ምዕራፍ ፳፭
በዳግም ምፅዓት ጊዜ ትዕቢተኞች፣ እናም ኃጢአተኞች እንደገለባ ይቃጠላሉ—ኤልያስ ከታላቁና ከአስፈሪው ቀን በፊት ይመለሳል—ሚልክያስ ፬ን አነጻፅሩ። ፴፬ ዓ.ም. ገደማ።
፩ እነሆም፣ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድ ቀን ይመጣል፤ እናም ትዕቢተኞች ሁሉ አዎን፣ እናም ኃጢያትን የሚሰሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፤ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፤ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም ይላል የሠራዊት ጌታ።
፪ ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩ፣ ለእናንተ የፅድቅም ልጅ ፈውስን በክንፎቹ ይዞ ይነሳል፤ እናንተም ትወጣላችሁ እናም እንደጥጃም በበረት ታድጋላችሁ።
፫ እናም ክፉዎችን ትረግጡአችዋላችሁ፤ እናም ይህንን በምሰራበት ቀን በደለኞች ከእግራችሁ ሥር አመድ ይሆናሉ፣ ይላል የሠራዊት ጌታ።
፬ ለእስራኤል ሁሉ ስርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝሁትን የባሪያዬን የሙሴን ህግ አስቡ።
፭ እነሆ፣ ታላቁና የሚያስፈራው የጌታ ቀን ሳይመጣ ነቢዩ ኤልያስን እልክላችኋለሁ፤
፮ እናም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፣ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።