2. ፓልማይራ-ማንቸስተር፣ ኒው ዮርክ፣ ፲፰፻፳–፲፰፻፴፩
-
የጆሴፍ ስሚዝ ቀዳማዊ በፍልጥ እንጨት የተሰራ ቤት መልአኩ ሞሮኒ በመስከረም ፳፩–፳፪፣ ፲፰፻፳፫ (እ.አ.አ.) በእዚህ ቤት ክፍል ውስጥ በጆሴፍ ስሚዝ ታየ (ጆ.ስ.—ታ ፩፥፳፱–፵፯ን ተመልከቱ)።
-
የጆሴፍ ስሚዝ ቀዳማዊ የእርሻ ቦታ ይህ የ፵፯ ሄክታር የእርሻ ቦታ ከ፲፰፻፳ እስከ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) ድረስ በስሚዝ ቤተሰብ ተሻሽሎ ነበር።
-
ቅዱስ ጥሻ በ፲፰፻፳ (እ.አ.አ.) ጸደይ መጀመሪያ በስሚዝ እርሻ ውስጥ በሚገኝ ጫካ ውስጥ የጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ የመጀመሪያ ራዕይ ደረሰ (ጆ.ስ.—ታ ፩፥፲፩–፳ን ተመልከቱ)።
-
የጆሴፍ ስሚዝ ቀዳማዊ ቤት ይህ ቤት መገንባት የተጀመረው በ፲፰፻፳፪ (እ.አ.አ.) በአልቭን ስሚዝ ነበር እናም የስሚዝ ቤተሰብ ከ፲፰፻፳፭ እስከ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) ድረስ ይኖሩበት ነበር።
-
የከሞራ ኮረብታ በመስከረም ፳፪፣ ፲፰፻፳፯ (እ.አ.አ.) መልአኩ ሞሮኒ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የወርቅ ሰሌዳዎችን ቤዚህ ቦታ (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፶–፶፬፣ ፶፱)።
-
የማርቲን ሀሪስ የእርሻ ቦታ ይህ የእርሻ ቦታ መፅሐፈ ሞርሞንን ለማተም በብድር ተይዞ እናም የአካባቢው ክፍልም ተሽጦ ነበር።
-
ኢ. ቢ. ግራንዲን የማተሚያ ሱቅ ፭ ሺህ መፅሐፈ ሞርሞን በዚህ ቦታ በ፲፰፻፳፱–፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) ታትመው ነበር።
-
ሀተዌይ ብሩክ በዚህ በመጀመሪያ በሚኖሩት በአብዛኛው ጊዜ ክሩክድ ክሪክ ተብሎ በሚታወቀው በዚህ ጅረት ውስጥ አንዳንድ የመጀመሪያ የቤተክርስቲያኗ ጥምቀቶች ተከናውነው ነበር።