2010–2019 (እ.አ.አ)
ሰንበት ደስታ ናት
ኤፕረል 2015


14:46

ሰንበት ደስታ ናት

በሰንበት ላይ ያላችሁ ጸባይ ወደ ደስታ እንደሚመራ እንዴት ለማረጋገጥ ትችላላችሁ?

ውድ ወንድሞችና እህቶች፣ እነዚህ የሁለት ቀን ጉባኤዎች ግርማዊ ነበሩ። በሚያነሳሱ መዝሙሮች እና በውበት በተደረጉ ጸሎቶች ከፍ ከፍ ብለናል። በብርሀን እና እውነት መልእክቶችም ነፍሳችን ተሻሽላለች። በዚህች የትንሳኤ ሰንበት፣ በአንድነት እና በልብ እግዚአብሔርን ስለነቢይ እናመሰግናለን።

ለእያንዳንዳችን የሚጠየቀው ጥያቄም፥ በዚህ ጉባኤ በሰማሁት እና በተሰማኝ ምክንያት፣ እንዴት እቀየራለሁ? የሚል ነው። መልሳችሁ ምንም ቢሆንም፣ ስለሰንበት ስላላችሁ ስሜት እና በዚያም ቀን ስላላችሁ ጸባይ እራሳችሁን እንድትመረምሩ እጋብዛችኋለሁ።

ሰንበትን “ደስታ”1 ብሎ በጠራት በኢሳይያስ ቃላት እገረማለሁ። ነገር ግን ሰንበት ለእኔ እና ለእናንተ በእውነትም ደስታ ነችን? ብዬ አስባለሁ።

በሰንበት ደስታ ያገኘሁት እንደ ቀዳጅ ጠጋኝ ዶክተር ብዙ ስራ በነበረብኝ ከብዙ አመት በፊት ነበር፣ ሰንበት የግል መፈወሻ ጊዜ የሆነችው። በእያንዳንዱ ሳምንት መጨረሻ ላይ፣ እጆቼን በሳሙናና ውሀ እና በቡሩሽ በተደጋጋሚ በመፈግፈጌ ምክንያት ይታመማሉ። ብዙ ከሚጠብቅብኝ ስራዬ ሸክም እረፍት ደግሞም ያስፈልገኝ ነበር። ሰንበት በጣም የሚያስፈልገውን እረፍት ሰጠችኝ።

አዳኝ “ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም” ሲል ምን ማለቱ ነበር?2 ከአስቸጋሪው የእለት ተእለቱ ሕይወት እውነተኛ እረፍት እንድናደርግና ለመንፈሳዊና አካላዊ መታደስ እድል እንድናገኝ ሰንበትን ለእኛ የሰጠን ስጦታ እንደሆ እንድንረዳ ፈልጎ እንደነበር አምናለሁ። እግዚአብሔር ይህን ልዩ ቀን የሰጠን፣ ለመዝናኛ ወይም ለእለት ተእለቱ ስራ ሳይሆን ከመንፈሳዊ እና ስጋዊ እረፍት ጋር ከስራ ማረፊያ እንዲሆን ነው።

በእብራውያን ቋንቋ፣ ሰንበት “እረፍት” ማለን ነው። የሰንበት እቅድ አለም ከተፈጠረችበት ጊዜ፣ ከስድስት ቀን ስራ በኋላ ጌታ ከፍጥረት ስራ ባረፈበት፣ የተጀመረ ነው።3 በኋላም ለሙሴ አስሩቱን ትዕዛዛት በሚገልጽበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር “የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ” ብሎ አዘዘ።4 በኋላም፣ ሰንበት እስራኤል ከግብጽ ባርነት መዳናቸውን የሚያስታውሱበት ቀን ሆነች።5 ምናልባት ከሁሉም ጠቃሚ በሆነ መልኩ፣ ሰንበት ጌታ ህዝቡን እንደሚያስቀድስ የምናስታውስበት፣ ቀጣይነት እንዳለው ቃል ኪዳን ተሰጠች።6

በተጨማሪም፣ አሁን በሰንበት ቀን የኢየሱስ ክርስቶስን የኃጢያት ክፍያ በማስታወስ ቅዱስ ቁርባንን እንቀበላለን።7 እንደገናም፣ የእርሱን ቅዱስ ስም በራሳችን ላይ እንደምንወስድ ቃል እንገባለን።8

አዳኝ ራሱን እንደ ሰንበት ጌታ አስተዋውቋል።9 ይህችም የእርሱ ቀን ናት! በተደጋጋሚ፣ ሰንበትን እንድንጠብቅ10 ወይም የሰንበት ቀንን ቅዱስ እንድናደርግ ጠይቆናል።11 ይህን ለማድረግም በቃል ኪዳን ስር ነን።

የሰንበትን ቀን እንዴት ቅዱስ ለማድረግ እንችላለን? በወጣትነቴ፣ በሰንበት ምን መደረግ እና አለመደረግ እንዳለባቸው ሌሎች ሰዎች ያሰባሰቡትን የስራ ዝርዝር አጠና ነበር። በሰንበት የማደርገው እና የግል አስተያየቴ በሰማይ አባቴና በእኔ መካከል ያለ ምልክት እንደሆነ ከቅዱሳት በጻህፍት የተረዳሁት በኋላ ነበር።12 ያንን በመረዳት፣ ይሚደረጉ እና የማይደረጉ ዝርዝሮች አያስፈልጉኝም። የምሳተፍባቸው ለሰንበት ቀን ትክክል እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ውሳኔ ማድረግ ሲኖርብኝ፣ ለእግዚአብሔር ምን ምልክት ለማሳየት እፈልጋለሁ?” ብዬ ራሴን ጠየኩኝ። ያም ጥያቄ ስለሰንበት ቀን ያለኝን ምርጫ ግልጽ ያደርግልኛል።

ስለሰንበት ቀን የሚነካ ትምህርት ከጥንት የመጣ ነው፣ በኋላኛው ቀናትም ከተስፋ ቃል ጋር እንደ አዲስ ቃል ኪዳን ክፍል ታድሷል። ይህን ሀይለኛ መለኮታዊ አዋጅ አድምጡ፥

“ከአለም ነገሮች ራስህን ንጹህ እና ነውር የሌለበት ለማድረግ ወደ ጸሎት ቤት ሂድ፣ እናም በቅዱስ ቀኔም ቅዱስ ስርዓቶችህን አቅርብ፤

“በእውነት ከስራህ እንድታርፍ እናም ለልዑልም አምልኮህን እንድትሰጥ ይህ ቀን ተሰጥቶሀልና፤…

“ጾምህ ፍጹም እንዲሆን፣ … ደስታህ እንዲሞላ፣ ምግብህን በአንድ ልብ [አዘጋጅ]።…በእውነት እላለሁ፣ ይህን ነገር ካላደረግህ፣ የምድር ሙላት፣ እንዲሁም የዱር አራዊቶች እና የሰማይ አዕዋፋት፣

“እነዚህን ነገሮች በምስጋና፣ እና በፈቃደኛ ልብ እና ፊት፣… [የምድር] … ሁሉ የአንተ ይሆናሉ።”13

የእነዚህን ቃላት ታላቅነት አስቡባቸው። የምድር ሙላት የሰንበትን ቀን ቅዱስ ለሚያደርጉት ቃል ኪዳን ተሰጥቷቸዋል።14 ኢሳይያስ ሰንበትን “ደስታ” ብሎ መጥራቱ የሚያስገርም አይደለም።

በሰንበት ላይ ያላችሁ ጸባይ ወደ ደስታ እንደሚመራ እንዴት ለማረጋገጥ ትችላላችሁ? ወደ ቤተመቅደስ ከመሄዳችሁ፣ ቅዱስ ቁርባን ከመሳተፋችሁ፣ እና ለማገልገል በተጠራችሁበት ትጉ ከመሆናችሁ በተጨማሪ፣ ምን አይነት ሌሎች እንቅስቃሴዎች በሰንበት ደስታ እንዲያመጡላችሁ ይረዷችኋል። ለእርሱ ያላችሁን ፍቅር ለማሳየት ምን ምልክት ትሰጡታላችሁ?

ሰንበት የቤተሰብ አንድነትን ለማጠናከር አስደናቂ እድል ይሰጣል። እግዚአብሔር እያንዳንዳችንን፣ እንደ ልጆቹ፣ ወደ እርሱ በቤተመቅደስ ውስጥ እንደ ቤተሰብ፣ ከቅድመ አያቶቻችን እና ከትውልዶቻችን ጋር፣ የታተሙ የተቀደሱ ቅዱሳን ሆነን እንድንመለስ ይፈልገናል።15

ሰንበትን ደስታ የምናደርገው ልጆቻችንን ስለወንጌል ስናስተምር ነው። እንደ ወላጆች ያለን ሀላፊነ ግልፅ ነው። ጌታ እንዳለው፣ “ወላጆች በፅዮን … ውስጥ ልጆች ኖሯቸው፣ ስምንት አመት ሲሆናቸው፣ ስለ ንስሀ፣ በህያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እምነት፣ እናም ስለ ጥምቀት እና እጆችን በመጫን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ስለመቀበል ትምህርትን ባያስተምሯቸው፣ ኃጢአቱ በወላጆች ራስ ላይ ይሆናል።”16

ከብዙ አመቶች በፊት፣ የቀዳሚ አመራር ስለ ቤተሰብ አብረው የሚያሳልፉበት ጥራት ያለው ጊዜ አስፈላጊነትን በትኩረት ተናግረውበት ነበር፣ እንዲህም ጻፉ፥

“በቤተክርስቲያኗ ቅርብ እንዲሆኑ የሚያደርጓቸውን የወንጌል መርሆች ልጆቻቸውን በማስተማር እና በማሳደግ ከሁሉም የተሻለ ጥረት እንዲያደርጉ ወላጆችን ሁሉ እንጠይቃለን። ቤት የጻድቅ ህይወት መሰረት ነው፣ እናም ሌላ ምንም ነገር ይህን ሊተካ ወይም ይህን በእግዚአብሔር የተሰጠ ሀላፊነትን አስፈላጊ ስራ ለማሟላት አይችልም።

“ወላጆች እና ልጆች ለቤተሰብ ጸሎት፣ ለቤተሰብ የቤት ምሽት፣ ለወንጌል ጥናት እና ትምህርት፣ እናም መልካም ለሆኑ የቤተሰብ መሳተፊያዎች ቀዳሚነትን እንዲሰጡ እንመክራለን። ሌሎች መከናወን ያለባቸው ወይም መሳተፊያዎች ምን ያህል ትክክለኛ ወይም ብቁ ቢሆኑም፣ ቤተሰቦች እና ወላጆች ብቻ በብቁ ለማከናወን የሚችሉትን በመለኮታዊነት የተመደቡ ሀላፊነቶችን እንዲተኩ መፍቀድ አያስፈልጋቸውም።”17

ይህን ምክር ሳሰላስልበት፣ ወጣት አባት እንደገና ብሆን እመኝ ነበር። አሁን ወላጆች የሰንበትም ይሁን የሌላ የቤተሰብ ጊዜ ትርጉም ያለው እንዲሆን የሚረዷቸው ብዙ አስደናቂ ነገሮች አሉ። LDS.orgMormon.org፣ የመፅሐፍ ቅዱስ ቪድዮዎች፣ የሞርሞን ቻናል፣ የወንጌል ስዕል መፅሐፍ ቤት፣ Friend፣New Era፣Ensign፣Liahona፣ እና ብዙ ተጨማሪዎችም አሏቸው። እነዚህ ነገሮች ወላጆች ለልጆቻቸው ያላቸውን ሀላፊነቶች እንዲያከናውኑ ይረዷቸዋል። ሌላ ምንም ስራ ከጻድቅ፣ ጥንቁቅ ወላጅነት በላይ ሊሆን አይችልም።

ወንጌልን ስታስተምሩ፣ ተጨማሪ ትማራላችሁ። ይህም ወንጌሉን እንድትረዱ ጌታ የሚረዳችሁ መንገድ ነው። እንዲህም አለ፥

“እናም የመንግስቱን ትምህርት እርስ በርስ ትማማሩም ዘንድ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።

በትጋት አስተምሩ … ይህም በፅንሰ ሀሳብ፣ በመሰረታዊ መርሆች፣ በትምህርት፣ በወንጌሉ ህግ፣ ከእግዚአብሔር መንግስት ጋር ግኑኝነት ባላቸው ሁሉም ነገሮች … ፈጽማችሁ እንድትማሩ ዘንድ ነው።”18

የወንጌል ጥናት ሰንበትን አስደሳች ያደርጋል። ይህም የተስፋ ቃል የቤተሰብ ቁጥርን፣ ምን አይነት መሆናቸውን፣ እና የሚገኙበትን ቦታ ችላ የሚል ነው።

ከቤተሰብ ጋር ጊዜ ከማሳለፍ በተጨማሪም፣ በቤተሰብ ታሪክ ስራ እውነተኛ የሆነ ደስታ ከሰንበት ለማግኘት ትችላላችሁ። በምድር ላይ ከእናንተ በፊት የነበሩትን የቤተሰብ አባላትን፣ በዚህ በነበሩ ጊዜ ወንጌልን ለመቀበል እድል ያልነበራቸውንም፣ መፈለግ እና ማግኘት ታላቅ ደስታ ማምጣት ይችላል።

ይህን ራሴም አይቸዋለሁ። ከብዙ አመታት በፊት፣ ውድ ባለቤቴ ወንዲ፣ የቤተሰብ ታሪክ ለመፈተሽ ለመማር ወሰነች። እድገቷ በመጀመሪያ ቀስተኛ ነበር፣ ግን ቀስ በቀስ፣ ይህን ቅዱስ ስራ ለመፈጸም እንዴት ቀላል እንደሆነ ተማረች። እንደዚህ ተደስታ አይቻት አላውቅም ነበር። ወደ ሌላ አገር ወይም ወደ ቤተሰብ ታሪክ መፈተሻ ቦታ መሄድም አያስፈልጋችሁም። በቤት፣ በኮምፒውተር ወይም በሞባይል በመረዳት፣ ለእነዚህ ስርዓቶች በጉጉት የሚጠብቁ ነፍሳትን ለማግኘት ትችላላችሁ። ቅድመ አያቶችን በማግኘት እና ከመንፈስ እስር ቤት ነጻ በማድረግ ሰንበትን አስደሳች አድርጉ!19

ለሌሎች፣ በተለይም ደህና ያልሆኑትን እና ብቸኛ ወይም እርዳታ የሚፈልጉትን፣ አገልግሎት በመስጠት ሰንበትን አስደሳች አድርጉ።20 መንፈሳቸውን ከፍ ማድረግ የእናንተንም ከፍ ያደርጋል።

ኢሳይያስ ሰንበትን እንደ ደስታ ሲገልጽ፣ ደግሞም እንዴት አስደሳች እንደምናደርጋት አስተምሮናል። እንዲህም አለ፥

“ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፥ ሰንበትንም …፥ የገዛ መንገድህንም ከማድረግ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፥

“በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል”21

በሰንበት “ፈቃድህን” ከማድረግ ለመከልከል ታላቅ ራስን መቆጣጠር ያስፈልገዋል። የምትፈልጉትን አንድ ነገር ራሳችሁን ለመከልከል ያስፈልጋችሁ ይሆናል። ራሳችሁን በጌታ ለመደሰት ከመረጣችሁ፣ ይህን እንደሌላ ማንኛውም አገር ለመመልከት ራሳችሁን አትፈቅዱም። ተራ እና የመዝናኛ መሳተፊያዎች በሌላ ጊዜ ለመከናወን ይችላሉ።

ይህን አስቡበት፥ አስራትም በመክፈል፣ የጨመርናቸውን አንድ አስረኛ ለጌታ እንመልሳለን። ሰንበትን ቅዱስ በማድረግ፣ ከሰባት ቀናት አንድን ለእርሱ እናስቀምጣለን። ስለዚህ ገንዘብን እና ጊዜን በየቀኑ ህይወት ለሚሰጠን በቅድስና መሰጠት የእኛ ክብር ነው።22

በእግዚአብሔር ያለ እምነት ለሰንበት ፍቅር ያመጣል፤ በሰንበት ማመን ለእግዚአብሔር ፍቅርን ያመጣል። ቅዱስ ሰንበት በእውነትም አስደሳች ነው።

አሁን፣ ይህ ጉባኤ ሲዘጋ፣ የትም ብንኖርም በቤተሰቦቻችን፣ በጎረቤቶቻችን፣ እና በጓደኞቻችን መካከል የአማኞች ምሳሌ መሆን አለብን።23 እውነተኛ አማኞች ሰንበትን ቅዱስ ያደርጓታል።

ይህን የምጨርሰው፣ መፅሐፈ ሞርሞንን በዘጋበት በሞሮኒ የደህና ሁኑ ልመና ነው። እንዲህም ጻፈ፣ “ወደ ክርስቶስ ኑ፣ እናም በእርሱም ፍፁማን ሁኑ፣ እናም ኃጢአተኝነትን በሙሉ ካዱ፤ እናም ለራሳችሁ ኃጢአተኝነትን በሙሉ ከካዳችሁ፣ እናም በሙሉ ኃይላችሁ እና አዕምሮአችሁ እና ጉልበታችሁ እግዚአብሔርን ከወደዳችሁ፣…በክርስቶስ…ቅዱስ ትሆናላችሁ።” 24

በልቤ ፍቅር ፣ እንደ ጸሎቴ፣ ምስክሬ፣ እና በረከቴ ይህን የምተውላችሁ በተቀደሰው በኢየሱስ ክርስቶ ስም ነው፣ አሜን።