መፅሐፉ
የቤተሰብ ታሪክ እና የቤተ መቅደስ ስራን የሁለም የግል አምልኮዋችን አካል መሆን አለባቸው።
የ12 ወጣት ስካውት ሳለሁ፣ በጣም እፈልገው የነበረውን የስካውት መሳርያዎቼ ላይ ተጨማሪ ስጦታል ተቀበልኩ። በጠንካራ የቆዳ ሽፋን የተሸፈነ መጥረቢያ ነበር። በሚቀጥለው የለሊት ሙሉ ጋራ መውጣት ላይ ከመሸ ነበር ካምፑ ጋር የደረስነው፣ ተከታታይ ባለው ጠንካራ እስኖ ረጥበን እና ቀዝቅዞን ነበር፣ የማስበው ሁሉ ነገር ቢኖር በትልቁ እሳት ማቀታጠልን ነበር ፣ በምቆርጥበት ጊዜ በጣም አናዳጅ ነበር ምክንያቱም በደንብ እየቆረጠ አይመስልም ነበር። በመናደዴ ውስጥ፣ ጠንክሬ ሰራሁ። ወደ ካምፑ ትንሽ የእንጨት ስባሪዎችን ይዤ ተመለስኩኝ። በሌላ ሰው እሳት አማካኝነት ችግሩን አገኘሁት። ከመጥረቢያው ላይ ያለውን የቆዳ ሽፋን አላነሳሁትም ነበር። ሪፖርት ማረግ እችላለሁ፣ ቢሆንም ፣ በመጥረቢያ ላይ ያለው የቆዳ ሽፋን ተቀዳዶ ነበር። የመቁረጥ ትኩረቴ ላይ፣ በሌሎች አሳሳቢ ነገሮች ትኩረቴን አጣሁ።
ወደ ዘላለማዊ ክብር ስንሰራ፣ በተጠየቁ ነገሮችላይ መስራት አለብን እናም በ አንድ ወይም በሁለት የታዘዝነው ነገር ላይ በማተኮር ወይም በማይገናኝ ነገሮች ላይ ሃሳባችንን ማጣት የለብንም። የእግዚአብሔርን መንግስት መሻት ወደ ሀሴት እና ደስታ ይመራል።1 ካስፈለገ፣ ለመለወጥ ፍቃደኞች መሆን አለብን። ከትላልቅ የሕይወታችን ስህተቶችን ማስተካከል የበለጠ የዘወትር ትናንሽ ስህተትን ማስተካከል አናሳ ህመም አላቸው ።
ብዙ ጊዜም አይደለም፣ እህት ፓከር እና እኔ የተወሰኑ የውጪ ሃገራት ላይ ተግዋዥን። ፓስፖርታችንን እና ሌላ ሰነዶችን አዘጋጀን። ሁሉንም አይነት መርፌዎችን ተወጋን፣ የጤና ፈተና፣ ቪዛ እና ማህተም አገኘን። መድረሻችን ላይ ሰነዶቻችን ሁሉ ተፈትሸው ነበር፣ ሁሉም የተተበከብን ነገሮች ሲሟሉ እንድንገባ ተፈቀደልን።
የሰማይን ክብር ለመውረስ ብቁ መሆን ሌላ ሀገር ለመግባት እንዳለው ዝግጅት ነው። ሁላችንም የራሳችንን መንፈሳዊ ፓስፖርት መያዝ አለብን። መስፈርቶቹን እና አይደለንም የምናወጣው፣ ነገር ግን፣ በግላችን፣ ሁሉንም ሟሟላት አለብን። የመዳን እቅድ ሁሉንም ትምህርት፣ ሕግጋት፣ትእዛዛት እና ለሰማይ ክብርብቁ ለመሆንየሚያስፈልጉትን ስርዓቶች ይዟል።2 ከዚያም፣ “በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ፣ የሰው ዘር በሙሉ ይድናል።”3 ቤተክርስቲያኗ ታግዘናለች ነገር ግን የኛን ፋንታ ለእኛ አታደርግልንም። ለሰማይ ክብር ብቁ መሆን በሕይወታችን ውስጥ ለማሳካት የምንጠረው ግብ ይሆናል።
ክርስቶስእኛን ለመርዳት ቤተክርስቲያኑን አቋቋመ። ቤተክርስቲያኑን እና ስዎቹን ለመምራት እንደ ነብያት፣ ትንቢት ተናጋሪ እና ገላጮች የምንደግፋቸውን 15 ወንዶች ሰዎችን ጠርቷል። የመጀመያ አመራር 4እና የአስራ ሁለቱ ጉባኤ አባላት5 በቤተክርስትያኑ ፕሬሰደንት አሰራር መሰረት በእድሜ ከሚበልጡት ሐዋርያት ጋር እኩል ኃይል እና ስልጣን 6አላቸው። ሰባዎቹ ደግሞ እንዲያግዙ ተጠሩ።7 መሪዎቹ የሰማይን ክብር የመውረስ መስፈርቶችን አላወጡም። እግዚያብሄር ነው ያወጣው! እነኚህ መሪዎች የተጠሩት ለማስተማር፣ ለማብራራት፣ ለማሳሰብ እና እንዲሁም በትክክለኛው የሕይወት ጎዳና ላይ እንድንቆይ 8እንዲያስጠነቅቁን ነው።
በቤተክርስቲያን የመመሪያ መፅሐፍ ላይ እንደተብራራው፥ “ግለሰብን እና ቤተሰብን ለሰማያዊ ክብር ብቁ እንዲሆኑ ለመርዳት ባለው አላማ ውስጥ ቤተክርስቲያኗ መለኮታዊ የተሾሙ ኃላፊነቶች ላይ ታተኩራለች። ይህ አባሎችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዲኖሩ መርዳትን፣ እስራኤልን በምስዮናውያን ስራ አማካኝነት መሰብሰብን፣ ለአጡ እና ለሚያስፈልጋቸው እንክብካቤን እና ቤተመቅደሶችን በመገንባት እና የውክልና ሥርዓቶችን በመፈጸም የሞቱትን መዳን እንዲችሉ ማድረግን ያጠቃልላል።”9 እነዚህ አራት ትኩረቶች እና ሁሉም ህግጋት፣ ትእዛዛት፣ እና ስርዓቶች አስፈላጊ ናቸው። በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ነ ኧነዚህን ነገሮች በማድረግ፣ በመንፈስ ፓስፖርታችን ላይ አስፈላጊ የሆኑ ማህተሞችን እያደረግን ነን።
በዚህ ጉባዬ ጊዜ ሁላችንንም የተሻለ ዝግጁ እንድንሆን ስለሚረዱን ፈተናዎች አየተምረናል።
ቤተሰብ የመዳን እቅድ ወይም “ታላቁ የደስታ እቅድ” 10የሚባለው ማዕከላዊ ሚና አለው እንዲሁም የመዳን እቅድ መኖር ምክንያት ነው። ፕሬዘዳንት ፓከር እንዲህ አሉ “በቤተክርስቲያን ውስጥ የሁሉም እንቅስቃሴ ታላቁ አላማ ባል እና ሚስት እንዲሁም ልጆች በቤት ውስጥ ደስተኛ መሆን ይችላሉ ።”11
ፕሬሰዳንት ስፔንሰር ደብሊው. ኪምቦል “ውጤታማነታችን፣ በግልም ሆነ እንደ ቤተክርስቲያን፣ በትልቁ የሚወሰነው የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በቤታችን ውስጥ በምን አይነት ታማኝነት እንደምናተኩር ነው።”12 የበተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ሥራ ወንጌልን ቤት ውስጥ የመኖር አካል ነው። ከቤተክርስቲያን እንቅስቃሴዎች በበለጠ መልኩ የቤተሰብ እንቅስቃሴ መኖር አለበት።
በመጀመሪያው አመራር እና በአስራ ሁለቱ ጉባኤ አባላት በቤተሰብ ታሪክ እና በቤተመቅደስ ስራ ላይ የታደሰ አፅእኖቶች አሉ።13 ለእነዚህ አፅእኖቶች የምሰጡት መልስ የግል እና የበተሰባችሁን ሐሰት እና ደስታ ይጨምርላችኋል።
ከትምህርትና ቃል ኪዳን ላይ፥ “የጌታ ታላቅዋ ቀን ደርሳለች.... እንደ ቤተክርስቲያ እና እንደ ሕዝብ እናም እንደ የኋለኛው ቀን ቁዱሳን፣ በፃድቅመሰዋት ለጌታ መስዋዕት እናቅርብለት፤ በእሱ ቅዱስ ቤተመቅደስ ውስጥ አናምጣለት፣..... የሙታናችንን ስም የያዘ መዝገብ፣ ተቀባይነት ያለው።” 14
ይህ መፅሐፍ የቤተክርስቲያኑ ውስጥ ያሉትን FamilyTree database መዝገቦች በመጠቀም ይዘጋጃል።
ይህንን መዝገብ እያጣራሁ እና መዝገቦችን ወደ ዳታበዝ እየጨመርኩኝ ነው ምክንያቱም የምወዳቸውን ሰዎች ስሞች እዚህ መፅሐፍ ላይ እንዲሆን እፈልጋለሁ። እናንተስ ትፈልጋላችሁ?
በትምህርትና ቃል ኪዳን ክፍል 128 ውስጥ እንዲህ እናነባለን “እኛ ያለ ቅድመ አያቶቻችን ፍፁም ተደርገን መሰራት አንችልም፤ እነሱም ካለኛ ፍፁም ተደርገው መሰራት አይችሉም።”15
የቤተሰብ ታሪክ ከዘር ግንድ፣ ህግጋት፣ ስሞች፣ ዳታዎች፣ እና ቦታዎች የበለጠ ነገር ነው። ካለፈ ነገር ላይ ከማተኮር የበለጠ ነው። የቤተሰብ ታሪክ የራሳችንን የአሁን ታሪክ መፍጠርን ያጠቃልላል። በእኛ ተወላጆች አማካኝነት የወደ ፊት ታሪክን ቅርፅ ስናስይዝ ያለውን የወደፊቱንም ያጠቃልላል። አንድ ወጣት እናት፣ ለምሳሌ፣ የበተሰቧን ታሪኮች እና ፎቶዎች ለልጆችዋ ስታካፍል የቤተሰብ ታሪክ ሥራ እየሰራች ነው።
ቅዱስ ቁርባንን መካፈል፣ ስብሰባዎችን መካፈል፣ ቅዱሳን መፅሃፍትን ማንበብን እናም የግል ፀሎት፣ የቤተሰብ ታሪክ እና የቤተ መቅደስ ስራን የመሳሰሉ ነገሮች የሁለም የግል አምልኮዋችን አካል መሆን አለባቸው። የወጣቱ እና የሌሎች ለትንብታዊው ግብዣ መልስ የሚያነሳሳ እና ይህ ሥራ መሰራት እንደሚችል እና በየትኛውም እድሜ ላይ ባሉ ሁለም አባላት መሰራት እንዳለበት የሚያረጋግጥ ነው።
ሽማግሌ ኩኢንቲን እንዳብራራው፣ “አሁን ትምህርቱ፣ ቤተመቅደሶች እና ቴክኖሎጂው አለን።” 16የቤተሰብ ታሪክ ሥራ አሁን ቀላል እና የተወሰነው ቅድሚያ በሚሰጡት አባላት ቁጥር ብቻ ነው። ስራው አሁንም ጊዜን እና መሰዋእትን ይጠይቃል፣ ነገር ግን ሁሉም ማድረግ ይችላል፣ ከጥቂት አመታት በፊት ከነበረው በቀላሉ ይዛመዳል።
አባሎችን ለመርዳት፣ አብዛኛውን ስራ በራሳችን ቤቶች ውስጥ ወይም በዋርዳችሁ ህንፃዎች እና ቤተመቅደስ ውስጥ መሰራት እንዲችል ቤተክስቲያኗ መዝገቦችን እና መሳሪያዎችን አብስባለች። አብዛኛዎቹ መሰናክሎች ተወግደዋል። ባለፉት ጊዜያትስለ ቤተሰብ ታሪክ ምንም አይነት አስተሳሰብ ኖሯችሁ ቢሆንም አሁን የተለየ ነው።
ይሁን እንጂ ፣ ቤተክርስቲያኗ ማስወገድ የማትችለው መሰናክል አለ። ይህንን ሥራ ለማድረግ የእያንድንዱ ግለሰብ መሰላቸት ነው። የሚጠበቀው ውሳኔ እና ጥቂት ጥረት ብቻ ነው። ሰፋ ያለ ግዜን አይጠይቅም። ተከታታይነት ያለው መደበኛ ትንሽ ጊዜ ከስራው ጋር ተያያዥነት ያለውን በረከት ያመጣል። ሌሎች እንዲረዷችሁ ለመጠየቅ እና እንድትማሩ፣ አንድ ደረጃ ለመራመድ ውሳኔ ስጡ። ይረዷችኋል! የምታገኗቸው እና ወደ ቤተ መቅደስ የምትወስዷቸው ስሞች “ለመፅሐፉ” 17መዝገብ ይሆናሉ።
ከአስገራሚ የአባሎች ተሳትፎ መጨመር ጋር፣ ጥቂት የቤተክርስቲያንአባሎች በቋሚነት እየፈለጉ እና ለቤተሰቦቻቸው የቤተ መቅደስ ሥርዓቶችን አያደረጉ እናገናችዋለን። 18 ቅድሚያ በምንሰጠው ውስጥ ይህ ሁኔታ ለውጥን ይጠይቃል። ለውጡን አትጣሉት፣ ተቀበሉት እና ተከተሉ! ለውጥ የታላቁ የደስታ እቅድ አካል ነው።
ይህ ስራ መሰራት አለበት። ለቤተክርስቲያኑ ጥቅም ሳይሆን ለሞቱብን እና ለራሳችን ነው። እኛ እና በቅርብ የሞቱ ዘሮቻችን በመንፈሳዊ ፓስፖርታችን ላይ ማህተብ ያስፈልገናል።
ትውልድን ተሻግሮ ያለውን የነተቤሰቦቻቸው “አንድነት” 19በቤተ መቅደስ ውስጥ ብቻ ነው ሚድነው። ደረጃዎቹ ቀላል ናቸው ፤ ስም ፈልጉ እና ወደ ቤተ መቅደስ ይዛቹሁ ሂዱ።. ከግዜ በኋላ አናንተም ሌሎችን መርዳት ትችላላችሁ።
በትንሽ ባልተለመዱ ሁኔታዎች ፣ ሁሉም ሰው ይሄን ማድረግ ይችላል!
ከዚህ ሥራ ጋር የተያያዙ የሚታዩ በረከቶች አሉ። ብዙ ወላጆች እና መሪዎች አሁን ያለው የዓለም ሁኔታ እና የቤተሰቦች እና ወጣቶች ላይ ያለው ተፅዕኖ አሳስቦዋቸዋል።
ሽማግሌ ቤድናር ቃል ገብቷል፥ “በቤተክርስቲያን ውስጥ ያላችሁትን ወጣቶች ስለ የኤልያስ መንፈስ ልምድ እንድትማሩ አጋብዛችኋለሁ......... ከጠነከረ የጠላት ተፅዕኖ እንደምትጠበቁ ቃል እገባላችኋለሁ። የሱን ቅዱስ ሥራ ስትለማመዱ እና ስትወዱት፣ በወጣትነታችሁ ውስጥ እና እድሜያችሁን በሙሉ ከአደጋ ትጠበቃላችሁ።”20
ወንድም እና እህቶች፣ የመጥረብያችንን ሽፋን አንስተን ወደ ሥራ የመሄጃ ሰዓት ነው። በጣም ለአነሱ ፍላጎቶች ብለን የራሳችንን እና የበተሰቦቻችንን የሰማይ ክብር መስዋት ማድረግ የለብንም።
ይህ በአባላት እና አባላት ባልሆኑት፣ በወጣቶች እና በሽማግሌዎች፣ በወንዶችና በሴቶች የሚሰራ የእግዚአብሔር ስራ ነው።
አንዱን ቃል በመቀየር የመዝሙር 324ን ቃላት በመጥቀስ ንግግሬን እፈጽማለሁ።
ኢየሱስ ንጉስ ነው! ስለእርሱ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን