አንጀለስ የሞርሞን የሻለቃ ጦር በእዚህ ቦታ ላይ በሐምሌ ፲፮፣ ፲፰፻፵፯ (እ.አ.አ.) ተለቀቁ።
-
ሳክርመንቶ አንዳንድ የተለቀቁ የሻለቃ ጦር አባላት በእዚህ ቦታ ላይ እና በአሜሪካ ወንዝ ላይ በስተምስራቅ ባለው በሳተር ሚል ውስጥ ሰሩ። በጥር ፲፰፻፵፰ (እ.አ.አ.) ወርቅ በተገኘበት ግዜ በእዚያ ይገኙ ነበር።
-
ሶልት ሌክ ስቲ ከ፲፰፻፵፯ (እ.አ.አ.) እስከ አሁን ድረስ የቤተክርስቲያኗ ተቅላይ መምሪያ። ብሪገም ያንግ በሶልት ሌክ ሸለቆ ውስጥ በሐምሌ ፳፬፣ ፲፰፻፵፯ (እ.አ.አ.) ደረሱ።