ቅዱስ ነገሮችን በከንቱ አታሳልፉ
ምርጫችሁን ስታስቡባቸው፣ “ውሳኔዎቼ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ላይ በጥብቅ የተተከሉ ናቸውን?” በማለት እራሳችሁን ጠይቁ።
ወንድሞችና እህቶች፣ በዚህ ህይወት የምናደርጋቸው ውሳኔዎች የዘለአለም ህይወታችን ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አላቸው። በምርጫዎቻችን ላይ ተፅዕኖ ያላቸው የሚታዩ እና የማይታዩ ሀይሎች አሉ። ይህንንም ነጥብ ከአምስት አመት በፊት ታላቅ ዋጋ እንድከፍል አድርጎኝ ሊችል በነበረው ነገር ተምሬአለሁ።
በደቦብ ኦመን ከቤተሰብ እና ጓደኞች ጋር አብረን እንጓዝ ነበር። በህንድ ባህር ዳርቻ ለመሸራሸር ወሰንን። እንደደረስን ወዲያውም፣ የ16 አመቷ ልጃችን ኔሊ በባህር ዳር አሸዋ እንደሆነ ወደመሰላት ነገር በመዋኘት ለመሄድ ጠየቀች። ውሀው በጣም እንደሚወዛወዝ ስላየሁ፣ አደገኛ ውሀ ነው ብዬ በማሰብ፣ እኔ በመጀመሪያ እሄዳለሁ አልኳትኝ።
ለአጭር ጊዜ ከዋኘሁኝ በኋላ፣ ባለቤቴን ጠራኋት እና ወደ ባህር ዳር አሸዋው ቅርብ እንደሆንኩኝ ጠየኳት። መልሷም፣ “አልፈኸው ሄደሀል” የሚል ነበር። እኔ ሳላውቀው ከባህር ዳሩ እየገፋኝ በሚሄድ ነፋስ1 ተገፍቼ ነበር እናም ወደ ባህሩ እየተገፋው ሄጄ ነበር።
ምን ማድረግ እንደሚገባኝ አላወኩም ነበር። ለማድረግ የማስብበት ነገር ቢኖር መመለስ እና ወደ ባህር ዳሩ ለመድረስ መዋኘት ብቻ ነበር።ያም መደረግ የማይገባበት ነገር ነበር። እርዳታ የለሽነት ተሰማኝ። እኔ ለመቆጣጠር ከማልችለው በላይ የሆነ ሀይል ወደ ባህሩ መሀከል እየጎተተኝ ነበር። ከዚህ በላይ መጥፎ የነበረውም፣ ባለቤቴ የእኔን ውሳኔ አምና ተከትላኝ ነበር።
ወንድሞችና እህቶች፣ እኔ እንደማልድን ትልቅ እድል እንዳለኝ እና በእኔ ውሳኔ ምክንያት የባለቤቴን ሞት እንዳመጣሁተሰምቶኝ ነበር። በታላቅ ጥረት እና መለኮታዊ እርዳታ ነው ብዬ በማስበው ሁኔታ፣ እግራችን ከበታች የሚገኘውን አሸዋ ነካ እናም በደህንነት ወደ ጓደኞቻችን እና ሴት ልጃችን በእግር በመራመድ ለመመለስ ቻልን።
በዚህ ህይወት ሞገዶች አሉ–አንዳንዶቹ ደህና የሆኑ ሌሎቹም ያልሆኑ ናቸው። ፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምባል እንዳስተማሩን በህይወታችን ውስጥ በባህር ላይ እንዳሉ ነፋሶች አይነት ሀይለኛ የሆኑ ነገሮች አሉ።2 እነዚህ ሀይሎች እውነተኛ ናቸው።2 እነርሱን ችላ ማለት አይገባንም።
ስለሌላ ሞገድ፣ በህይወቴ ታላቅ በረከት ስለሆነው መለኮታዊ ሞገድ፣ ልንገራችሁ። እኔ ወደቤተክርስቲያኗ የተቀየርኩኝ ነኝ። ከመቀየሬ በፊት፣ የህይወቴ አላማ በበረዶ ለመንሸራተት ነበር፣ እናም ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በኋላ ይህን አላማ ለማሟላት ወደ አውሮፓ ሄድኩኝ። መልካም በሚመስል ህይወት ለትንሽ ወር ካሳለፍኩኝ በኋላ፣ መሄድ እንደሚገባኝ ስሜት መጣልኝ። በዚያ ጊዜ የስሜቱ ምንጭ ምን እንደነበር አላወቅኩም ነበር፣ ነገር ግን ይህን ለመከተል መረጥኩኝ። ልክ እንደ እኔ የሌላ ሀይማኖት አባላት ከነበሩት ጓደኞቼ ጋር ወደ ፕሮቮ ዮታ መጣሁ።
በፕሮቮ እያለሁ፣ ከእኔ የተለየ ህይወት የሚኖሩ ሰዎች ጋር ተገናኘሁ። ለምን እንደሆነ ባላውቀውም፣ ወደ እነርሱ የሚያቀርብ ስሜት ነበረኝ። እነዚህን ስሜት ለመቋቋም ጣርኩኝ፣ ነገር ግን ወዲያው ኖሮኝ የማላውቀው ሰላም እና ምቾት ተሰማኝ። ልዩ የሆነውን ሞገድ መቀበል ጀመርኩኝ–ይህም የሚያፈቅር የሰማይ አባት እና የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ መረጃን ያመጣልኝ ነበር።
ከጓደኞቼ ጋር በ1972 (እ.አ.አ) ተጠመቅኩኝ። ለመከተል የመረጥኩት ይህ አዲስ ሞገድ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፣ ለህይወቴ አቅጣጫንና ትርጉምን ሰጠው።፡ነገር ግን፣ ፈተና ያልነበረው አልነበረም። ሁሉም ነገር ለእኔ አዲስ ነበር። በጊዜም የጠፋሁና የተምታታው መሰለኝ። በጓደኞቼና በቤተሰቦቼ ጥያቄዎች እና ፈተናዎች ቀረቡብኝ።
ምርጫ ማድረግ ነበረብኝ። አንዳንዱ ጥያቄዎቻቸው ጥርጣሬን እና እርግጠኛ አለመሆንን አመጡብኝ። ይህም ምርጫ አስፈላጊ ነበር። ለመልስ የት እሄዳለሁ? መንገዴ ስህተተኛ እንደሆነ ሊያሳምኑኝ የፈለጉ ብዙ ነበሩ–እነርሱም የአስደናቂ ደስታ ምንጭ ከሆነውሊጎትቱኝ ወስነው ነበር። “በሁሉም ነገሮች ተቃራኒ አለ” የሚለውን መርሆ እና ለራሴ የመስራትንና ነጻ ምርጫዬን ለሌሎች ያለመተው አስፈላጊነትን በደንብ ተምሬ ነበር።3
“ምን ያህል ከፍተኛ መፅናኛ ካመጣልኝ ለምን እዞራለሁ?” በማለት ራሴን ጠየኩኝ። ጌታ ኦሊቨር ካውደሪን እንዲያስታውስ እንዳደረገው፣ “ስለዚህ ጉዳይ በአዕምሮህ ሰላም አለተናገርኩልህምን?”4 አጋጣሚዬ እንደዚህ ነበር። ስለዚህ፣ በተጨማሪ የልብ ውሳኔ ወደ ሰማይ አባት፣ ወደ ቅዱሳን መጻህፍት፣ እና ወደምመካባቸው ጓደኞች ዞር አልኩኝ።
ቢሆንም፣ መልስ ልሰጣቸው የማልችል ብዙ ጥያቄዎች ነበሩ። የፈጠሩትን አለመረጋገጥ እንዴት መልስ ለመስጠት እችላለሁ? ወደ ህይወቴ የመጣውን ሰላም እና ደስታ እንዲያጠፉ ከመፍቀድ፣ በጌታ ጊዜ ሁሉንም ነገሮች እንደሚገልጽልኝ በማመን፣ እነዚህን ለጊዜ ወደጎን አስቀመጥኳቸው። ለነቢዩ ዮሴፍ ስሚዝ ባላቸው ሰላምን አግኝቻለሁ፥ “እነሆ፣ እናንተ ትትንሽ ልጆች ናችሁ እናም ሁሉንም ነገር አሁን ለመሸከም አትችሉም፤ በጸጋ እና በእውነት እውቀት ማደግ አለባችሁ።”5 የማይታወቀውን እና ጥያቄ ያለበትን ሞገድ በመተው፣ እውነት እንደሆነ የማውቀውን ላለመጣል ወሰንኩኝ። ኤን. ኤልደን ታነር እንዳሉት፣ “የወንጌልን እውነቶች ለመቀበል... እና የማይረዳውን እነዚያን ነገሮች በእምነት መቀበል ለሰው እንዴት ጥበበኛና የሚሻል እንደሆነ” ተማርኩኝ።6
ለእውነተኛ ጥያቄ ምንም ቦታ የለም ማለት ነው? የትኞቹን ቤተክርስቲያኖች አባል መሆን እንደሚገባው ለመጠየቅ ወደ ቅዱስ ጥሻ የተሸሸገውን ወጣት ልጅ ጠይቁት። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን በእጃችሁ ያዙ፣ እናም በዚህ በተነሳሳ መዝገብ ውስጥ፡የተገለጹት እውነት በትጋት ሚፈለግበት ምክንያት እንደሆነ እወቁ። ዮሴፍ እንዳገኘው፣ “ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ለእርሱም ይሰጠዋል።”7 ቅን የሆነ ጥያቄ በመጠየቅ እና መለኮታዊ መልሶችን በመፈለግ፣ እውቀታችንን እና ጥበባችንን በማሳደግ “በመስመር ላይ መስመር፣ በስርዐት ላይ ስርዐት”8 እንማራለን።
ጥያቄው “ለታማኝ እና ቅን ጥያቄ ቦታ አለ?” የሚል ሳይሆን፣ ነገር ግን “ጥያቄዎች ሲመጡ ወዴት እዞራለሁ?” የሚል ነው። “ጥያቄዎች ቢኖሩኝም የማውቀውን እውነት አጥብቆ ለመያዝ ጥበብ ይኖረኛልን?” ከመጨረሻው እስከ መጀመሪያው ሁሉን ነገሮች የሚያውቅ መለኮታዊ ምንጭ እንዳለ እመሰክራለሁ። ሁሉም ነገሮች በእርሱ ፊት ይገኛሉ።9 ቅዱሳት መጻህፍትም እንደሚመሰክሩት “እርሱ በተጣመመ መንገድ አይጓዝም...ወይም ካለውም አይለወጥም።”10
በዚህ ስጋዊ ጉዞ ምርጫችን እኛን ብቻ ይነካሉ ብላችሁ አታስቡ። በቅርብ ወጣት ሰው በቤቴ ጎበኘኝ። መልካም መንፈስ ነበረው፣ ነገር ግን በቤተክርስቲያኗ በሙሉ ተሳታፊ እንዳልሆነ ተሰማኝ። አባቱ ለእናቱ ታማኝነቱን እስካጣ እና ወላጆቹ እንደሚፋቱና ወንድሞቹና እህቶቹ ስለቤተክርስቲያኗ በመጠራጠር ተሳታፊነትን እስከሚያቆሙ ድረስ ወንጌል በሚገኝበት ቤት ውስጥ እንዳደገ ነገረኝ። በአባቱ ምርጫ ምክንያት ውድ የሆኑ ነፍሳትን ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በረከቶች ውጪ ከሚያሳድገው ወጣት አባት ጋር ሲነጋገር ልቤ ተነክቶ ነበር።
ሌላ የማውቀው፣ አማኝ የቤተክርስቲያኗ አባል የነበረ ሰው ስለአንድ ትምህርት ጥያቄዎች ነበሩት። የሰማይ አባትን መልስ እንዲሰጠው ሳይጠይቅ፣ በአለማዊ ምንጭ መልስ ለማግኘት ለመመካት መረጠ። የሰዎችን ክብር ሲፈልግ፣ ልቡ ትክክል ወዳልሆነው አቅጣጫ ዞረ። ለጊዜም ቢሆን ኩራቱ የሚያስረካ ነበር፣ ነገር ግን ከሰማይ ሀይል ተቆርጦ ነበር።11 እውነትን ሳያገኝ፣ ምስክርነቱን አጣ እና አብሮም ብዙዎቹን የቤተሰብ አባላቱን ይዞ ሄደ።
እነዚህ ኁለት ሰዎች በማይታየው ሞገድ ተያዙ እናም ብዙዎችን ይዘው ሄዱ።
በሌላም በኩል፣ በምድር ምንም ሀብት ባይኖራቸውም፣ በዳግም የተመለሰውን ንጹህ ትምህርት ለልጆቻቸው ከማስተማር በተጨማሪ ይህን በህይወታቸው ስለኖሩበት ስለባለቤቴ ወላጆች ስለ ላሩ እና ሉዊስ ሚለር አስባለሁ። ይህን በማድረግ ዘራቸውን በወንጌል ፍሬ እና በዘለአለማዊ ህይወት ተስፋ ባርከዋል።
በቤታቸው ክህነት የተከበረበት፣ ፍቅርና ስምምነት በብዛት የሚገኝበት፣ እና የወንጌል መርሆዎች ህይወታቸውን የሚመራበት ንድፍ መስርተው ነበር። ሉዊስ እና ላሩ ጎን በጎን በኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ መኖር ማለት ምን እንደሆነ አሳዩ። ልጆቻቸውም የትኛው የህይወት ሞገድ ደስታን እና ሰላምን እንደሚያመጣ በግልጽ አዩ። እናም እንደዚህም መረጡ። ፕሬዘደንት ኪምባል እንዳስተማሩት፣ “ጥንካራ፣ የማይነቃነቅ ሞገድ ወደ ጻድቅ ህይወት አላማችን እንዲሄድ ለማድረግ ከቻልን፣ እኛና ልጆቻችን የችግር፣ የተስፋ መቁረጥ፣ እና የፈተናዎችን ተቃራኒ ንፋስ በመቋቋም ወደፊት ልንገፋ እንችላለን።”12
ምርጫችን ትርጉም አላቸውን? እኛን ብቻ ነው የሚነኩት? ቤተሰባችንን ዳግም በተመለሰው ወንጌል ዘለአለማዊ ሞገድ ላይ አስገብተናቸዋልን?
ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ የሚያስደነግጠኝ የአዕምሮ ስዕል አለ። በዚያ በመስከረም ቀን፣ በህንድ ባህር ላይ እየተንሸራሸርን እያለን፣ ለሴት ልጄ ኔሊ፣ “አዎን፣ ሂጂ። ወደ ባህር ዳሩ አሸዋ በመዋኘት ሂጂ” ብላትስ ኖሮ። ወይም እኔን በምሳሌ ተከትላኝ ተመልሳ በመዋኘት ለመምጣት ባትችልስ ኖሮ? ምሳሌዬ በባህሩ ሞገድ ተጎትታ እንደገና እንዳትመለስ የሚያደርግ ውጤት በነበረበት ለመኖር እችል ነበርን?
ለመከተል የምንመርጣቸው ሞገዶች አስፈላጊ ናቸውን? ምሳሌ የምናቀርብባቸው ትርጉም አላቸውን?
የሰማይ አባት ምርጫችንን የሚመራልን የመንፈስ ቅዱስ ታላቅ ስጦታ ሰጥቶናል። እነዚህን ለመቀበል ብቁ ሆነን በምንኖርበት ጊዜም መነሳሻ እና ራዕይ ለመስጠት ቃል ገብቶልናል። ይህን መለኮታዊ ስጦታ እንድትጠቀሙበት እና ምርጫችሁን ስታስቡባቸው፣ “ውሳኔዎቼ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ላይ በጥብቅ የተተከሉ ናቸውን?” በማለት እራሳችሁን እንድትጠይቁ እጋብዛችኋለሁ። ትልቅም ይሁን ትንሽ፣ የሰማይ አባት የዘለአለም በረከቶች በአላማ ለእናንተ እና ለምታፈቅሯቸው ለማረጋገጥ ማስተካከል የሚያስፈልጋችሁን እንድታደርጉ እጋብዛችኋለሁ።
ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችን እና ቤዛችን እንደሆነ እመሰክራለሁ። ከእርሱ ጋር የምንሰራቸው ቃል ኪዳኖች ቅዱስ እንደሆኑም እመሰክራለሁ። ከቅዱስ ነገሮች ጋር መቀለድ የለብንም።13 በታማኝነት እንድንቆይ የምጸልየው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።