የካርታዎች ዝርዝር በካርታዎች ላይ አንድ ቦታን ለማግኘት ይረዳችኋል። እያንዳንዱ ቦታ የካርታ ቁጥር እና መጠቆሚያ በቁጥር እና በፊደል የተሰራ ነው። ለምሳሌ የፎርት ሆል ማመልከቻ እንደ ፮:ለ፩ ተሰጥቷል፤ ይህም ካርታ ፮፣ አራት መአዘን ለ፩ ማለት ነው። በእያንዳንዱ ካርታ ላይ ያለ አራት መአዘንን ለማግኘት በካርታው ከፍተኛ እና በጎን ላይ የሚገኙትን ማጣቀሻዎች ተጠቀሙባቸው። የቦታዎቹ ሌላ ስም በቅንፎች ውስጥ ተዘርዝረዋል፣ ለምሳሌ፣ ካውንስል ብላፍስ (ኬንስቪል)።