ከዚህ በፊት በማይታወቅ ሁኔታ የተዘጋጀች
የሚያድኑ ስነ-ስርዓቶችን ለመቀበል እና ከነዚህ ጋር የተያያዙትን ቃል ኪዳኖች በሙሉ ልብ ለመጠበቅ ብቁ ለመሆን እንዘጋጅ።
ከልጆቻችን ታናሿ ከትምህርት ቤት የመጀመሪያውን ቀን ፈጽማ ወደ ቤት ስትመለስ፣ “እንዴት ነበር?” ብዬ ጠየኳት።
እርሷም “መልካም ነበር” ብላ መለሰች።
በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ግን፣ ወደ ት/ቤት እንድትሄድ ሳስነሳት፣ እጆቿን አጥፋ እና በእርግጠኛነት “ት/ቤት ሄጄ ነበር” አለች። ት/ቤት መሄድ የአንድ ጊዜ ብቻ ድርጊት እንዳልሆነ እና ለብዙ አመቶች ወደ ት/ቤት በሳምንት ለአምስት ቀናት መሄድ እንዳለባት እንድታውቅ አላዘጋጀኋትም እናም አልገለጽኩላትም ነበር።
የመዘጋጀትን መሰረታዊ መርህ ስናስብበት፣ ከእኔ ጋር ይህን ትዕይንት በአዕምሮዋችሁ ተመልከቱ። እናንተ በቤተመቅደስ በሰለስቲያል ክፍል ውስጥ ተቀምጣችኋል እናም የተለያዩ ወንድና ሴት ሙሽራዎች ለጊዜ እና ለዘለአለም ለመተሳሰር በጸጥታ ሲገቡና ሲወጡ ተመለከታችሁ። አንድ ሙሽራ ከምታገባው ጋር እጅ በእጅ ተያይዛ ገባችው። የለበሰችው ቆንጆ የሆነ የቤተመቅደስ ቀሚስና የተረጋጋ፣ ሰላም የሚታይበት ፣ እና የሞቀ አመለካከት ያልው ፊት ነው። ተዘጋጅታለች፣ ነገር ግን ትኩረቷ የተሳበባት አይደለችም። ተቀመጠች፣ ወደዚህና ወደዚያ ዞረች፣ እናም በድንገትም በስሜት ተሸነፈች። እምባዎቿ የመጡት ለነበረችበት ቦታ እና እርሷንና የህይወት ፍቅሯን ለሚጠብቀው ቅዱስ ስርዓት ድንቀት እና ክብር ስለነበራት ነው። አመለካከቷም፣ “ዛሬ በጌታ ቤት ውስጥ በመገኘት፣ ከዘለአለማዊ ጓደኛዬ ጋር ጋር የዘለአለም ጉዞዬን ለመጀመር በመዘጋጀቴ ምን ያህል ምስጋና ይሰማኛል” የሚል ይመስላል። እርሷም ለድርጊት በላይ ለሆነ የተዘጋጀት ትመስል ነበር።
በቅርብ ጊዜ ውዷ የልጅ ልጃችን በትራሴ ላይ “ወደ ቤተ-መቅደስ ውስጥ ስገባ የሚያስደንቀኝ አንድ ነገር ቢኖር፣ በዚያ ውስጥ የሚገኘው ሰላማዊ፣ አፍቃሪ መንፈስ ነው።...ሰዎች ወደ ቤተ-መቅደስ ሄደው መነሳሻን ለመቀበል ይችላሉ” የሚል መልእክት ትታልኝ ነበር።1 ትክክል ነች። በቤተ-መቅደስ ውስጥ መነሳሻን እና ራዕይን ለመቀበል–እናም የህይወት ፈተናዎችን የመቋቋም ሀይልን እናገኛለን። የቤተሰቧን ስም ለመጠመቅ እና ለመረጋገጥ በተደጋጋሚ በመሄድ ስለቤተመቅደስ ስትማር የቤተመቅደስ ስርዓቶችን፣ ቃል ኪዳኖችን፣ እና በረከቶችን ለእራሷ እና ከመጋረጃው በኋላ ለሚገኙት ሌሎች ለመቀበል ትዘጋጃለች።
ሽማግሌ ራስል ኤም ኔልሰን እንዳስተማሩት፣ “ቤተመቅደሶች ለሰዎች እንደተዘጋጁ፣ ሰዎችም ለቤተመቅደስ እራሳቸውን ማዘጋጀት ይገባቸዋል።”2
ስለሻምበል ሞሮኒ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ እንደገና ሳነብም፣ የሞሮኒ ታላቁ ድርጊት ቢኖር ኔፋውያንን የሚያስፈሩትን የላማናውያንን ወታደሮች ለመቋቋም በጥንቃቄ ማዘጋጀቱ ነው። ህዝቡን በደንብ አዘጋጅቶ፣ “በከፍተኛ ሁኔታ [ላማናውያን] እስከሚገርማቸው ድረስ ... ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ [ኔፋውያን]ተዘጋጅተው ነበር” የሚለውን እናነባለን።3
“ታይቶበማይታወቅ ሁኔታ ተዘጋጅተው ነበር” የሚለው አንቀጽ ትኩረቴን ያዘው።
ለቅዱስ ቤተ-መቅደስ በረከት እንዴት በተሻለ መንገድ ለመዘጋጀት እንችላለን? ጌታ እንዳስተማረው፣ “እና ደግሞም፣ እንዳትታለሉም ለሁሉም ነገሮች ንድፍን እሰጣችኋለሁ፤ ሰይጣን በምድር ላይ አለና፣ እና አገሮችን እያሳታቸውም ይሄዳል።”4 የቅዱሳት መጻህፍት ንድፎች እናስብባቸው። ሞሮኒ ለጠላቶቹ የተዘጋጀበት የተደጋገመ እና ትጋታዊ እምነት አስፈልጎት ነበር፣ እናም በቤታችን ውስጥ ልንጠቀምባቸው ስንጥር እነዚህ ንድፎችም አንድ አይነት ጥረት ያስፈልጋቸዋል።
ስለአምስቱ ልባሞች እና አምስቱ ሰነፎች አዳኝ ስለነገረው አስደሳች ተረች ለማዳመጥ የሚያስደክመኝ አይደለም። ይህም ተረት ለዳግም ምፅዓት ስለመዘጋጀት የሚያስተምር ቢሆንም፣ እኛም ለተዘጋጁት የመነፈሳዊ ምግብ የሚሆነውን የቤተመቅደስ በረከቶች ለመቀበል ከመዘጋጀት ጋር ልናመሳስለው እንችላለን።
በማቴዎስ 25 ውስጥ እንደምናነበው፥
“በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።
“ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ።…
“ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ።
“ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።
“እኩል ሌሊትም ሲሆን። እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።
“በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ።
“ሰነፎቹም ልባሞቹን። መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን አሉአቸው።
“ልባሞቹ ግን መልሰው። ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ አሉአቸው።
“ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ፥ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ፥ ደጁም ተዘጋ።
“በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና። ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን አሉ።
“እርሱ ግን መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም አለ።”5
ለሞኞቹ ወጣት ሴቶች የማያዝኑ ማንም የሉም። አንዳንዳችን ለሌሎቹ ወጣት ሴቶች እንዲህ ለማለት እንፈልጋለን፥ “ሁሉም ደስተኛ እንዲሆኑ ለመካፈል አትችሉምን?” ነገር ግን አስቡበት። ይህ አዳኝ የተናገረው ታሪክ ነውም እናም አምስቱን “ልባሞች” እና አምስቱን “ሞኞች” ብሎ የጠራቸው ።
ይህን ምሳሌ ለቤተመቅደስ እንደ መዘጋጀት ንድፍ ስናስብበት፣ “የመንፈስ መዘጋጀት ዘይት ለመካፈል አይቻልም” ተብሎ የኋለኛው ቀን ነቢይ ያስተማሩትን ቃላት እናስብበት።6 ፕሬዘደንት ኪምባል ለምን “ልባሞቹ” አምስት ወጣት ሴቶች “ከሞኞቹ” ጋር ዘይታቸን ለመካፈል እንዳልቻሉ ለመግለጽ በመርዳእንዲህ አሉ፣ “በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ መሳተፍ ጠብ በጠብ ለመብራታችን ዘይት እንጨምራለን። መጾም፣ የቤተሰብ ጸሎት፣ የቤት ለቤት ማስተማር፣ የሰውነት ፍላጎቶችን መቆጣጠር፣ ወንጌልን መስበክ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን ማጥናት፣ እነዚህ እያንዳንዱ የመለኮታዊነት እና የታዛዥነት ስራዎች ለምናጠራቅመድ የዘይት ጠብ የምንጨምርባቸው ናቸው። የደግነት ስራ፣ አስራት መክፈል፣ ንጹህ ሀሳብ እና ስራ…እነዚህም በአስፈላጊነት በለሊት የሚያስፈልገንን የመብራታችን ዘይትን ይጨምሩልናል።”7
ቅዱስ ስርዓትን ለራሳችሁና ለሌሎች ለመቀበል ለመዘጋጅት የሚረዳንን የመዘጋጃ ንድፍ ታያላችሁን? በውድ የመንፈስ ዘይታችን ውስጥ ተጨማሪ ለማስገባት ምን ሌሎች ትትንሽ ነገሮች ለማድረግ እንችላለን?
ከሽማግሌ ሪቻርድ ጂ ስካት እንደተማርነው፣ “የቤተመቅደስ በረከቶችን ለመደሰት የቅል ብዉነት አስፈላጊ ነው። …ብቁ የሆኑ ጸባዮች በተደጋጋሚ፣ በምምህርት ትምህርት በሚመኩ መልካም ምርጫዎች የተሰሩ ናቸው።”8 ተደጋጋሚ የሚለውን ቃላት እወዳለሁ። በተደጋጋሚ ለመስራት፣ ፅኑ፣ የምይለወጥ፣ እና ለመመካት የሚችል መሆን አለበት። ምን አይነት ታላቅ የብቁነት መርሆ መግለጫ ነው።
በመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “በቅድስና ቤት ብቻ ነው ከቤተመቅደስ ጋር ለመነጻጸር የሚችለው”9 በማለት እንድናስታውስ አድርጎናል።ቤታችን ወይም የምንከራያቸው ቤቶች የዚህ መግለጫዎች ናቸውን? በቅርብ ግዜ ከዎርዳችን አንዷ ውድ ወጣት ሴት ወደ ቤታችን መጣች። ወንድሟ ከሚስዮን በቅርብ እንደተመለሰ በማወቅ፣ በቤት እርሱን ማግኘቷ እንዴት እንደሚሰማት ጠየኳት። እርሷም በጣም ጥሩ ነው አለች፣ ነገር ግን ሙዚቃው ለመቀነስ እንደሚችል አንዳንዴ ይጠይቃል አለች። እንዲህም አለች፣ “መጥፎ ሙዚቃም አልነበረም!” ራሳችንን አሁን መመዘን እና ቤታችን የመንፈስ ስሜት እንዲሰማን የምንዘጋጅበት እንዲሆን ማረጋገጥም ይገባናል። ቤታችን መንፈስ እንዲገባበት የምንቀበልበት ቦታ በማድረግ ስናዘጋጅ፣ ወደ ጌታ ቤት ስንገባ “እንደ ቤት” ውስጥ እንዳለን እንዲሰማን እንዘጋጃለን።
ወደ ቤተ-መቅደስ ውስጥ ለመግባት እራሳችንን በብቁነት ስናዘጋጅ እና ለቤተ-መቅደስ ቃል ኪዳኖች ታማኝ ስንሆን፣ ጌታ “የተባዙ በረከቶችን” ይሰጠናል።10 ጥሩ ጓደኛዬ ቧኒ ኦስካርሰን በቅርብ ጊዜ እንዲ ስትል የቅዱስ መጻህፍትን ቃላት ቀይራ ነበር፣ “ብዙ በሚጠበቅበት፣ ብዙ ይሰጣል።”11 በዚህ አስተያየት በጣም እስማማለሁ። ወደ ቤተ-መቅደስ የምንመጣው ዘለአለማዊ በረከቶችን ለመቀበል ስለሆነ፣ ለእነዚያ በረከቶች ከፍተኛ የሆኑ መለኪያ እንደሚኖራቸው ሊገርመን አይገባም። ሽማግሌ ኔልሰን እንዳስተማሩት፣ “ቤተ-መቅደስ የጌታ ቤት ስለሆነ፣ የመግቢያ መለኪያ በእርሱ ይቀመጣል። ሰው የሚገባው እንደ እንግዳው ነው። የቤተ-መቅደስ መግቢያ ፈቃድ መያዝ ዋጋው ታላቅ የሆነ ነው እናም ይህም ለእግዚአብሔር እና ለነብያቱ ታዛዥ የመሆን ምልክት ነው።”12
በአለም ታዋቂ አትሌቶች እና የዩንቨርስቲ የዶክተርነት ተማሪዎች ለብዙ ጊዜ ይዘጋጃሉ። እንደዚህም፣ በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ለዘለአለማዊነት ብቁ ለመሆን የሚፈልጉትም የታዛዥነት ምግባርን በየቀኑ በመከተል ከፍተኛ በሆነ የታዛዥነት መለኪያ እንዲኖሩም ይጠበቅባቸዋል።
በተደጋጋሚ እና በትጋት ዘይትን ጠብ በጠብ ወደ መንፈሳዊ ብርሀናችን ስናስገባ፣ እነዚህን ቀላል እና ትትንሽ ነገሮች በማድረግ በሚያስደንቅ መዘጋጃ “ብርሀናችን እንዲበራ” ለማድረግ እንችላለን።13 የካስማ ፕሬዘደንት የሆነው ባለቤቴ በቅርብ ሰው የተዘጋጀ እንደሆነ እና ወደ ቤተመቅደስ ለመግባት ብቁ እንደሆነ ለማወቅ የሚችለው፣ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ለማግኘት ሲመጡ “ክፍሉን እንደ ብርሀን ስለሚያበሩ” ነው ብሏል።
በከርትላንድ ቤተ-መቅደስ መክፈቻ ጸሎት ውስጥ፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ጌታን “በጌታ ቤት መግቢያ በር ላይ የሚገቡት ህዝብ ሁሉ ሀይልህ እንዲሰማቸው፣ ...በአንተም እንዲያድጉ፣ እና የመንፈስ ቅዱስን ሙላት እንዲቀበሉ፣ እና አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ ለመቀበል [እንዲዘጋጁም]” ጠየቀ።14
ለእኛ ወደ ቤተ-መቅደስ መሄድ ከአንድ ጊዜ ድርጊት ከመሆን በላይ እንዲሆንልን እጸልያለሁ።፡የሚያድኑ ስነ-ስርዓቶችን ለመቀበል እና ከነዚህ ጋር የተያያዙትን ቃል ኪዳኖች በሙሉ ልብ ለመጠበቅ ብቁ ለመሆን እንዘጋጅ። ይህን ስናደርግ፣ የመንፈስ ቅዱስ ሙሉነትን እና የጌታን ሀይል በቤቶቻችን እና በግለሰብ ህይወታችን ውስጥ ለመቀበል ብቁ እንሆናለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።