አጠቃላይ ጉባኤ
ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በቃል ኪዳን ግንኙነት መጓዝ
የጥቅምት 2023 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


10:24

ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በቃል ኪዳን ግንኙነት መጓዝ

ስለእኛ የቆሰለው እና የተሰበረው፣ ሥጋዊ ተፈጥሮ በእኛ ላይ የሚያስከትለው አሉታዊ ውጤት እኛንም እንዲሰማን ይፈቅዳል፣ ነገር ግን እነዚያን ፈተናዎች ብቻችንን እንድንጋፈጥ አይጠይቀንም።

መልካም ጓደኛዬ የሆነው ኢላን በእስራኤል ውስጥ የሚገኝን አንድ የእግር ጎዞ መንገድን እንዳውቀው አደረገኝ። “ይህም የኢየሱስ የመንገድ በመባል ይታወቃል፣ ምክንያቱም ብዙዎች፣ ኢየሱስ ከናዝሬት ወደ ቅፍርናሆም ሲጓዝ የሄደበት መንገድ ነው ብለው ስለሚያምኑበት ነው” አለኝ። በዚያው ጊዜ እና እዚያው መንገዱን ልጓዝበት ፈለግኩኝ ስለዚህ ወደ እስራኤል ለመሄድ እቅድ ማውጣት ጀመርኩኝ።

ከጉዞው ከስድስት ወራት በፊት ቁርጭምጭሚቴ ተሰበረ። ባለቤቴ ጉዳቱ አስጨንቆት ነበር፤ ከሁሉም በላይ እኔን ያሳሰበኝ “የኢየሱስን መንገድ” እንዴት እጓዛለሁ የሚለው ጉዳይ ነበር። በተፈጥሮዬ ግትር ነኝ፤ ስለዚህ የአውሮፕላን ቲኬቱን አልሰረዝኩትም ነበር።

በዚያ የሰኔ ማለዳ የእስራኤል ዜጋ የሆነች አስጎብኚያችንን ስናገኝ አስታውሳለሁ። ከመኪናው ወረድኩኝ ከዚያም ሁለት ክራንቾች እና የተጎዳውን እግሬን የምደግፍበትን የጉልበት ስኩተር አወጣሁኝ። አስጎብኚያችን ማያ የጉልበት መደገፊያዬን ለአፍታ አየት አድርጋ፣ “ውይ፣ በዚህ ሁኔታሽ ይህንን መንገድ መሄድ የምትችይ አይመስለኝም” አለችኝ።

“ምንአልባት እችላለሁ፣” ብዬ መለስኩኝ። “የሆነ ሆኖ ከመሞከር የሚያግደኝ ምንም ነገር የለም።” ጭንቅላቷን በመጠኑ ነቀነቀችና ጉዞ ጀመርን። በተሰበረ እግሬ መንገዱን መጓዝ እንደምችል ስላመነች ወድጃት ነበር።

በቁልቁለቱ መንገድ እና በድንጋዮቹ ላይ ለተወሰነ ጊዜ ራሴን ችዬ ተጓዝኩኝ። ከዚያም ማያ በቅንነት በማደርገው ጥረት ተነክታ ቀጭን ገመድ አወጣችና ከስኩተሩ መያዣ ጋር አስራ መጎተት ጀመረች። ዳገቱን ወደ ላይ፣ በሎሚ የፍራፍሬ ዛፎች መሃል እና በገሊላ ባህር ዳርቻ ላይ ጎተተችኝ። ጉዞው እንዳበቃ በራሴ በምንም ላከናውነው የማልችለውን አንድ ነገር እንዳከናውን ለረዳችኝ ለደጓ አስጎብኚዬ ምስጋናዬን ገለፅኩላት።

ሄኖክ በአገሩ ሁሉ እንዲዞር እና ስለ እርሱ እንዲመሰክር ጌታ በጠራው ጊዜ ሄኖክ አመንትቶ ነበር።1 ገና ልጅ ነበር፤ አፉም ኰልታፋ ነበር፤ እርሱ ባለበት ሁኔታ ያንን መንገድ እንዴት ሊጓዘው ይችላል? በእርሱ ውስጥ በተሰበረው ነገር ምክንያት እይታው ተጋርዶ ነበር። ለእርሱ እንቅፋት ስለሆነበት ነገር ጌታ የሰጠው መልስ “ከእኔ ጋር ተራመድ” የሚል ቀላል እና ፈጣን የሆነ ምላሽ ነበር።2 እንደ ሄኖክ ሁሉ፣ ስለእኛ የቆሰለው እና የተሰበረው፣ 3ሥጋዊ ተፈጥሮ በእኛ ላይ የሚያስከትለው አሉታዊ ውጤት እኛንም እንዲሰማን እንደሚፈቅድ ማስታወስ አለብን፤ ነገር ግን እነዚያን ፈተናዎች ብቻችንን እንድንጋፈጥ አይጠይቀንም።4 የታሪካችን ክብደት ወይም አሁን እየተጓዝን ያለንበት መንገድ ምንም ይሁን ምን ከእርሱ ጋር እንድንራመድ ይጋብዘናል።5

በምድረ በዳ ጌታን ያገኘውን በችግር ውስጥ የነበረውን ወጣት አስቡ። ያዕቆብ ከቤቱ ርቆ ተጉዞ ነበር። በዚያ የድቅድቅ ጨለማ ሌሊት፣ መሰላልን ብቻ ሳይሆን አምስት ነገሮችን ያካተቱ ተስፋዎች ብዬ መጥራት የምወደውን ትርጉም ያላቸው የቃል ኪዳን ተስፋዎችን የያዘ ህልምን አየ።6 በዚያ ሌሊት፣ ጌታ ከያዕቆብ አጠገብ ቆመ፤ ራሱንም የያዕቆብ አባት አምላክ ሲል አስተዋወቀ፤ ከዚያም የሚከተሉትን ተስፋዎች ሰጠው፦

  • እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ።

  • እጠብቅሃለሁ።

  • ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ።

  • አልተውህምና።

  • ለአንተ የገባኋቸውን ቃልኪዳኖች እጠብቃለሁ7

ያዕቆብ የሚያደርገው ምርጫ ነበረው። ከአባቱ አምላክ ጋር ተዋውቆ ብቻ ሕይወቱን ዝም ብሎ ለመኖር መምረጥ ይችላል ወይም ከእርሱ ጋር ቁርጠኛ የሆነ የቃል ኪዳን ግንኙነት በመመሥረት ሕይወቱን ለመኖር ሊመርጥ ይችላል። ከዓመታት በኋላ፣ ያዕቆብ በጌታ የቃል ኪዳን ተስፋዎች ውስጥ ስለሚኖር ህይወት ምስክርነቱን የሰጠው፦“እግዚአብሔር በመከራዬ ጊዜ ሰማኝ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር [ነበር]።8 ህይወታችንን ከእሱ ጋር ለማጣመር ከመረጥን ጌታ ልክ ለያዕቆብ እንዳደረገው በመከራችን ጊዜ ለሁላችንም መልስ ይሰጠናል። በመንገዱ ላይ ከእኛ ጋር ለመራመድ ቃል ገብቷል።

ይህን በቃል ኪዳን መንገድ መጓዝ ብለን እንጠራዋለን—ይህ በጥምቀት ቃል ኪዳን የሚጀምር እንዲሁም በቤተመቅደስ ውስጥ ወደምናደርጋቸው ጥልቅ ቃል ኪዳኖች የሚመራ መንገድ ነው። ምናልባት እነዚህን ቃላት ስትሰሙ አማራጭ መጠቆሚያ ሳጥኖች ወደ ሃሳባችሁ መጥተው ይሆናል። ምናልባት፣ የምታዩት ነገር ቢኖር መሥፈርቶች ያሉት መንገድ ብቻ ሊሆን ይችላል። በቅርበት ማየት የበለጠ ትኩረትን የሚስብ ነገር ይገልፃል። ቃል ኪዳን ውል ማለት ብቻ አይደለም፤ ሆኖም እርሱም አስፈላጊ ነው። ጥምረትም ነው። ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “የቃል ኪዳን መንገድ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት የሚመለከት ነው” ሲሉ አስተምረዋል።9

ስለጋብቻ ውል አስቡ። የሠርጉ ቀን አስፈላጊ ነው፤ ነገር ግን በእኩል ደረጃ አስፈላጊ የሆነው ከዚያ በኋላ አብሮ በሚኖረው ህይወት ውስጥ የሚፈጠረው ግንኙነት ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ያለን የቃል ኪዳን ግንኙነትም እንዲሁ ነው። ሁኔታዎች ተዘጋጅተዋል እንዲሁም በመንገዱ ላይ የሚጠበቁ ነገሮች ይኖራሉ። እርሱ ግን እያንዳንዳችን በምንችለው መጠን፣ በፍጹም የልብ ዓላማ እንድንመጣ፣ እና ከእርሱ ጋር “ወደ ፊት እንድንገፋ”10 የገባው ቃል በረከቶቹ እንደሚመጡ በማመን እንድንመጣ ይጋብዘናል። አብዛኛውን ጊዜ እነዚያ በረከቶች የሚመጡት በእርሱ ጊዜ እና በእርሱ መንገድ፣ ይኸውም በ38 ዓመት፣11 በ12 ዓመት፣12 ወዲያው13 እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ያስታውሱናል። ጉዟችሁ እንደሚጠይቀው፣ የእርሱ እርዳታም እንዲሁ ይሆናል።14

የእርሱ ተልዕኮ በገዛ ፈቃድ ዝቅ ብሎ ማገልገል ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ባለንበት ቦታ ባለንበት ሁኔታ ያገኘናል። የአትክልቱ ሥፍራ፣ የመስቀሉ እና የመቃብሩ ምክንያት ይሄ ነው። አዳኙ የተላከው መቋቋም እንድንችል ለመርዳት ነው።15 ነገር ግን ባለንበት ቦታ መቆየት የምንሻውን ነፃ መውጣት አያስገኝልንም። ልክ ያዕቆብን እዚያ በትቢያ ላይ እንዳልተወው ሁሉ፣ ጌታ ማንኛችንንም ባለንበት አይተወንም።

በተጨማሪም የእርሱ ተልዕኮ ወደ ላይ ከፍ ከፍ ማድረግ ነው። እርሱ ወዳለበት ከፍ ከፍ ለያደርገን በውስጣችን ይሰራል፤ በዚህ ሂደት ውስጥም እንደ እርሱ እንድንሆን ያስችለናል።16 ኢየሱስ ክርስቶስ ከፍ ከፍ ሊያደርገን መጥቷል።17 እንድንሆን ሊረዳን ይፈልጋል። የቤተመቅደስ ምክንያት ይሄ ነው።

እኛን ከፍ ከፍ የሚያደርገን ሂደቱ ብቻ ሣይሆን የአዳኛችን ጓደኝነት እንደሆነ ማስታወስ አለብን። እናም የቃል ኪዳን ግንኙነት ምክንያት ይሄነው።

እስራኤል በነበርኩበት ጊዜ የምዕራቡን ግንብ ጎብኝቻለሁ። ለአይሁዳውያን ከሁሉም ቅዱስ የሆነው ሥፍራ ይሄ ነው። ከቤተመቅደሳቸው የተረፈው ይሄ ነው። የልብስ አመራረጣቸው የመሰጠታቸው ምልክት ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ለመሠረቱት ግንኙነት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መግለጫ ነው። ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማንበብ፣ ለማምለክ እና ጸሎt ለማድረስ ግንቡን ይጎበኛሉ። ቤተ መቅደስ በመካከላቸው እንዲኖራቸው የሚያቀርቡት ተማጽኖ በቀን ተቀን ሕይወታቸው፣ በእያንዳንዱ ጸሎታቸው ውስጥ አለ፤ ይህም የቃል ኪዳን ቤት ናፍቆት ነው። ቅንዓታቸውን አደንቃለሁ።

ከእስራኤል ወደ አገሬ ከተመለስኩኝ በኋላ፣ በዙሪያዬ የሚደረጉትን ቃልኪዳኖችን የሚመለከቱ ውይይቶች በቅርበት አዳምጥ ነበር። ሠዎች በቃል ኪዳን መንገድ መጓዝ ያለብኝ ለምንድን ነው ብለው እንደሚጠይቁ አስተዋልኩኝ። ቃል ኪዳኖችን ለመግባት ወደ አንድ ቤት መግባት ያስፈልገኛልን? የተቀደሱ የቤተመቅደስ ልብሶችን የምለብሰው ለምንድን ነው? ከጌታ ጋር ለሚደረግ የቃል ኪዳን ግንኙነት ግብዓቶችን መመደብ አለብኝ? የእነዚህ ጥሩ እና አስፈላጊ ጥያቄዎች መልስ ቀላል ነው። ይህም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ምን ያህል ደረጃ ያለው ግንኙነት ማድረግ እንደምትፈልጉ ስለሚወስን ነው።18 ለእነዚያ በጣም የግል ለሆኑ ጥያቄዎች እያንዳንዳችን የየራሳችንን ምላሽ ማግኘት ይኖርብናል።

የእኔ እነሆ፣ ይህንን መንገድ መለኮታዊ እውቅና እንዳላትእና በጥልቅ እንደታመነች “እንደተወደደች የሰማያዊ ወላጆች ሴት ልጅ”19 20 ቅ እጓዛለሁ።21 እንደ ቃል ኪዳን ልጅ፣ ቃል የተገቡትን22 በረከቶች ለመቀበል ብቁ ነኝ። ከጌታ ጋር ለመራመድ መርጫለሁ23 እንደ ክርስቶስ ምስክር እንድቆምም ተጠርቻለሁ24 መንገዱ ከባድ እንደሆነ ሲሰማኝ፣ በሚያስችል ጸጋ እጠነክራለሁ።25 ቤተመቅደስ በገባሁኝ ቁጥር ከእርሱ ጋር ጥልቅ የሆነ የቃል ኪዳን ግንኙነት ይኖረኛል። በመንፈሱ ተቀድሻለሁ26 የእርሱ ሀይል ተሰጥተውኛል27 እንዲሁም መንግስቱን ለመገንባት ተለይቻለሁ።28 ቀን ተቀን ንስሐ በመግባት ሂደት እና በየሳምንቱ በቅዱስ ቁርባን በመሳተፍ፣ ጽኑ እና የማይነቃነቅ29 ለመሆን መልካም30 እያደረኩ መሄድን እየተማርኩኝ ነው። ይህንን መንገድ የምጓዘው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር፣ ዳግም እንደሚመጣ ቃል የተገባበትን ቀን በመጠበቅ ነው። ከዚያምየእርሱ ሆኜ እታተማለሁ31እንዲሁም እንደ ቅዱስ 32የእግዚአብሔር ልጅ ከፍ ከፍ እደረጋለሁ።

ለዚህ ነው በቃል ኪዳን መንገድ ላይ የምጓዘው።

ለዚህ ነው ከቃል ኪዳን መንገዱ ጋር የምጣበቀው።

ለዚህ ነው ወደ ቃል ኪዳኑ ቤት የምገባው።

ለዚህ ነው የተቀደሱ የቤተ መቅደስ ልብሶችን እንደ ቋሚ የቃል ኪዳኖቼ አስታዋሽ የምለብሰው።

ምክንያቱም ከእርሱ ጋር ቁርጠኛ በሆነ የቃል ኪዳን ግንኙነት መኖር እፈልጋለሁ።

ምናልባት እናንተም ትፈልጋላችሁ። ባላችሁበት ጀምሩ።33 ያላችሁበት ሁኔታ እንቅፋት አይሁንባችሁ። በመንገዱ ላይ ያላችሁ ፍጥነት ወይም መንገዱን የጀመራችሁበት ቦታ እድገት የማድረግን ያህል አስፈላጊ እንዳልሆነ አስታውሱ።34 በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ ያሉ የምታምኗቸው ሰዎች ካወቁት አዳኝ ጋር እንዲያስተዋውቋችሁ ጠይቋቸው። ስለእርሱ ይበልጥ ተማሩ፡፡ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት ለግንኙነቱ ድጋፍ ስጡ፡፡ ዕድሜአችሁ ወይም ሁኔታችሁ ምንም ቢሆን ግድ የለም። ከእሱ ጋር መሄድ ትችላላችሁ።

የኢየሱስን መንገድ ከተጓዝን በኋላ፣ ማያ ገመዷን አልወሰደችውም። ከስኩተሬ ጋር እንደታሰረ ተወችው። በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ የወንድሞቼ ልጆች እና ጓደኛቸው በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ተራ በተራ ጎትተው ወሰዱኝ።35 የኢየሱስ ታሪኮች ያላመለጡኝ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ወደፊት ስለሚመጣው ትውልድ ጥንካሬ እንዳስታውስ አደረገኝ። ከእናንተ መማር እንችላለን። መሪ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የማወቅ ልባዊ ፍላጎት አላችሁ። ከእርሱ ጋር የሚያስተሳስረንን የገመድ ጥንካሬ ታምናላችሁ። ሌሎችን ወደ እርሱ የመሰብሰብ ተሰጥኦ አላችሁ።36

እንደ እድል ሆኖ፣ ይህን መንገድ በምንጓዝበት ድምፃችንን ከፍ አድርገን የማበረታቻ ቃላት እየተለዋወጥን አብረን እንጓዛለን።37 ከክርስቶስ ጋር ያለንን የግል ተሞክሮዎች ስናካፍል፣ የግል አምልኮታችንን እናጠናክራለን። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. የሄኖክ ሕዝቦች ፣መንገድ ስተዋል፣ ክርስቶስን ክደዋል፣ በጨለማ የራሳቸውን ምክር ፈልገዋል (ሙሴ 6፥27–28 ይመልከቱ)። በሰው ልጆች ላይ የነበረውን እምነት ባጣ ጊዜ መመሪያ ለማግኘት ፊቱን ወደ ጌታ መለሰ። ይህ የሄኖክ ጥሪ ጌታ ለሁላችን የሚያደርገው ተመሳሳይ ጥሪ ነው “ከእኔ ጋር ተራመዱ” (ሙሴ 6፥34፤ ደግሞም ማቴዎስ 11፥28 ይመልከቱ።) ነገር ግን ምናልባት ባላችሁበት ሁኔታ ምክንያት ይህንን መንገድ መጓዝ ስለመቻላችሁ እርግጠኛ አትሆኑ ይሆናል። በሆነ መንገድ እንቅፋት እንደተጋረጠባችሁ ይሰማችሁ ይሆናል። ምናልባት በቃል ኪዳኑ መንገድ መጓዝ የሚያስፈልገን ባለንበት ሁኔታ ምክንያት ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱም በሆነ መንገድ እንቅፋት ስለተጋረጠብን እና የእርሱን እርዳታ ስለምንፈልግ ሊሆን ይችላል።

  2. ሙሴ 6፥23–34 ይመልከቱ።

  3. “Jesus of Nazareth, Savior and King,” መዝሙር፣ ቁጥር. 181 ይመልከቱ።

  4. ኤተር 12፥27 ይመልከቱ

  5. ማቴዎስ 11፥28-30 ይመልከቱ።

  6. ሴት ልጆቼ በየማለዳው ይህንን ባለ አምስት ጣት ቃል ለልጆቻቸው (ለልጅ ልጆቼ) በሹክሹክታ መናገር ይፈልጋሉ—ይህም የሰማይ አባት ስለ እያንዳንዱ ልጆቹ በመለኮታዊ እንደሚያውቅ ማስታወሻ ነው።

  7. ዘፍጥረት 28፥10–22 ይመልከቱ። የአብርሃም ቃል ኪዳንም የዚያ ምሽት ዋና አጽንዖት ነበር። እነዚህ የአብርሃም ቃል ኪዳን ክፍሎች በሕይወታችን ውስጥ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ ማዕከላዊ ሚና ይጫወታሉ፡- 1. የዘላለማዊ ውርስ ተስፋ(ቁጥር 13)፤ 2. ዘላለማዊ ዘር (ቁጥር 14) እንዲሁም 3. የበረከት እና ሁሉንም የምድር ሕዝቦች የመባረክ ኃላፊነት (ቁጥር 15)።

  8. መዝሙር 35፥3፤ ትኩረት ተጨምሯል። የያዕቆብ ወላጆች ሊገድለው ከነበረው ከዔሳው ራሱን እንዲያርቅ እና በቃል ኪዳኑ ውስጥ ሊያገባት የሚችለውን ሴት ለማግኘት እድል ያገኝ ዘንድ ከቤት እንዲወጣ መመሪያ ሰጡት።( ዘፍጥረት 27፥41–4528፥1–2, 5ይመልከቱ)።

  9. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን፣” ሊያሆና፣ ጥቅምት 2022 (እ.አ.አ)፣ 11።

  10. 2 ኔፊ 31፥20

  11. ዮሐንስ 5፥5 ይመልከቱ፣ የቤተሳይዳ መጠመቂያ ታሪክ።

  12. ማርቆች 5፥25 ይመልከቱ፣ የክርስቶስን ጨርቅ የነካችው ሴት ታሪክ።

  13. ማቴዎስ 14፥31 ይመልከቱ፣ ጴጥሮስ በውሃ ላይ የተራመደበት ታሪክ።

  14. “How Firm a Foundation፣” መዝሙር፣ ቁጥር 85ን ይመልከቱ።

  15. 1 ኔፊ 11፥16–33ይመልከቱ።

  16. ፊልጵስዩስ 1፥62፥13የሞርሞን ቃላት 1፥7 ይመልከቱ።

  17. ዮሀንስ 12፥32 ይመልከቱ።

  18. መንገድ አብዛኛውን ጊዜ እንደ አቅጣጫ አመላካች ወይም የርቀት መረጃ ሰጪ ባሉ ቁልፍ ባህሪያት ይገለጻል። በትክክለኛው መንገድ ላይ መሆናችሁን ወይም በትክክለኛው አቅጣጫ እድገት እያደረጋችሁ መሆኑን የሚረጋገጥበት መንገድ ነው። ግንኙነት ቁልፍ በሆኑ ባህርያት ሊገለጽ ይችላል። አንዳንዶቹ የሚጠበቅ ነገርን (ኤርሚያስ 29፥11ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥7 ይመልከቱ)፤ መገዛትን (ሞዛያ 3፥19አልማ 7፥2313፥28 ይመልከቱ )፤ ትህትናን፣ ታዛዥነት፣ ተዕግስትን፣ ራስን መስጠትን፣ እምነትን (ምሣሌ 3፥5 ይመልከቱ)፤ እንዲሁም ፍቅርን (ሮሜ 8፥31–39 ይመልከቱ) ያካትታሉ።

  19. የወጣት ሴቶች ጭብጭ፣” የወንጌል ቤተመጻህፍት፣ አትኮሮት ተጨምሯል፤ ደግሞም Bonnie H. Cordon, “Beloved Daughtersሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 67 ይመልከቱ።

  20. ዮሐንስ 4፥1–29 ይመልከቱ፣ በጉድጓዱ አጠገብ የነበረችው ሴት ታሪክ።

  21. አልማ 38፥1–3 ይመልከቱ።

  22. ዘሁልቁ 6፥23–27 ይመልከቱ።

  23. ኢያሱ 24፥22 ይመልከቱ።

  24. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥3 ይመልከቱ፣ የኤማ ስሚዝ ታሪክ።

  25. 1 ቆሮንቶስ 15፥9–10

  26. 2 ዜና መዋዕል 20፥1–17፣ በተለይ ቁጥር 14 ይመልከቱ።

  27. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥1–46 ይመልከቱ።

  28. 1 ሣሙኤል 16፥11–13

  29. አስቴር 4፥16 ይመልከቱ፣ የአስቴር ታሪክ።

  30. የሐዋሪያት ስራ 10፥38 ይመልከቱ።

  31. ኢሳይያስ 43፥1–5 ይመልከቱ።

  32. ዘዳግም 28፥1–9 ይመልከቱ።

  33. አንድ ጥሩ ጓደኛ በማንኛውም ግንኙነት ውስጥ የእርምጃ ጥሪ አስፈላጊ መሆኑን እንዳስታውስ አደረገኝ።

  34. ከክርስትን ኦልሰን ጋር የተደረገ ንግግር፣ መስከረም 2023 (እ.አ.አ)።

  35. ለማክ አስዎልድ፣ ለቻምደን አስዎልድ፣ ለ አሽተን ማቴኒ፣ ና ለጃክ በትለር፣ እኔን ስለጎተታችሁ አመሰግናለሁ።

  36. “የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ወጣቶች ዛሬ በምድር ላይ ባለው ታላቅ አላማ–የእስራኤል መሰብሰብ–ውስጥ እንዲሳተፉ በጌታ የወጣቶች ሻለቃ ውስጥ እንዲመዘገቡ እንደጋበዝኳቸው ታስታውሳላችሁ። ይህንን ግብዣ ለወጣቶቻችን ያቀረብኩት ከወትሮው በተለየ መልኩ ለሌሎች በመድረስ እና ያመኑትን አሳማኝ በሆነ መልኩ በማካፈል ችሎታ ስላላቸው ነው” (ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Witnesses, Aaronic Priesthood Quorums, and Young Women [ምስክሮች፣ የአሮናዊ ክህነት ቡድኖች፣ እና ወጣት ሴቶች]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 39)።

  37. “የእግዚአብሔር መንግስት … በሁሉም አቅጣጫ በሞት እንደተከበበች ከተማ ነች። እያንዳንዱ ሰው በግድግዳው ላይ ለመከላከል የራሱ ቦታ አለው እና ማንም በቆመበት ሌላ ሊቆም አይችልም፣ ነገር ግን ‘እርስ በርሳችን እንድንበረታታ ምንም የሚከለክለን የለም’” (Martin Luther, in Lewis William Spitz, The Renaissance and Reformation Movements [1987], 335)።