ጌታ ለእኛ እቅድ አለው!
እየኖርን እንዳለነው በመኖርን ከቀጠልን፣ የተገቡት የበረከት ቃለኪዳኖች ይፈጸማሉ?
ተናጋሪዎች በራሳቸው ቋንቋ ለመናገር ምርጫ ባላቸው በዚህ ታሪካዊ አጠቃላይ ጉባኤ ላይ መካፈል ታላቅ እድል ነው። በዚህ መድረክ ባለፈው ጊዜ ስናገር፣ የእንግሊዘኛ አነጋገሬ አሳስቦኝ ነበር። አሁን፣ የፖርቹጊስ ቋነቋዬ ፍጥነት ያሳስበኛል። ከምስሉ ስር ከሚጻፈው የበለጠ ፈጥኜ መናገር አልፈልግም።
ሁላችንም በህይወታችን ታላቅ ውሳኔ ተለማምደናል ወይም ገና እንወስናለን። ይሄንን ስራ ልቀጥልበት ወይስ ያኛውን? ሚስኦን ላገልግል? ይህ ለእኔ ትዳር ትክክለኛው ሰው ነው?
ትንሽ ለውጥ ወሳኝ የወደፊት ውጤት የሚያመጣባቸው በህይወታችን በተለያዩ ክፍሎች ያሉ ሁኔታዎች እነዚህ ናቸው። በፕሬዘዳንት ዴይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ ቃላት፤ “ጌታን ከማገልገል አመታት በኋላ….. ፣ በግለሰቦች፣ ትዳሮች እና ቤተሰቦች ያሉ የደስታ እና የሀዘን ልዩነት የሚመጣው በአነስተኛ ስህተት ብቻ መሆኑን ተምሬያለሁ። (“A Matter of a Few Degrees፣” Ensign or Liahona፣ May 2008፣ 58)).
እንዴት ብናሰላ ነው እነዚህን ትንንሽ ስህተቶች ልናስወግድ የምንችለው?
መልእክቴን ለማብራራት የግል ተሞክሮዬን እጠቀማለሁ።
በ1980ዎቹ መጨረሻ፣ ወጣቱ ቤተሰቤ በሚስቴ፣ ሞኒካ፣ ከአራቱ ውስጥ ሁለቱ ልጆቼ እና በእኔ የተገነባ ነበር። በብራዚል፣ ሳኦ ፖሎ እንኖር ነበር፣ እኔ ለጥሩ ድርጅት እሰራ ነበር..፣ የዩኒቨርሲቲ ጥናቴን ጨርሼ ነበር፣ እና እንኖር ከነበረበት አጥቢያ ከኤጲስ ቆጶስነቴ ተነስቼ ነበር። ህይወት ጥሩ ነበር፣ እና ሁሉም ነገር መሆን እንዳለበት የሆነ ይመስል ነበር---አንድ የድሮ ጓደኛ መጥቶ እስከጎበኘን ጊዜ ድረስ።
ከጉብኝቱ መጨረሻ ላይ፣ ሀሳብ ሰጠ እና አመለካከቴ እንዳይረጋጋ ያደረገ ጥያቄ ጠየቀ። እንዲህ አለ፣ “ካርሎስ፣ የቤተሰብህ፣ ስራህ እና የቤተክርስቲያን አገልግሎትህ ሁሉም ነገር መለካም የሆነ ይመስላል ግን--” እና ከዛም ጥያቄው ቀጠለ፣ “አሁን እየኖርክ እንዳለኸው መኖር ከቀጠልክ፣ በፓትሪያርካል ቡራኬህ ላይ ቃል የተገቡት በረከቶች ይፈጸማሉ?”
የፓትሪያርካል በረከቴን በዚህ መልኩ አስቤው አላውቅም ነበር። ደጋግሜ አንብቤዋለሁ ነገር ግን በፍጹም ቃል ወደ ተገቡት የወደፊት በረከቶች በመመልከት እና የአሁኑ አኗኗሬን በማገናዘብ አልነበረም።
ከጉብኝቱ በኋላ፣ ትኩረቴን ወደ ፓትሪያርካል በረከቴ አደረኩኝ፣ “እየኖርን እንዳለነው ብንኖር፣ የተገቡት የበረከት ቃሎች ይፈጸማሉ?” የሚለውን እያሰብኩ። ከጥቂት ማሰላሰል በኋላ፣ አንዳንድ ለውጦች አስፈላጊ እንደነበሩ ተሰማኝ፣ በተለይም በትምህርቴ እና ስራዬ ጋር በተገናኘ።
የትኛው ነው ትክክል እና ስህተት በሚል ምርጫ ሳይሆን መልካሙ እና የተሸለው የቱ ነው በሚል ነው፣ ልክ ሽማግሌ ኦክስ ሲያስተምሩን እንዳሉት፤ “የተለያዩ ምርጫዎችን ስናስብ፣ አንድ ነገር መልካም መሆኑ በቂ እንዳልሆነ ማስታወስ አለብን። ሌሎች ምርጫዎች የተሸሉ ናቸው እና እንደገና ሌሎች ደግሞ ምርጥ ናቸው።” (“Good፣ Better፣ Best፣” Ensign or Liahona፣ Nov. 2007፣ 104–5).
እንዴት ነው ታዲያ ምርጡን ውሳኔ ማድረጋችንን እርግጠኛ መሆን የምንችለው?
የተማርኳቸው መርሆዎች እነዚህ ናቸው።
መርህ ቁጥር አንድ፤ አማራጮችን የወደፊቱን ፍጻሜ በአእምሮአችን በመያዝ እናስብ።
በወደፊት ውጤታቸው ላይ ካለ ጠለቅ ያለ እይታ በእኛ እና በምንወዳቸው ዙሪያ የምንሰጠው ውሳኔ አደጋ ሊያመጡ ይችላሉ። ስለሆነም፣ በእነዚህ ውሳኔዎች ሊመጣ የሚችለውን ውጤት ከገመትን፣ አሁን መውሰድ ያለብንን ምርጡን መንገድ በታላቅ ጥራት መመልከት እንችላለን።
ማን እንደሆንን፣ ለምን እዚህ እንዳለን፣ እና በዚህ ህይወት ጌታ ከእኛ ምን እንደሚጠብቅ መረዳት የሚያስፈልገንን ጥልቅ እይታ ለማግኘት የሚረዳን።
ጥልቅ እይታ መኖር የቱን መንገድ መውሰድ እንዳለብን የሚሰጠውን መገለጥ ከቅዱስ መጽሀፍት ምሳሌዎች ማግኘት እንችላለን።
ሙሴ ከጌታ ጋር ፊት ለፊት ተነጋገረ፣ ስለ ደህንነት እቅድ ተማረ፣ እና ስለዚህም እስራኤልን በመሰብሰቡ የነበረውን የነብይነት ድርሻ በተሻለ ተረዳ።
“እና እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፣ እነሆ እኔ ሀያሉ ጌታ እግዚአብሔር ነኝ…
“ የእጆቼን ስራ አሳይሀለሁ…
“ እናም ሙሴ፣ የእኔ ልጅ፣ ለአንተ ስራ አለኝ።”(Moses 1፥3–4፣ 6)
በዚህ መረዳት፣ ሙሴ በበርሀ ውስጥ ብዙ መከራን መቋቋም እና እስረኤልን ወደ ቤት መመለስ ችሎ ነበር።
ሌሂ፣ የመጸሀፈ ሞርሞን ታላቁ ነብይ፣ ህልምን አለመ፣ እና በራእዩ ውስጥ ቤተሰቡን ወደ ቃልኪዳን ምድር የመምራት ተልኮውን ተማረ።
“እናም እንዲህ ሆነ ጌታ አባቴን አዘዘው፣ በህልምም እንኳን፣ ቤተሰቡን በመውሰድ ወደ ምድረበዳ መሰደድ እንዳለበት
“… እናም ቤቱን፣ የውርሱን መሬት፣ እና ወርቁን፣ እና ብሩን፣ እና ውድ ነገሮቹን ትቶ ሄደ” (1 ኔፊ2፥2፣ 4)
የጉዞ ውጣውረድ እና በኢየሩሳሌም የነበረውን ምቹ ኑሮ ጥሎ መሄድ ቢኖርበት ሌሂ ለራእዩ ታማኝ ሆኖ ቆየ።
ነብዩ ዮሴፍ ስሚዝ ሌላ ታላቅ ምሳሌ ነው። በብዙ መገለጦች፣ ከመጀመሪያው መገለጥ ጀምሮ፣ ሁሉንም ነገሮች የመመለስ ተልኮውን ማጠናቀቅ ችሏል። (ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥1–26 ተመልከቱ).
እና እኛስ ደግሞ? ጌታ ከእያንዳንዳችን የሚጠብቀው ምንድን ነው?
መረዳትን ለማግኘት መልአክ ማየት አይጠበቅብንም። ቅዱስ መጽሀፍት፣ ቤተመቅደስ፣ በህይወት ያሉ ነብያት፣ የፓትሪያርካል በረከቶቻችን፣ የተነሳሱ መሪዎች፣ እና፣ ከሁሉም በላይ፣ ውሰኔዎቻችንን የሚመራ የግል መገለጥ አለን።
መርህ ቁጥር ሁለት፤ ለሚመጡት ችግሮች መዘጋጀት አለብን።
በጣም ቀላሎቹ፣ በአብዛኛው ፣ በተቃራኒው ናቸው። የጠቀስኳቸውን ነብያት ምሳሌ ማየት እንችላለን።
ሙሴ፣ ሌሂ፣ እና ዮሴፍ ስሚዝ ምርጫቸው ትክክል ቢሆንም ቀላል ጉዞ ግን አልነበራቸውም።
ለውሳኔዎቻችን ዋጋ ለመክፈል ፍቃደኞች ነን? ከምቾት ቀጠናችን ወጥተን ወደ ተሻለ ቦታ ለመጓዝ ዝግጁ ነን?
ወደ ፓትሪያርክ ቡራኬዬ ተሞክሮ ስመለስ፣ በዚያ ጊዜ ተጨማሪ ትምህርት መሻት እንዳለብኝ እና አሜሪካ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲ ለትምህርት እድል ለመመዝገብ ውሳኔ ላይ ደረስኩ። ብመረጥ ኖሮ፣ ስራዬን መተው፣ ያለንን በሙሉ መሸጥ፣ እና እንደ ስኮላርሺፕ ተማሪ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መጥቼ ለሁለት አመት መኖር ነበረብኝ።
የቶፍል እና ጂኤምኤቲ ፈተናዎች መወጣት ያለብኝ የመጀመሪያ ችግሮች ሆኑ። ዩኒቨርሲቲ እኔን ከመቀበላቸው በፊት ብዙ አይሆንም እና ጥቂት ምናልባቶችን ያካተተ ረጅም ሶስት የዝግጅት አመታትን ፈጀ። በሶስተኛው አመት መጨረሻ ከስኮላርሺፑ ሀላፊ የተቀበልኩትን የስልክ ጥሪ አስታውሰዋለሁ።
እነዲህ አለ፣ “ካርሎስ፣ ጥቂት መልካም ዜና እና ጥቂት መጥፎ ዜና አለኝ ላንተ። ጥሩው ዜና በዚህ አመት ካሉት ሶስት የመጨረሻዎች ውስጥ አንዱ ነህ።” በወቅቱ አንድ ብቻ ነበር ክፍት ቦታ የነበረው። “መጥፎው ዜና ሌላኛው ተቀናቃኝ የታዋቂ ሰው ልጅ ነው፣ ሌላኛው ደግሞ የሌላ ታዋቂ ሰው ልጅ ነው፣ እና ከዛ አንተ አለህ።”
በፍጥነት መልሼ፣ “እና እኔ… የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ።”
አስደሳቹ፣ የምድራዊ ወላጅነት የውሳኔ መለኪያ አልነበረም፣ እና በዚያ አመት፣ 1992፣ እኔን ተቀበሉኝ።
የሀያሉ እግዚአብሔር ልጆች ነን። እርሱ አባታችን ነው፣ ይወደናል፣ እና እርሱ ለእኛ እቅድ አለው። በዚህ ምድር ላይ ያለነው ጊዜያችንን ለማባከን፣ ለማርጀት እና ለመሞት አይደለም። እግዚአብሔር እንድናድግ እና አቅማችንን እንድናሳካ ይፈልጋል።
በፕሬዘዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ቃላት፤ “እያንዳንዳቹ፣ ያላገባችሁ ወይም ያገባችሁ፣ በየትኛውም እድሜ ያላችሁ፣ ለመማር እና ለማደግ እድል አላችሁ። ምድራዊም ሆነ መንፈሳዊ፣ እስከ መጨረሻው መለኮታዊ አቅማችሁ ድረስ፣ እውቀታችሁን አስፉ” (“The Mighty Strength of the Relief Society፣” Ensign፣ Nov. 1997፣ 95).
መርህ ቁጥር ሶስት፤ ይህንን ራእይ ለምንወዳቸው ሰዎች ማካፈል አለብን
ላማን እና ልሙኤል እያደረጉ የነበረውን የለውጥ አስፈላጊነት እንዲረዱ ለመርዳት ሌሂ ከጥቂት ሙከራዎች በላይ ሞከረ። የአባታቸውን ራእይ አለመካፈላቸው በጉዞ ወቅት እንዲያጉረመርሙ ምክንያት ሆናቸው። ኔፊ፣ በሌላ ጎኑ፣ አባቱ ያየውን ለማየት ጌታን ለመነ።
“እናም እንዲህ ሆነ እኔ፣ ኔፊ የአባቴን ቃላት ሁሉ ከሰማሁ በኋላ፣ እርሱ በራዕይ ስላያቸው ነገሮች፤… እኔ… በመንፈስ ቅዱስ ሀይል እነዚህን ነገሮች እመለከት እንዲሁም እሰማ እና አውቅ ዘንድ ፈለግሁ።” (1ኛ ኔፊ 10፣ 17)
በዚህ ራእይ፣ ኔፊ የጉዞውን መከራ መቋቋም ብቻ ሳይሆን አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ቤተሰቡን ለመምራትም ቻለ።
አንድን መንገድ ለመውሰድ በምንወስን ጊዜ፣ የምንወዳቸው ሰዎች ላይ ተጽእኖ የሚፈጠርበት፣ እና የምርጫውን ውጤትም የሚካፈሉን የመኖራቸው እድል ሰፊ ነው። እኛ የምናየውን ማየት ይችላሉ እና ተመሳሳይ ውጥናችንን መካፈል ይችላሉ። ይሄ ሁሌ የሚቻል አይደለም፣ ግን ሲከሰት፣ ጉዞው በጣም ቀላል ነው።
እንደማብራሪያ በተጠቀምኩት የግል ተሞክሮ፣ የሚስቴ እርዳታ ያለጥርጥር አስፈልጎኝ ነበር። ልጆቹ ገና ወጣት በሆናቸው ብዙም የሚሉት አልነበረም፣ ነገር ግን የሚስቴ እርዳታ ወሳኝ ነበር። በመጀመሪያ፣ ሞኒካ እና እኔ በእቅድ ላይ እሷ ምቾት እስኪሰማት እና እስከምትሰጥ ድረስ ባለው ለውጥ ላይ መወያየት እንደነበረብን፣ አስታውሳለሁ። ይሄ የተካፈልነው ራእይ ለውጡን እንድትደግፍ ብቻ ሳይሆን በስኬቱ ላይ ወሳኝ ክፍል እንድትሆን አደረገ።
ጌታ በዚህ ህይወት ለእኛ እቅድ እንዳለው አውቃለሁ። ያውቀናል። ለእኛ ምርጥ ምን እንደሆነ ያውቃል። ነገሮች በመልካም ስለተጓዙ ብቻ የተሸለ ነገር ስለመኖሩ በየጊዜው መሞከር የለብንም ማለት አይደለም። እየኖርን እንዳለነው መኖር ከቀጠልን፣ ቃል የተገቡልን በረከቶች ይፈጸማሉ?
እግዚአብሔር ህያው ነው። እርሱ የእኛ አባት ነው። አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ህያው ነው፣ እና በእርሱ የክፍያ መስዋእት የየቀን ችግሮቻችንን ለመወጣት ጥንካሬ እናገኛለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።