ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 27–ህዳር 2 (እ.አ.አ)፦ “ቤት በስሜ”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124


“ጥቅምት 27– ህዳር 2፦ ‘ቤት በስሜ’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
የናቩ፣ ኢለኖይ ስዕል

ቆንጆዋ ናቩ፣ በሌሪ ሲ. ዊንቦርግ Copyright 2023

ጥቅምት 27–ህዳር 2 (እ.አ.አ)፦ “ቤት በስሜ”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124

ያለፉት ስድስት ዓመታት ለቅዱሳን አስቸጋሪ ቢሆኑም፣ በ1839(እ.አ.አ) ፀደይ ላይ ነገሮች ቀና ማለት ጀመሩ፦ ስደተኞቹ ቅዱሳን ከክውንሲ፣ ኢለኖይ ዜጎች ዘንድ ርህራሄን አግኝተዋል። ጠባቂዎች ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች የቤተክርስቲያኗ መሪዎች በሚዙሪ ምርኮን እንዲያመልጡ ፈቀዱላቸው። እናም ቅዱሳን እንደገና የሚሰበሰቡበት መሬት ቤተክርስቲያኗ በኢለኖይ ውስጥ ገዛች። አዎ፣ ረግረጋማ የሆነ፣ በትንኝ የተሞላ መሬት ነበር፣ ነገር ግን ቅዱሳን ቀድሞ ካጋጠሟቸው ፈተናዎች ጋር ሲወዳደሩ፣ ይህ ለመኖር የሚቻልበት ይመስል ነበር። ስለዚህ ረግረጋማውን መሬት አደረቁ እና ናቩ ብለው ለጠሯት አዲስ ከተማ መተዳደሪያን አዘጋጁ። ይህም ስም በእብራይስጥ “ቆንጆ” ማለት ነው፣ ምንም እንኳን በጊዜው ከቀጥተኛ አባባል ይልቅ ቢያንስም የእምነታቸው መግለጫ ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ጌታ ነቢዩን በጥድፊያ ስሜት እየገፋፋው ነበር። ዳግም የሚመልሳቸው ተጨማሪ እውነቶች እና ሥርዓቶች ነበሩት፣ እንዲሁም “[ቅዱሳኑን] በክብር፣ ህያውነት፣ እና በዘለአለማዊ ህይወትንም [ለማጎናፅፍ]” ይፈልጋል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥55)። በብዙ መንገዶች፣ እንደእነዚህ ተመሳሳይ የሆኑ የእምነት እና አጣዳፊ ስሜቶች በዛሬውም የጌታ ስራ የሚታዩ ናቸው።

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥399–427፤ “ቤተክርስቲያኗን በናቩ ማደራጀት፣” Revelations in Context [ራዕያት በአገባብ] 264–71 ተመልከቱ።

በኢለኖይ ውስጥ ስለሚገኙት የቤተክርስቲያኗ ታሪካዊ ቦታዎች በተጨማሪ ተማሩ

ምስል
የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥2–11

ሌሎች ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ መጋበዝ እችላለሁ።

ጌታ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ “ለሁሉም ሀገሮች መሪዎች” “[ወንጌሉን] … በቅድስና [እንዲያውጅ]” ነገረው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥2–11 ተመልከቱ)። ይህን ሀላፊነት ቢሰጣችሁ፣ የእናንተ አዋጅ ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ዳግም ስለተመለሰው ወንጌሉ ምን ይላል? እንዲሁም በየቀኑ ከምትገናኟቸው ሰዎች ጋር ምስክርነታችሁን በተለምዶ እና በተፈጥሮ እንዴት ማካፈል እንደምትችሉ አስቡ።

በተጨማሪም “የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሙላት ዳግም መመለስ፦ ለሁለት መቶኛ አመት መታሰቢያ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” ወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥12–21

ጌታ የሚያምነው ደቀመዝሙር መሆን እችላለሁ።

አዳኝ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥12–21 ውስጥ እንዳደረገው፣ እናንተም ከሌሎች ጋር በእነርሱ የምታዩትን የክርስቶስ አይነት ባህርይ ለማካፈል አስቡበት። ፍቅሩን እና እምነቱን ለእናንተ የገለፀላችሁ እንዴት ነው?

በተጨማሪም ሪቻርድ ጄ. ሜይንስ, “Earning the Trust of the Lord and Your Family[የጌታን እና የቤተሰባችሁን አመኔታ ማግኘት]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 75–77።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥22–24፣ 60–61

ጌታ ሌሎችን እንድቀበል ይፈልጋል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥22–24፣ 60–61 ውስጥ ባሉት የጌታ መመሪያዎች ላይ ስታሰላስሉ፣ ቤታችሁን እና አጥቢያችሁን ጌታ ናቩ እንድትሆን እንዳሰበው እንዴት ማድረግ እንደምትችሉ አስቡ።

በተጨማሪም “የሁሉም ጓደኛ” (ቪዲዮ), ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

ምስል
የናቩ ቤተመቅደስ በሚገነባበት ጊዜ

ጆሴፍ ስሚዝ በናቩ ቤተመቅደስ ዝርዝር በጌሪ ኢ. ስሚዝ

ትምህር እና ቃል ኪዳኖች 124፥25–45፣ 55

ቤተመቅደስ ለጌታ የምንገነባው ቅዱስ ስርዓቶችን ለመቀበል ነው።

ጌታ ለምን ህዝቡ “ለቅዱስ ስሜ ህዝቤ ሁልጊዜ [ቤተመቅደስ] እንዲገነቡ” የሚያዝዝ ይመስላችኋል? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥25–45፣ 55 ውስጥ የምታገኟቸውን ምክንያቶች ለመዘርዘር አስቡበት። ሌሎችንም “We Love Thy House, O God [ቤትህን እናፈቅራለን፣ አምላክ ሆይ]” (መዝሙሮች፣ ቁ. 247) አይነት መዝሙር ውስጥ ወይም “What Is a Temple? [ቤተመቅደስ ምንድን ነው?]” በሚል ቪድዮ ውስጥ ማግኘት ትችሉ ይሆናል (የወንጌል ላይብረሪ)። የቤተመቅደስ ግንባታ ሥራ ጌታ እንደሚወዳችሁ ምልክት ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?

የናቩ ቤተ መቅደስ (እ.አ.አ) በ1840 ዎቹ ከተገነባ ጊዜ ጀምሮ፣ ከ300 በላይ ቤተመቅደሶች ተገንብተዋል ወይም እንደሚገነቡ ማስተዋወቂያ ተሰጥቷል። ፕሬዚዳንት ራስል ኤም ኔልሰን እንዳስተማሩት፦ “በቤተመቅደስ ውስጥ የምናሳልፋቸው ጊዜዎች “ለእኛና ለቤተሰቦቻችን ደህንነት እና ከፍ መደረግ አስፈላጊ እንደሆኑ እናውቃለን። … የጠላት ጥቃቶች፣ በትልቅነት እና በአይነት፣ በብዙ እጥፍ እያደጉ ናቸው። በቤተመቅደስ ውስጥ በየጊዜው ለመገኘት ያለን ፍላጎት ከዚህ በፊት ከነበረው በላይ ታላቅ ነው” (“አርአያ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን መሆን፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 114)። ቤተመቅደስ “የጠላትን ጥቃቶች” ለመቋቋም የረዳችሁ እንዴት ነው? የፕሬዚዳንት ኔልሰንን ምክር ለመከተል ምን አይነት ነገር የማድረግ ስሜት ይሰማችኋል?

በተጨማሪምWhy Latter-day Saints Build Temples [የኋለኛው ቀን ቅዱሣን ቤተመቅደሶችን ለምን እንደሚገነቡ]temples.ChurchofJesusChrist.org ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥45–55

ጌታ ትእዛዛቱን ለማክበር የሚጥሩ ሰዎችን ይባርካል።

ቅዱሳን በጃክሰን ካውንቲ፣ ሚዙሪ ቤተመቅደስ እንዲገነቡ ታዘው ነበር፣ ነገር ግን “በጠላቶቻቸውም[ተደናቀፉ]” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥51)። ቁጥር 49–55 የእግዚአብሔርን ትእዛዛት መታዘዝ ለሚፈልጉ ነገር ግን በቤተሰብ ወይም በሌሎች ሁኔታዎች ምክንያት እንዳይፈጽሙ ለሚከለከሉ ሰዎች የሚያረጋጋ መልእክት ይዟል። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ፣ እንዲህ ባለ ሁኔታ ውስጥ ላለ ሠው ሊረዳ የሚችል ምን ምክር ታገኛላችሁ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥91–92

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
ጌታ በፓትሪያርክ በረከት በኩል ይመራኛል።

የነቢዩ አባት የሆኑት ጆሴፍ ስሚዝ፣ ቀዳማዊ ከሞቱ ከአጭር ጊዜ በኋላ፣ ጌታ ሀይረም ስሚዝን አባቱ ይዘውት ወደ ነበረው ጥሪ ጠራው—የቤተክርስቲያኗ ፓትሪያርክ። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥91–92 ውስጥ ስለዚህ ነገር ልታነብቡ ትችላላችሁ።

ስለፓትሪያርኮች እና ስለፓትሪያርክ በረከቶች ታሪክ ተጨማሪ ለማወቅ፣ እዚህ ይጫኑ

ከዚህ በፊት ስለፓትሪያርክ በረከት ሰምተው ለማያውቁ ሠዎች እንዴት ትገልፁታላችሁ? አንድ ሰው ይህን እንዲቀበል ለማበረታታት ምን ትላላችሁ? ለእነዚህ ጥያቄዎች መልሶች ለማግኘት በሽማግሌ ራንዶል ኬ ቤኔት መልእክት “Your Patriarchal Blessing—Inspired Direction from Heavenly Father [የፓትሪያርክ በረከቶች—” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)፣ 42–43) ውስጥ ወይም Topics and Questions [ርዕሶች እና ጥያቄዎች]፣ “የፓትሪያርክ በረከቶች” (የወንጌል ላይብረሪ) ተመልከቱ።

ባጠናችኋቸው እና ባጋጠሟችሁ ነገሮች መሠረት፣ የሚከተለውን አረፍተ ነገር እንዴት እንደምትጨርሱ አስቡ፦ “የፓትሪያርክ በረከት እንደ ነው።” የሰማይ አባት ልጆቹ የፓትሪያርክ በረከት እንዲቀበሉ የሚፈልገው ለምንድን ነው?

የፓትሪያርክን በረከት ካልተቀበላችሁ፣ ለመቀበል ለመዘጋጀት ምን ማድረግ ትችላላችሁ? የፓትሪያርክ በረከት ከተቀበላችሁ፣ ይህን ስጦታ ከፍ አድርጋችሁ እንደምትመለከቱት ለእግዚአብሔር ለማሣየት የምትችሉት እንዴት ነው?

በተጨማሪም ካዙሂኮ ያማሺታ፣ “When to Receive Your Patriarchal Blessing [የፓትሪያርክ በረከታችሁን መቼ እንደምትቀበሉ]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ፣ 88–90፤ አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ18.17፣ የወንጌል ላይብረሪ።

ከልብ ማስተማር። ማስተማር በጣም ጠቃሚ የሚሆነው የግል ልምዶችን እና ምስክርነቶችን ሲያካትት ነው። ለምሳሌ፣ የፓትሪያርክ በረከት የተቀበላችሁ ከሆነ፣ ስለእነዚህ ልዩ በረከቶች ለማስተማር ስትዘጋጁ ከልሱት። ስለ በረከቶቻችሁ አመስጋኝ የሆናችሁት ለምንድን ነው? ሌሎች የራሳቸውን እንዲቀበሉ እና የፓትሪያርክ በረከቶችን በተደጋጋሚ እንዲያጠኑ የምታነሳሱት እንዴት ነው?

ምስል
የልጆች ክፍል ምልክት 02

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥15፣ 20

ኢየሱስ ክርስቶስ ቅንነትን ይወዳል።

  • ልጆች ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥15፣ 20 የተማሩትን እንዲያስታውሱ ለመርዳት፣ የልብ ቅርፅ እንዲሥሉ እና ከርክመው እንዲያወጡት ልትረዷቸው ትችላላችሁ። በልቦችም ላይ፣ ከእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ዋና ሀረጎችን እንዲፅፉ ልትረዷቸው ትችላላችሁ። እንደ “Stand for the Right [ትክክል ለሆነው ቁሙ]” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣፣ 159) ዓይነት መዝሙር ይህን ውይይት ለማጠናከር ሊረዳ ይችላል።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥15፣ 20ን አብራችሁ ካነበባችሁ በኋላ፣ ምናልባት በገጽ 31 ላይ በለወጣቶች ጥንካሬ፥ ምርጫ የማድረግ መመሪያ ውስጥ የሚገኘውን በሐቀኝነት መኖር ምን ማለት እንደሆነ ልጆቻችሁ እንዲያውቁ ለመርዳት ትችሉ ይሆናል። ጌታ “በ[ጆርጅ ልብ] ሐቀኝነት ምክንያት” በቁጥር 20 ላይ በተለይ ስለ ጆርጅ ሚለር ምን አለ? እንዲሁም ከራሳችሁ ልምድ ወይም ከጓደኛ መጽሄት ካገኛችሁት ሐቀኝነትን የሚያሳዩ ምሳሌዎችን ማጋራት ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ በዚህ ሳምንት ሐቀኝነትን ለማሳየት ግብ እንዲያወጡ ጋብዙ እና ሲያደርጉ ምን እንደተሰማቸው እንዲነግሯችሁ አድርጉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥28–29፣ 39

እግዚአብሔር ህዝቡ ቤተመቅደሶችን እንዲገነቡ አዝዟል።

  • የጥንት ቤተመቅደስን እና ከሚኖሩበት ቦታ ቅርብ የሆነ ቤተመቅደስን ጨምሮ፣ ልጆቻችሁ የቤተመቅደሶችን ሥዕሎች መመልከት ያስደስታቸው ይሆናል (ChurchofJesusChrist.org/temples/list ተመልከቱ)። እነዚህን ፎቶዎች እና ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥39ን፣ በጥንትም ጊዜ ሆነ በእኛ ቀናት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝቡን ቤተመቅደስ እንዲገነቡ ሁልጊዜም እንደሚያዝ ለመግለጽ ልትጠቀሙባቸው ትችላላችሁ (በተጨማሪም የዚህን ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ ተመልከቱ)።

  • በቤተመቅደስ አቅራቢያ የምትኖርሩ ከሆነ፣ ልጆቻችሁን ወደዚያ መውሰድን እና በቤተመቅደሱ ግቢ ውስጥ በጥልቅ አክብሮት መራመድን አስቡ። በቤተመቅደሱ ውጫዊ ክፍል ላይ “ቅድስና ለጌታ—የጌታ ቤት” የሚሉትን ቃላት እንዲፈልጉ ጋብዟቸው። እነዚህ ቃላት ምን ትርጉም እንዳላቸው ከልጆቻችሁ ጋር ተነጋገሩ።

  • ልጆቻችሁ ወደ ቤተመቅደስ ለመግባት ለሚችሉበት ቀን በጉጉት እንዲጠብቁ ለመርዳት፣ በአባሪ ሀ ውስጥ የሚገኘው “ለቅድመ ዓያቶች መጠመቅ እና ማረጋገጫ መቀበል” የሚለውን ርዕስ መጠቀምን አስቡ (በተጨማሪም “ቤተመቅደስና እና የደስታ እቅድ” በአባሪ ለ ውስጥ ተመልከቱ)።

ምስል
የሰለሞን ቤተመቅደስ

የሰሎሞን ቤተመቅደስ፣ በሳም ሎውሎር

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥91–92

ጌታ በፓትሪያርክ በረከት በኩል ይባርከኛል።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 124፥95–92 አብራችሁ ስታነቡ፣ ልጆቻችሁ ጌታ ሀይረም ስሚዝን ምን እንዲያደርግ እንደጠራው እንዲፈልጉ እርዷቸው። የፓትሪያርክ በረከት ምን እንደሆነ ተነጋገሩ፦ ይህም ጌታ ስለራሳችን ማንነት እና ምን እንድንሰራ እንዲሁም ማን እንድንሆን እንደሚፈልግ የሚያስተምረን ልዩ በረከት ነው። በአባሪ ሀ ውስጥ የሚገኘውን የፓትርያርክ በረከትን መቀበል አንቀጽ ልጆቻችሁ የፓትሪያርክ በረከትን እንዲቀበሉ ለማዘጋጀት እንዲረዳችሁ ለመጠቀም አስቡበት።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

አትም