ቅዱሳት መጻህፍት
፫ ኔፊ ፳፩


ምዕራፍ ፳፩

መፅሐፈ ሞርሞን ሲመጣ እስራኤል ትሰበሰባለች—አህዛብም ነፃ ህዝብ በመሆን በአሜሪካ ይደራጃሉ—ካመኑ እናም ታዛዥ ከሆኑ ይድናሉ፤ አለበለዚያ ይቆረጣሉ እናም ይጠፋሉ—እስራኤል አዲሲቷን ኢየሩሳሌ ትመሰርታለች፣ እናም የጠፉት ነገዶችም ይመለሳሉ። ፴፬ ዓ.ም. ገደማ።

እናም እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች፣ ህዝቤን የእስራኤልን ቤት፣ ለረጅም ጊዜ ከተበተኑበት የምሰበስበት፣ እናም በድጋሚም ፅዮንንም በመካከላቸው የምመሰርትበት የሚፈፀሙበትን ጊዜ ታውቁ ዘንድ ምልክትን እሰጣችኋለሁ—

እናም እነሆ፣ ለምልክት እንዲሆናችሁ የምሰጣችሁ ነገር ይህ ነው—እውነት እላችኋለሁ የያዕቆብ ቤት ስለሆኑት እነዚህ ሰዎች በተመለከተ፣ እናም በእነርሱም ስለሚበተኑት ህዝቦቼ በተመለከተ እነዚህን የምነግራችሁና፣ ከዚህ በኋላም በራሴና፣ አብም በሚሰጣችሁ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት የሚታወጅላችሁ ነገሮች ያውቁ ዘንድ ለአህዛብ እንዲያውቁት ይደረጋል፤

እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በአብ አማካኝነት እነዚህን ነገሮች እንዲያውቁ በሚደረግበት እናም በአብም ከእነርሱም ወደ እናንተ በሚመጣበት ጊዜ፤

እነዚህ ነገሮች ከእነርሱ ለዘራችሁ ቅሪት ይመጡ ዘንድ፤ ይኸውም አብ ከህዝቡ ከእስራኤል ቤት ጋር የገባው ቃል ኪዳን ይፈፀም ዘንድ፣ ይህ እነርሱ በዚች ምድር ይደራጁ ዘንድ፣ እናም በአብ ኃይልም ነፃ ሰዎች በመሆን ይቋቋሙ ዘንድ፣ ይህ የአብ ጥበብ ነውና።

ስለዚህ፣ ይህም ሥራ እናም በመካከላቸሁ ከዚህም በኋላ የሚሰራው በአህዛብ አማካኝነት በክፋታቸው እምነት አጥተው ለመነመኑት ለዘሮቻችሁ በሚደርስበት ጊዜ፤

ኃይሉን ለአህዛብ ያሳይ ዘንድ፣ ይህም ከአህዛብ እንዲመጣ፣ ይኸውም አህዛብ ልባቸውን ካላጠጠሩ፣ ንሰሃ ቢገቡና በስሜ ቢጠመቁ እናም የትምህርቴን እውነተኛ ነጥቦች ቢያውቁ፤ ከህዝቦቼም ከእስራኤል ቤት ጋር እንዲቆጠሩ የአብ ፈቃድ ነውና፤

እናም እነዚህ ነገሮች በሚሆኑበት ጊዜ ዘሮቻችሁ እነዚህን ነገሮች ማወቅ ይጀምራሉ—ይህም የእስራኤል ቤት ለሆኑት የገባው ቃል ኪዳን እንዲፈፀም የአብ ስራ እንደተጀመረ እንዲያውቁ ዘንድ ለምልክት ይሆንላቸዋል።

እናም ያ ቀን በሚመጣበትም ጊዜም ነገሥታት አፋቸውን ይዘጋሉ፤ ያልተነገራቸውን ያያሉና፤ እናም ያልሰሙትን ያስተውላሉን።

በዚያን ቀን፣ ለእኔም ሲል አብ ሥራን ይሰራል፣ ሥራውም በመካከላቸው ታላቅ እንዲሁም ድንቅ ሥራ ይሆናል፤ እናም አንድ ሰው ለእነርሱ ቢያውጅላቸውም በእነርሱ መካከል ይህን የማያምኑ ይኖራሉ።

ነገር ግን እነሆ፣ የአገልጋዬ ህይወት በእጄ ትሆናለች፤ ስለዚህ ምንም እንኳን በእነርሱ የተነሳ እርሱ ቢጠፋም፣ አይጎዱትም። ይሁን እንጂ እርሱን እፈውሰዋለሁ፤ ማስተዋሌም ከዲያብሎስ ሴራ የበለጠ መሆኑን አሳያቸዋለሁ።

፲፩ ስለዚህ አብም እርሱን ወደ አህዛብ እንዲያመጣው ባደረገው፣ እናም ለአህዛብ ያመጣው ዘንድ ስልጣንን በሰጠው ኢየሱስ ክርስቶስ በሆንኩት በእኔ ቃል የማያምን፣ (ሙሴ እንደተናገረውም ይፈፀማል) የቃል ኪዳን ህዝብ ከሆኑት ከህዝቦቼም መካከል ይለያል

፲፪ እናም ህዝቤ የያዕቆብ ቅሪት የሆኑት ከአህዛብ መካከል ይሆናሉ፤ አዎን በመካከላቸው በዱር አውሬዎች መካከል እንዳለ አንበሳ፣ በበጎች መንጋ መካከል ከሄደ እንደሚረጋግጣቸውና፣ እንደሚቆራርጣቸው የአንበሳ ግልገል ይሆናሉ፣ እናም ማንም ለማዳን አይቻለውም።

፲፫ እጃቸው በጠላቶቻቸው ላይ ከፍ ይላል፣ እናም ጠላቶቻቸው ሁሉ ይጠፋሉ።

፲፬ አዎን፣ ንሰሃ ካልገቡ ለአህዛብ ወዮላቸው፤ አብም እንዲህ ይሆናል ይላል፣ በዚያም ቀን ፈረሶቼን ከመካከላቸው አጠፋለሁ፣ ሰረገሎቻቸውንም እሰብራለሁ።

፲፭ እናም የምድራችሁን ከተሞች አጠፋለሁና ምሽጎቻችሁን በሙሉ አፈራርሳለሁ፤

፲፮ እናም መተትንም ከምድራችሁ አጠፋለሁና፣ ምዋርተኞችም ከእንግዲህ አይኖራችሁም፤

፲፯ የተቀረፀውን ምስላችሁን እና ሐውልቶቻችሁንም ደግሞ በመካከላችሁ አጠፋለሁ፣ እናም ከእንግዲህ የእጆቻችሁን ስራ አታመልኩም፤

፲፰ እናም የማምለኪያ ዐፀዶቻችህንም ከመካከላችሁ እነቅላለሁ፥ ከተማዎቻችሁንም አፈርሳለሁ።

፲፱ እናም እንዲህ ይሆናል፣ ሀሰቶችም፣ ማጭበርበርም፣ ምቀኝነትም፣ ፀብም፣ የካህናት ተንኮል፣ እናም ዝሙት ሁሉ ከእንግዲህ ይወገዳሉ።

አብም እንዲህም ይሆናልና ይላል፣ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በዚያን ቀን ንሰሃ ያልገባ፣ እናም ወደ ተወደደው ልጄ ያልመጣ ከህዝቤ መካከል እለየዋለሁ፤

፳፩ እናም አረመኔዎች ላይ እንደማደርገውም፣ በእነርሱም ላይ ተለማምደው በማያውቁት ዓይነት ቁጣ እና መዓት እበቀላቸዋለሁ።

፳፪ ነገር ግን ንሰሃ ከገቡና ቃሌን ካዳመጡ፣ እናም ልባቸውንም ካላጠጠሩ፣ ቤተክርስቲያኔን በእነርሱ መካከል እመሰርታለሁና፣ ወደ ቃልኪዳኑ ይመጣሉ፣ እናም ለርስታቸውም ምድሪቷን ከሰጠኋቸው ከእነዚህ ከያዕቆብ ቅሪቶች ጋር ይቆጠራሉ

፳፫ እናም የያዕቆብ ቅሪት የሆኑ ህዝቦቼንና፣ ደግሞ የሚመቱትን የእስራኤል ቤት የሆኑትን ሁሉ፣ እነርሱም አዲሲቷ ኢየሩሳሌም ተብላ የምትጠራውን ከተማ ይመሰርቱ ዘንድ ይረዳሉ።

፳፬ እናም ከዚያም በምድረ ገፅ ላይ በሙሉ የተበተኑትን፣ በአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ይሰባሰቡ ዘንድ ህዝቦቼን ይረዳሉ።

፳፭ እና ከዚያም የሰማይ ኃይልም በእነርሱ መካከል ይወርዳል፤ እናም ደግሞ እኔም በመካከላቸው እሆናለሁ።

፳፮ እናም በዚያን ቀንም ይህም ወንጌል በዚህ ህዝብ ቅሪት በሆኑት መካከል በሚሰበክበት ወቅት የአብ ስራ ይጀመራል። እውነት እላችኋለሁ፣ በዚያን ቀን በተበተኑት ህዝቦቼ መካከል፣ አዎን፣ አብ ከኢየሩሳሌም ባስወጣቸው፣ በጠፉት ነገዶችም መካከል ቢሆን የአብ ስራ ይጀመራል።

፳፯ አዎን፣ አብን በስሜ ይጠሩት ዘንድ ወደ እኔም እንዲመጡ መንገዱን ለማዘጋጀት በተበተኑት ህዝቦቼ ሁሉ መካከል ስራው ከአብ ጋር ይጀመራል።

፳፰ አዎን፣ እናም ህዝቡም ወደ ራሱ ሀገር፣ ወደ ርስት ምድሩ ይሰበሰብ ዘንድ መንገድን በማዘጋጀት በሀገሪቱ ሁሉ መካከል ከአብ ጋር ስራው ይጀመራል።

፳፱ እናም እነርሱም ከሁሉም ሀገሮች ይወጣሉ፤ እናም በችኮላም ሆነ በመኮብለል አይሄዱም፣ አብም እኔም በፊታቸው እሄዳለሁም፣ በኋላቸውም ጠባቂአቸው እሆናለሁ ይላልና።