3. የኒው ዮርክ፣ የፔንስልቬኒያ፣ እና የኦሀዮ፣ ዩ.ኤስ.ኤ. አካባቢ
-
ሳውዝ ቤይንብርጅ ጆሴፍ ስሚዝ እና ኤማ ሄል በጥር ፲፰፣ ፲፰፻፳፯ (እ.አ.አ.) ተጋቡ (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፶፯)።
-
ኮልስቪል በ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) የቤተክርስቲያኗ የመጀመሪያ ቅርንጫፍ በጆሴፍ ናይት ታላቁ ቤት ውስጥ ተደራጀ።
-
በሀርመኒ ውስጥ የጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ ቤት አብዛኛው የመፅሐፈ ሞርሞን ትርጉም የተፈጸመው በዚህ ቦታ ነበር። የክህነት ስልጣን በ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) በዳግም የተመለሰው በዚህ አካባቢ ነው (ት. እና ቃ. ፲፫፤ ፻፳፰፥፳፤ ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፸፩–፸፪ን ተመልከቱ)።
-
ፈየት ሶስቱ ምስክሮች የወርቅ ሰሌዳዎችን እና መልአክ ሞሮኒን በዚህ አዩ (ት. እና ቃ. ፲፯)። የመፅሐፈ ሞርሞን ትርጉን በሰኔ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) በእዚህ ቦታ ተፈጸመ። ቤተክርስቲያኗ በሚያዝያ ፮፣ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በእዚህ ቦታ ተደራጀች (ት. እና ቃ. ፳–፳፩ን ተመልከቱ)።
-
ሜንዶን የብሪገም ያንግ እና የሒበር ሲ ኪምባል የመጀመሪያ ቤት።
-
ከርትላንድ በ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) ወደ ላማናውያን የተላኩት ሚስዮኖች በእዚህ ቦታ አለፉ እናም በከርትላንድ አካባቢ ስድኒ ሪግደንን እና ሌሎችን አጠመቁ። ይህም ከ፲፰፻፴፩ እስከ ፲፰፻፴፰ (እ.አ.አ.) ድረስ የቤተክርስቲያኗ ጠቅላይ መምሪያ ቦታ ነበር። የዚህ ዘመን የመጀመሪያው ቤተመቅደስ የተገናባው በእዚህ ቦታ ነበር እናም በመጋቢት ፳፯፣ ፲፰፻፴፮ (እ.አ.አ.) ተቀደሰ (ት. እና ቃ. ፻፱ን ተመልከቱ)።
-
የኢሪ መስኖ በኒው ዮርክ (ኮልስቪል፣ ፈየት፣ እና ማንቸስተር) ውስጥ የሚገኙት ሶስት የቤተክርስቲያኗ ቅርንጫፎች በኢሪ መስኖ በኩል እና በእሪ ሀይቅ ወደ ከትርላንድ ኦሀዮ በሚያዝያና ግንቦት ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) ተሰደዱ።
-
ሀይረም ጆሴፍ እና ኤማ ከመስከረም ፲፰፻፴፩ እስከ መስከረም ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) ድረስ በእዚህ ቦታ ይኖሩ ነበር። ጆሴፍ እና ስድኒ ሪግደን በመፅሐፍ ቅዱስ የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም (ጆ.ስ.ት.) ላይ ይሰሩ ነበር። የተቀበሉት ራዕይ እነዚህ ነበሩ፥ ት. እና ቃ. ፩፣ ፷፭–፸፩፣ ፸፫፣ ፸፬–፸፯፣ ፸፱–፹፩፣ ፺፱፣ ፻፴፫።
-
አምኸርስት በጥር ፳፭፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) ጆሴፍ ስሚዝ እንደ ታላቅ ክህነት ፕሬዘደንት ተሾመ (ት. እና ቃ. ፸፭ን ተመልከቱ)።
-
ቶራንቶ የቤተክርስቲያኗ ሶስተኛው ፕሬዘደንት ጆን ቴይለር እና የሀይረም ስሚዝ ባለቤት ሜሪ ፊልዲንግ ስሚዝ ቤት።