2010–2019 (እ.አ.አ)
የክህነት ሀይል
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


2:3

የክህነት ሀይል

የምትሸከሙትን ቅዱስ ክህነት ማጉላት በቤተሰቦቻችሁ እና በቤተክርስቲያን ጥሪያችሁ ውስጥ ላለው ለጌታ ስራ በጣም አስፈላጊ ነው።

ውድ ወንድሞቼ፣ ከፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን በራዕይ የመጣ ማስታወቂያ ሰምተናል። አስፈላጊ ማብራሪያዎችንም ከሽማግሌዎች ክርስቶፈርሰን እና ራዝባንድ እናም ከፕሬዘደንት አይሪንግ ሰምተናል። ከዚህ በኋላ የሚባለው፣ በተጨማሪም ከፕሬዘደንት ኔልሰን፣ እናንተ፣ የጌታ መሪዎች እና የክህነት ተሸካሚዎች፣ በኃላፊነታችሁ አሁን ምን እንደምታደርጉ የሚያብራራ ነው። በዚህ ለመርዳት፣ የምትሸከሙትን ክህነት የሚገዙ አንዳንድ መሰረታዊ መርሆችን እገመግማለሁ።

፩. ክህነት

የመልከ ጼዴቅ ክህነት እግዚአብሔር “የሰውን ዘለአለማዊ ህይወት ለማምጣት” (ሙሴ 1፥39) ያለውን ስራ ለማከናወን በሀላፊነት የሚሰጠው መለኮታዊ ስልጣን ነው። በ1892 (እ.አ.አ) ይህም በጆሴፍ ስሚዝ እና በኦሊቨር ካውደሪ ላይ በአዳኝ ሐዋሪያት በጴጥሮስ፣ በያዕቆብ፣ እና በዮሀንስ የተሾሙበት ነበር (ት. እና ቃ. 27፥12 ተመልከቱ)። ይህም ቅዱስ እና እኛ ለመግለጽ ካለን ሀይል በላይ ሀይለኛ የሆነ ነው።

የክህነት ቁልፎች የክህነት ስልጣንን መለማመድን የሚመሩባቸው ሀይሎች ናቸው። ይህም ሆኑ፣ ሐዋሪያት የመልከ ጼዴቅ ክህነትን በጆሴፍ እና በኦሊቨር ላይ ሲያረጋግጡ፣ የዚህን ልምምድ የሚመሩበትን ቁልፎች ደግመውም ሰጡአቸው (ት. እና ቃ. 27፥12–13 ተመልከቱ)። ነገር ግን በዚያ ጊዜ ሁሉም የክህነት ቁልፎች አልተሰጡም ነበር። ለዚህች “የዘመን ሙላት” (ት. እና ቃ. 128፥18) አስፈላጊ የሆኑት ቁልፎች እና እውቀቶች በሙሉ የተሰጡት “መስመር በመስመር” (ቁጥር 21) ነበር። ተጨማሪ ቁልፎችም ከሰባት አመት በኋላ በከርትላንድ ቤተመቅደስ ተሰጥተው ነበር (ት. እና ቃ. 110፥11–16)። እነዚህ ቁልፎች የተሰጡት በዚያ ጊዜ የተሰጡትን ሀላፊነቶች፣ ለምሳሌ የሙታን ጥምቀትን፣ የሚመራበት የክህነት ስልጣን ለመስጠት ነበር።

የመልከ ጼዴቅ ክህነት የክብር ማመልከቻ ወይም መሰየሚያ አይደለም። ይህም ለልጆቹ ጥቅም የሚደረገውን የእግዚአብሔር ስራ የሚከናወንበት በአደራ የተሰጠ መለኮታዊ ሀይል ነው። ክህነትን የሚሸከሙ ሰዎች “ክህነቱ” እንዳልሆኑ ሁልጊዜም ማስታወስ አለብን። “ክህነት እና ሴቶች” ማለት ትክክል አይደለም። “የክህነት ተሸካሚዎች እና ሴቶች” ማለት ይገባናል።

፪. የአገልግሎት ሚኒስቴር

አሁን ክህነት ከሚሸከሙት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እደሚጠብቅ እናስብበት—ነፍሳትን ወደ እርሱ እንዴት እንደምናመጣ።

ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ እንዳስተማሩት፥ “በእውነትም ቤተክርስቲያኗ በፍጹምነት ተደራጅታለች ተብሏል። አስቸጋሪው ነገር ቢኖር፣ እነዚህ ድርጅቶች በሚያርፍባቸው ሀላፊነቶች ላይ በሙሉ ንቁ የሆኑ አይደሉም። በእነርሱ የሚፈለገውን ነገር በሙሉ በማወቅ ሲነቁ፣ ሀላፊነቶቻቸውን በተጨማሪ ታማኝነት ያሟላሉ፣ እናም የጌታ ስራ በሙሉ ጠንካራ እና ሀይለኛ እናም በአለም ላይ ተፅዕኖ ያለው ይሆናል።”1

ፕሬዘደንት ስሚዝ ደግመውም እንዲህ አስጠነቀቁ፥

“ከተለያዩ የቅዱስ ክህነት ሀላፊነቶች እና ስርዓቶች ጋር የተገናኘ በእግዚአብሔር የተሰጠን ክብር፣ በሰው እንደመጣ አይነት ማዕረግ መጠቀም ወይም ማሰብ አይገባም፤ ማጌጫ ወይም የጌታነት መግለጫ አይደሉም፣ ነገር ግን እንደምናገለግለው በምንናዘዘው በመምህር ስራ ውስጥ ለትሁት አገልግሎት የምንመደብበት ነው። …

“… ለነፍሳት ለነፍሳት ደህንነት ይምንሰራ ነን፣ እና ይህም የሚያርፍብን ከሁሉም በላይ ታላቅ የሆነ ሀላፊነት እንደሆነ ሊሰማን ይገባናል። ስለዚህ፣ ሁሉንም ነገሮች፣ አስፈላጊ ከሆነ፣ ለእግዚአብሔር ፍቅር፣ ለሰዎች ደህንነት፣ እና የእግዚአብሔር መንግስት በምድር ድል እንድታገኝ በመስዋዕት ለመስጠት ፈቃደኝነት ሊሰማን ይገባናል።”2

፫. የክህነት ሀላፊነቶች

በጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ፣ የመልከ ጼዴቅ ክህነት የተለያዩ ስራዎች አሉት። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ሊቀ ካህናትን “በውጪ በተበተኑት በተለያዩ ካስማዎች አገልጋዮች እንዲሆኑ የተመደቡ” (ት. እና ቃ. 124፥134)። ካህናትን እንደ “[በጌታ ቤተክርስቲያን] የማይጓዙ አገልጋዮች ” (ት. እና ቃ. 124፥137) ብሎ ይጠቅሳቸዋል። ስለእነዚህ የተለያዩ ስራዎች የሚያስተምሩ ተጨማሪ ትምህርቶችን እንኚህ ናቸው።

ሊቀ ካህን በመንፈሳዊ ነገሮችን ያስተዳድራሉ (ት. እና ቃ. 107፥10፣ 12)። ደግሞም ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ እንዳስተማሩት፣ “እንደ ሊቀ ካህን እስከተሾመ ድረስ፣ [እርሱ] … ወጣቶችን የእድሜ አጋጣሚ እንዲያገኙ በማድረግ፣ እና በሚኖርበት በዚህም ህብረተሰብ መካከል የሀይል ግለሰብ በመሆን፣ ለማስመሰል ብቁ የሚሆን ምሳሌ በሽማግሌና በወጣቱ ለማሳየት፣ እና በአስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን ግን በልዩም በምሳሌ የጻድቅነት አስተማሪ ለመሆን ራሱን ለማስገኘት ግድታ ይሰማዋል።”3

ስለሽማግሌ ሀላፊነቶች፣ የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ሽማግሌ አር. መኮንኪ እንዳስተማሩት፥ “ሽማግሌ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ነው። … ጓደኞቹን በማገልገል፣ በመምህሩ ምትክ እና ቦታ ውስጥ ለመቆምየተመደበ ነው። እርሱም የጌታ ወኪል ነው።”4

ሽማግሌ መኮንኪ አስንድ ሰም “ሽማግሌ ብቻ ነው” የሚለውን አባባል ተችተዋል። “በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የሚገኝ እያዳንዱ ሽማግሌ እንደ ቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት ያህል ክህነት አለው … ፣” ብለዋል። “ሽማግሌ ምን ነው? እርሱም እረኛ፣ ከመልካሙ እርኛ መንጋ መካከል የሚያገለግል እረኛ ነው።”5

በዚህ በመልካሙ እረኛ መንጋዎች መካከል በማገልገል አስፈላጊ ስራ ውስጥ፣ በመልከ ጼዴቅ ክህነት ውስጥ በሊቀ ካህን እና በሽማግሌ ሀላፊነት መካከል ምንም ልዩነት የለም። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታላቁ ክፍል 107 ውስጥ፣ ጌታ እንደሚያውጀው፣ “ሊቀ ካህናት እንደ መልከ ጼዴቅ ስርዓት፣ በቀዳሚ አመራር መመሪያ በመንፈሳዊ ነገሮች በማስተዳደር ሀላፊነታቸው፣ እና ደግሞም በሽማግሌ አመራር፣ [ወይም በማንኛውም የአሮናዊ] ሀላፊነቶች ለማስተዳደር መብት አላቸው።” (ት. እና ቃ. 107፥10፤ ደግሞም ቁጥር 12 ተመልከቱ)።

ለክህነት ተሸካሚዎች ከሁሉም በላይ አስፈላጊ መሰረታዊ መርሆ ቢኖር የመፅሐፈ ሞርሞን ነቢይ ያዕቆብ ያስተማረው መርሆ ነው። እርሱ እና ወንድሙ ያዕቆብ ለህዝብ እንደ ካህናት እና አስተማሪዎች ከተቀቡ በኋላ፣ እንዲህ አወጀ፣ “እናም ኃላፊነቱንም በመውሰድ፣ የእግዚአብሔርን ቃል በሙሉ ትጋት ካላስተማርናቸው የህዝቡን ኃጢኣት በራሳችን ላይ በመቀበል ኃላፊነታችንን ለጌታ አጎላን” (ያዕቆብ 1፥19)።

ወንድሞች፣ እንደ ክህነት ተሸካሚዎች ሀላፊነታችን ኮስታራ ጉዳይ ነው። ሌሎች ድርጅቶች መልእክታቸውን ለማቅረብ እና ሌሎች ስራዎቻቸውን ለማከናወን በአለማዊ መሰረቶች ለመረካት ይችላሉ። ነገር ግን እኛ የእግዚአብሔርን ክህነት የምንሸከም ወደ እግዚአብሔር ሰለስቲያል መንግስት መግቢያን የሚቆጣጠር መለኮታዊ ሀይል አለን። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ራዕያዊ መግቢያ ላይ ጌታ የገለጸው አላማዎች እና ሀላፊነቶች አለን። ለአለም ይህን ማወጅ አለብን፥

“ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው የአለም አዳኝ በሆነው በጌታ እግዚአብሔር ስም ይናገር፤”

ደግሞም እምነትም በምድር ይበዛ ዘንድ፤

ዘለአለማዊ ቃልኪዳኔ ይመሰረት ዘንድ፤

“የወንጌሌ ሙላት በደካሞች እና በተራ ሰዎች አማካይነት በነገስታት እና በገዢዎች ፊት እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ይታወጅ ዘንድ ተሰጥቷቸዋል” (ት. እና ቃ. 1፥20–23)።

ይህን መለኮታዊ ሀላፊነት ለማከናወን፣ የክህነት ጥሪያችንን እና ሀላፊነቶቻችንን “ማጉላት” አለብን (ት. እና ቃ. 84፥33 ተመልከቱ)። ፕሬዘደንት ሔሮልድ ቢ. ሊ ክህነትን ማጉላት ምን ማለት እንደሆነ ገልጸዋል፥ “ሰው የክህነት ተሸካሚ ሲሆን፣ እርሱም የጌታ ወኪል ይሆናል። ጥሪውን በጌታ መልእክተኛነት ላይ እንዳለ ማስብ ይገባዋል። ክህነትን ማጉላት ማለት ይህ ነው።”6

ስለዚህ፣ ወንድሞች፣ ጌታ ራሱ አንድ ወንድ ወይም ሴት ልጁን እንድትረዱ ቢጠይቃችሁም—በአገልጋዮቹ በኩል ይህን አድርጓል—ስራውን ትቀበላላችሁን? ከተቀበላችሁስ፣ እንደ እርሱ ወኪል “በጌታ መልእክተኛነት፣” ቃል በገባበት እርዳታ ላይ በመመካት ትሰራላችሁን?

ፕሬዘደንት ሊ ክህነትን ስለማጉላት ሌላ ያስተማሩት ነበር፣ “በአንድ ነገርን በአጉሊ መነፅር ስትመለከቱትይህም በአይናችሁ ለማየት ከምትችሉት በላይ ትልቅ ያደርገዋል፤ ያም አጉሊ መነፅር ነው። አሁን፣ … ማንም ክህነታቸውን የሚያጎሉ ከሆኑ—ይህም ማለት፣ መጀመሪያ ከሚያስቡበት በላይ ታላቅ ካደረጉት—ያም ክህነታችሁን የምታጎሉበት መንገድ ነው።”7

ይህም የክህነት ተሸካሚ የክህነት ሀላፊነቱን የሚያጎላበት ምሳሌ ነው። ይህን የሰማሁት በአይደሆ የካስማ ጉባኤ አብረውኝ ከነበሩት ከሽማግሌ ጀፍሪ ዲ. ኤሪክሰን ነበር። እንዳገባ አንድ ወጣት ሽማግሌ፣ በጣም ደሀ ሆኖ እና የመጨረሻ የኮሌጅ ትምህርት አመቱን ለመፈጸም እንደማይችል እየተሰማው፣ ጄፍሪ ከትምህርት ለመውጣት እና የተሰጠውን የስራ ለመቀበል ወሰነ። ከትንሽ ቀናት በኋላየክህነት ቡድኑ ፕሬዘደንት ወደ እርሱ ቤት መጣ። “የያዝኩትን የክህነት ቁልፍ ትርጉም ተረድተሀልን?” ብሎ የክህነት ሸንጎ ፕሬዘደንቱ ጠየቀው። ጀፍሪ እረዳለሁ ብሎ ሲመልስ፣ ፕሬዘደንቱ ትምህርትን ለማቆም እንደወሰነ እንደሰማ፣ ጌታ ይህን መልእክት በመተናት ባልቻለበት ምሽት ለእርሱ እንዲሰጠው እንደፈለገው ነገረው፥ “እንደ ክህነት ቡድን ፕሬዘደንትህ፣ የኮሌጅ ትምህርትህን እንዳታቆም እመክርሀለሁ። ይህም ከጌታ ለአንተ የመጣ መልእክት ነው።” ጄፍሪ ትምህርቱን ቀጠለ። ከአመታት በኋላ እንደ ውጤታማ የንግድ ሰው በነበረበት ጊዜ አገኘሁት እናም ለሚያዳምጡት የክህነት ተሸካሚዎች እንዲህ ሲላቸው ሰማሁ፣ “ያም [ምክር] በህይወቴ ላይ ሙሉ ተፅዕኖ ነበረው።”

የክህነት ተሸካሚ ክህነቱን እና ጥሪውን አጎላ፣ እና ያም በእግዚአብሔር ልጅ ህይወት ላይ “ተፅዕኖ” ነበረው።

፬. ክህነት በቤተሰብ ውስጥ፥

እስከ አሁን ድረስ፣ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ስላለው የክህነት ስራን ተናግሬአለሁ። አሁን በቤተሰብ ውስጥ ስላለ ክህነት እናገራለሁ። በቁልፍ እጀምራለሁ። የክህነት ስልጣን የሚለማመደው ለዚህ ስራ ቁልፎችን በሚያዘው ሰው አመራር በኩል ብቻ የሚለው መርሆ የቤተክርስቲያኗ መሰረታዊ መርሆ ነው ነገር ግን ይህን በቤተሰብ የክህነት ስልጣን መለማመድ ላይ ለመጠቀም አይቻልም።8 ክህነትን የሚሸከም አባት ባለው በክህነት ስልጣን መሰረት ቤተሰቡን ይመራል። የቤተሰብ አባላቱን ለመምከር፣ የቤተሰብ ስብሰባ ለመጥራት፣ የክህነት በረከት እባለቤቱና ለልጆቹ ለመስጠት፣ ወይም ለቤተሰብ አባላቱ እና ለሌሎች የሚፈውስ በረከቶችን ለመስጠት የክህነት ቁልፎች መመሪያ ወይም ፈቃድ አያስፈልገውም።

ቤተሰብ አብረው ሲያጠኑ

አባቶች በቤተሰቦቻቸው ክህነታቸውን ቢያጎሉ፣ በምንም ከሚያደርጉት ያህል የቤተክርስቲያኗን ተልእኮ ወደፊት ይገፋሉ። የመልከ ጼዴቅ ክህነት ያላቸው አባቶች ለቤተሰብ አባላቶቻቸው በረከቶችን ለመስጠት የክህነት ሀይል ይኖራቸው ዘንድ ትእዛዛትን ማክበር ያስፈልጋቸዋል። የቤተሰብ አባላት አባታቸውን በረከት እንዲሰጧቸው ለመጠየቅ እስከሚፈልጉ ድረስ፣ አባቶች ፍቅራዊ የቤተሰብ ግንኙነትን ማሳደግ ይገባቸዋል። እናም ወላጆች በቤተሰብ ውስጥ ተጨማሪ የክህነት በረከቶች እንዲኖሩ ማበረታታት ይገባቸዋል።

የክህነት በረከቶች

የቤተሰብ አዋጅ እንደሚያስተምረው፣ አባቶች ከባለቤቶቻቸው ጋር “እንደ እኩል ጓደኞች” ይሰራሉ። 9 እናም፣ አባቶች፣ የክህነት ሀይል እና ተፅዕኖአችሁን ለመለማመድ እድል ሲኖራችሁ፣ ይህንንም “በማሳመን፣ በትእግስት፣ በደግነት፣ እና በትህትና፣ እና ግብዝነት በሌለው ፍቅር” (ት. እና ቃ. 121፥41) አድርጉት። ያም የክህነት ስልጣንን የመለማመድ ከፍተኛ መሰረት ከሁሉም በላይ በቤተሰብ ውስጥ አስፈላጊ የሆነ ነው። ፕሬዘደንት ሔሮልድ ቢ. ሊ የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት እንደሆኑ ወዲያው እንደሰጡት ምክር፥ “በቤት ውስጥ ችግር፣ አስፈሪ በሽታ፣ ወይም ታላቅ ውሳኔ መሰራት ከሚያስፈልግበት ጊዜ በላይ የምትሸከሙት የክህነት ሀይል ከሁሉም በላይ አስደናቂ የሚሆኑበት ሌላ ምንም ጊዜ የለም። … የሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ሀይል በሆነው፣ በክህነት ሀይል ውስጥ የጌታ ፍላጎት ከሆነ ታዕምራቶችን የሚፈጸምበት ሀይል ይገኛል፣ ነገር ግን ያን ክህነት ለመጠቀም፣ ለዚህ መለማመድ ብቁ መሆን አለብን። ይህን መርሆ ለመረዳት መውደቅ የዚያን ታላቅ ክህነት የመያዝ በረከቶችን ለመቀበል መውደቅ ነው።”10

ውድ ወንድሞቼ፣ የምትሸከሙትን ቅዱስ ክህነት ማጉላት በቤተሰቦቻችሁ እና በቤተክርስቲያን ጥሪያችሁ ውስጥ ላለው ለጌታ ስራ በጣም አስፈላጊ ነው።

ክህነቱ የእርሱ ስለሆነው ስለእርሱምም እመሰክራለሁ። በእርሱ የኃጢያት ክፍያ ስቃይና መስዋዕት እናም ትንሳኤ፣ ወንዶች እና ሴቶች ሁሉ የአለሟችነት መረጋገጫ እና ለዘለአለም ህይወት እድል አላቸው። እያንዳንዳችን በዚህ ታላቅ የሰማይ አባታችን እግዚአብሔር ስራ ክፍላችንን ለማከናወን ታማኝ እና ትሁት እንሁን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. Teachings of Presidents of the Church: Joseph F. Smith (1998), 343.

  2. Teachings: Joseph F. Smith, 340, 343.

  3. Joseph F. Smith, Gospel Doctrine, 5th ed. (1939), 182.

  4. Bruce R. McConkie, “Only an Elder,” Ensign, June 1975, 66; emphasis in original not preserved.

  5. Bruce R. McConkie, “Only an Elder,” 66; emphasis in original not preserved.

  6. Teachings of Presidents of the Church: Harold B. Lee (2000), 93.

  7. The Teachings of Harold B. Lee, ed. Clyde J. Williams (1996), 499.

  8. See Dallin H. Oaks, “Priesthood Authority in the Family and the Church,” Liahona, Nov. 2005, 24–27.

  9. ቤተሰብ፥ ለአለም አዋጅ፣” Liahona፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 145።

  10. Teachings: Harold B. Lee, 97.