2010–2019 (እ.አ.አ)
በጥበብ ምረጡ
ኦክተውበር 2014


15:19

በጥበብ ምረጡ

“ክፉን ለመጥላት መልካሙንም ለመምረጥ [እወቁ]” (ኢሳይያስ 7፥15)።

ውድ ወንድሞች፣ በዚህ ምሽት ከእናንተ ጋር ስለውሳኔዎች እና ምርጫዎች ምክር ለመካፈል ፍላጎቴ ነው።

በሳንፍራንሲስኮ ቤይ አካባቢ ጠበቃ በነበርኩበት በወጣትነቴ ጊዜ፣ የቻርሊ ብራውን በበዓል ጊዜ በቴሌቪዝን የሚታየውን ለሚያዘጋጅ ካምፓኒ ህጋዊ ስራ ፈርማችን ሰራ።.1 የቻርልስ ሾልትዝ እና እርሱ የሰራቸውን፣ከቻርሊ ብራውን፣ ከሉሲ፣ እና ከሌሎች አስደናቂ ሰዎች ጋር የፒናትስ ተከታይ ሆንኩኝ።

ከምወዳቸው ቀልድ መፅሄቶች አንዱ ሉሲ የምታደርገውን የሚያሳይ ነበር። እንደማስታውሰው፣ የቻርሊ ብራውን የቤዝቦል ቡድን በጣም አስፈላጊ በሆነ ጨዋታ ላይ ነበር። ሉሲ ኳሱን በመጫወቻው ምድር በቀኝ በኩል ሆና ወደላይ የተመታው ኳስ ወደ እርሷ መጣ። የመጫወቻው ቦታዎች ነጥብ ለማስቆጠር በተዘጋጁ ተጫዋቾች ተሞልቶ ነበር፣ እናም ይህም የጨዋታው የመጨረሻ ድርጊት ነበር። ሉሲ ኳሱን ከያዘችው፣ ቡድኗ ያሸንፋል። ሉሲ ኳሱን ሳትይዘው ከጣለችው፣ ሌላኛው ቡድን ያሸንፋል።

በቀልድ መፅሄት ብቻ ውስጥ እንደሚደረገው፣ ኳሱ ከላይ ወደ ሉሲ ሰዎርድ ተጫዋጮቹ በሙሉ ከበቧት። ሉሲም “ኳሱን ከያዝኩት፣ ጀግና እሆናለኡ፤ ካልያዝኩት ፣ ፍየል እሆናለሁ።”

ኳሱ ወደእርሷ መጣ፣ እና አብረዋት የሚጫወቱት በጉጉት እየተመለከቷት፣ ሉሱ ኳሱን ጣለችው። ቻርሊ ብራውን የእጅ ጓንቱን በንዴት ጣለው። ሉሲ ጓደኞቿን ተመለከተች፣ እጆቿን በከንፈሯ ላይ አደረገችና፣ እንዲህ አለች፥ “ስለ አገሬ የውጭ አገር አቅዋም ሀሳቤን ይዞ ኳሱን እንድይዝ እንዴት ትጠብቁብኛል?”

ይህም በብዙ አመት ውስጥ ሉሲ ከጣላቻቸው ኳሶች አንዱ ነበር፣ እናም ለእያንዳንዱም አዲስ ምክንያት ነበራት።2 ሁልጊዜም የሚያስቅ ቢሆንም፣ ሉሲ የምትለውየውድቀቷን ምክንያት ለመስጠት የምትጠቅምበት ነበር፣ ኩሱን ለመያዝ ለወደቀችበት እውነት ያልሆኑ ምክንያቶች ትሰጥ ነበር።

በፕሬዘደንት ቶማስ  ኤስ. ሞንሰን አገልግሎት፣ ውሳኔዎች እጣ ፈንታዎችን ይወስናሉ በማለት በብዙ ጊዜ አስተምረዋል።3 በዚያም መርሆ መሰረት፣ በዚህ ምሽት ያለኝ ምክር ትክክለኛው የሆነውን ውሳኔዎች ለማድረግ ከሚከለክላችሁ ማንኛውም ምክንያቶች በላይ እንድትነሱ በተለይም ኢየሱስ ክርስቶስን በማገልገል፡፡ በኢሳይያስ ውስጥ “መጥፎውን መቃወም እና መልካሙን መምረጥ” እንዳለብን ተምረናል፡፡”4

ሰይጣን በብዙ አዲስ እና ብልጥ በሆኑ መንገዶች በሰዎች ላይ ተፅዕኖ በሚኖርበት በዚህ ቀን፣ ምርጫዎቻችን እና ውሳኔዎቻችንእንደምንኖርበት በምናውጃቸው አላማዎች መሰረት በጥንቃቄ እንዲሰሩ ዘንድ ይህም በልዩ አስፈላጊ እንደሆነ አምናለሁ። ትእዛዛትን ለማክበር እና ቅዱስ ቃል ኪዳናትን በጥብቅ ለማክበር ፍጹም የሆነ ውሳኔ ያስፈልገናል። ምክንያቶች ከቤተመቅደስ በረከቶች፣ ለሚስዮን ብቁ ከመሆን፣ እና ከቤተመቅደስ ጋብቻ የሚያስወግዱን እንዲሆኑ ስንፈቅድ፣ እነዚህም በጣም የሚጎዱ ናቸው። በእነዚህ አላማዎች እንደምናምን በአፍ ስንናገር፣ ግን እነዚህን ለማከናወን የሚያስፈልጉትን ችላ ማለታችን የሚያሳዝንነው።5

አንዳንድ ወጣቶች በቤተመቅደስ የመገባት ፍላጎታቸውን ይናገራሉ፣ ነገር ግን ወደ ቤተመቅደስ ለማግባት ብቁ ከሚሆኑት ጋር ጊዜ አያሳልፉም። በእርግጥም፣ አንዳንዶች በቀጠሮ አይወጡም። ወጣት ወንዶች፣ ከትክክለኛው እድሜ በኋላ ሳታገቡ ለብዙ ጊዜ ስትቆዩ፣ ባለማግባታችሁ በተጨማሪ የተመቻችሁ ትሆናላችሁ። ነገር ግን የሚገባችሁ የማይመቻመሁ መሆን ነው። እባካችሁ በመንፈሳዊ እና መሀበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በቤተ-መቅደስ ጋብቻ ግባችሁ ላይ “በጉጉት መሳተፍን” ጀምሩ6

አንዳንዶች ጋብቻን ትምህርት እስከሚፈጽሙና ስራ እስከሚያገኙ ድረስ ይጠብቁታል።፡በአለም እነዚህ ተቀባይ ቢሆኑም፣ ይህ ምክንያት እምነትን አያሳይም፣ በዚህ ዘመን የተሰጡትን ምክሮች መከተልን አያሳይም፣ እናም ከትክክለኛ ትምህርት ጋር የሚስማማ አይደለም።

በቅርብ ጊዜ ከአንድ መልካም ወጣት ሰው ጋር ተገናኝቼ ነበር። አላማው ወደ ሚስዮን ለመሄድ፣ ለመማር፣ በቤተመቅደስ ለማግባት፣ እና ታማኝ ደስተኛ ቤተሰብ ለማግኘት ነበር። በአላማዎቹ ተደስቼ ነበር። ነገር ግን በተጨማሪ ስንነጋገር፣ የሚያደርገው እና የሚመርጣቸው ነገሮች ከአላማው ጋር የተስማሙ አለነበሩም። ወደ ሚስዮን ለመሄድ በእውነት እንደሚፈልግ እና በሚስዮን ለመሄድ እንዳይችል የሚያደርጉትን ጥፋቶች እያስወገደ እንደሆነ ስሜት ነበረኝ፣ ነገር ግን በየቀኑ የሚያደርጋቸው ነገሮች ለሚያጋጥሙት የሰውነት፣ የስሜት፣ የማህበራዊ፣ እና የመንፈሳዊ ችግሮች የሚያዘጋጁት አልነበሩም።7 በሀይል ለመስራት አልተማረም። ስለትምህርቱ ላይ የተኮሳተረ አይደለም። ወደ ቤተክርስቲያን ይሄዳል፣ ነገር ግን መፅሐፈ ሞርሞንን አላነበበም። ብዙ ጊዜዎችን በኮምፒውተር ጨዋታዎች እና መገናኛዎች የሚያጠፋ ነበር። ወደ ሚስዮን መሄዱ ብቻ ብቁ የሆነ ይመስለዋል። ወጣት ወንዶች፣ እባካችሁ ብቁ የሆኑ ድርጊቶችን ለማድረግ እና የጌታችን እና አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወኪል ለመሆን በመኮሳተር ተዘጋጁ።

ሀሳቤ ህይወትን ወደዚህ ወይም ወደዚያ በሚያደርገው ውሳኔ ላይ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን ይህም በህይወታችን ሁልጊዜ በምናደረገው ውሳኔዎች፣ እንዲሁም አብዛኛውን ጊዜአችንን በምናሳልፍባቸው ልዩ ባልሆኑት ውሳኔዎች ላይ ነው። በእነዚህ ጉዳዮች፣ መረጋጋትን፣ መመዛዘንን፣ እና በልዩም ጥበብን ትኩረት እንድንሰጥ ያስፈልገናል። ምክንያቶች ከመስጠት በላይ ከፍ ለማለት እና መልካም የሆኑ ምርጫዎችን ለማድረግ እንችላለን።

ለመረጋጋት፣ ለመመዛዘን፣ እና ጥበባዊ ስለመሆን መልካም ምሳሌ ቢኖር ኢንተርኔትን በመጠቀም ላይ ነው። የሚስዮን ስራን ለማከናወን፣ በክህነት ሀላፊነቶች ለመርዳት፣ ለቅዱስ ቤተመቅደስ ስርዓቶች ውድ ቅድመ አባቶችን ለማግኘት፣ እና ብዙ ሌሎችን ለማድረግ ለመጠቀም ይቻላል። መልካም ለማድረግ ያለው ችሎታ ታላቅ ነው። መጥፎ የሆኑ ብዚ ነገሮች፣ እንዲሁም ወሲባዊ ነገሮች የሚያሳዩትን፣ በኢንተርኔት የሚታዩትን ክፉ ነገሮች8 እና ድንገተኛ ንግግሮችን ለማስተላለፍ እንደሚያስችል እናውቃለን። ወንድም ራንዳል  ኤል ሪድ ባለፈው አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ስለኢንተርኔት በመናገር እንዳስተማሩት፣ “ጊዜአችሁን በሚያጠፋ እና ችሎታችሁን በሚያዋርዱ መጨረሻ በሌላቸው ነገሮች እራሳችሁን ለማጥመድ ትችላላችሁ።”9

ጊዜ የሚያጠፉ እና ጻድቅን የሚቃወሙ የሚገኙት በኢንተርኔት ብቻ አይደለም፤ በሁሉም ቦታ ይገኛሉ። ወጣቶቹን ብቻ ሳይሆን እኛንም ለመበከል ይችላሉ። በሁከት ውስጥ ባለ አለው ውስጥ ነው የምንኖረው።10 “ደስታ እና መጫወቻን” እና ምግባረ ጡ ያልሆኑትን እና በትክክል የማይሰሩትን ህይወቶች በሚያመልክበት ተክብበን ነው የምንገኘው። እነዚህ በሚተላለፉበት መገናኛ ዘዴዎች በዝቶ የሚገኙ

ሽማግሌ ዴቪድ  ኤ በድናር በቅርብ አባላት በህብረተሰብ መተላለፊያ ዘዴዎች እንደራሳቸው እንዲሆኑ አስጠንቅቀዋል።11 አርተር  ሲ ብሩክስ የሚባል ታዋቂ የሀሳብ ተካፋዪ ሰው ይህን ነጥብ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ነበር። የህብረተሰብ መተላለፊያ ዘዴዎች ስንጠቀምበት፣ ደስተኛውን የህይወታችንን ነገሮች እንደምናስተላልፍ፣ ነገር ግን በትምህርት ቤት ወይም በስራ የሚያስቸግሩንን እንደማናስተላልፍ አስመክቶ ነበር። ሙሉ ያልሆነ ህይወትን ነው የምናሳየው--አንዳንዴም እራስን ከፍ በሚያስደርግ ወይም ውሸተኛ በሆነ ሁኔታ። ይህን ህይወት እንካፈላለን፣ ከዚያም የህብረተሰብ መተላለፊያ ዘዴዎች ጓደኞቻችንን የውሸት ህይወት እንቀበላለን። ብሩክስ እንዳስመለከተው፣ “የጌዜአችሁን ክፍል ከሆናችሁበት በላይ ደስተኛ እንደሆናችሁ በውሸት ማሳየት፣ እና ሌላውን ጊዜአችሁን ሌሎች ከእናንተ በላይ ምን ያህል ደስተኛ እንደሆኑ በመመልከት ማሳለፍ ስለራሳችሁ እንዴት አይከፋችሁም።”12

አንዳንዴ አስፈላጊ ባልሆኑ፣ በሞኝነት፣ ምንም ትርጉብ በሌለው ድምጽ፣ እና በየጊዜው መጣላት እንደምንጥለቀለቅ አይነት ስሜት ይኖራል። ይህን ትኩረት የሚስበውን ስንተው እና አካባቢያችንን ስንመለከት፣ ወደ ጻድቅ አላማዎች ባለው ዘለአለማዊ ፍላጎት የሚረዱን ምንም ነገሮች የሉም። አንድ አባት በእነዚህ ትኩረትን በሚስቡ ነገሮች እንዲሳተፍ ልጆቹ በተደጋጋሚ በሚጠይቁበት ጌዜ በጥበብ መልስ ሰጥቷል። እንዲህም ጠየቀ፣ “ይህ መልካም ሰው ያደርገናልን?”

ትልቅም ይሁኑ ትንሽ፣ በዳግም ከተመለሰው ወንጌል ጋር ለማይስማሙት ለመጥፎ ምርጫዎች ምክንያት ስንሰጥ፣ የሚያስፈልጉንን በረከቶችና መጠበቂያቆችን እናጣለን እናም በአብዛኛው ጊዜም በኃጢያት እንያዛለን ወይም መንገዳችንን እንስታለን።

በልዩም ሀሳብ የሚይዘኝ በሞኝነት13 እና “በአዲስ ነገሮች በሙሉ” ላይ አጥብቆ በማሰላሰል ምክንያት ነው። በቤተክርስቲያኗ ሁሉንም አይነት እውነትን እና እውቀትን እናበረታታለን እናው እናከብራለን። ነገር ግን ባህር፣ እውቀት፣ እና የህብረተሰብ ምግባር ከእግዚአብሔር የደህንነት አላማና ከኢየሱስ ክርስቶስ አስፈላጊ ክፍል የተለዩ ከሆኑ፣ የህብረተሰብ መሰባበር ይመጣል።14 በእኛ ቀናት፣ በብዙ ነገሮች ፣ በልዩም በሳይንስ እና በመተላለፊያዎች፣ እድገት ቢኖርም አስፈላጊ የሆኑ መርሆች ጠፍተዋል እናም የደስተኛነት እና ደህና መሆን ተቀንሰዋል።

ሐዋሪያው ጳውሎስ በአቴና በአርዮስፋጎስ ፊት ለመናገር ሲጋበዝ፣ በዚህ ቀን የሚገኙትን እውቀተኛ ነን የሚሉትን እና የእውነት ጥበብ የማይገኝበትን ነበር ያየው።15 በሐዋሪያት ስራ ይህን ታሪክ እናነባለን፥ “የአቴና ሰዎች ሁሉና በዚያ የኖሩ እንግዶች አዲስ ነገርን ከመናገርና ከመስማት በቀር በሌላ ጉዳይ አይውሉም ነበር።”16 ጳውሎስ ትኩረት የሰጠው በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ላይ ነበር። የተሰበሰቡት መልእክቱ ስለሀኡማኖት እንደሆነ ሴርዱ፣ አንዳንዶቹ ተሳለቁበት፤ ሌሎችም እንዲህ በማለት ችላ አሉት፣ “ስለዚህ ነገር ሁለተኛ እንሰማሃለን።”17 ጳውሎስ ከአቴና ያለ መልካም ውጤት ወጣ። ዲን ፋራር ስለዚህ ጉብኝት እንዲ ጽፏል፣ “በአቴና ምንም ቤተክርስቲያን አልመሰረተም፣ ለአቴና ምንም ደብዳቤ አልጻፈም፣ እናም ምንም እንኳን በአካባቢው ቢጓዝም፣ በአቴና ውስጥ እግሩን እንደገና አላሳረፈም።”18

የሽማግሌ ዳለን  ኤች ኦክስ “በመልካም፣ የተሻለ፣ እና በጣም ጥሩ” ከሆኑት መካከል ልዩነትን የሚያሳየው የተነሳሳ መልእክት ምርጫዎችን እና ቀደምነትን ለመመዘን የሚያስችለውን መንገድ ይሰጣል።19 ብዙ ምርጫዎች በፍጥረት ክፉ አይደሉም፣ ነገር ግን የህይወት ጊዜአችንን የሚይዝብን እና መልካም ምርጫዎችን ከመምረጥ የሚገድበን ከሆኑ ግን፣ ከዚያም አደገኛ ይሆናሉ።

ብቁ የሆኑ መሳተፊያዎችም ከሁሉም በላይ ከሚሻሉት አላማዎች ትኩረት የሚስቡ እንደሆኑ የመወሰን መመዘን ያስፈልጋቸዋል። በወጣትነቴ እኔ ከአባቴ ጋር ሊረሳ የማይቻል ውይይት ነበረኝ። ብቁ የሆኑ ወጣቶች እንደ ስራ እና ቤተሰብን እንደመደገፍ አይነት የሆኑ የረጅም ጊዜ አላማ ለማድረግ ትኩረት እንደሚሰጡ አላመነም።

ለአባቴ ሁልጊዜም ቀደምነት ያላቸው ነገሮች ቢኖሩ ትርጉም ያለው ጥናት እና የስራ አጋጣሚ ናቸው። እንደ ክርክር እና የተማሪዎች መንግስት አይነት መሳተፊያዎች ከአስፈላጊው አላማዎቼ ጋር ግንኙነት ያለው እንደሆነ ተረድቶ ነበር። የእግር ኳስ፣ የቅርንጫፍ ኳስ፣ ቤዝ ቦል፣ እና በሪጫ በመሳተፍ የማሳልፋቸውን ብዙ ጊዜዎች አስፈላጊነት ግን ሊረዳ አልቻለም። አትሌት መሆን ጥንካሬን፣ ጽናትን፣ እና የቡድን ስራ ለመገንባት እንደሚያስችል ይቀበላል፣ ነገር ግን በአንድ ስፖርት ላት ለትንሽ ጊዜ ትኩረት መስጠት የሚሻል እንደሆነ ሀሳብ አቀረበ። በእርሱ ስፖርቶች መልካም እንደሆኑ ነገር ግን ለእኔ የሚሻሉ እንዳልሆኑ አስተያየት ነበረው። አንዳንድ ስፖርቶች አስፈላጊ ከሆኑ የረጅም ጊዜ አላማዎችን መስዋዕት በማድረግ ታዋቂነትን ለመገንባት እንደሚጥር ሀሳብ ይዞት ነበር።

በዚህ አጋጣሚ ምክንያት፣ ሉሲን ቤዝ ቦል የምትጫወትበትን ታሪክ የምወደው በአባቴ አስተያየት እኔ ኳሱን ከመያዝ በላይ የውጪ አገር ፖልሲን ማጥናት እንዳለብኝ ስለሚያስብ ነበር። እናቴ ስፖርቶችን ትወድ እንደነበር ግልጽ ማድረግ እፈልጋለሁ። በስፖርት የምጫወተው በሆስፒታል ከገባች ብቻ ነው።

የአባቴን ምክር ለመከተል እና በኮሌጅ ስፖርትን ላለመጫወት ወሰንኩኝ። ከዚያም የስታንፈርድ የእግር ኳስ አሰልጣኝ ከእኔና ከመርልን ኦልሰን ጋር ለምሳ ለመገናኘት እንደሚፈልግ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የእግር ኳስ አስልጣኔ ነገረኝ። ከእኔ ታናሽ የሆናችሁ መርልንን አታውቁትም ይሆናል። ከእርሱ ጋር በሎጋን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አብሬ እግር ኳስ እጫወት የነበረው ታዋቂ ሰው ነበር። መርልን በሀገሯ ታዋቂ በሆኑ የእግር ኳስ ቡድኖች ለእነርሱ እንዲጫወት የተመለመለ ሰው ነበር። በኮሌጅ ታዋቂ የእግር ኳስ ተጫዋች ሆኖ ሽልማት አግኝቶ ነበር። መርልን በመጨረሻም በአገር የእግር ኳስ ቡድን ውስጥ ለመጫወት ከተመረጡት በሶስተኛው ቡድን ውስጥ ተመርጦ ለ14 አመት በተደጋጋሚ በፕሮፌሽናል ቡድኖች ውስጥ ተጫውቶ ነበር። በ1982 ዓ/ም በእግር ኳስ ተዋቂ ሰዎች ተመርጠው በሚሞገሱበት አዳራሽ ውስጥ እንዲገባ ተመርጦ ነበር።20

ከስታንፈርድ አስልጣኝ ጋር የነበረን ምሳ በብሉበርድ ምግብ ቤት በሎጋን ዩታ ውስጥ ነበር። በእጅ ከተጨባበጥን በኋላ፣ አንዴም ቢሆን አይኔን አልተመለከተውም ነበር። ከመርልን ጋር ተነጋገረ እና እኔን ችላ አለኝ። ከምሳው በኋላ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ እኔ ዞር አለ ግን ስሜን ለማስታወስ አልቻለም ነበር። ከዚያም መርልንን እንዲህ አለው፣ “ስታንፈርድን ከመረጥክ እና ጓደኛህን ይዘህ ለመምጣት ከፈለክ፣ ጥሩ የክፍል ውጤት ስላለው ሊደረግ ይቻላል።” ይህ አጋጣሚ የአባቴን ጥበባዊ ምክር መከተል እንደሚገባኝ ማረጋገጫ ሰጠኝ።

ፍላጎቴ እናንተ በስፖርት እንዳትሳተፉ ወይም ኢንተርኔትን ወይም ሌሎች ብቁ የሆኑ ወጣቶች የሚሳተፉበትን ነገሮች እንዳትሳተፉበት ለመገፋፋት አይደለም።እነዚህ በመጠን፣ በመመዘን፣ እና በጥበብ መደረግ የሚገባቸው መሳተፊያዎች ናቸው። በጥበብ ስትጠቀሙባቸው፣ ህይወታችንን ያሻሽላሉ።

ነገር ግን፣ ሁሉንም፣ ወጣቶችንና ሸምጋላዎችን፣ አላማዎችን እንዲገመግሙ እና ራስን ለመቆጣጠር እንዲጥሩ አበረታታለሁ። የየቀኑ ድርጊቶቻችን እና ምርጫዎቻችን ከአላማዎቻችን ጋር የተያያዙ መሆን ይገባቸዋል። ከምክንያቶች እና ትኩረት ከሚስቡት በላይ ከፍ ማለት ያስፈልገናል። ኢየሱስ ክርስቶስን በጻድቅ ለማገልገል ከገባናቸውን ቃል ኪዳኖች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ምርጫዎች ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው።21 አይናችንን ከአላማው ዞር ለማድረግ ወይም ኳሱን ለምንም ምክንያት መጣል አይገባንም።

ይህ ህይወት እግዚአብሔርን ለመገናኘት የምንመርጥበት ጊዜ ነው።22 ደስተኛ ሰዎች ነን። መልካም ቀልድን እናውቃለን እናም ከጓደኞች እና ቤተሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፍን እንወዳለን። ነገር ግን ለህይወታችን እና ለምርጫዎቻችን መሰረት የሆነ አላማ እንዳለ ማወቅ ያስፈልገናል። እድገትን የሚያስወግዱ ትኩረትንየሚያስቱ ነገሮች እና ምክንያቶች ጉዳት ያመጣሉ፣ ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስን እና በቤተክርስቲያኑ ያለን እምነት የሚቀንስ የሚያሳዝን ነው።

ጸሎቴም እንደ ካህናት ድርጊታችን በመምህር አገልግሎት ላይ ካሉት ከሚጠበቀው ጋር አንድ እንዲሆኑ ነው። በሁሉም ነገሮች “በኢየሱስ ክርቶስ ምስክርነት ጀግናዎች”23 መሆን ሰዎችን በሰለስቲያል እና በተረስትሪያል መንግስት መካከል በመግባት የሚለያየው እንደሆነ ማስታወስ ይገባናል። ከሚከፋፍለው በሰለስቲያል በኩል ለመገኘት እንፈልጋለን። እንደ እርሱ አንዱ ሐዋርያ፣ ስለኃጢያት ክፍያ እና ስለአዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊነት በጥብቅ እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ሊ መንድልሰን-ቢል መለንዴዝ፣ Production TV Specials

  2. ከሳተርን ጨረቃ ትኩረቷን እንድትስት ካደረጋት እና በጓንታዋ ውስጥ ስላለው በሽታ የሚያመጣ ነገር እንዳለበት በማሰብ፣ ሉሲ ሁልጊዜም ኳሱን ለጣለችበት ምክንያት ትሰጣለች።

  3. “Decisions Determine Destiny,” chapter 8 in Pathways to Perfection:Discourses of Thomas S. Monson(1973), 57–65 ተመልከቱ።

  4. ኢሳይያስ 7፥15

  5. “ማድረግ ምን ማድረግ መልካም እንደሆነ እንደማወቅ ቀላል ቢሆን ኖሮ፣ የጸሎት ቤቶች ቤተክርስቲያኖች እና የደሀ ሰዎች ቤቶች ቤተምንግስቶች ይሆኑ ነበር” (ውልያም ሼክስፒር, The Merchant of Venice, act 1, scene 2, lines 12–14).

  6. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥27

  7. Adjusting to Missionary Life (booklet, 2013), 23–49 ተመልከቱ።

  8. ስተፍኒ ሮዝንብሉም፣ “Dealing with Digital Cruelty,” New York Times, ነሀሴ 24, 2014, SR1 ተመልከቱ።

  9. ራንድ ኤል. ርድ፣ “The Choice Generation,” Ensign or Liahona, May 2014, 56.

  10. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥26 ተመልከቱ

  11. ዴቪድ ኤ. በድናር፣ “To Sweep the Earth as with a Flood” (speech delivered at BYU Campus Education Week, ነሀሴ 19, 2014); lds.org/prophets-and-apostles/unto-all-the-world/to-sweep-the-earth-as-with-a-flood ተመልከቱ።

  12. አርተር ሲ. ብሩክስ፣ “Love People, Not Pleasure,” New York Times, ሀምሌ 20, 2014, SR1.

  13. በሚያሳዝን ሁኔታ፣ በጊዜአችን እያደገ ያለው ጊዜ የሚያጠፋ ነገር ቢኖር ሞኝነት ነው። አዳኝ ሰዎችን የሚበክሉ ነገሮችን ሲዘረዝር፣ ሞኝነቱን ጨምሮ ነበር (ማርቆስ 7፥22 ተመልከቱ)።

  14. ይህም የደረሰው በጥንት ክሪክ እና ሮሜ፣ እናም በመፅሐፈ ሞርሞን ስልጣኔዎች ውስጥ ነበር።

  15. ፍሬድሪክ ደብሊው. ፋራር፣ The Life and Work of St. Paul (1898), 302. There were philosophers of all kinds, including Epicureans and Stoics, rival groups who some described as the Pharisees and the Sadducees of the pagan world. See also Quentin L. Cook, “Looking beyond the Mark,” Ensign, Mar. 2003, 41–44; Liahona, Mar. 2003, 21–24 ተመልከቱ።

  16. የሐዋሪያት ስራ 17፥21

  17. የሐዋሪያት ስራ 17፥32.

  18. ፋራር፣ The Life and Work of St. Paul, 312.

  19. ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “Good, Better, Best,” Ensign or Liahona, ህዳር 2007, 104–8.

  20. Merlin Olsen was a hall of fame football player, actor, and NFL commentator for NBC. He won the Outland Trophy playing football for Utah State University. He played pro football for the Los Angeles Rams. On TV he played Jonathan Garvey opposite Michael Landon on Little House on the Prairie and had his own TV program, Father Murphy. Merlin is now deceased (Mar. 11, 2010), and we miss him very much.

  21. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥5 ተመልከቱ

  22. አልማ 34፥32 ተመልከቱ

  23. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥79.