2010–2019 (እ.አ.አ)
ራዕይ ለቤተክርስቲያኗ እና ራዕይ ለህይወታችን
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


2:3

ራዕይ ለቤተክርስቲያኗ እና ራዕይ ለህይወታችን

በመጪዎቹ ቀናት፣ ያለ መንፈስ ቅዱስ አመራር፣ አቅጣጫ ማሳየት፣ ማፅናናት፣ እና የማይለወጥ ተጽዕኖ በመንፈሳዊነት መቆየት አይቻልም።

በዚህ አጠቃላይ ጉባኤ እሁድ ፋሲካን ከእናንተ ጋር ማክበር እንዴት ያለ ታላቅ ክብር ነው! በዚህች ምድር የተጓዘውን በጣም አስፈላጊ ፍጡር የሆነውን በማምለክ በዚህች ምድር ላይ ተከስቶ የነበረውን እጅግ አስፈላጊ የሆነውን ክስተት ከማክበር የበለጠ የተሻለ ነገር ሊኖር አይችልም። በዚህች፣ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን፣ በጌቴሴማኒ የአትክልት ሥፍራ የጀመረውን ወሰን የሌለውን የኃጢያት ክፍያውን እርሱን እናመልካለን። ለእያንዳንዳችን ኃጢአቶች እና ድክመቶች ለመሰቃየት ፈቃደኛ ነበር ስቃዩ “በእያንዳንዱ ቀዳዳ እንዲደማ” ምክንያት ሆነ። 1 እርሱ በቀራንዮ መስቀል ላይ ተሰቅሏል2 እናም በሶስተኛው ቀን የሰማይ አባታችን ልጆች የመጀመሪያ ትንሳኤ ሆኖ ተነስቷል። እወደዋለሁ እናም እርሱ ህያው እንደሆነ እመሰክራለሁ! ቤተክርስቲያኗን የሚመራው እናም የሚቆጣጠራው እርሱ ነው።

ያለ አዳኛችን ወሰን የሌለው የኃጢያት ክፍያው፣ አንዳችንም ወደ ሰማይ አባታችን የመመለስ ተስፋ ፈፅሞ አይኖረንም ነበር። ያለ እሱ ትንሳኤ፣ ሞት መጨረሻ ይሆን ነበር። የአዳኛችን የኃጢያት ክፍያ የዘለአለም ህይወትን ምርጫ እና ህያውነትን ለሁሉም እውን አድርጓል።

ጥር 2, 2018 (እ.አ.አ) ማገባደጃ ላይ፣ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን ከመጋረጃው ጀርባ ማለፋቸውን ባለቤቴ፣ ዌንዲ፣ እና እኔ  በስልክ ጥሪ ነቅተን ሲነገረን መጽናናት ተሰማን፣ ይህም በእሱ ድንቅ ተልዕኮ እና ለተከታዮቹ በሚሰጠው ሰላም ምክንያት ነው።

Pፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እና ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን

ፕሬዘደንት ሞንሰን ይናፍቁናል! የእርሱን ህይወታቻውንና ታሪካቸውን እናከብራለን። እሳቻውን በሚያውቋቸው እና በሚወዷት ቤተክርስቲያን ላይ ሁሉ የማይጠፋ አሻራ የጣሉ፣ ታላቅ መንፈሳዊ መሪ ናቸው።

እሁድ፣ ጥር 14፣ 2018 (እ.አ.አ)፣ በሶልት ሌክ ቤተመቅደስ የላይኛው ክፍል፣ ቀዳሚ አመራር ቀላል ግን በጌታ በተመሰረተው ሥርዓት ዳግም ተደራጅቷል። ከዚያም ትላንትና ጠዋት በዋና ጉባኤ፣ በመላው ዓለም የቤተክርስቲያኗ አባላት በሐዋርያት አስቀድሞ የተፈፀመውን ድርጊት ለማፅናት እጆቻቸውን ወደ ላይ አንስተዋል። ለማያቋሪጥ ድጋፈችሁ በትህትና አመስጋኝ ነኝ።

በትከሻዎቻቸው ላይ ለቆምኩባቻውም አመስጋኝ ነኝ። በአስራ ሁለት ሐዋሪያት ቡድን ውስጥ ለ34 ዓመታት የማገልገል እና ከ16 ቀደምት የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘዳንቶች 10 በግል ለማወቅ እድል አግኝቻለሁ። ከእያንዳንዳቸው ብዙ ተምሬያለሁ።

ለአያቶቼም ውለታ አለብኝ። ስምንቱ ቅድመ አያቶቼ በአውሮፓ ውስጥ ወደ ቤተክርስቲያኗ የተለወጡ ነበሩ። እያንዳንዳቻው እነዚህ ታማኝ ነፍሳት ወደ ጽዮን ለመምጣት ሁሉን መስዋዕት አደረጉ። በቀጣዮቹ ትውልዶች፣ ግን፣ ሁሉም ቅድመ አያቶች ያን የህል ፀንተው አልቆዩም። ከዚህ የተነሳ፣ በወንጌል-ተኮር ቤት ውስጥ አላደግክኩም።

የፕሬዘደንት ኔልሰን ወላጆች
የወጣት ፕሬዘደንት ኔልሰን ቤተሰብ

ወላጆቼን ወደድኳቸው። ሁለንተናዬ እነርሱ ነበሩ እናም ወሳኝ ትምህርቶችን አስተምረውኛል። ለእኔ እና ለወንድሞቼና እህቶቼ እነሱ ለፈጠሩት ደስተኛ ህይወት አመስግኜአቸው አልጨርስም። እናም ገና፣ ልጅ እያለሁ፣ አንድ ነገር እንደጎደለኝ አውቄ ነበር። አንድ ቀን በከተማ ባቡር ላይ ዘልዬ ስለ ቤተክርስቲያኗ የሚያስተምር መጽሐፍ ለማግኘት ወደ ኤልዲኤስ የመጽሐፍ መደብር ሄደኩኝ። ስለወንጌል መማር አስደሰተኝ።

የጥበብን ቃልን በተረዳሁ ጊዜ፣ ወላጆቼ ይህን ሕግ እንዲኖሩ ፈለግሁ። ስለዚህ ፣አንድ ቀን በጣም ትንሽ ወጣት እያለሁ፣ ወደ ምድር ቤታችን ሄጄ በሲሚንቶው ወለል ላይ እያንዳንዱን የአልኮል ጠርሙስ ሰባበርኩኝ! አባቴ ይቀጣኛል ብዬ አስቤ ነበር፣ ነገር ግን አንድም ቃል አልተናገረም።

እያደግሁ ስሄድ እና የሰማይ አባትን እቅድ ታላቅነት መረዳት ስጀምር፣ አብዛኛውን ጊዜ ለራሴ እንዲህ አልኩኝ፣ “ምንም የገና በዓል አልፈልግም! እኔ ከወላጆቼ ጋር መታተም እፈልጋለሁ።” ወላጆቼ ዕድሜያቸው ከ80 በላይ እስኪሆን ድረስ ይህ ብዙ የተጠበቀው ምኞት አልሆነም ነበር፣ እና በኋላም ተፈፅሟል። በዚያ ቀን የነበረኝን ደስታ ለመግለፅ አልችልም፣3 እናም ያን መተሳሰራቸው እና ከእነርሱ ጋር የመተሳሰሬ ደስታ በእያንዳንዱ ቀናት ያስደስተኛል።

ራስል እና ዳንዜል ኔልሰን

በ1945፣ በሕክምና ትምህርት ቤት ሳለሁ፣ ዳንትዘል ዋይትን በሶልት ሌክ ቤተመቅደስ ውስጥ አገባሁ። እሷና እኔ በዘጠኝ ግሩም ሴቶች ልጆችና በአንድ ውድ ወንድ ልጅ ተባርከናል። ዛሬም በማደግ ላይ ያለው ቤተሰባችን በሕይወቴ ውስጥ ካሉት ታላቅ ደስታዎች አንዱ ናቸው።

ፕሬዘደንት ኔልሰንና እህት ኔልሰን እናም ሴት ልጆቻቸው
ፕሬዘደንት ኔልሰን እና ወንድ ልጃቸው

በ2005፣ ከ 60 ዓመት የትዳር ሕይወት በኋላ፣ የእኔ ውድ ዳንትዘል በድንገት ወደ ቤት ተጠራች። ለተወሰነ ጊዜ፣ ሀዘኔ የማያንቀሳቅስ ነበር። ነገር ግን የፋሲካ መልዕክት እና የትንሣኤ ተስፋ ደግፎኛል።

ዌንዲ እና ራስል ኔልሰን

ከዚም ጌታ ዌንድ ዋትሰንን ወደ ጎኔ አመጣት። በሚያዚያ 6፣2006 (እ.አ.አ)፣በሶልት ሌክ ቤተመቅደስ  ውስጥ ታተምን። በጣም ነው የምወዳት። በጣም ልዩ ሴት ናት— ለእኔ፣ ለቤተሰባችን፣ እናም ለመላ ቤተክርስቲያን ታላቅ በረከት ናት።

እያንዳንዱ እነዚህ በረከቶች ሁሉ የመጡት የመንፈስ ቅዱስን መነሳሳቶች በመፈለግና በመከተል ነው። ፕሬዚዳንት ሎሬንዞ ስኖው እንዳሉት፣ “ይህ ለሁሉም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ታላቅ እድል ነው... በህይወታችን በየቀኑ የመንፈስን መገለጦች የማግኘት መብታችን ነው።”4

እንደ ቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት አዲስ ጥሪ ከተሰጠኝ ጀምሮ መንፈስ በተደጋጋሚ በአዕምሮዬ ላይ በተደጋጋሚ ካሳደረእብኝ ነገሮች ውስጥ አንዱ ጌታ ሐሳቡን እና ፈቃዱን ለመግለጽ ምን ያህል ፈቃደኛ እንደሆነ ነው። ራዕይን የማግኘት እድል እግዚአብሔር ለልጆቹ ከሰጠው ከታላቅ ስጦታዎች ውስጥ አንዱ ነው።

በመንፈስ ቅዱስ መገለጦች፣ ጌታ በሁሉም የፅድቅ ሥራዎቻችን መሻት ላይ ይደግፈናል። በቀዶ ጥገና ክፍል ውስጥ፣ በታካሚ አጠገብ ቆሜ— ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቀውን አሰራር እንዴት እንደሚሠራ እርግጠኛ ሳልሆን—እናም መንፈስ ቅዱስ በአዕምሮዬ ውስጥ ቴክኒኩን ሥዕላዊ በሆነ መንገድ ሲገልጽልኝ ተሞክሮ ነበረኝ።5

ለዌንድ የጋብቻ ጥያቄዬን ለማጠናከር፣ “ስለራዕይ አውቃለሁ እናም እንዴት እንደምቀበለውም አውቃለሁ” አልኳት። ለእሷ ምስጋና ይገባታል— እናም እደተረደሁት ከሆነ፣ ሁሌም እንደምታደርገው— ስለ እኛ የራሷን ራዕይ ፈልጋለች እናም ተቀብላለች፣ ይህም አዎን እንድትል ብርታት ሰጥቷታል።

እንደ አስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን አባል፣ ለራዕይ በየቀኑ እጸልይ እና ለልቤና ለአዕምሮዬ በተናገረኝ ጊዜ ሁላ ለጌታ ምስጋና አቅርቤአለሁ።

የዚህንም ተአምር ተመልከቱ! የቤተክርስቲያናችን ጥሪ ምንም ይሁን ምን፣ ምክር እና አቅጣጫ መቀበል፣ ስለአደጋዎችና ሐሳብን ከሚያዛቡ ነገሮች ለመጠንቀቅ፣ እና በራሳችን ልናከናውናቸው የማንችላቸውን ነገሮች ለማከናወን እንችል ዘንድ ወደ ሰማይ አባታችን መጸለይ እንችላለን። መንፈስ ቅዱስን በእውነቱ ከተቀበልን እና የእርሱን መነሳሳቶች ለማስተዋልና ለመረዳት የምንማር ከሆነ፣ በትላልቅ እና በትናንሹ ጉዳዮች ላይ እንመራለን።

በቅርቡ ሁለት አማካሪዎችን የመምረጥ አስጨናቂ ተግባር ሲያጋጥመኝ፣ እኔ ከማፈቅራቸው እና ከማከብራቸው አስራ ሁለት ሰዎች እንዴት ሁለት አማካሪዎችን ልመርጥ እንደምችል አሰብኩኝ ።

ምክንያቱም ጥሩ ተነሳሽነት በጥሩ መረጃ ላይ የተመሰረተ መሆኑን በማወቄ ምክንያት፣ ከእያንዳንዱ ሐዋርያት ጋር በጸሎት አንድ ለአንድ በጸሎት ተገናኝቼ ነበር።6 ከዛም በቤተመቅደስ ውስጥ በአንድ የግል ክፍል ውስጥ እራሴን ለይቼ የጌታን ፍቃድ ጠየቅሁ። ፕሬዚዳንት ዳለን ኤች ኦክስን እና  ፕሬዘደንት ሄንሪ ቢ አይሪንግን  በቀዳሚ አመራር ውስጥ የኔ አማካሪዎች ሆነው እንዲያገለግሉ እንድመርጣቸው ጌታ እንዳዘዘኝ እመሰክራለሁ።

በተመሳሳይ መንገድ፣ የሽማግሌ ጌረት ደብሊው. ጎንግ እና የሽማግሌ ዩለሲስ ሶሬስ እንደ ሐዋሪያት እንዲሾሙ ጥሪንውን ጌታ በመንፈስ መምራቱን እመሰክራለሁ። እነርሱን ወደዚህ ልዩ የወንድማማችነት አገልግሎት እንኳን ደህና መጣችሁ እላቸዋለሁ።

እንደ ቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ጉባኤ ስንሰበሰብ፣ የመሰብሰቢያ ክፍሎቻችን የራዕይ ክፍሎች ይሆናሉ። መንፈስ ቅዱስ በግልፅ ይገኛል። ውስብስብ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ስንታገል፣ እያንዳንዱ ሐዋሪያ ሃሳቡንና አመለካከቱን በነፃነት ሲገልፅ አስደናቂ ሂደት ይገለጣል። በመጀመሪያ እይታችን ውስጥ ብንለያይም፣ ለእያንዳንዳችን ያለን ፍቅር ግን የማያቋርጥ ነው። የእኛ አንድነት ለቤተክርስቲያኑ ያለውን የጌታን ፈቃድ እንድናስተውል ይረዳናል።

በስብሰባዎቻችን ላይ፣ የብዙሃን ድምጽ በጭራሽ አይሰራም! አንድ ላይ እስክንሆን ድረስ በፀሎት እርስ በእርሳችን እንደማመጣለን እና እንነጋገራለን። ሙሉ በሙሉ ስምምነት ላይ ስንደርስ፣ የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ተፅዕኖ በጣም ልዩ ነው! “በስሜት አንድነት ከእግዚአብሔር ሀይል እናገኛለን።”7 ብሎ ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ በሚያስተምርበት ጊዜ ያወቀውን ተሞክሮ እናያለን። የትኛውም የቀዳሚ አመራር አባል ወይም የአስራ ሁለት ቡድን አባል የጌታ ቤተክርስቲያን ውሳኔዎች በራሱ እውቀት ውሳኔ አይሰጥም!

ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ጌታ እንድንሆን የሚፈልገውን— እንዴት ክርስቶስን መሰል አገልጋዮች— ወንዶች እና ሴቶች መሆን እንችላለን? ግራ ለሚያጋቡ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው? የጆሴፍ ስሚዝ የቅዱስ ጫካ ድንቅ ተሞክሮ የሚያስተምረን ነገር ቢኖር፣ ሰማያቶች ክፍት እንደሆኑ እና እግዚአብሔር ለልጆቹ እንደሚናገር ነው።

ጥያቄዎቻችንን ለመፍታት እንድንከተላቸው ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ ለእኛ ምሳሌ ሰጥቶናል። ጥበብ ቢጎድለን እግዚአብሔርን መጠየቅ እንደምንችል በያዕቆብ ቃል ኪዳን ተመርቶ፣8 ወጣቱ ጆሴፍ ጥያቄውን በቀጥታ ወደ ሰማይ አባት ወሰደ። የግል መገለጥን ፈልገ፣ እናም የእሱ መሻት ይሄን የመጨረሻውን ዘመን ከፈተ። የግል ራዕይን ለማግኘት ፈለገ፣ እናም የእርሱ ፍለጋ ይህን የመጨረሻውን ዘመን ከፈተ።

በተመሳሳይ መንገድ፣ ፍላጎታችሁ የሚከፍትላችሁ ምንድን ነው? የትኛው ጥበብ ነው የሚጎድላችሁ? ለማወቅ ወይም ለመረዳት ምን አስቸኳይ ፍላጎት ይሰማችሁ ይሆን? የነቢዩን ጆሴፍን ምሳሌ ተከተሉ። በየጊዜው መሄድ የምትችልበት ጸጥ ያለ ቦታ ፈልጉ። በየጊዜው መሄድ የምትችሉበት ጸጥ ያለ ቦታን ፈልጉ። ልባችሁን ለሰማይ አባታችሁ አፍስሱ። ለመፍትሄና ለመፅናኛ ወደ እርሱ ዙሩ።

ስለሚያሳስባችሁ፣ ስለሚያስፈራችሁና ለድክመቶቻችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጸልዩ—አዎን፣ ለልባችሁ ምኞቶችም ጭምር። እና ከዚያም አዳምጡ! ወደ አእምሮአችሁ የሚመጡትን ሐሳቦች ጻፉ። ስሜቶቻችሁን መዝግቡ እና እንድታደርጉ በተነሳሳችሁት እርምጃዎች ተከታሉ። ይህን ሂደት በየቀኑ፣ በየወሩ፣ በየዓመቱ ስትደግሙት፣ ወደ “ራዕይ መሰረታዊ መርሆች” ታድጋላችሁ።9

እግዚአብሔር በእውነቱ እናንተን ሊናገራችሁ ይፈልግ ይሆን? አዎ! “ሰው የሚዙሪን ወንዝ ከተወሰነለት መንገድ ለማስቆም የእርሱን ደካማ ክንድ እንደሚዘረጋ ሁሉ፣ ሁሉን ቻይ በኋለኛው ቀን ቅዱሳናት እራሶች ላይ ከሰማይ ዕውቀትን ማፍሰሱን እንደማገድ ያህል ነው። 10

ስለ እውነቱ መጠራጠር አያስፈልጋችሁም። 11 ማንን በጥንቃቄ መተማመን እንደምትችሉ ማሰብ የለባችሁም። በግል ራዕይ አማካኝነት፣ መጽሃፈ ሞርሞን የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ነብይ እንደ ሆነ ፣እና ይህች የጌታ ቤተክርስቲያን እንደሆነች እናንተ የራሳችሁን ምስክር ልትቀበሉ ትችላላችሁ። ሌሎች የሚናገሩትም ሆነ የሚያደርጉት ምንም ይሁን ምን፣ ማንም ስለ እውነቱ በልባችሁና እና በአዕምሮአችሁ የተመሰከራላችሁን ምስክር ሊወስድባችሁ አይችልም።

የግል ራዕይን ለመቀበል አሁን ካለው መንፈሳዊ ችሎታችሁ በላይ እንድትሳቡ እመክራችኋለሁ፣ ጌታ እንዲህ ብሎ ቃል ገብቷል “ከጠየቃችሁ፣ በራእይ ላይ ራዕይን፣ በእውቀት ላይ እውቀትን ታገኛላችሁ፣ ምስጢሮችና ሰላማዊ የሆኑ ነገሮችን እንድታውቁ—ደስታ የሚያስገኘውን ፣የዘላለም ሕይወት የሚያስገኘውን ታውቃላችሁ።”12

የሰማይ አባታችሁ እንድታውቁ የሚፈልገው ብዙ ነገሮች አሉ። ሽማግሌ ኔል  ኤ ማክስዌል እንደስተማሩት፣ “ለማየት አይን ላላቻው እና ለማዳመጥ ጆሮዎች ላላቸው ሰዎች ፣ አብ እና ወልድ የጠፈርን ሚስጥሮች እየሰጡ ናቸው።”13

እንደ የበለጠ ንጹህነት፣ ትክክለኛ ታዛዥነት፣ የልብ ፍለጋ፣ በየቀኑ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የክርስቶስን ቃላት መመገብ፣14 እናም ለቤተመቅደስ እና ለቤተሰብ ታሪካዊ ስራ መደበኛ ጊዜ እንደመስጠት እንዳለ ቅንብር ሰማያትን የሚከፍት ነገር የለም።

እርግጥ ለመሆን፣ ሰማያት የተዘጉ እንደሆኑ የሚሰማችሁ ጊዜዎች አሉ። ነገር ግን ታዛዥ በመሆን፣ ጌታ ለሰጣችሁ ለእያንዳንዱ በረከቶች ምስጋናችሁን በመግለጽ፣ እናም የጌታን የጊዜ ሰንጠረዥ በትዕግስት በማክበር የምትቀጥሉ ከሆነ፣ የምትፈልጉትን እውቀትና መረዳት እንደምትቀበሉ ቃል እገባለሁ። ጌታ ለናንተ ያለው እያንዳንዱ በረከት— ተዓምራትም—ይከተላሉ። የግል ራዕይ ለእናንተ የሚያደርገው ይህን ነው።

ስለወደፊት ብሩህ ተስፋ አለኝ። እያንዳንዳችን ለማደግ፣ አስተዋጽዖ ለማድረግ፣ እና ወንጌልን ወደ እያንዳንዱ የምድር ክፍል ለመውሰድ በእድሎች ይሞላል። ግን እኔ ስለ ወደ ፊት ቀናት ምንም እውቀት የሌለኝ አይደለሁም። የምንኖረው ውስብስብና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በሚሄድ ጠበኛ ዓለም ውስጥ ነው። የማኅበራዊ ሚዲያዎች በቋሚነት መኖራቸው እና የ24-ሰዓት የዜና ዑደት ምንም በማያቋርጥ መልዕክቶች ይደበድበናል። በፍተኛ ቁጥር የሚቆጠሩ ድምፆች እና እውነትን የሚያጠቁ የሰዎችን ፍልስፍናዎች የመለወጥ ተስፋን የምንፈልግ ከሆነ፣ ራዕይን ለመቀበል መማር አለብን።

አዳኛችን እና ቤዛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እጅግ ታላቅ ስራውን አሁን እና ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ መካከል ያከናውናል። እግዚአብሔር አብ እና የተወደደው ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ይህንን ምድር በግርማዊነትና ክብር ስያስተዳድሩ ተዓምራዊ ምልክቶችን እናያለን። ነገር ግን በመጪዎቹ ቀናት፣ ያለ መንፈስ ቅዱስ አመራር፣ አቅጣጫ ማሳየት፣ ማፅናናት፣ እና የማይለወጥ ተጽዕኖ በመንፈሳዊነት መቆየት አይቻልም።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ራዕይን ለመቀበል መንፈሳዊ አቅማችሁን እንድትጨምሩ እማጸናለሁ። ይህ የትንሳኤ ሰንበት በህይወታችሁ ውስጥ ትርጉም ያለው ቅጽበት ይሁን። የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ለመደሰት እና የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ በተደጋጋሚ እና በበለጠ በግልጽ ለማዳመጥ የሚያስፈልገውን መንፈሳዊ ሥራ ለመሥራት ምረጡ።

ከሞሮኒ ጋር፣ በዚህ የፋሲካ ሰንበት ሕይወታችሁን ሊለውጥ የሚችል እና ከሚለውጠው ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታ በመጀመር፣ “ወደ ክርስቶስ እንድትመጡ፤ እናም መልካሙን ስጦታ እንድትይዙ” 15 እመክራችኋለሁ።

እኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች ነን። በጣም አስፈላጊ የሆነው መንፈስ ቅዱስ የሚመሰክርላችሁ ሐቅ ቢኖር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑንና፣ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ነው። ሕያው ነው! እርሱ ከአብ ጋር ጠበቃችን፣ ምሳሌያችን፣ ቤዛችን ነው። በዚህ የፋሲካ እሁድ፣ የእሱን የስርየት መስዋዕት፣ የእርሱ ትንሳኤ፣ እና የእርሱ መለኮታዊነቱን እናከብራለን።

ይህቺ የእርሱ ቤተክርስቲያኑ ናት፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል በዳግም ተመልሳለች። ለእያንዳንዱ ለእናንተ ፍቅሬን እየገለፅኩ፣ ስለዚህ የምመሰክረው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።