2010–2019 (እ.አ.አ)
ዘለአለማዊ ህይወት–የሰማይ አባታችንን እና ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ለማወቅ
ኦክተውበር 2014


14:35

ዘለአለማዊ ህይወት–የሰማይ አባታችንን እና ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ለማወቅ

እግዚአብሔር እና ክርስቶስ አባት እና ልጅ – የማይለያዩ፣ ልዩ፣ በአላማቸው አንድ የሆኑ ግለሰቦች ናቸው።

ከብዙ አመታት በፊት በእያንዳነዱ ዘመን የነበሩትን ዋና ምስክርነት ለማጥናት እድሉን ወስጄ ነበር። እያንዳንዳቸው ስለ አብ እና ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጠንካራ ምስክርነትን አካፍለዋል።

እነዚህን ምስክርነቶች---እና እነሱን የመሰሉትን ሳነብ---እንዴት በጥልቁ የሰማይ አባት ታላቅ ልጁን እንደሚወድ እና እንዴት ኢየሱስ ለሰማይ አባት በመታዘዝ ፍቅሩን ማሳየቱ ሲሰማኝ ሁሌም ልቤን ይነካኛል። እነርሱን እና እርስ በእርስ ያላቸውን ፍቅር ለማወቅ አስፈላጊውን ነገር ስናደርግ፣ “የእግዚአብሔር ታላቁ ስቶታ” የሆነውን ዘለአለማዊ ህይወት እንደምናገኝ እመሰክራለሁ።1 “አንተ ብቸኛውን እውነተኛ እግዚአብሔርን እና የላከውን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ፣ ይሄ ነው የዘለአለም ህይወት።”2

ይሄን ስጦታ የእኛ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? ይህም የሚመጣው በዚህ ቀን ጠዋት ያስተምሩት እና ይነጋገሩበት በነበረው በግል ራዕይ በኩል ነው።

እግዚአብሔር መኖሩን እና ፍቅሩ ሊሰማችሁ እንደሚችል ለመጀመሪያ ያወቃችሁበትን ጊዜ ታስታውሳላችሁ? እንደ ወጣት ልጅ፣ ወደ ብርሀናማ ሰማይ እመለከት እና የእርሱ መኖር ይሰማኝ ነበር። ከትንሽ ነብሳት እስከ ግዙፍ ዛፎች---በታለቅ የእግዚአብሔር ፍጥረት ውበትን ለማወቅ እጓጓ ነበር። የዚህን ምድር ውበት ሳስተውል፣ የሰማይ አባት እንደሚወደኝ አውቄ ነበር። ቀጥተኛ የእርሱ መንፈሳዊ ልጁ መሆኔን፣ ሁላችንም የእግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች መሆናችንን አውቄ ነበር።

እንዴት ነው ይህን ያወቁት? ብላችሁ ትጠይቁ ይሆናል። ቅዱስ መጽሀፍት እንደሚያስተምሩት፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ለአንዳንዶች በመንፈስ ቅዱስ ተገልጽዋል፣ እና … ለሌሎች የእነርሱን ቃላት እንዲያምኑ ተሰጥቷል፣ በእምነት ከቀጠሉ የዘለአለማዊ ህይወት ይኖራቸው ዘንድ።”3 በእኔ አመለካከት፣ ይሄ አንዳንድ ሰዎች በሌሎች ምስክርነት ላይ ለዘለአለም ጥገኛ ይሆናሉ ማለት አይደለም።

ከወላጆቼ፣ መምህሮቼ፣ ቅዱስ መጽሀፍት፣ እና በተለይም ከመንፈስ ቅዱስ ስለ ሰማይ አባት እና አዳኛችን በሰጡት ትምህርት እና ምስክርነት ስማር የእኔ ምስክርነት አደገ። እምነትን ስለማመድ እና ለትእዛዛት ስታዘዝ፣ እየተማርኩ የነበረው እውነት እንደነበረ መንፈስ ቅዱስ መሰከረ። ያ እኔ ለራሴ ያወኩበት መንገድ ነው።

በዚህ ሂደት፣ መሻት ቁልፍ ነው። ኔፊ እያንዳንዳችንን እንደሚጋብዘው የክርስቶስን ቃል ተመገቡ እላችኋለሁ፤ እነሆም የክርስቶስ ቃል ማድረግ ያለባችሁን ነገሮች በሙሉ ይነግራችኋል።”4

ከስምንት አመት ልደቴ በፊት፣ ስለ ጥምቀት የበለጠ ማወቅ ፈልጌ ነበር። ቅዱስ መጽሀፍትን አነበብኩ እና ጸለይኩ። ማረጋገጫ ሲሰጠኝ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እንደምቀበል ተማርኩ። እግዚአብሔር እና ክርስቶስ በአላማቸው የተጣመሩ ግን በየእራሳቸው ሆነው አባት እና ልጅ መሆናቸውን እየተረዳሁ መጣሁ። “ቅድሚያ ስለወደዱን እንወዳቸዋለን።”5 እርስ በእርሳቸው እንዴት እንደሚዋደዱ እና ለመልካም አብረው እንደሚሰሩ ደጋግሜ አጤንኩ። ይህን እውነት ከሚያስተምሩ ብዙ ጥቅሶች ጥቂቱን አድምጡ፤

ስለ ቅድመ ምድራዊ ህይወታችን ሲያስተምር፣ የሰማይ አባት ኢየሱስ ክርስቶስን “ተወዳጁ ልጄ፣ ከመጀመሪያው የተወደደ እና የተመረጠ”6 በማለት ገልጾታል። አብ ምድርን ሲፈጥር፣ የደረገው “በአንድያ ልጁ” ነው።7

የኢየሱስ እናት፣ ማርያም፣ “የሀያሉን ልጅ” እንደምታመጣ ተነግሯት ነበር።8 እና ኢየሱስ ወጣት ልጅ ሳለ፣ ለእናቱ “በአባቴ ስራ መሆን” እንዳለበት ለእናቱ ነግሯት ነበር። 9 ከአመታት በኋላ፣ አዳኝ ሲጠመቅ፣ የሰማይ አባት ከሰማይ ተናገረ፣ እንዲህ ብሎ፣ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው።”10

ደቀመዛሙርቱ እንዲጸልዩ ለማስተማር፣ ኢየሱስ እነዚህን ቃላት ተናገረ፤

“በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ።

“መንግስትህ ትምጣ። ፍቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን።”11

ኒቆዲሞስን ሲያስተምር፣ “እግዚአብሔር ምድርን ስለሚወድ አንድያ ልጁን ሰጥቷል።” 12 ተአምራቱን ሲገልጽ እንዲህ አለ፣ “አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ምንም ሊያደርግ አይችልም፤ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋል።”13

የሀጢያት ክፍያው ሰአት ሲቃረብ፣ ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ጸለየ፣ “አባት ሆይ፣ ሰአቱ ደርሷል…. እኔ ለደርገው የሰጠኸኝን ስራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ።”14 ከዛም፣ የሀጢያቶቻችን ክብደት ስወርድበት፣ እንዲ ለመነ፣ “አባቴ፣ ቢቻልስ፣ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን።”15 በመስቀል ላይ በመጨረሻ ጊዜው፣ ኢየሱስ ጸለየ፣ “የሚያደርጉትን አያውቁም እና አባት ሆይ፣ ይቅር በላቸው” እና ከዛም በከፍተኛ ድምጽ ጮኸ፣ “አባት ሆይ፣ ነብሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ።”16

ከዛም ፣ “ከሞት ትንሳኤ ማድረግ እና ወደ አባቱ መንግስት መግባት እንዲችሉ ሀይል ለመስጠት” የሞቱትን ነብሳት ጎበኘ።17 ከአዳኝ ትንሳኤ በኋላ፣ ለመቅደላዊት ማርያም ተገልጦ፣ እንዲህ አለ፣ “ወደ እኔ እና አንቺ አባት አርጋለሁ።”18

አሜሪካ አህጉር ወዳሉት ህዝቦች ሲመጣ፣ አባቱ እንዲህ ብሎ አስተዋወቀው፣ “በእርሱ ደስ የሚለኝ፣ ስሜንም ያከበርኩበት፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው።”19 ኢየሱስ ወደ ህዝቡ ሲወርድ፣ እራሱን እንዲህ ብሎ አስተዋወቀ፤ “እነሆ፣ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ፣ የአለምን ሀጢያቶች በላዬ በመውሰድ አባቶን አክብሬያለሁ።”20 ወንጌሉን ሲያስተም፣ እንዲህ አብራራ፤

“እርሱ አብ ለእኔ የሰጠኝ ትምህርት ነው፤ ስለአብ እመሰክራለሁ፣ እንዲሁም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል።”21

“በእውነትም፣ አብ እና እኔ አንድ ነን።”22

በእነዚህ ጥቅሶች አብ እና ወልድ የተለያዩ ግለሰቦች መሆናቸውን የሚያሳይ ትስስር መመልከት እንችላለን? ታዲያ እንዴት ነው “አንድ” የሆኑት? አንድ ግለሰብ ስለሆኑ ሳይሆን፣ “የሰውን አለመሞት እና ዘለአለማዊ ህይወትን ለማምጣት” በእኩል ተሰጥተው በሚሰሩበት አላማ ስለተጣመሩ ነው።23

ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው፣ ግን ለአባቱ በመጸለይ እና የአባቱን ፍቃድ እንደሚያደርግ በመናገር እራሱን እንደተለየ ግለሰብ በተከታታይ ይለያል። በኔፊያቶች መሀል ሲያገለግል፣ እንዲህ ብሎ ለመነ፣ “አባት ሆይ፣ አንተ በእኔ እንዳለህ እኔ እና አንተ አንድ እንደሆንን፣ እኖም በእነርሱ እሆን ዘንድ፣ በእነርሱም እከበር ዘንድ ስለአለም አልጸልይም፣ ከአለም ስለሰጠኸኝ እንጂ።”24

ይሄ በአይምሮአችሁ እንዳለ፣ የወንጌል መመለስ በአንድ ሳይሆን ሁለት የከበሩ ግለሰቦች መገለጽ መጀመሩ አይገርመንም። ስለ መጀመሪያ ራእዩ፣ ነቢዩ ዮሴፍ ስሚዝ መሰከረ፣ “አንደኛው አናገረኝ፣ በስሜ በመጥራት፣ ወደ ሌላኛው በመጠቆም--- —ይህ የምወደው ልጄ ነው፣ ስማው!25

ወጣቱ ነብይ፣ በማይነቃነቅ እምነት ወደ ጫካ ያመራው፣ ስለ ብቸኛው የእውነት እግዚአብሔር እና እርሱ ስለላከው፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት እና ምስክርነት ይዞ ተመለሰ። ዮሴፍ፣ ከእርሱ በፊት እንደነበሩት ነብያት፣ ወደ ዘለአለማዊ ህይወት የሚወስደውን እውቀት ለአለም ለመመለስ መሳሪያ ሊሆን ነበር።

እናንተም ከቅዱስ መጽሀፍት እና በዚህ አጠቃላይ ጉባኤ፣ የሰማይ አባታችንን እና “ይሄ ነብያት እና ሐዋርያት የመሰከሩለትን ኢየሱስ”26 መሻት ትችላላችሁ። ስትፈልጉም፣ እውነቱን ለእራሳችሁ ማወቅ ትችሉ ዘንድ የሰማይ አባት ለእናንተ በስላሴዎች ሶስተኛ ክፍል፣ እኛ መንፈስ ቅዱስ ብለን በምናውቀው፣ የመንፈስ ክፍል፣ ልዩ መንገድ እንዳዘጋጀ ትረዳላችሁ።

“እና እነዚህን ነገሮች ስትቀበሉ”---ዛሬ ያልኩትንም ጨምሮ---“እነዚህ ነገሮች ሀሰት እንደሆኑ ዘለአለማዊ አባታችሁን በክርስቶስ ስም እንድትጠይቁት እመክራችኋለሁ፣ እናም በንጹህ ልባችሁ፤ ከእውነተኛ ስሜት በክርስቶስ አምናችሁ ከጠየቃችሁት በመንፈስ ቅዱስ ኀይል እውነቱን ይገልጽላችኋል።

“እናም የሁሉንም ነገር እውነታ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ታውቁታላችሁ።”27

ወንድሞች እና እህቶች፣ የሰማይ አባታችን ይሄን እውቀት አሁን እንድንሻ እንደሚፈልግ እመሰክራለሁ። የነብዩ ሔለማን ቃላት ከምድር ይጮሀሉ፤ “አስታውሱ፣ አስታውሱ የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በክርስቶስ፣ አዳኝ በሆነው በዓለቱ መሰረታችሁን መገንባት እንዳለባችሁ…. ሰዎች ከገነቡበት ሊወድቁበት በማይችሉበት አለት።”28 በእርግጥም፣እኛም አንወድቅም።

ያ ጽኑ መሰረት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ “የሰማይ አለት” ነው። 29ቤታችንን በእርሱ ላይ ከገነባን፣ የኋለኛው ቀን ዝናብ ቢዘንብ፣ ጎርፍ ቢመጣ፣ እና ነፋስ ቢነፍስ፣ ግን ቤታችን እና ቤተሰባችን በክርስቶስ ላይ ስለተመሰረተ አንወድቅም።30

እንዲህ ያለው ቤት “የክብር ቤት” እንደሆነ እመሰክራለሁ።31 እዚያ ለሰማይ አባት በተወዳጅ ልጁ ስም ለመጸለይ እንሰባሰባለን። እዚያ እናከብራቸዋለን እና ምስጋና እንሰጣቸዋለን። እዚያ መንፈስ ቅዱስንእና “ቃል የገባልንን የመጀመሪያ ደረጃ መንግስቱንም፣ ዘለአለማዊ ህይወት” እንቀበላለን።32

አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ህያው እንደሆነ ልዩ ምስክርነቴን አካፍላለሁ። ዘለአለማዊ የሰማይ አባታችን ይወደናል እናም ይጠብቀናል። መንፈስ ቅዱስ ይሄ እውነት እንደሆነ ይመሰክራል። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።