2010–2019 (እ.አ.አ)
ቅዱስ ቁርባን እና ሀጢያት ክፍያ
ኦክተውበር 2014


12:5

ቅዱስ ቁርባን እና ሀጢያት ክፍያ

የቅዱስ ቁርባን ስነ-ስርዓት ለእያንዳንዳችን ብዙ ቅዱስ እና የነፃ መሆን ይፈልጋል።

በጌትሰመኒ እና ካልቫሪ ዋዜማ ለት፣ ኢየሱስ ሐዋርያቶቹን ለአንድ መጨረሻ ጊዜ ለማምለክ በአንድ ላይ ሰበሰበ። ቦታው በኢየሩሳሌም ውስጥ በሚገኘው የአንድ ደቀመዝሙር የላይኛው ክፍል ውስጥ ነበር እናም ወቅቱ የጌታ እራት የሚከበርበት ጊዜ ነበር። 1

ከፊታቸው ባህላዊው የፋሲካ በአል ምግብ የሚሰዋ ጠቦት፣ ወይን እና እርሾ ያልገባበት ቂጣ፣ የቀድሞው የእስራኤል ልጆች ከባርነት እና ከሞት 2የመዳን ምልክት እና እንዲሁም የወደፊት ገና የሚታይ ቤዛነትን አካቶ ነበር።3 ምግቡ ወደ መጨረሻው ሲቃረብ፣ ኢየሱስ ዳቦ ወሰደ፣ ባረከው እና ቆረሰው4 እና ለሐዋርያቶቹ እንዲህ በማለት ሰጣቸው፣ “ውሰዱ፣ ብሉ።”5 “ስለ እናንተ ምሰጠው ስጋዬ ይ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት።”6 በተመሳሳይ ሁኔታ፣ የወይኑን ኩባያ ወሰደ፣ ባረከው እና በእርሱ ዙሪያ ላሉት እንዲህ በማለት አካፈለ፥ “ይህ ፅዋ ሰለ እናንተ በሚፈው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።”7 “ለሀጢያት ይቅርታ የፈሰሰ ነው።”8 “ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት።”9

በዚህ ቀላል ነገር ግን ሀይለኛ መንገድ፣ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር ህዝቦች አዲስ ስነ-ስርዓትን አስተዋወቀ። ካሁን በኋላ የእንስሳት ደም አይፈስም ወይም የእንስሳት ስጋ ገና በሚመጣው በአዳኙ ክርስቶስ መሰዋትነትን በማሰብ አይበላም።10 በምትኩ የክርስቶስን የተቆረሰውን ስጋ እና የፈሰሰውን ደም የሚወክል አዳኝ መስዋትነቱን ለማስታወስ ይወሰዳል እንዲሁም ይበላል።11 በእዚህ አዲሱ ስነ-ስርዓት ላይ መካፈል ለሁሉም ኢየሱስን ቃል እንደተገባላቸው ክርስቶስ እመቀበላቸውን እና በሙሉ ልብ እርሱን ለመከተል እና ትዕዛዙን ለመጠበቅ ፍቃደኞች መሆናቸውን ያሳያል።

ከዛ በተከተሉት ሰአታት ውስጥ፣ ኢየሱስ ወደ ጌተሰሜኒ ገባ፣ ወደ ቀራኒዮ ተወሰደ፣ እና በድል መቃብሩን ተለየ። ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ፣ የኢየሱስ አማኝ ደቀ መዝሙሮች በኢየሩሳሌም ውስጥ እና በአካባቢዋ በሳምነቱ የመጀመሪያ ቀን “ዳቦ ሊቆርሱ”12 ተሰበሰቡ እና “በመተማመን” አደረጉ።13 በእርግጥ፣ ይህን ያደረጉት የሚሄደውን ጌታ ለማስታወስ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ለእነሱ በዋለው አስደናቂ ቤዛነት ምስጋናን እና እምነትን ለማቅረብ ነበር።

ከሁሉም በላይ፣ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን በአሜሪካ ሲጎበኝ፣ በእነርሱም መካከል ቅዱስ ቁርባንን መሰረተ።14 ይህን በማድረግ፣ እንዲህ አለ፣ “ይህንንም እናንተ ዘወትር አድርጉ”15 እናም “ይህም ለአብ እኔን ሁልጊዜ እንደምታስታውሱኝ ምስክራችሁ ይሆናል።” 16እንደገናም፣ በዳግም መመለስ መጀመሪያ ላይ፣ ለድሮ ደቀመዛሙርቱ እንደሰጣቸው አይነት መመሪያ በመስጠት፣ ጌታ የቅዱስ ቁርባን ስርዓትን መሰረተ። 17

የቅዱስ ቁርባን ስነ-ስርዓት “በቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉት በጣም ቅዱስ እና የነፃ ስነ-ስርዓት” ተብሎ ይጠራል።18 ለእያንዳንዳችን የበለጠ ቅዱስ ሊሆን ይገባል። ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱ ሊያድንነ ምን እንዳደረገ ሊያስታውሰን እና የማዳኑን ስራ እንዴት በተገቢው ሁኔታ እንደምንጠቀምበት እና ከዛ ከእግዚአብሔር ጋር በድጋሚ እንዴት እንደምንኖር ሊያስተምረን ስነ-ስርዓቱን አስተዋወቀ።

በተፈረፈረ እና በተቆረሰ ዳቦ የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋ ማለትም በህመም፣ በስቃይ፣ በሁሉም አይነት ፈተናዎች19 የተመታውን፣ እንዲሁም ከእያንዳንዱ ቀዳዳ እሰኪደማ ድረስ ስቃይን የተሸከመውን ስጋ፣20 በስቅላቱ ውስጥ ስጋው የተበጫጨቀውን እና ልቡ የተሰበረውን ሰውነቱን እንደምናስታውስ እናሳያለን።21 ያ ሰውነት በሞት ሲያርፍ በድጋሚ መቼም ህመምን፣ መበስበስን ወይም ሞትን ላለማወቅ ከመቃብር እንደተነሳ እምነታችንን እናሳያለን።22 ዳቦውን ለራሳችን በመውሰድ፣ ልክ እንደ ክርስቶስ ሟች አካል የእኛም አካል ከሞት እስር እንደሚለቀቅ፣ ከመቃብር በድል እንደሚነሳ እና ወደ ዘላለማዊ መንፈሳችን ተመልሰን እንደምንቋቋም እናምናለን።23

በትንሽዬ የውኃ ኩባያ፣ ኢየሱስ ያፈሰሰውን ደም እና ለሁሉም የሰው ዘር የገባውን መንፈሳዊ ስቃይ እንደምናስታውስ እናሳያለን። ታላቅ የደም ጠብታዎችን በጌተሰመኒ እንዲፈሱ ያደረገውን እናስታውሳለን።24 ከወሰዱት ሰዎች ብልዞችን እና ግርፊያዎችን እንደተቀበለ እናስታውሳለን።25 በቀራኒዮ ከእጆቹ፣ ከእግሮቹ እና ከጎኑ የፈሰሱትን ደም እናስታውሳለን።26 እንዲሁም ስለ ስቃዩ የራሱን የግል አገላለፅ እናስታውሳለን፥ “እንዴት እንደሚያም አታውቁም፣ እንዴት አሰቃቂ እንደነበር አታውቁም፣ አዎ፣ ለሸከም እንዴት እንደሚከብድ አታውቁም።”27 ውኃውን ለራሳችን በመውሰድ የእርሱን ደም እና ለሀጢያታችን የከፈለውን ስቃይ እንቀበላለን እና የወንጌሉን መርሆች እና ትምህርቶች ስናቅፍ እና ስንቀበል ለሀጢያቶችንን እርሱ እንደሚከፍል እናምናለን።

ስለሆነም፣ በዳቦ እና በውኃ የክርስቶስን እኛን ከሞት እና ከሀጢያት ማዳን እንድናስታውስ እንደረጋለን። መጀመሪያ የዳቦው እና ሁለተኛ የውኃው ቅደም ተከተል አስፈላጊ ነው። ዳቦውን በመውሰድ የራሳችንን የማይቀር ትንሳኤ ከአካል እና ከመንፈስ መገናኘት የበለጠውን እናስታውሳለን። በትንሳኤ ኃይል ሁላችንም ወደ እግዚአብሔር መገኛ እንመለሳለን።28 ያ እውነታ የሕይወታችንን መሰረታዊ ጥያቄ ያቀርባል። ሁላችንንም ያጋጠመን መሰረታዊ ጥያቄ እንደምንኖር አይደለም፣ ነገር ግን ከሞትን በኋላ ከማን ጋር ነው የምንኖረው የሚለው ነው። ሁላችንም ወደ አግዚአብሔር መገኛ ስንመለስ እያንዳንዳችን ከእርሱ ጋር አንቆይም።

በሟችነት ጊዜአችን እያንዳንዳችን በሀጢያት እና በመተላላፍ እንቆሽሻለን።29 ንፁ የማይሆኑ ሃሳቦች፣ ቃሎች እና ስራዎች ይኖሩናል።30 በአጭሩ ንፁ አንሆንም። ኢየሱስ ግልፅ አድርጎ በእግዙአብሔር ፊት ንፁ ያለመሆን ውጤት አስቀምጦታል፥ “ምንም ንፁ ያልሆነ… በእርሱ መገኛ ሊኖር አይችልም።”31 ያ እውነታ ወደ ወጣቱ አልማ ቤት ተወስዶ ነበር። ከቅዱስ መልዐክ ጋር ሲገናኝ በእሱ ንፁ አለመሆን የተነሳ በጣም ተሰቃይቶ፣ ተጨንቆ እና ተጎድቶ “ነፍሰ እና ስጋዬም ፈፅሞ እንደሚጠፋ… በአምላኬ ፊት እንደማልቆም” ተሰምቶት ነበር።32

የቅዱስ ቁርባኑን ውኃ በመካፈል፣ እንዴት ከሀጢያት እና ከመተላለፍ ንፁ መሆን እንደምንችል እንማራለን እናም ስለሆነ በእግዚአብሔር መገኛ መቆም እንችላለን። ንፁ ደሙን በማፈፍስስ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእያንዳንዱ ሀጢያት እና መተላለፍ የፍትህን ፍርድ አሟልቷል። ንስሀ ለመግባት በእርሱ እምነት ካለን፣ የደህንነትን ስነ-ስርዓቶች እና ቃል-ኪዳኖችን ከጥምቀት ጀመሮ ከተቀበልን እና መንፈስ ቅዱስን ከተቀበልን ንፁ ሊያደርገን እድል አቀረበ። መንፈስ ቅዱስ ከተቀበልን በኋላ እንነፃለን እንዲሁም እንቀደሳለን። ኢየሱስ ይህንን ትምህርት በጣም ግልፅ እንደዚህ በማለት አደረገልን፥

“በመንግስተ ሰማይ ረከሰ ነገር ሊገባ አይችልም።… በደሜ ልብሳቸውን ካፀዱት በስተቀር በእረፍቱ የሚገባ ማንም የለም።…

“እንግዲህ ትዕዛዜ ይህች ናት፥ በምድር ዳርቻ ያላችሁ ሁሉ ንስሀ ግቡ፣ እና ወደ እኔ ኑ፣ መንፈስ ቅዱስን በመቀበል ትቀደሱ ዘንድ በስሜ ተጠመቁ።”33

ይህ የክርስቶስ ትምህርት ነው።34 ይህንን ትምህርት ስንቀበል እና ሕይወታችንን በዛ መሰረት ስንመራ፣ በእውነቱ በክርስቶስ ደም ታጥበናል እና ነፅተናል።35

በቅዱስ ቁርባን ፀሎቶች አማካኝነት፣ ለእዚህ የክርስቶስ ትምህርት ተቀባይነታችንን እና በዛ መሰረት ለመኖር የእኛን መሰጠት እንገልፃለን። ለእግዚአብሔር የዘላለም አባታችን ፀሎት ውስጥ ውድ ልጁን “ሁል ጊዜ እንደምናስታውሰው” እናውጃለን። መጀመሪያ፣ ለማስታወስ ፍቃደኝነታችንን እንመሰክራለን። ከዛ በእርግጥ እንደምናስታውስ እንመሰክራለን። ይህን በማድረግ ውስጥ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እና እኛን ከሞት እና ከሀጢያት ላዳነን እምነት ለመለማመድ ቁርጠኝነትን እናደርጋለን።

በተጨማሪም “ትዕዛዞቹን እንደምንጠብቅ” እናውጃለን። ያ ንስሀ ለመግባት መሰጠት ነው። ሀሳባችን፣ ቃሎቻችን ወይም ድርጊቶቻችን ካለፉት ጊዜ መሆና ካለባቸው ከቀነሱ፣ እራሳችንን እንደገና በሚመጡት ቀናት ውስጥ ሕይወታችንን ከእርሱ ጋር ለማጣበቅ በበለጠ ሁኔታ በድጋሚ ቃል እንገባለን።

“የልጁን ስም በላያችን ላይ ለመውሰድ ፍቃደኞች እንደሆንን” እናውጃለን።36 ያ እራሳችንን ለእርሱ ስልጣን አሳልፎ ለመስጠት እና ለራሳችን የመዳን ስነ-ስርዓቶችን እና ቃል-ኪዳኖችን መቀበልን የሚያካትተውን ስራውን ለመስራት ቅን መሰጠት ነው።37

እራሳችንን ለእነዚህ መርሆች ስንሰጥ፣ በቅዱስ ቁርባን ፀሎት ውስጥ “የእርሱ መንፈስ ከእኛ ጋር እንደሚሆን” ቃል ተገብቶልናል።38 መንፈስ ቅዱሰን እንደገና መቀበል በጣም ታላቅ በረከት ነው። ምክንያቱም መንፈሱ ከሀጢያት እና ከመተላለፍ የሚያነፃን እና የሚቀድሰን ተወካይ ነው።39

ወንድሞች እና እህቶች፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ እና በዘለአለም ውስጥ በጣም አስፈላጊ ሆነው ክስተት ኢየሱስ ክርስቶስ ሀጢያት ክፍያ ነው። የሀጢያት ክፍያውን ያከናወነው የቅዱስ ቁርባንን ስነ-ስርዓት እንድናስታውስ እንዲረዳን ብቻ ሳይሆን ዚህን ታላቅ የፀጋ ተግባር በረከቶችን እንድንሻ ሰጥቶናል። በዚህ ቅዱስ ስነ-ስርዓት ውስጥ በተደጋጋሚ እና በቅንነት መሳተፍ ከጥምቀት በኋላ እና የመንፃት ሂደትን ተከትለን እንድንጨርስ ለመርዳት የክርስቶስን ትምህርት እንድናቅፍ እና እንድንኖር ይረዳናል። በእርግጥ የቅዱስ ቁርባን ስነ-ስርዓት በእምነት እስከ መጨረሻው እንድንፀና እና ኢየሱስ እንዳደረገው በፀጋ ላይ ፀጋ የአባትን ሙሉነት እንድንቀበል ይረዳናል።40

የኢየሱስ ክርስቶስን ሁላችንንም ከሞት እና ከሀጢያት የማዳን ኃይል እንዲሁም የክህነቱ የስነ-ስርአቶች ኃይል ቅዱስ ቁርባንን ጨምሮ “የአባት የእግዚአብሔርን ፊት እንድናይ እና እንድንኖር”41 እንደሚያዘጋጀን እመሰክራለው። በሚቀጥለው ሳምንት እንዲሁም በእያንዳንዱ በሚከተለው ሳምንት ቅዱስ ቁርባንን ጥልቅ በሆነ ምኞት እና የበለጠ ቅን በሆነ አላማ እንድንወስድ እፀልያለው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።