ቀና ስለመሆን
እራሳችንን ትሁት እናድርግ እና ከሰው ሙገሳ ይልቅ እይታችንን ወደ እግዚአብሔር ፍቃድ ብቻ እናድርግ።
በ18ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ውስጥ፣ የሩሲያዋ ታላቋ ካተሪን በብዙ ከውጪ አምባሳደሮች ጋር በመሆን የግዛቷን ደቡባዊ ክፍል እንደምትጎበኝ አሳወቀች። የአከባቢው መሪ፣ ግሪጎሪ ፖተምኪ፣ እነዚህን ጎብኚዎች ለማስደነቅ በጣም ፈልጎ ነበር። የሀገሪቱን ስኬቶች ለማየት ረጅም እርቀት ሄደ።
እንደ ጉዞው ክፍል፣ ለአምባሳደሮቹ በዳርቻ ያሉትን በኢንደስትሪ እና ደስተኛ የከተማ ሰዎች የተሞሉትን አስገራሚ መንደሮች በኩራት እየጠቆመች፣ ካተሪን በድኒይፐር ወንዝ ላይ አለፈች። አንድ ችግርብቻ ነበር፤ ለማሳየት ያህል ብቻ ነበር። ፖተምኪን የሱቆች እና ቤቶች የወፍራም ወረቀት የህንፃ ፊተኛ ገፅን አስባስቦ እንደነበር ይነገራል። እንዲያውም የብልፅግና ኢኮኖሚ ገፅታን ለመፍጠር በስራ የተጠመዱ የሚመስሉ ሰራተኞችን አስቀምጧል። በወንዙ መታጠፊያ አከባቢ ዘግጅቱ ሲያበቃ፣ የፖተምኪን ሰዎች የውሸት መንደሮቹን አነሳሱ እና ለካተሪን ቀጣይ እይታ ወደ አነስተኛ ወንዝ በችኮላ ለዝግጅት ሄዱ።
የዘመኑ የታሪክ ምሁራን የዚህን ታሪክ እውነታ ቢጠራጠሩም፣ “ፖተመኪን መንደር” የሚለው ቃል የአለማችን መዝገበ ቃላት ውስጥ ገብቷል። ከሆነው በላይ ነን ብሎ ሌላውን ለማሳመን የሚደረግን ጥረት መጠቆሚያ ሆኗል።
ልቦቻችን በትክክለኛው ቦታ ላይ ናቸውን?
ምርጥ ሆኖ መታየት መፈለግ የሰው ተፈጥሮአዊ ክፍል ነው። አብዛኞቻችን ከቤታችን ውጪ በጣም ጠንክረን የምንሰራው እና ወጣት የአሮናዊ ክህነት ወንድሞች ድንገት ልዩ ሰው ያጋጥመን ይሆን ብለው ፀጉራቸውን በቦታው የሚያስተካክሉት በዚሁ ምክንያት ነው። ጫማችንን በማስዋብ፣ በምርጥ ጠረን በመሽተት፣ ወይም የቤት ለቤት አስተማሪዎች ከመድረሳቸው በፊት ቆሻሻ እቃዎችን መደበቅ ምንም ችግር የለውም። ሆኖም፣ አክርረን ከወሰድነው፣ ለማስደነቅ ያለን ፍላጎት ከጠቃሚነት ወደ መታለያ ይቀየራል።
የጌታ ነብያት “ወደ ጌታ በአፋቸው የሚቀርቡ፣ እና በከንፈራቸው የሚያከብሩት፣ ነገር ግን ልባቸውን ከእርሱ ያራቁትን” አስመልቶ የማስጠንቀቂያ ድምፅ ሁሌም አንስተዋል።1
ልቦቻቸው ትሁት እና ቀና ከነበሩት ሀጢአተኞች ጋር አዳኙ የሚረዳ እና ሩህሩህ ነበር። ነገር ግን እንደ ፀሀፍቶች፣ ፈሪሳዊያን እና ሰዶቃን ላሉ ግብዞች ላይ በፃዲቅ ቁጣ ተነስቶ ነበር-- እነርሱም ሙገሳን፣ ተፅእኖ፣ እና የአለም ሀብት ለማግኘት ሰዎችን ከመባረክ ይልቅ ሲነቅፉ የቆዩ ፃዲቅ መስሎ ለመታየት ሲሞክሩ ነበር። አዳኙም ከ “በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጥ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮች” ጋር አነፃፅሯቸዋል።2
በጊዜአችን፣ “ሀጢአታቸውን የሚሸፍኑ፣ ወይም ኩራታቸውን ወይም ከንቱ ምኞታቸውን ለማርካት” የሚሞክሩ የክህነት ተሸካሚዎችን ጌታ በተመሳሳይ ጠንካራ ቃላት አለው። ይህንን ሲያደርጉ፣ እርሱ እንዲህ አለ “ሰማያት እራሳቸውን ያሸሻሉ፤ የጌታ መንፈስ ያዝናል፤ እና ሲሸሽ፣ ለዛ ሰው ክህነቱ ወይም ስልጣኑ መብቂያ ነው።”3
ይሄ ለምን ይከሰታል? ለምድነው አንዳንዴ በውጪአዊ ንቁ፣ የበለፀግን፣ እና የተሰጠን መስለን ለመታየት የምንሞክረው-- ውስጣችን ግን ባለራእዩ ለኤፌስኦኖች እንዳለው-- እኛም “የቀደመውን ፍቅር(አችንን) ትተናል”? 4
በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ “የእግዚአብሔራዊነት ቅርፅን” “በሀይሉ” 5 በማሳሳት፣ በወንጌል መሰረት ውስጥ ትኩረታችንን አጥተናል። ይሄም ውጫዊ የደቀመዝሙርነት አገላለፃችንን ለግል ጥቅም እና ተፅእኖ ሌሎችን ለማስደነቅ ስናውል በተለየ ሁኔታ አደገኛ ነው። በዚያ ጊዜ ነው ወደ ፈሪሳዊያን ግዛት የመግባት አደጋ ላይ የምንሆነው ፣ እና ፈጣን የአካሄድ ማስተካከያ ለማድረግ ልባችንን መገምገም ያለብን ወሳኝ ሰአት ነው።
ፖተምኪን ዝግጅቶች
ይሄ ከሆነው በተሻለ ለመቅረብ ያለው ፈተና በግል ህይወታችን ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በቤተክርስቲያን ስራችንም ሊገኝ ይችላል።
ለምሳሌ፣ መሪዎች ለአመቱ ምኞታዊ የሆነ አላማን ያቀዱበት አንድ ካስማ አውቃለሁ። አላማዎቹ ወጋ ያላቸው መስለው ቢታዩም፣ ያተኮሩት ሞቅ ባሉ እና በሚያስደንቁ አዋጆች ወይም በቁጥሮች እና ፐርሰንቶች ላይ ነበር።
እነዚህ አላማዎች ውይይት ከተደረገባቸው እና ከተስማሙባቸው በኋላ፣ አንድ ነገር የካስማ ፕሬዘዳንቱን ያሳስበው ጀመር። እንደ በቅርብ ፈት የሆች ልጆች ያላት ወጣት እናቶች ያሉ የካስማ አባላቱን አሰበ። በጥርጣሬ ወይም ብቸኝነት ወይም ያለ መድህን በክፉ የጤና ሁኔታ ስለ ሚታገሉ አባላት አሰበ። በተሰበሩ ትዳሮች፣ ሱሶች፣ ስራ ፈትነት፣ እና የአእምሮ ህመም ላይ ተንጠላጥለው ያሉ አባላትን አሰበ። እና የበለጠ ስለ እነርሱ ባሰበ ቁጥር፣ የበለጠ እራሱን ትሁት የሆነ ጥያቄ ጠየቀ፤ አዲሶቹ አላማዎቻችን በእነዚህ አባላት ህይወት ውስጥ ልዩነትን ይፈጥራሉ ወይ?
“አገልግሎታችን ምንድነው?” ብለው መጀመሪያ ቢጠይቁ ኖሮ እንዴት የካስማው አላማዎች የተለዩ ሊሆኑ እንደሚችሉ ማገናዘብ ጀመረ።
ስለዚህ ይሄ የካስማ ፕሬዘዳንት ወደ አማካሪዎቹ ተመልሶ ሄደ፣ እና በአንድነት ትኩረታቸውን ለወጡ። “የተራቡ፣…መፅዋቾች፣… እርቃናቸውን ያሉ፣… ህሙማን እና የተጎሳቆሉ በአጠገባቸው እያለፉ፣ እነርሱን አለማስተዋልን” እነደማይፈቅዱ ወሰኑ።6
አዲስ አላማዎችን አቀዱ፣ በሰው ዘንድ በእነዚህ አዲስ አላማዎች ስኬት ሁሌ እንደማይለካ በማስተዋል---እንዴት ነው አንድ ሰው የግል ምስክርነትን፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፣ ወይም ለሌሎች ያለንን ርህራሄን ሊለካ የሚችለው?
ነገር ግን ብዙዎቹ “ልትቆጥሩ የምትችሉት ብዙዎቹ ነገሮች፣ አይቆጠሩም። ብዙዎቹ ልትቆጥሩ የማትችሏቸው ነገሮች፣ በእውነትም ይቆጠራሉ ” 7
የድርጅት እና የግል አላማዎቻችን አንዳንዴ የፖተምኪን መንደር የዘመኑ ተመሳሳይ ቢሆኑስ ብዬ አስባለሁ። ከሩቅ አስደናቂ መስለው ነገር ግን የተወዳጅ ሰዎቻችንን ፍላጎት ለማሟላት የማይችሉ ናቸውን?
ውድ ወንድሞቼ እና የክህነት ተሸካሚዎችጓዶች፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ቢቀመጥ እና የሀላፊነታችንን ውጤት ቢጠይቅ፣ በዝግጅቶች እና ቁጥሮች ላይ ይበልጥ ትኩረት ያደርጋል ብዬ አላስብም። አዳኝ ማወቅ የሚፈልገው የልባችንን ሁኔታ ነው። ማወቅ የሚፈልገው በእኛ ጥበቃ ስር ያሉትን፣ ሚስቶቻችንን እና ቤተሰብ እንዴት እንደምንወድ እና እንደምናገለግል--የየቀን ሸክማቸውን እንዴት እንደምናቀል፣ እና ወደ ሰማይ አባት እንዲቀርቡ እንዴት እየረዳናቸው እንደሆነ ነው። እና አዳኝ እኛ እራሳችን ወደ እርሱ በመቅረብ እያደግን መሆኑን ማወቅ ይፈልጋል።
ለምንድነው እዚህ ያለነው?
የራሳችንን ልብ መፈለግ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፣ እራሳችንን ልንጠይቅ እንችላለን፣ ለምንድነው በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የምናገለግለው?
እንዲህም መጠየቅ እንችላለን፣ ለምንድነው ዛሬ እዚህ ስብሰባ ውስጥ ያለነው?
ቀለል ባለ ደረጃ ያንን ጥያቄ ብመልሰው፣ እዚህ ያለሁት ፕሬዘዳንት ሞንሰን ንግግር እንዳደርግ ስላዘዙኝ ነው ማለት የምችል ይመስለኛል።
ስለዚህ በእውነትም አማራጭ አልነበረኝም።
ከዚያ በተጨማሪ፣ ሚስቴ እዚህ እንድካፈል ትጠብቃለች። እና እንዴት ለእሷ አይሆንም ለማለት እችላለሁ?
ነገር ግን ስብሰባዎችን ለመካፈል እና ህይወታችንን እንደ ተሰጠን የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት ለመኖር የተሻሉ ምክንያቶች እንዳሉ ሁላችንም እናውቃለን።
እኔ እዚህ ያለሁበት ምክንያት በሙሉ ልቤ መምህሬን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ስለምፈልግ ነው። በዚህ ታላቅ ምክንያት ከእኔ የሚጠይቀውን ሁሉ ለማድረግ እጓጓለሁ። በመንፈስ ቅዱስ ለመታነፅ እና በተሾሙ አገልጋዮቹ በኩል እግዚአብሔር ሲናገር ድምፁን ለመስማት እራባለሁ። የተሻለ ሰው ለመሆን፣ በክርስቶስ ወንድሞቼ እና እህቶቼ አነሳሽ ምሳሌዎች ከፍ ለማለት እና እርዳታ ለሚፈልጉ በተሻለ እንዴት እንደማገለግል ለመማር ነው እዚህ ያለሁት።
በአጭሩ፣ እኔ እዚህ ያለሁት የሰማይ አባቴን እና ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ስለምወድ ነው።
ይሄ የእናንተም ምክንያት እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ። አዳኝን ለመከተል ማወጅ ብቻ ሳይሆን መስዋእቶችን ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነው ለዚህ ነው ።
ከጭላንጭል ወደ ደመራ
ምስክርነታችሁ የዳበረም እና ጤናማ ይሁን ወይም በቤተክርስቲያን ውስጥ እንቅስቃሴአችሁ የፖተምኪን መንደር በጣም የመሰለ ቢሆን፣ መልካሙ ዜና ባላችሁም ማንኛውም ጥንካሬ ላይ መገንባት ትችላላችሁ። በዚህ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመንፈሳዊ መጠንከር እና ቀን በቀን የወንጌል መርሆችን በመተግበር ወደ አዳኝ መቅረብ ትችላላችሁ።
በትእግስት እና ፅናት፣ የደቀመዝሙርነት ትንሽዋተግባር ወይም ትንሽዋ የእምነት ፍም እንኳ የተቀባ የህይወት ደማቅ ደመራ ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ ማነስ እና ደካማነት ከተሰማችሁ፣ በቀላሉ ደካማ ነገሮችን ጠንካራ ወደሚያደርገው ወደ ክርስቶስ ኑ።8 ከመሀላችን የመጨረሻ ደካማው፣ በእግዚአብሔር ፀጋ፣ በመንፈሳዊ ግዙፍ ሊሆን ይችላል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር “ሰውን አይለይም።”9 እርሱ የእኛ “ታማኝ እግዚአብሔር ነው፣ ከሚወዱት እና ትእዛዙን ከሚጠብቁት ጋር ቃሉን እና ምህረቱን ይጠብቃል።”10
እግዚአብሔር አንድ የጀርመን ደሀ ስደተኛን ከመካከለኛ ቤተሰብ ከቤተክርስቲያን ዋና ቅርንጫፍ ግማሽ አለም እርቆ ከሚገኝ ጦርነት ካመሰው አገር ከደረሰለት እና ከረዳው፣ እናም ለእናንተም እንደሚደርስ የእኔ ፅኑ እምነት ነው።
የተወደዳችሁ በክርስቶስ ወንድሞቼ፣ የፍጥረት እግዚአብሔር፣ ወደ ህዋ ህይወትን የተነፈሰው፣ በእርግጥ ወደ እናንተ ህይወትን ለመተንፈስ ሀይል አለው። በእርግጥም እናንተ መሆን የምትፈልጉትን የብርሀን እና እውነት ቅን መንፈሳዊ ሊያደርጋችሁ ይችላል።
የእግዚአብሔር ቃልኪዳኖች እርግጥ እና እውነተ ናቸው። ከሀጢአታችን ይቅር መባል እና ከእርክስና ሁሉ መንፃት እንችላለን።11 እና በግል ህይወታችን እና በቤተሰባችን ውስጥ እውነተኛ መርሆችን መላበስ እና መኖርን ከቀጠልን፣ ወደ እዚህ ነጥብ እንደርሳለን “ከእንግዲህ ወዲህ አንራብም።… በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛችን ይሆናልና፣ ወደ ህይወትም ውኃ ምንጭ ይመራናል፣ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከአይናችን ያብሳል።”12
ቤተክርስቲያኑ የፈውስ ቦታ ነው፣ የመደበቂያ አይደለም
ነገር ግን እኛ በግል፣ ግትራዊነት፣ እና ድርጅታዊ ከፊል ህንፃ መሳይ ጀርባ ከተደበቅን ይሄ ሊከሰት አይችልም። ይሄ አይነት አረቴፊሻል ደቀመዝሙርነት እኛ በእውነት የሆነውን ከማየት ማገድ ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን በአዳኝ የሀጢአት ክፍያ ተአምር አማካኝነት በእውነት ከመቀየር እኛን ያግደናል።
ቤተክርስቲያኑ ሌሎች መንፈሳዊነታችንን፣ ብቃታችንን፣ ወይም ብልፅግናችንን እንዲያደንቁ እራሳችንን የምናሳየበት የማሳያ ቦታ አይደለም አይደለም። ጥገና የሚያስፈልጋቸው መኪኖች ለጥገና እና መልሶ ለማገልገል የሚመጡበት እንደ አገልግሎት ማእከል ነው።
እና ሁላችንም ጥገና፣ ድጋፍ፣ እና የመልሶጥቅም የመስጠት እርዳታን አያስፈልገንምን?
ወደ ቤተክርስቲያን የምንመጣው ችግሮቻችንን ለመደበቅ ሳይሆን እነርሱን ለማዳን ነው።
እና እንደ ክህነት ተሸካሚዎች፣ ተጨማሪ ሀላፊነት አለብን--- “የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፣ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፣ ለግል ጥቅም ሳይሆን ነገር ግን በበጎ ፍቃድ፤ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እነጂ መኀበሮቻችሁን በኀይል አትግዙ።”13
አስታውሱ፣ ወንድሞች፣ “እግዚአብሔር ትእቢተኞችን ይቃወማል፣ ለትሁታን ግን ፀጋን ይሰጣል።”14
በዚህ ምድር ላይ የተጓዘው ታላቁ፣ ሁሉን ቻዩ፣ ሁሉን አሳኪው ሰው በጣም ትሁትም ነበር። እርሱ በጣም አስደናቂ የሆኑ እንዳንድ አገልግሎቱን በግል ጊዜአት አከናወነ፣ ጥቂት ተመልካች ባለበት፣ እነርሱንም ያደረገውን ለማንም ሰው እንዳይናገሩ ጠየቀ።.15 አንድ ሰው መልካም ብሎ ሲጠራው፣ አስተያየቱን በፍጥነት በመቀየር፣ እግዚአብሔር ብቻ እውነተኛ መልካም እንደሆነ ይገልፃላ።16 በግልፅም የአለም ሙገሳ ለእርሱ ምንም ትርጉም አልሰጠውም፤ ብቸኛ አላማው አባቱን ማገልገል እና “እርሱን የሚያስደስተውን ነገር ሁሌም ማድረግ” ነበር።17 የመምችህራንን ምሳሌ በመከተል መልካምን እናደርጋለን፡፡
እርሱ እንደወደደው እኛም እንውደድ
ወንድሞች፣ ይህ የእኛ ከፍተኛ እና ቅዱስ ጥሪ ነው---የኢየሱስ ክርስቶስ ወኪል መሆን፣ እርሱ እንደወደደው ለመውደድ፣ እርሱ እንዳገለገለው ለማገልገል፣ “የደከሙትን እጆች ከፍ ለማድረግ፣ እና የደከሙ ጉልበቶችን ለማጠንከር፣”18 “ያጡ እና እርዳታ የሚሹትን ለመንከባከብ፣”19 እና ጋለሞታዎችን እና የማደጎ ልጆችን ለመንከባከብ ነው።20
በቤተሰባችን ውስጥ፣ በህብረታችን፣ በአጥቢያችን፣ በካስማችን፣ በማህበረሰባችን፣ እና አገራችን ውስጥ ስናገለግል ለራሳችን ትኩረት የመስጠት ፈተናን እንቋቋማለን እና ፣ በምትኩ፣ በጣም ለበለጠ ክብር፤ ትሁት፣ የጌታችን እና አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅን ደቀመዛሙርት ለመሆን እንጥራለን። ይህን ስናደርግ፣ ወደ ምርጡ፣ በጣም ቅን፣ እና የተከበረው ማንነታችን ወደሚያመራው መንገድ ላይ ስንጓዝ እራሳችንን እናገኛለን። ይህንን በመምህራችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እመሰክራለሁ፣ አሜን።