ኑ እና ተመልከቱ
የኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሁል ጊዜ የሚስዮን ቤተክርስቲያን ነበር እናም ሁል ጌዜም ይሆናል።
መልዕክቴ በተለየ ሁኔታ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባሎች ላልሆኑት ግለሰቦች ነው። ብዙዎቻችሁ አንስታችሁት ልታውቁ ስለምትችሉት መሰረታዊ የሆነ ጥያቄ እናገራለው፥ “ለምንድን ነው የኋለኛው ቀን ቅዱሳኖች ስለ ሚያምኑት ነገር ለመናገር እና ስለ ቤተክርስቲያናቸው እንድናውቅ ለመጋበዝ የሚጓጉት?”
የጌታ መንፈስ በጥሩ ሁኔታ መናገር እንድችል እንዲረዳኝ፣ እናም ለዚህ ጠቃሚ ጥያቄ መልስ ስሰጥ በግልፅ እንድትረዱኝ እፀልያለው።
መለኮታዊ ውክልና
ኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ደቀመዛሙርት ሁሌም ታታሪ ሚስዮኖች ሆነው ነበር እናም ሁሌም ይሆናሉ። ሚስዮን የክርስቶስ ተከታይ ሆኖ አዳኝ መሆኑን ይመሰክራሉእና የወንጌሉን እውነታዎች ያውጃሉ።
የኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሁል ጊዜ የሚስዮን ቤተክርስቲያን ነበር እናም ሁል ጌዜም ይሆናል። በአዲስ ኪዳን ላይ እንደተዘገበው በጌታ ለሐዋሪያዎቹ የተሰጠውን የአዳኙ ቤተክርስቲያን እያንዳንዱ አባል መለኮታዊውን ውክልና ለማሳካት እርዳታ ለማድረግ ሀላፊነትን ተቀብለዋል።
እንግዲህ ሂዱና አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፣
ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው፤ እነሆም እኔ እስከ አለም ፍፃሜ ድረስ ሁልጌዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። አሜን። (ማቴዎስ 28፥19–20)
የኋለኛው ቀን ቅዱሳኖች ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እና መልሶ ስለተቋቋመው የእርሱ ወንጌል የማስተማርንይህን ሀላፊነትበቁም ነገር ይወስዱታል። በጥንት ጊዜ በአዳኙ የተመሰረተው አንድ አይነት ቤተክርስቲያን እንደገና በምድር ላይ በእርሱ በኋለኛው ቀን እንደተመሰረተ እናምናለን።የእርሱ ወንጌልትምህርት፣ መሰረታዊ ወርሆች፣ የክህነት ስልጣን፣ ስነስርዓቶችች፣ እና ቃልኪዳኖች ዛሬም በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ይገኛል።
ከእኛ ጋር ቤተክርስቲያን እንድትካፈሉ እና ከሚስዮኖች ጋር እንድትማሩ ስንጋብዛችሁ፣ ምርት ልንሸጥላችሁ እየሞከርን አይደለም። እንድ ቤተክርስቲያኗ አባልነታችን፣ የመንግስተ ሰማይ ውድድር ሽልማቶችን ወይም የጉርሻ ነጥቦችን አንቀበልም። ዝም ብለን የቤተክርስቲያኑን ቁጥር መጨመር እየፈለግን አይደለም። እናም በተለየ አስፈላጊነት፣ እኛ እንደምናምነው እንድታምኑ ለማስገደድ አንሞክርም። መልሶ ስለተቋቋመውን ወንጌል እውነቶች እንድትሰሙ የምንጋብዛችሁ፣ ከእናንተ ጋር የምናካፍለውን ነገሮችን እንድታጠኑ፣ እንድታሰላስሉ፣ እንድትፀልዩ፣ እና እውነት መሆናቸውን ለራሳችሁ ለማወቅ እንድትችሉ ነው።
አንዳንዶቻችሁ “ነገር ግን በኢየሱስ አምኛለው እናም ትምህርቶቹን ተከትያለው” ወይም “እግዚአብሔር በእርግጥ በሕይወት እንደሚኖር እርግጠኛ አይደለሁም” ብላችሁ መልሳችሁ ሊሆን ይችላል።የእኛ ግብዣዎች ሐይማኖታዊ ባህላችሁን ወይም የሕይወት ተሞክሮአችሁን ለመቀነስ የምንሞክርበት አይደለም። እውነት እንደሆነ የምታውቁትን ነገሮች፣ መልካም እና የሚደነቁ ነገሮችን ጠብቁ፣ -እናም መልዕክታችን ፈትኑ። ልክ ኢየሱስ ሁለት ደቀ መዛሙርቱን “መጥተው እንዲያዩ”(ዮሀንስ 1፥39) እንደጋበዘው፣ እኛም መልሶ የተቋቋመው የኢየሱስሰ ክርስቶስ ወንጌል እውነት ነው ብላችሁ የምታምኑትን ነገሮች የሚያሰፋ እና የሚመግብ እንደሆነ መጥታችሁ እንድታዩ እንጠይቃችኋለን።
በእርግጥ፣ ይህንን መልዕክት ለሁሉም ሀገራት፣ ዘሮች፣ቋንቋዎች እና ህዝቦች ለማካፈል የጠበቀ ሀላፊነት ይሰማናል።እናም ለእዛ ነው ዛሬ ከ87ሺህ በላይ በሆኑ የሚስዮኖች ሀይል በአለም ዙሪያ ከ150 በላይ በሆኑ ሀገራት ውስጥ የምንሰራው። እነዚህ አስደናቂ ወንዶችና ሴቶች እናም እድሜአቸው የገፋ ጥንዶች የቤተክርስቲያናችንን አባላት የኢየሱስ ክርስቶስን ዘላለማዊ ወንጌል ለማወጅ እያንዳንዳችን የተቀበልነውን መለኮታዊ ሹመትና የግል ሀላፊነታቸውን ለሟሟላት ያግዛሉ።” (ት. እና ቃ. 68:1 ተመልከቱ)
ከመንፈስ ተግባር የላቀ
ነገር ግን ይህንን መልዕክት ለማወጅያለን ጉጉት የመንፈሳዊ ተግባር ውጤት ብቻአይደለም።መልሶ የተቋቋመውን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ከእናንተ ጋር የማካፈል ምኞታችን እነዚህ እውነታዎች ለእኛ ምን ያህል ጠቃሚ መሆናቸውን የሚያሳይ ነፀብራቅ ነው።እኛ ለምን እምነታችንን ለእናንተ ለማስረዳት እንደምንሻ እኔ እና ባለቤቴ ከብዙ አመታት በፊት በሁለት ወንድ ልጆቻችን ባገኘነውን የሕይወት ልምድ አማካኝነት በበለጠ ሁኔታ መግለፅ እንደምችል አምናለው።
አንድ ምሽት ሱዛን እና እኔ በቤታችን ውስጥ ከመስኮት አጠገብ ቆምን እና ሁለቱ ትንንሽ ወንድ ልጆቻችን ውጪ ሲጫወቱ ተመለከትን። በጫወታቸው ወቅት ከሁለቱ ታናሹ ልጅ በትንሽ አደጋ ውስጥ ተጎድቶ ነበር። በጣም እንዳልተጎዳ በፍጥነት ተገነዘብን፣ እናም አፋጣ እርዳታ እንዳንሰጠው ወሰንን። ስለ ወንድማዊ ደግነት መርህ የነበረንን የቤተሰባችንን ውይይት እንደገባቸው ለማየት ፈለግን። ከዛ ቀጥሎ የተከሰተው ነገር አስገራሚም እና አስተማሪም ነበር።
ታላቅ ወንድምዬው ታናሽ ወንድሙን አፅናናው እና በጥንቃቄ ወደ ቤት እንዲመለስ ረዳው። ሱዛን እና እኔ ቀጥሎ የሚከሰተውን ነገር ለማየት እቃ ቤቱ ጋር ሆንን እናም ተጨማሪ የሰውነት ጉዳት የሚከሰት ከሆነ ወይም አስከፊ ጉዳት የሚከሰት ከሆነ ወዲያው ጣልቃ ለመግባት ዝግጁ ነበርን።
ታላቁ ወንድም አንድ ወንበር ወደ እቃ ቤቱ እቃ ማጠቢያ ሳበ። ወንበሩ ላይ ወጣ፣ ወንድሙንም ወንበሩ ላይ እንዲወጣ አገዘው፣ ውኃውን ከፈተው እና በታናሽ ወንድሙ በተፋቀው እጅ ላይ ብዙ የእቃ ማጠቢያ ሳሙና ማፍሰሱን ቀጠለ። ቆሻሻውን ቀስ ብሎ ለማስወገድ የተቻለውን አደረገ። የትንሹን ወንድም ሁኔታን በትክክል ለመግለፅ ከመጽሐፍ ቅዱሳት በወጣ ቋንቋ ብቻ ሊገለፅ ይችላል፥ “እናም ይጮኻሉ፣ እናም ዋይ እያሉ ያለቅሳሉ፣ እናም በትካዜ ይጮኻሉ፣ እናም ጥርሳቸውን ያፋጫሉ” (ሞዛያ 16:2).እናም ያ ትንሽዬ ልጅም ጮኸ!
ፅዳቱ ካለቀ በኋላ፣ እጁ በጥንቃቄ በፎጣ ደረቀ። በመጨረሻ ጩኸቱ ቆመ። ከዛ ታላቁ ወንድም ባንኮኒው ላይ ወጣ፣ ሳጥን ከፈተ እና አዲስ የቆዳ ቅባት መድሀኒት አገኘ። በወንድሙ ላይ ያለው የተላጠ ነገር ትላቅ ወይም ሰፊ ባይሆንም ኖሮ፣ ታላቁ ወንድም በተጎዳው እጅ ላይ ሁሉንም የቆዳ ቅባት መድሀኒት አደረገበት። ጩኸቱ አልቀጠለም፣ ትንሹ ወንድም በግልፅ የቅባቱን ውጤት ከእቃ ማጠቢያው ሳሙና የበለጠ አድንቆት ነበር።
ታላቁ ወንድም ቅባቱን ወዳገኘበት ሳጥን እንደገና ተመለሰ እና አዲስ የፋሻ ሳጥን አገኘ። ከዛ ፈታውና በወንድሙ እጅ ላይ ከላይ እስከ ታች ከእጅ አንጓው እስከ ክርስ ፋሻውን አደረገበት። ድንተኛ አደጋው በመቀረፉ፣ እና እቃ ቤቱ በቅባት እና በመጠቅለያ ሞልቶ፣ ሁለቱ ወንድማማቾች ብሩህ በሆነ ፈገግታ እና ደስተኛ ፊት ከወንበሩ ወረዱ።
ከዛ በኋላ የተከሰተው በጣም አስፈላጊ ነው። የተጎዳው ወንድም የቀረውን ፋሾች፣ ያለቀውን የቆዳ ቅባት ሰበሰበ እና ወደ ውጪ ተመልሶ ወጣ። ቶሎ ብሎ ጓደኞቹን ፈለገ እና ቅባቱን እና ፋሻውን እጃቸው ላይ ማድረግ ጀመረ። ሱዛን እና እኔ በቅንነቱ፣ ጉጉት እና በመልሱ ፍጥነት በጣም ተገረምን።
ያ ትንሽ ልጅ ያደረገውን ለምንድነው ያደረገው? እርሱ በተጎዳበት ሰአት የረዳውን ተመሳሳይ ነገር ለጓደኞቹ ወዲያው እና በቀላሉ ለመስጠት ፈለገ።ያ ትንሽ ልጅ ያንን ነገር ለማድረግ መለመን፣ መሰማት ወይም መገፋፋት አልነበረበትም። ለማካፈል የነበረው ፍላጎት በቀላሉ እርዳታ የሚሰጥ እና ጥቅም ያገኘ ሰው ልምድ ውጤት ነው።
ብዙዎቻችን እንደ ጎልማሶች በጣም የተሰቃየንበትን ህመም የሚያስወግድ ህክምና ወይም መድሀኒት ስናገኝ ወይም ፈተናዎችን በድፍረት እና እንቆቅልሾችን በታጋሽነት መጋፈጥ የሚያስችለን ምክርን ስንቀበል በተመሳሳይ መልኩ ፀባያችንን እናሳያለን። ለእኛ በጣም ትርጉም የሚሰጡንን ነገረሮች ወይም የረዱንን ነገሮች ከሌሎች ሰዎች ጋር መካፈል በጭራሽ ያልተለመደ ነገር አይደለም ።
አንድ አይነት ንድፍ በታላቅ መንፈሳዊ ነገሮች ጥቅሞችና የሚያስከትለው ውጤት ላይ የተረጋገጠ ነው። ለምሳሌ፣ መጽሐፈ ሞርሞን በሚባል የቅዱስ መጽሐፍ ይዘት ውስጥ ሌሂ የሚባል የጥንት ነቢይ-መሪስለ ተቀበለው ህልም ያስተምራል። በሌሂ ህልም ውስጥ መአከላዊ ዋናው ነገር የሕይወት ዛፍ ነው- ይህም“የእግዚአብሔርን ፍቅር ከሁሉም ነገሮች በላይ አስፈላጊ የሆነውን” እና “ለነፍስ በጣም ደስ የሚያሰኘውን” የሚወክል ነው( 1 ኔፊ 11፥22–23 ፤ 1 ኔፊ 8፥12፣ 15 ተመልከቱ)።
ሌሂ አብራራ
“እናም እንዲህ ሆነ፣ ሄጄ ከፍሬዋ ተካፈልኩ። ከዚ በፊት ከቀመስኩት ሁሉ ጣፋጭ እንደሆነች አየሁ። ከዚ በፊት ካየሁትም ንጣት ሁሉ በላይ ነጭ የሆነች ፍሬ መሆኗን ተመለከትኩ።
“ከዚያ ካለው ፍሬ በተካፈልኩ ጌዜ ነፍሴ እጅግ በታላቅ ደስታ ተሞላች፤ ስለሆነም ቤተሰቦቼ ደግሞ ይካፈሉት ዘንድ መመኘት ጀመርኩ”(1 ኔፊ 8፥11–12፣ ትኩረት ተጨምሮበት)።
እግዚአብሔር ለልጆቹ ያለው ፍቅር ታላቁ መገለጫ የክርሰቶስ ምድራዊ አገልግሎቱ፣ የሀጢያት ክፍያው እና ትንሳኤው ነው። ዛፉ ላይ ያለው ፍሬ የአዳኙን የሀጢያት ክፍያ በረከቶች ይወክላል።
የሌሂ የዛፉን ፍሬ ለመብላት የነበረው የፈጠነ መልስ እና ተለማመደው ታላቅ ደስታ ፍሬውን ከቤተሰቡ ጋር ለመካፈል እና ቤተሰቡን ለማገልገል የነበረው አዳጊ ፍላጎት ነበር። ስለሆነም፣ ወደ ክርስቶስ ሲመለስ፣ በፍቅር እና በአገልግሎት ወደ ሌሎች ሰዎችም ተመለሰ።
ሌላው በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ ጠቃሚ ክፍል አንድ ኢኖስ ስለተባለ ሰው የቅን እና የልመናፀሎቱ በእግዚአብሔር ከተሰማ እና ከተመለሰ በኋላ ምን እንደተከሰተ ይገልፃል።
እርሱ አለ፥
“እናም ነፍሴ ተራበች፤ እናም በፈጣሪዬ ፊት ተንበረከክሁ፣ እናም ለነፍሴ በሀይለኛ ፀሎትና ልመና ወደ እርሱ ጮህኩ፣ እናም ቀኑን ሙሉ ጮህኩ፤ አዎን፣ ምሽቱ ሲመጣ ድምፄን ሰማይ እስከሚደርስ ከፍ አደረኩት።
“እናም አንድ ድምፅ ወደ እኔ መጣ፣ እንዲህም አለኝ፥ ኢኖስ ሀጢያትህ ይቅር ተብሎልሀል እናም አንተ የተባረክ ነህ።
“እናም እኔ ኢኖስ እግዚአብሔር ሊዋሽ እንደማይችል አውቃለው፤ ስለሆነም፣ በደሌ ተወግዶልኛል።
“እናም ጌታ፣ ይህ እንዴት ሆነ? አልኩት።
“እናም እርሱም አለኝ፥ ባላየኸውና ሰምተህ በማታውቀው በክርስቶስ ባለህ እምነት ምክንያት ነው… ስለሆነም ሂድ እምነትህ አድኖሀል።
“አሁን እንዲህ ሆነ፣ እነዚህን ቃላት በምሰማ ጊዜ ለኔፋውያን ወንድሞቼ ደህንነትን ማሰብ ጀመርኩ፤ ስለሆነም፣ ለእርሱ ነፍሴን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር አፈሰስኩ” (ኤኖስ 1፥4–9፣ ትኩረት ተጨምሮበት)።
ኢኖስ “በሙሉ ልቡ”ወደ ጌታ ሲመለስ (1 ኔፊ 31፥13)፣ ለቤተሰቡ፣ ለጓደኞቹ እና ለተባባሪዎቹ ደህንነት ያለው መጨነቅ በአንድ ጊዜ ጨመረ።
ከእነዚህ ሁለት ታሪኮች የምንማረው የሚጸና ትምህርት ቢኖር፣አንድን ተግባር ዝምብለን ከማከናወን በላይ የሆነ ቅን እና እውነተኛ አገልግሎት ማድረግ ከመቻላችን በፊት፣የኢየሱስ ክርስቶስን የሀጢያት ክፍያ በረከቶች በግል ህይወታችን ውስጥ የማለማመድ አስፈላጊነት ነው። እንደ ሌሂ፣ ኢኖስ እና በታሪኩ ውስጥ በገለፅኩት የእኛ ትንሽ ወንድ ልጅ፣ እኛ እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክረስቲያን አባላት ከመንፈሳዊ ጥርጣሬ እና ከሀጢያት ጋር የሚገናኘው ጭንቀት ተሰምቶናል። እንዲሁም የአዳኙን ወንጌል መርሆች በመማር እና በመኖር ብቻ የሚገኘውን የሚያጠራውን፣ የህሊና ሰላምን፣ መንፈሳዊ ፈውስን እና እድሳትን እና ምሪት የሚሰጠውን ተለማምደናል።
የኢየሱስ ክርስቶስ የሀጢያት ክፍያ ንፁ እና ፅዱ መሆን የሚያስችልየመንፈሳዊ ቁስሎችን የሚፈውስ፣ ጥፋተኝነትን የሚያስወግድ ማፅጃ የሚሆን እናም በጥሩ እና በመጥፎ ጊዜአት ታማኝ እንድንሆን ከለላ ይሰጣል።
ፍፁም እውነት አለ
ለእናንተ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል ላልሆናችሁት የቤተሰብ አባላት፣ እኛ ለምን ሚስዮኖች እንደሆንን ለማስረዳት መሰረታዊ ምክንያቶችን ለመግለፅ ሞክሪያለው።
ፍፁም እውነት ሙሉ በሙሉ እውነተኛ የሆኑትን ነገሮች ለማዋረድ እና ለማጥፋት እየጨመረ ባለበት አለም ውስጥ ይገኛል። በመጪው ቀን “ይንበረከኩ ዘንድ” እና “ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው”(ፊልጵስዮስ 2፥10–11)። ክርስቶስ ኢየሱስ ፍፁም በሆነ ሁኔታ ከዘላለማዊው አብ የተወለደ አንድያ ልጅ ነው። እንደ እርሱ ቤተክርስቲያን አባላት፣ እንደሚኖር እና ቤተክርስቲያኑ በሙሉነቱ በእነዚህ የኋለኛው ቀናት እንደተቋቋመች እንመሰክራለን።
እንድትማሩ እና መልዕክታችንን እንድትፈትኑ የምናበረክታቸው ጥሪዎች የሚመነጩት የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በሕይወታችን ውስጥ ባበረከተው አዎንታዊ ስሜት ነው። አንድ አንድ ጊዜ በሙከራችን ወቅት የማንመች ወይም ቀጥተኛ ወይም የማናቋርጥ ልንሆን እንችላለን፣ ነገር ግን ፍላጎታችን ግን ለእኛ በጣም ታላቅ ዋጋ ያላቸውን እውነቶች ከእናንተ ጋር ለመካፈል ነው።
እንደ ጌታ አንዱ ሐዋርያ እና በነፍሴ ሙሉ ጉልበት፣ የእርሱን መለኮታዊነት እና እውነተኛነት እመሰክራለው። እናም “እንድትመጡ እና እንድታዩ”(ዮሀንስ 1፥39) እጋብዛችኋለው። ቅዱስ በሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።