እምነታችሁን መለማመድ የመጀመሪያ ተቀዳሚ አድርጉ
አሉታዊ ውጣውረዶች በህይወታችን ውስጥ ቢኖሩም እንኳን፣ እምነታችን በንቃት ለመለማመድ ጊዜ ሊኖረን ይገባል።
አዳምና ሔዋን በኤደን ገነት ሳሉ፣ ለእለት መቆያ የሚያስፈልጋቸው ሁሉ በብዛት ተሰቷቸው ነበር። አስቸጋሪ ሁኔታ፣ ውጣ ውረድ ወይም ህመም አልነበራቸውም።አስቸጋሪ ጊዜያትን አሳልፈው ስለማያውቁ፣ ደስተኛ መሆን እንደሚችሉ አያውቁም ነበር። መከራ በፍጹም ስላልነበራቸው፣ ስለዚያም ሰላም ሊሰማቸው አይችልም ነበር።
በኋላም አዳምና ሔዋን ከመልካም እና ክፉ የእውቀት ዛፍ ከሆነው ፍሬ ያለመብላት ትእዛዝን ተላለፉ። እንደዚያ በማድረጋቸው በየዋህ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸው ቀረ። የተቃርኖን መርህ መለማመድ ጀመሩ። ጤናቸውን የሚያደክም ህመም ያጋጥማቸው ጀመረ። ሀዘንም ደስታም ጭምር ይሰማቸው ጀመር።
አዳም እና ሔዋን የተከለከለውን ፍሬ በመውሰዳቸው፣ የመልካም እና ክፉ እውቀት ወደ አለም ተዋወቀ።የእነርሱ ምርጫ እኛ እንድንሞከር እና እንድንፈተን ወደዚህ ምድር እንድንመጣ አስችሎናል።1 መወሰን እንድንችል እና ለምርጫችን ተጠያቂ እንድንሆን በሚያደርግ ነጻ ምርጫ ተባርከናል። ውድቀቱ የደስታም እና የሀዘንም ስሜት በህይወታችን መከሰት እንዲችሉ አድርጓል።ብጥብጥ ስለሚሰማን ሰላምን መረዳት እንችላለን።2
ይህ እኛ ላይ እንደሚከሰት የሰማዩ አባታችን ያውቅ ነበር። ሁሉም የእርሱ ፍጹም የደስታ እቅዱ ክፍል ነው። በሀጢያት ክፍያው በሟችነት ጊዜ አስቸጋሪ ልምዶች ለማሸነፍ፣ በፍጹም ታዛዥ በሆነው ልጁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት መንገዱን አዘጋጀ።
የምንኖረው በሙከራ ጊዜያት ነው። በአለም ያሉትን የክፋት ምንጮች በሙሉ መዘርዘር አይጠበቅብኝም። የአለም ክፍል የሆኑትን ፈተናዎች እና ልብ ምቶች መግለጽ አስፈላጊ አይደለም።እያንዳንዳችን ከፈተና፣ ከህመም እና ሀዘን ጋር የየራሳችንን ትግል በደንብ እናውቃለን።
ወደዚህ የመምጣታችን አላማ ለመፈተን፣ ለመሞከር፣ እና ለመጎልበት እንደሆነ በቅድመ ሟችነት አለም ተምረናል።3 የጠላታችን ክፋት እንደሚገጥመን እናውቅ ነበር። አንዳንዴ የሟችነትን ነገሮች ከአውንታዊው ይልቅ አሉታዊውን የበለጠ እንደምናውቅ ይሰማናል። ነብዩ ሌሂ እዲህ አስተማረ፣ “በሁሉም ነገሮች ተቃርኖ ይኖር ዘንድ አስፈላጊ ነው።”4 በህይወት የሚያጋጥሙን አሉታዊ ውጣውረዶች ቢኖሩም፣ እነታችንን ለመለማመድ ጊዜ ሊኖረን ይገባል። ይህ ልምድ አውንታዊ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የሐጢያት ክፍያ ላይ በእምነት የተሞላ ሀይልን ወደ ህይወታችን ይጋብዛል።
የሰማዩ አባታችን ወደ ክርስቶስ እንድንመጣ እና በሐጢያት ክፍያው ላይ እምነት እንድንለማመድ ለመርዳት መሳሪያ ሰቶናል። እነዚህ መሳሪያዎች መሰረታዊ ልምድ ሲሆኑ፣ በሟችነት ውጣውረድ ውስጥ ሰላምን ለማግኘት ቀላሉን መንገድ ያቀርባሉ። ዛሬ ከእነዚህ መሳሪያዎች ውስጥ አራቱን ለመወያየት መርጫለሁ። ስናገር፣ በእያንዳንዱን መሳሪያ የግላችሁን ተጠቃሚነት እያመዛዘናችሁ አስቡ፣ ከዛ እንዴት በእያንዳነዱ መሳሪያ የበለጠ መጠቀም እንደምትችሉ ለማወቅ ከጌታ ምሬትን እሹ።
ጸሎት
የመጀመሪያው መሳሪያ ጸሎት ነው። በየጊዜው ከሰማይ አባትህ ጋር ለመነጋገር ምረጡ። በየቀኑ ሀሳባችሁን እና ስሜታችሁን ከእሱ ጋር ለማካፈል ጊዜ ውሰዱ። የሚያሳስባችሁን ነገር ሁሉ ንገሩት። በጣም በአስፈላጊ እንዲሁም በለማዳዊ የህይወታችሁ ሁኔታዎች ሁሉ ላይ ፍላጎት አለው። ሙሉ ስሜታችሁን እና ልምዶቻችሁን አካፍሉት።
ነጻ ምርጫችሁን ስለሚያከብር፣ የሰማይ አባት ለእሱ እንድትጸልዩ በፍጹም አያስገድዳችሁም። ነገር ግን ምርጫችሁን ስትለማመዱ እና በሁሉም የህይወታችሁ ክፍሎች እሱን ስታስገቡ፣ ልባችሁ በጥልቅ ሰላም መሞላት ይጀምራል። ያ ሰላም በትግሎቻችሁ ላይ ዘለአለማዊ ብርሀንን የቀይሳል። እነዚህን ውጣውረዶች ከዘለአለማዊ እይታ እንድታመዛዝኑ ይረዳችኋል።
ወላጆች፣ ልጆቻችሁን በጠዋት እና ማታ የቤተሰብ ጸሎት ሀይል በጥበቃ እርዷቸው። ልጆች በክፉ ምኞት፣ ስስት፣ ኩራት፣ እና በሌሎች ሐጢአታዊ ባህሪዎች ጥርቅም በየቀኑ የተጋለጡ ናቸው። ከቤተሰብ ጸሎት በሚመነጨው ታላቅ በረከቶች ልጆቻችሁን ከአለማዊ አሉታዊ ተጽእኖዎች ጠብቋቸው። የቤተሰብ ጸሎት በየቀኑ ህይወታችሁ ጥያቄ የሌለው ቀዳሚ ምርጫችሁ ይሁን።
የቅዱስ መጽሀፍ ጥናት
ሁለተኛው መሳሪያ በቅዱስ መጽሐፍት ውስጥ ያሉ የእግዚአብሔርን ቃል እና የነብያትን ቃላት ማጥናት ነው። በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር እናወራለን። እርሱ በአብዛኛው ጊዜ በተጻፉት ቃሉ ለኛ መልሶ ያናግረናል። የመለኮታዊ ድምጾቹን ለማወቅ፣ የእርሱን ቃላት አንብቡ፣ ቅዱስ መጽሐፍትን አንብቡ፣ እና አሰላስሉ።5 የየቀኑ ህይወት ጥልቅ ክፍል አድርጓቸው። ልጆቻችሁ እንዲያስተውሉ፣ እንዲረዱ፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ምሬትን እንዲተገብሩ ከፈለጋችሁ፣ ቅዱስ መጽሀፍትን አብራችኋቸው አንብቡ።
ቅዱስ መጽሐፍትን ለማጥናት ጊዜ የለም የሚለውን የሴጣን ውሸት አትስሙ። እነሱን ለማንበብ ጊዜ መውሰድን ምረጡ። የእግዚአብሔር ቃላትን መመገብ ከእንቅልፍ፣ ከትምህርት፣ ከስራ፣ ከቴሌቪዥን ሾው፣ ከቪድዮ ጨዋታዎች ወይም ከማህበራዊ ገጽ ይበልጣል። የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት የቅድሚያ ምርጫችሁን ማስተካከል ይኖርባችኋል። እንደዚያ ከሆነ፣ አድርጉት።
ቅዱሳት መጻህፍትን በየቀኑ በማጥናት ስለሚመጡት በረከቶች ብዙ የነቢያት ቃል ኪዳኖች አሉ።. 6
ይህን ቃል በመግባት ድምጼን እጨምራለሁ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት በግል እና ከቤተሰባችሁ ጋር በየቀኑ ጊዜ ስትሰጡ፣ ሰላም በህይወታችሁ ይዘልቃል። ያ ሰላም ከውጪኛው አለም አይደለም የሚመጣው። ሰላም ከቤታችሁ፣ በቤተሰባችሁ ውስጥ፣ ከራሳችሁ ልብ ይመጣል። የመንፈስ ስጦጣ ይሆናል። በአቅራቢያችሁ ባለው አለም ያሉ ሌሎች ላይ ተጽእኖ እንድታሳድሩ ከእናንተ ይመነጫል። ለአለም ሰላም በጥቅሉ ለመጨመር እናንተ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ታደርጋላችሁ።
የህይወታችሁ ውጣውረድ ይቆማል ብዬ አላውጅም። አስታውሱ አዳም እና ሔዋን በኤደን ገነት እያሉ፣ ከውጣውረድ ነጻ ነበሩ፣ ግን ደስታን፣ ሀሴትን እና ሰላምን ለመለማመድ አልቻሉም። ውጣውረዶች የዚህ አለም አስፈላጊ ክፍል ናቸው።7 ቀጣይነት ባለው የየቀን ቅዱስ መጽሐፍ ጥናት፣ በአከባቢያችሁ ካለ ሁካታ ሰላምን ታገኛላችሁ እና ፈተናን ለመቋቋም ጥንካሬ ታገኛላችሁ። በእግዚአብሔር ጸጋ ጠንካራ እምነትን ታካብታላችሁ እና በኢየሱስ ክርስቶስ የሀጢአት ክፍያ አማካኝነት በእግዚአብሄር ጊዜ ሁሉም እንደሚስተካከል ታውቃላችሁ።
የቤተሰብ ምሽት
ቤተሰባችሁን ለማጠንከር እና ሰላምን ለማጎልበት ስትሰሩ፣ ይህን ሶስተኛ መሳሪያ አስታውሱ፤ ሳምንታዊ የቤተሰብ ምሽት። ከብዙ ስራ ቀን በኋላ እንደ ተጨማሪ ነገር ብቻ የቤተሰብ ምሽትን ላለማድረግ አስቡበት። በሰኞ ምሽት ቤተሰባችሁ በአንድ ላይ ቤት ለመሆን ወስኑ። ከቤተሰባችሁ ጋር በቤት ውስጥ ከምታጠፉት ጊዜ ይልቅ የስራ ጥያቄዎችን፣ ስፖረት፣ ተጨማሪ እንቅስቃሴዎች፣ የቤት ስራ፣ ወይም ሌላ ማንኛውም ነገር እንዳይበልጥባችሁ።
የአመሻሻችሁ አቀማመጥ ከተመደበው ጊዜ አይበልጥም። ወንጌል በታቀደ መልኩ እና በየሁኔታዎች ውስጥ መሰበክ አለበት። ለእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ትርጉም ያለው ልምድ አድርጉት። የቤተሰብ ምሽት በመልካም ቦታ ምስክርነት የመስጫ ውድ ሰአት ነው፤ ማስተማርን፣ ማቀድን እና የተደራጀ ተሰጥኦን ለመማር፤ የቤተሰብ ትስስርን ለማጠንከር፤ የቤተሰብ ባህልን ለማሳደግ፤ እርስ በእርስ ለመነጋገር፤ እና በተለይም፣ በአንድ ላይ ለመደሰት!
በባለፈው የሚያዚያ አጠቃላይ ጉባኤ ላይ፣ እህት ሊንዳ ኤስ. ሪቭስ በአጽኖት አውጀች፤ “የየቀን የቅዱስ መጽሐፍት ጥናት እ ጸሎት እና ሳምንታዊ የቤተሰብ ምሽት በረከቶችን መመስከር አለብኝ። ጭንቀታችንን በማስወገድ፣ ለህይወታችን ምሬት በመስጠት እና ለቤታችን ጥበቃ እንዲጨምር የሚረዱ ድርጊቶች ናቸው።”8 እህት ሪቭ በጣም ብልህ ሴት ነች። የእነዚህ ሶስት ወሳኝ ልምዶች የራሳችሁ ምስክርነት እንዲኖራችሁ በአጽኖት እገፋፋችኋለሁ።
ቤተ-መቅደስ መካፈል
አራተኛው መሳሪያ ቤተ-መቅደስ መሄድ ነው። ከእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ ሌላ ሰላማዊ ቦታ በዚህ ምድር ላይ እንደሌላ ሁላችንም እናውቃለን። የቤተ-መቅደስ መግቢያ ከሌላችሁ፣ እንዲኖራችሁ ብቁ ሁኑ። መግቢያ ካላችሁ፣ በየጊዜው ተጠቀሙበት።9 ቤተ-መቅደስ የምትሆኑበትን ቋሚ ጊዜ አዘጋጁ። እዚያ ከመሆን ማንም ወይም ምንም ነገር እንዳይከለክላችሁ።
በቤተ-መቅደስ ሆናችሁ፣ የስርአቶችን ቃላት አድምጡ፣ አሰላስሉ፣ ጸልዩባቸው፣ እና ትርጉማቸውን ለመረዳት እሹ። የኢየሱስ ክርስቶስን የሀጢያት ክፍያ ሀይል ለመረዳት ቤተ-መቅደስ አንዱ ምርጥ ቦታ ነው። እርሱን እዚያ እሹ። የራሳችሁን የቤተሰብ ስም በቤተመቅደስ በማኖር የበለጠ ብዙ በረከት እንደሚመጣ አስታውሱ።
በኢየሱስ ክርስቶስ የሀጢያት ክፍያ ውስጥ ለህይወታችሁ መጠበቅ እነዚህ አራት መሳሪያዎች መሰረታዊ ልምዶች ናቸው። አዳኛችን የሰላም ልኡል እንደሆነ አስታውሱ። በዚህ ሟች ህይወት ሰላም የሚመጣወ በእርሱ የቤዛ መስዋእት ነው። በቀጣይነት ጠዋት እና ማታ ስንጸልይ ፣ ቅዱስ መጽሐፍቶቻችን በየቀኑ ስናጠና፣ ሳምንታዊ የቤተሰብ ምሽት ሲኖረን፣ እና ቤተ-መቅደስ በቋሚነት ስንሄድ፣ ወደ “እርሱ እንድንመጣ” ግብዣውን መልስ እየሰጠን ነው። እነዚህን ልምዶች የበለጠ ስናዳብር፣ ሴጣን እኛን ለመጉዳት የበለጠ ይነሳሳል፣ ነገር ግን ያንን ለማድረግ ብቃቱ ያነሰ ይሆናል። እነዚህን መሳሪያዎች በመጠቀም፣ የእርሱን የቤዛ መስዋእትነት ሙሉ ስጦታ ለመቀበል ምርጫችንን እንለማመዳለን።
እነዚህን ነገሮች ስታደርጉ የህይወት ትግል ሁሉ የጠፋል እያልኩ አይደለም። ከመከራ እና ፈተና ማደግ እንድንችል ነው ወደዚህ ሟች ህይወት የመጣነው። ውጣውረዶች የበለጠ እንደ ሰማይ አባታችን እንድንሆን ያደርጉናል፣ እና የኢየሱስ ክርስቶስ የሐጢያት ክፍያ እነዚህን ውጣውረዶች እንድንቋቋም ያስችለናል።10 በጽናት ወደ እርሱ ስንመጣ፣ ማንኛውን ፈተና፣ ማንኛውንም የልብ ህመም፣ ሁሉንም የሚያጋጥሙን ውጣውረዶች መቋቋም እንደምንችል እመሰክራለሁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።