አጠቃላይ ጉባኤ
ከጀግናም በላይ
የጥቅምት 2023 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


10:8

ከጀግናም በላይ

ኢየሱስ ክርስቶስ ጀግናችን ብቻ ሳይሆን፣ ጌታችን እና ንጉሳች፣ አዳኝ እና የሰው ዘር ቤዛም እንደሆነ እመሰክራለሁ።

ከ1856 እስከ 1860 (እ.አ.አ)፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን አቅኚዎች ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆ ሲጓዙ ከ1 ሺህ ማይል (1600 ኪሎ ሜትር) በላይ ንብረታቸውን በእጃቸው ይጎትቱ ነበር። ከመቶ ስልሳ ሰባት ዓመታት በፊት በዚህ ሳምንት፣ በጥቅምት 4 ቀን1856 (እ.አ.አ) ፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ በኤድዋርድ ማርቲን እና በጄምስ ዊሊ የሚመሩ ሁለት የእጅ ጋሪ ኩባንያዎች አሁንም በመቶዎች የሚቆጠሩ ማይሎች ርቀት ከሶልት ሌክ ውጪ ሆነው እንደሚገኙ ሲያውቁ ተገረሙ፣ ክረምቱ በፍጥነት እየቀረበ ነበርና።1 በሚቀጥለው ቀን፣ ከዚህ በምንሰበሰብበት ብዙም ሳይርቅ፣ ፕሬዘደንት ያንግ በቅዱሳኑ ፊት ቆሙ እና እንዲህ አወጁ፦ “ብዙ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የእጅ ጋሪ እየጎተቱ ሜዳ ላይ ነው ያሉት እናም እዚ መምጣት ይኖርባቸዋል። … በሜዳ ላይ ያሉትን ሰዎች ሄዳችሁ አምጧቸው።”2

ከሁለት ቀናት በኋላ የመጀመሪያዎቹ የነፍስ አድን ቡድኖች የእጅ ጋሪ መስራቾችን ለመፈለግ ሄዱ።

የዊሊ ኩባንያ [Willie company] አባል ዋናው የነፍስ አድን ቡድን ከመድረሱ በፊት ስለነበረው ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታን ገለጸ። እንዲህ ሲል አካፈለ፣ “ሁሉም የሚጠፋ ሲመስል እና ለመኖር ምንም ምክንያት የሌለ ሲመስል… ከጠራ ሰማይ እንደሚወጣ ነጎድጓድ፣ እግዚአብሔር ጸሎታቸንን መለሰ። አዳኞች ምግብ እና እቃዎችን ይዘው ሲመጡ … ታዩ። … ስለዳንን እግዚአብHእኢርን አመሰገንን።”3

እነዚህ የነፍስ አዳኞች በከፋ የአየር ሁኔታ ውስጥ የገዛ ህይወታቸውን አደጋ ላይ በመጣል የተቻላቸውን ያህል ብዙ ሰዎች ወደ ቤት በሰላም በማምጣት ለመስራቾቹ ጀግኖች ነበሩ። ከእነዚህ መካከል አንዱ ጀግና ኤፍሬም ሀንክስ ነበር።

በጥቅምት አጋማሽ ውስጥ፣ ስለ እጅ ጋሪው አስቸጋሪ ሁኔታ ሳያውቅ ሀንክስ ሶልት ሌክ ሲቲ ውስጥ ወደሚገኘው ቤቱ እየተመለሰ ነበር እናም በምሽት ወቅት እንደዚህ በሚል ድምጽ ነቃ “የእጅ ጋሪው ሰዎች ችግር ውስጥ ናቸው፣ እና አንተ ትፈለጋለህ፣ ሄደ ትረዳቸዋለህን?”

ያም ጥያቄ በአእምሮው ውስጥ እያስተጋባ፣ ወደ ሶልት ሌክ ስቲ በፍጥነት ተመለሰ። እና ፕሬዘዳንት ሄበር ሲ ኪምቦል ለተጨማሪ በጎ ፈቃደኞች ያቀረቡትን ጥሪ ሲሰሙ፣ ሃንክስ በማግስቱ በብቻው ለማዳን ለመሞከር ተነሳ። በፍጥነት በመጓዝ፣ በመንገድ የነበሩትን ሌሎች አዳኞችን ቀደማቸው እና የማርቲን ኩባንያ [Martin company] ላይ ሲደርስ፣ ሀንክስ እንዲህ አስታወሰ፣ “ካምፓቸው ውስጥ ስገባ ያጋጠመኝ እይታ ከትውስታዬ ውስጥ መቼም አይፋቅም … [እና] ደንዳና ልብን ለመንካት በቂ ነበር።”4

ኤፍሬም ሀንክስ ከድንኳን ወደ ድንኳን እየሄደ የታመሙትን በመባረክ ቀናትን አሳለፈ። እንዲህ አለ፣ “ብዙ ጊዜ፣ የታመሙትን ስንባርክ እና ህመሙን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስንገሥፅ ታማሚዎቹ በአንድ ላይ ተሰብስበው ወዲያውኑ ያገግሙ ነበር።”5 ኤፍረም ሀንክስ ለእነዚያ የእጅ ጋሪ ፈር ቀዳጆች ለዘለአለም ጀግናቸው ነው።

ከዚህ አስደናቂ የማዳን ጋር በሚመሳሰል መልኩ በህይወታችን እና በታሪክ ሂደት ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ክስተቶች በተደጋጋሚ የግለሰቦች ወንዶች እና ሴቶች፣ እንዲሁም ታላላቅ አርቲስቶች፣ ሳይንቲስቶች፣ የንግድ መሪዎች እና ፖለቲከኞች፣ ውሳኔዎች እና ድርጊቶች ውጤቶች ናቸው። እነዚህ የተለዩ ግለሰቦች ብዙውን ጊዜ የጀግንነት ተግባራቸውን ለማክበር ሐውልቶችን እና መታሰቢያዎችን በመገንባት እንደ ጀግኖች ይከበራሉ።

ትንሽ ልጅ ሳለሁ፣ የመጀመሪያ ጀግናዎቼ አትሌቶች ነበሩ። የቀድሞ ትውስታዬ የዋና ሊግ የቤዝቦል ተጫዋቾችን የቤዝቦል ካርዶችን መሰብሰብ ነበር። እንደ ልጅ “ጀግኖችን ማምለክ” የሚያስደስት እና በየዋህነት የሚደረግ ሊሆን ይችላል፣ ለምሳሌ ልጆች በሃሎዊን በአል ላይ እንደሚወዷቸው ልዕለ ጀግኖች ይለብሳሉ። ምንም እንኳን ብዙ ችሎታ ያላቸውን እና አስደናቂ የሆኑ ወንዶችን እና ሴቶችን በችሎታዎቻቸው እና በአስተዋጽኦዎቻቸው ብናደንቅም እና ብናከብርም፣ እነሱ የሚከበሩበት ደረጃ ከመጠን በላይ ከሆነ፣ ልክ እንደ እስራኤል ልጆች የወርቃማ ጥጃን በሲና ተራራ ላይ እንደማምለክ ይሆናል።

እንደ ጎልማሶች ከዚህ በፊት የልጅነት በየዋህነት የሚደረግ የነበረው ጨዋታ የፖለቲከኞችን፣ የብሎገሮችን፣ የማህበራዊ ሜዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን፣ የአትሌቶችን ወይም የሙዚቀኞችን “ጀግኖች ማምለክ” “ከሚገባው በላይ [እንድናተኩር]” 6 ሲያደርገን እና በእውነት አስፈላጊ የሆነውን ነገር ማየት ሲያቅተን መሰናክል ይሆናል።

የእስራኤል ልጆች ችግር በጉዟቸው ላይ ወደ ቃል ኪዳን ምድር ያመጡት ወርቅ አይደለም፣ ነገር ግን ወርቁ እንዲሆን የፈቀዱት ጣኦት ነበር፣ ከዛ የአምልኳቸው ምልክት ሆነ፣ ቀይ ባህርን ከፍሎ ከባርነት ካወጣቸው ከያሕዌ ትኩረታቸውን አዞሩ። በጥጃው ላይ የነበራቸው ትኩረት እውነተኛውን በእግዚአብሔር ማምለክ ችሎታቸው ላይ ተጽዕኖ አሳደረ።7

ጀግናው—የእኛ ጀግና—አሁን እና ሁሌም፣ ኢየስስ ክርስቶስ ነው፣ እንዲሁም በቅዱሳት መፃሕፍት ውስጥ እንደሚገኘው እና በሕይወት ባሉ ነቢያቶች ቃላት አማካኝነት፣ ከእርሱ ትምህርቶች የሚያሰናክለን ማንኛውም ነገር ወይም ማንኛውም ሰው በቃልኪዳን መንገዱ ላይ እድገታችንን አሉታዊ በሆነ መንገድ ተጽዕኖ ያደርግበታል። ይህ አለም ከመፈጠሩ ጊዜ በፊት በሰማይ አባት የተነደፈው የማደግ እና እንደ እርሱ የመሆን እድላችንን የሚጨምረውዕቅድ ተግዳሮት እንደገጠመው ግልጽ ሲሆን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመለከትን።

ኢየሱስ ክርስቶስ የአባታችንን እቅድ በመከላከል መሪ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በአፈፃፀሙ ላይ እጅግ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። በሃጢያት አማካኝነት እያንዳንዳችን የሚኖረንን በራሳችን መክፈል የማንችለውን እዳ ለመክፈል ለአባት ምላሽ ሰጠ እና እራሱን “ለሁሉም ቤዛ [ለመስጠት]” ፍቃደኛ ሆነ።8

ፕሬዘደንት ዳለን ኤች. ኦክስ እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል፣ “በሰማይ አባታችን ዕቅድ ውስጥ የተዘረዘረውን ከምድራዊ ሕይወት ጉዞአችን እስከ ፍጻሜያችን የሚያስፈልገውን ሁሉንም ነገር [ኢየሱስ ክርስቶስ] አድርጎታል።”9

በጌተሰማኔ የአትክልት ስፍራ ውስጥ፣ ከአቅም በላይ የሆነ ተግባር ሲያጋጥመው፣ አዳኙ በድፍረት እንዲህ አለ፣ “ነገር ግን የኔ ፈቃድ አይሁን ያንተ እንጂ” እንዲሁም በህይወት የሚኖሩትን ሁሉ ሰዎች ህመሞች፣ በሽታዎች እና ሃጢያቶች በራሱ ላይ መውሰዱን ቀጠለ።10 ፍጹም በሆነ የታዛዥነት እና የቁርጠኝነት ተግባር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ከፍተኛውን በሁሉም ፍጥረት የጀግንነት ተግባር የሆነውን በእርሱ አስደናቂ ትንሳኤ በመጨረስ አጠናቀቀ።

በቅርቡ የጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ፣ ፕሬዘደንት ረስል አም. ኔልሰን እንደዚህ አስታውሰውናል፣ “ምንም አይነት ጥያቄዎች ወይም ችግርች ቢኖሯችሁ፣ መልሱ ሁል ጊዜም በኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት እና ትምህርት ውስጥ ይገኛል። ስለኃጢያት ክፍያው፣ ፍቅሩ፣ ምህረቱ፣ አስተምሮቱ፣ እና በዳግም ስለተመለሰችው የፈውስ፣ የእድገት፣ እና የማቀላቀል ወንጌሉ የበለጠ ተማሩ። ፊታችሁን ወደ እርሱ መልሱ! እርሱን ተከተሉ!”11 እኔም፣ “እርሱን እመርጣለሁ” በማለት እጨምራለሁ።

በውስብስብ አለማችን ውስጥ፣ ሕይወት ግራ የሚያጋባ እና ከአቅም በላይ ሲመስል ግልጽነትን ለማግኘት ወደ ማህበረሰቡ ጀግኖች መዞር ፈታኝ ሊሆነ ይችላል። እነሱ በወኪልነት የሚከፈሉባቸውን ልብስ እንገዛለን፣ እነሱ የሚድግፉትን የፖለቲካ አስተሳሰብ እንቀበላለን እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ ውስጥ እነሱ ያካፈሉትን ሃሳቦች እንከተላለን። ይህ ለተወሰነ ጊዜ መልካም ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን እንዲህ አይነቱ ጀግና አምልኮ የእኛ ወርቃማ ጥጃ እንዳይሆን መጠንቀቅ ይኖርብናል። ትክክለኛውን ጀግና መምረጥ ዘላለማዊ ውጤቶች አሉት።

ቤተሰባችን እንደ ሚስዮን መሪዎች ለማግልገል ስፔን ስንደርስ ለመከተል ከምንመርጣቸው ጀግኖች ጋር ዝምድና ያለውን ሽማግሌ ኒል ኤ. ማክስዌል የተካፈሉትን ጥቅስ አገኘን። እንዲህ ብለዋል፣ “የእግዚአብሔርን መንግስት ለመከተል መጀመሪያ ካልመረጣችሁ፣ በምትኩ የመረጣችሁት መጨረሻ ላይ ምንም ለውጥ አያመጣም።”12 ወንድሞች እና እህቶች፣ የንጉሶች ንጉስ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን በመምረጥ ነው የእግዚአብሔርን መንግስት የምንመርጠው። ማንኛውም ሌላ ምርጫ ከምድራዊ ሃይል ወይም ከወርቃማ ጥጃ ጋር እኩል የሆነን ነገር እንደመምረጥ ነው፣ እናም በመጨረሻም ያስወድቀናል።

በብሉይ ኪዳን የዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ፣ የትኛውን ጀግና መምረጥ እንደነበረባቸው በግልጽ ስላወቁት ስለ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብድናጎ ታሪክን እናነባለን … እናም ማንኛውንም የንጉስ ናቡከደነጾር ጣኦታት አልነበረም። በድፍረት እንዲህ ሲሉ አወጁ፦

“የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳት እቶን ያድነናል።

ነገር ግን ንጉስ ሆይ እርሱ ባያድነን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምከው ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ።”13

ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳስተማረው፣ “ብዙ አማልክት አሉ”14 እና እንድንሰግድላቸው፣ እንድናመልካቸው እና እንድንቀበላቸው የተጋበዝናቸው ብዙ ጀግኖች እንዳሉም ለመጨመር እፈልጋለሁ። ነገር ግን የዳንኤል ሦስቱ ወዳጆች እንደሚያውቁት፣ ለማድረስ ዋስትና ያለው አንድ ብቻ ነው—ምክንያቱም እሱ አስቀድሞ ስላለ እና ሁልጊዜም ስለሚኖር ነው።

ወደ ቃል ኪዳኑ ምድር ወደ እግዚአብሔር መገኛ መመለሻ ጉዟችን ውስጥ፣ ለእኛ ችግሩ ፖለቲከኛ፣ ሙዚቀኛ፣ አትሌት ወይም ቭላገር አይደለም፣ ይልቁንስ አዳኛችንን እና ቤዛችንን በመተካት የትኩረታችን ዋነኛ ነገር እንዲሆኑ ለመፍቀድ መምረጥ ነው።

በቤትም እንሁን በእረፍት ላይ፣ የሰንበት ቀንን ለማክበር ስንመርጥ እርሱን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን፣ እንመርጠዋለን። በቅዱሳት መጻህፍት እና በህይወት ባሉ ነቢያት ትምህርቶች አማካኝነት የእርሱን ቃላት ስንመርጥ፣ እርሱን እንመርጠዋለን። ቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ለመያዝ ስንመርጥ፣ እሱን ለመጠቀም ብቁ ሆነን ስንኖር እንመርጠዋለን። “በተለይም የሃሳብ ልዩነት ሲኖረን” ሰላም ፈጣሪዎች ስንሆን እና ተጨቃጫቂ ለመሆን አሻፈረኝ ስንል እርሱን እንመርጣለን። 15

ከኢየሱስ ክርስቶስ የበለጠ በጭራሽ ማንም መሪ የበለጠ ድፍረት አላሳየም፣ ማንም በጎ አድራጊ የበለጠ ደግ አልሆነም፣ ማንም የጤና ባላሞያ የበለጠ በሽታን አልፈወሰም እናም ማንም አርቲስት የበለጠ ፈጣሪ አልነበረም።

በጀግኖች አለም ውስጥ ሥጋዊ ለሆኑ ወንዶች እና ሴቶች ከቆሙ የመታሰቢያ ሐውልቶች እና ሙዚየሞች አንድ ከሁሉም ልቆ የሚቆም አለ። ኢየሱስ ክርስቶስ ጀግናችን ብቻ ሳይሆን፣ ጌታችን እና ንጉሳች፣ አዳኝ እና የሰው ዘር ቤዛም እንደሆነ እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. Studies devoted to the Willie and Martin handcart companies include LeRoy R. and Ann W. Hafen, Handcarts to Zion: The Story of a Unique Western Migration, 1856–1860 (1960); Rebecca Cornwall and Leonard J. Arrington, Rescue of the 1856 Handcart Companies (1981); Howard K. and Cory W. Bangerter, Tragedy and Triumph: Your Guide to the Rescue of the 1856 Willie and Martin Handcart Companies, 2nd ed. (2006); and Andrew D. Olsen, The Price We Paid: The Extraordinary Story of the Willie and Martin Handcart Pioneers (2006).

  2. Brigham Young, “Remarks,” Deseret News, Oct. 15, 1856, 252.

  3. John Oborn, “Brief History of the Life of John Oborn, Pioneer of 1856,” 2, in John Oborn reminiscences and diary, circa 1862–1901, Church History Library, Salt Lake City.

  4. Ephraim K. Hanks’s narrative, in Andrew Jenson, “Church Emigration,” Contributor, Mar. 1893, 202–3.

  5. Hanks, in Jenson, “Church Emigration,” 204.

  6. ያዕቆብ 4፥14

  7. ዘጸአት 32 ይመልከቱ።

  8. 1 ጢሞቴዎስ 2፥6፤ ደግሞም ማቴዎስ 20፥28ን ይመልከቱ።

  9. ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “What Has Our Savior Done for Us? [አዳኛችን ምን አድርጎልናል]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)።

  10. ሉቃስ 22፥39–44ን ይመልከቱ።

  11. ረስል ኤም. ኔልሰን፣ “The Answer Is Always Jesus Christ [መልሱ ሁል ጊዜም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)።

  12. Attributed to 18th-century English clergyman William Law; quoted in Neal A. Maxwell, “Response to a Call,” Ensign, May 1974, 112.

  13. ዳንኤል 3፥13–18ን ይመልከቱ።

  14. 1 ቆሮንቶስ 8፥5

  15. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “አስታራቂዎች ይፈለጋሉ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ.)፣ 98።