2010–2019 (እ.አ.አ)
ብርሀናችሁንማካፈል
ኦክተውበር 2014


12:18

ብርሀናችሁንማካፈል

በእምነታችንበፅኑነትመቆምእናእውነተኛውንትምህርትለማወጅድምጻችንንከፍማድረግአለብን።

በዚህምሽትያሉንንሁለትአስፈላጊሀላፊነቶችንለመመልከትእፈልጋለሁ።እነዚህምመጀመሪያ፣በህይወታችንውስጥየወንጌልንብርሀንበየጊዜውመጨመር፣እናሁለተኛምያንንብርሀንከሌሎችጋርመማካፈልናቸው።

እህቶች፣እንዴትአስፈላጊእንደሆናችሁታውቃላችሁን? እያንዳንዳችሁአሁንበሰማይአባትየደህንነትአላማውስጥዋጋያላችሁናችሁ።የምናከናውነውስራአለ።በዳግምስለተመለሰውወንጌልእውነትእናውቃለን።እውነትንለመጠበቅተዘጋጅተናልን? በዚህምመኖርያስፈልገናል፣ይህንንምመካፈልያስፈልገናል።በእምነታችንበፅኑነትመቆምእናእውነተኛውንትምህርትለማወጅድምጻችንንከፍማድረግአለብን።

በመስከረም 2014 (እ.አ.አ) እናEnsignእና Liahona,ውስጥ፣ሽማግሌኤም. ራስልባለርድእንዲህጽፈዋል፥ “ተጨማሪየሆኑየሴቶችንልዩ፣ተፅዕኖያላቸውድምጾችእናእምነቶችያስፈልጉናል።ስለሁሉምነገሮችምስክራቸውንለመስጠትእንዲችሉዘንድትምህርትንእንዲማሩናየምናምነውእንዲገባቸውእንፈልጋቸዋለን።”1

እህቶች፣በኢየሱስክርስቶስያለኝንእምነትታጠናክራላችሁ።ምሳሌአችሁንተመልክቻለሁ፣ምስክራችሁንሰምቻለሁ፣እናምከብራዚልእስከቦትስዋናድረስምእምነታችሁተሰምቶኛል።በቤተሰቦቻችሁእናበእጅስልካችሁቁጥራቸውካሏችሁሰዎችእናምበኢንተርኔትውስጥከሚገኙትጓደኞቻችሁእናበዚህምሽትበአጠገባችሁበሚገኙትሰዎችሁሉእምነታችሁይሰማል።በሀሪየትኦክዶርፍእንዲህከጻፈችውጋርእስማማለሁ፣ “እናንተህይወታችሁንበምትኖሩበትመንገድወንጌሉአስደሳችመልእክትእንደሆነስታሳዩምእየጨለመችባለችውአለምውስጥሀይልያሏችሁእናፅኑምኞትያሏችሁምሳሌዎችናችሁ።”2

ፕሬዘደንትቶማስኤስሞንሰንእንደጠቆሙት፣ “ብርሀንለሌሎችለመስጠትከፈለጋችሁ፣እራሳችሁምመድመቅአለባችሁ።”3የእውነትብርሀንበውስጣችንእንዲደምቅእንዴትለማድረግእንችላለን? አንዳንዴድምቀትየሌለውአምፑልአይነትእንደሆንኩኝይሰማኛል።ለመድመቅእንዴትእችላለሁ?

ቅዱሳትመጻህፍትእንደሚያስተምሩት፣ “ከእግዚአብሔርየሆነውብርሀንነው፤እናብርሀንንተቀብሎበእግዚአብሔርየሚቀጥል፣ተጨማሪብርሀንንይቀበላል።”4ቅዱሳትመጻህፍትእንዳሉትበእግዚአብሔርመቀጠልአለብን።ወደብርሀንምንጭወደሆኑት – ወደሰማይአባትእናኢየሱስክርስቶስመሄድይገባናል።በውስጡየሚገኙትበሙሉወደክርስቶስእናወደታላቁየኃጢያትክፍያእንደሚያመለክቱእያወቅንወደቤተመቅደስምለመሄድእንችላለን።

ቤተመቅደሶችበአካባቢያቸውያላቸውንውጤትአስቡበት።የከተማመሀከልንወብታማያደርጋሉ፣ከከፍተኛኮረብታዎችይበራሉ።እንዴትነውወብትየሚያደርጉትእናየሚያበሩት? ቅዱስመጻህፍትእንደሚሉት፣ “እውነትያበራልና”5እናምቤተመቅደሶችበውስጣቸውእውነትንእናየዘለአለምአላማንይዘዋል፣እናንተምእንደዚህናችሁ።

ፕሬዘደንት ጆርጅ ኪው. ካነን በ1877 (እ.አ.አ) እንዳሉት “እያንዳንዷ ቤተመቅደስ …ሰይጣን በምድር ላይ ያለውን ሀይል ትቀንሳለች።”6በምድርላይቤተመቅደስበተገነባበትበማንኛውምቦታጭለማንእንደሚገፋአምናለሁ።ቤተመቅደስየሰውዘርንለማገልገልአላማአለውእናምለሰማይአባትልጆችሁሉወደእርሱየመመለስናከእርሱጋርየመኖርችሎታንይሰጣል።አላማችሁከእነዚህየተቀደሱህንጻዎች፣ከእነዚህየጌታቤቶችጋርአንድአይደሉምን? ጭለማንለመግፋትእናምወደሰማይአባትብርሀንለመመለስሌሎችንማገልገልናመርዳትአይደሉምን?

ቅዱስየቤተመቅደስስራዎችበክርስቶስያለንንእምነትያጠናክራሉ፣ከዚያምየሌሎችንእምነትላይተፅዕኖይኖረናል።የቤተመቅደስመንፈስንበመመገብ፣በህይወታችንውስጥየአዳኝንየኃጢያትክፍያእውነትነት፣ሀይል፣እናተስፋለመማርእንችላለን።

ከብዙአመትበፊትቤተሰባችንከባድችግርደረሰበት።ወደቤተመቅደስሄድኩኝእናበዚያምበቅንነትጸለይኩኝ።የእውነትጊዜዎችተሰምቶኝነበር።ስለድካሜግልጽየሆነስሜትተሰማኝ፣እናምደንግጬነበር።መንፈስበሚያስተምርበትበዚያጊዜም፣በጌታመንገድሳይሆንበራሷመንገድነገሮችንየምታደርግ፣እናበምታከናውነውበማንኛውምነገርእርሷእንዳደርገችውየምታስመስልኩራትያላትሴትአየሁ።ራሴንእንደምመለከትአውቅነበር።በልቤምወደሰማይአባት “እንደዚያሴትለመሆንአልፈልግም፣እንዴትእቀየራለሁ?” በማለትአለቀስኩኝ።

በቤተመቅደስውስጥበነበረንጹህየራዕይመንፈስ፣ስለቤዛበጣምአስፈላጊነትተማርኩኝ።ወዲያውምወደአዳኝኢየሱስክርስቶስተመለስኩኝእናጭንቀቴቀልጦሲጠፋተሰማኝእናምልቤምበታላቅተስፋተሞላ።እርሱምየእኔብቸኛተስፋነበርእናምእርሱንአጥብቄለመያዝፈለግኩኝ።ስለራሷየምታተኩረው፣የፍጥርሴት “የእግዚአብሔር” እናተፅዕኖላለባትሰዎች “ጠላት”7እንደሆነችግልጽሆነልኝ።በዚያቀንበቤተመቅደስውስጥየኩራትጸባዬየሚቀየረውእናመልካምለማድረግየምችለውበኢየሱስክርስቶስየኃጢያትክፍያበኩልብቻእንደሆነተማርኩኝ።ፍቅሩበግልጽተሰማኝእናምበመንፈስእንደሚያስተምረኝናምንምነገርወደኋላሳላደርግልቤንለእርሱከሰጠሁእንደሚቀይረኝአወኩኝ።

አሁንምድካሜንእታገልበታለሁ፣ነገርግንበኃጢያትክፍያውመለኮታዊእርዳታላይእምነቴንአሳርፋለሁ።ይህንጹህትምህርትየመጣውወደቤተመቅደስስለገባሁ፣እረፍትናመልሶችንስለፈለግሁነው።ወደቤተመቅደስሸከምይዤገባሁ፣እናምከሁሉምበላይሀይልያለውንአዳኝአውቄወጣሁ።ሸክሜየቀለለእናደስተኛነበርኩኝምክንያቱምብርሀኑንተቀብያለሁእናምእርሱለእኔያለውንአላማምተቀብያለሁ።

በአለምባሉትቦታዎች፣ቤተመቅደሶችበውጪየራሳቸውየሆነልዩመልክእናንድፍአላቸው፣ነገርግንበውስጥሁሉምዘለአለማዊውንብርሀን፣አላማ፣እናእውነትይዘዋል።በ1 ቆሮንቶስ 3፥16 እንደምናነበው፣ “የእግዚአብሔርቤተመቅደስእንደሆናችሁየእግዚአብሔርምመንፈስእንዲኖርባችሁአታውቁምን?” እኛምእንደእግዚአብሔርሴትልጆችበአለምቦታዎችውስጥተፈጥረናል፣እናምእያንዳንዳችንምእንደቤተመቅደሶቹአይነትየራሳችንየሆነመልክእናየውጪንድፍአለን።በውስጣችንየመንፈስብርሀንአለን።ይህምየመንፈስብርሀንየአዳኝብርሀንየሚንጸባረቅበትነው።ሌሎችወደዚህድምቀትተስበውይመጣሉ።

በምድርላይ፣ከሴትልጅነት፣እናትነት፣መሪነት፣እናአስተማሪነትእስከእህትነት፣ደሞዝተኝነት፣ሚስትነት፣እናተጨማሪአይነቶችየሆኑየራሳችንሀላፊነቶችአሉብን።እያንዳንዱምተፅዕኖአለው።የወንጌልንእውነቶችእናየቤተመቅደስቃልኪዳኖችንበህይወታችንውስጥስናንጸባርቅ፣እያንዳንዱምሀላፊነትስነምግባርአለው።

ሽማግሌዲ. ቶድክርስቶፈርሰንእንዳሉት፣ “በሁሉምድርጊቶች፣በምንምሌላግንኙነቶችውስጥማንምሌላሰውያለውእኩልየማይሆንበትተፅዕኖእናትሊኖራትትችላለች።”8

በልጆቻችንወጣትነት፣ከባለቤቴዴቪድጋርአብሬመርከቡንእንደምነዳአይነትይሰማኝነበር፣እናምየ11 ልጆቻችንመርከቦችወደአለምባህሮችለመጓዝእየተዘጋጁበወደብላይሲንሳፈፉበአእምሮዬእመለከትነበር።ዴቪድእናእኔበየቀኑከትንሾቹየቡድንተጓዥመርከቦቻችንጋርወዴትእንደምንሄድከጌታየየቀኑንመነሳሻመፈለግእንደሚያስፈልገንይሰማንነበር።

የየቀኑስራዬልብሶችንበማጠፍ፣የልጆችንመጻህፍትበማንበም፣እናእራትበማዘጋጀትአይነትበሚረሱነገሮችየተሞሉነበሩ።አንዳንዴበቤታችንመደብውስጥእነዚህሁልጊዜምበሚደረጉትየቤተሰብጸሎት፣የቅዱሳትመጻህፍትጥናት፣እናየቤተሰብየቤትምሽትአይነትትትንሽነገሮችታላቅነገሮችእንደሚከናወኑለማየትአንችልም።ነገርግን፣እንዚህአጋጣሚዎችዘለአለማዊትርጉምያላቸውናቸው።ልጆቻችንበወንጌልብርሀንየተሞላእና “ለእግዚአብሔርአገልግሎትለመሄድየተዘጋጁ” 9በባህርየሚጓዙጀልባዎችሲሆኑታላቅደስታይመጣል።የእምነትናየአገልግሎትትትንሽስራዎቻችንበእግዚአብሔርለመቀጠልእናበመጨረሻምየዘለአለምብርሀንንእናግርማንወደቤተሰባችን፣ጓደኞቻችን፣እናተገናኞቻችንለማምጣትየምንችልበትነው።በእርግጥበሌሎችላይተፅዕኖሊኖራችሁትችላላችሁ!

የመጀመሪያክፍልእድሜያላትልጅምንአይነትተፅዕኖሊኖራትእንደምትችልአስቡበት።ትንሹንልጃችንንበመጫወቻቦታበጠፋበትጊዜየሴትልጃችንእምነትቤተሰባችንንባረከ።ቤተሰብእርሱንለመፈለግበየቦታውተሯሯጡ።የዘጠኝአመትሴትልጄእጄንጎተተችናእንዲህአለች፣ “እማ፣እንጸልይ?” ትክክልነበረች! ቤተሰብበሚመለከቱንሰዎችመካከልተሰበሰበእናልጃችንንለማግኘትእንድንችልጸለይን።አገኘነው።ለመጀመሪያክፍልሴትልጆችምእንዲህእላለሁ፣ “እባካችሁወላጆቻችሁእንዲጸልዩበየጊዜውእንዲያስታውሱአድርጉ።”

በዚህበጋ 900 ወጣትሴቶችበአላስካበሚሰበሰቡበትለመገኘትእድልነበረኝ።ተፅዕኖአቸውታላቅነበር።ወደመሰፈሪያውበመንፈስተዘጋጅተው፣መፅሐፈሞርሞንንበማንበብ፣እና “ህያውክርስቶስ፣የሐዋሪያትምስክር”ንገምግመውመጡ።በሶስተኛውምሽት፣ሁሉም 900 ወጣትሴቶችአብረውተነስተውጽሁፉንበሙሉቃልበቃልአነበቡ።

መንፈስትልቅአዳራሹንሞላእናከእነርሱጋርአብሬለማንበብበጣምፈለግኩኝ።ነገርግንይህንለማድረግአልቻልኩም።ይህንአልሸመደድኩምነበር።

እነዚህእህቶችእንዳደረጉትእኔም “የህያውክርስቶስን” ቃላትመማርጀምሬአለሁ፣እናምበእነርሱተፅዕኖምክንያትሐዋሪያትስለክርስቶስያላቸውንምስክርነትደጋግሜሳነብአዳኝንሁልጊዜእንዳስታውስየገባሁትንየቅዱስቁርባንቃልኪዳንንበሙሉለመኖርችያለሁ።ቅዱስቁርባንትልቅየሆነትርጉምእንዲኖረውምአድርጎልኛል።

በዚህአመትበታህሳስ 25 “ህያውክርስቶስን” በመሸምደድእናበልቤይህንበታላቅዋጋበመያዝለአዳኝየገናስጦታለማቅረብተስፋአለኝ።የአላስካእህቶችለእኔእንደነበሩልኝ፣እኔምመልካምተፅዕኖለማድረግእንድችልተስፋአለኝ።

ከዚህበሚቀጥሉት “በህያውክስቶስ” ቃላትውስጥራሳችሁንለማግኘትትችላላችሁን? “ሁሉምየእርሱንምሳሌእንዲከተሉይለምናል።የፍልስጢንመንገዶችንተራምዷል፣የታመሙትንፈውሷል፣የታወሩትእንዲያዩአድርጓል፣እናምሞታንንአስነስቷል።”10

እኛየቤተክርስቲያኗእህቶችበሽተኞችንእየፈወስንየፊልስጢምንመንገድአንራመድም፣ነገርግንለታመሙት፣ለደከሙትግንኙነቶችለመጸለይእናየኃጢያትክፍያየፍቅርፈውስንለማድረግእንችላለን።

እንደአዳኝአይነስውርየሆኑትንለመፈወስባንችልም፣በመንፈስስውርለሆኑትስለደህንነትአላማለመመስከርእንችላለን።በዘለአለምቃልኪዳኖችውስጥስለክህነትሀይልየሚረዱበትንአይንለመክፈትእንችላለን።

አዳኝእንዳደረገውየሞቱትንአናስነሳም፣ነገርግንየሙታንንስምለቤተመቅደስስራበማግኘትልንባርካቸውእንችላለን።ከዚያምበእርግጥምከመንፈስእስርቤታቸውእናስነሳቸዋለንእናየዘለአለምህይወትመንገድንእናቀርብላቸዋለን።

ህያውአዳኝ፣ኢየሱስክርስቶስ፣እንዳለን፣እናበእርሱሀይልእናብርሀንየአለምንጭለማለመግፋት፣ለምናውቀውእውነትድምጽንለመስጠት፣እናሌሎችወደእርሱእንዲመጡተፅዕኖለማድረግእንደምንችልእመሰክራለሁ።በኢየሱስክርስቶስስም፣አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ኤም. ራስልባለርድ, “Men and Women and Priesthood Power,” Ensign, Sept. 2014, 32; Liahona,መስከረም 2014, 36.

  2. ሔርየት አር. ኡክዶርፍ, The Light We Share(Deseret Book Company, 2014 (እ.አ.አ))፣ 41 በፍቃድ የተጠቀመ፡፡

  3. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን, “For I Was Blind, but Now I See,” Ensign,ግንቦት 1999, 56; Liahona,ሐምሌ 1999, 69.

  4. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50:24.

  5. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88:7.

  6. ጆርጅኪው. ካነን, in Preparing to Enter the Holy Temple (booklet, 2002), 36.

  7. ሞዛያ 3:19.

  8. ዲ. ቶድክርስቶፈርሰን, “The Moral Force of Women,” Ensign or Liahona,ህዳር 2013, 30.

  9. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 4:2.

  10. “ህያው ክርስቶስ፥የሐዋሪያት ምስክርነት፣” Ensign or Liahona,ሚያዝያ 2000, 2.