ቋሚ አጋራችን
እናንተ እና እኔ መንፈስ ቅዱስን ቋሚ አጋራችን ለማድረግ እድል አለን።
የተወደዳችሁ ወንድሞች እና እህቶች፣ በዚህ ጉባኤ ላይ በሚፈስ ራእይ ተባርከናል። የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋዮች የእውነት፣ የመበረታታት እና የአቅጣጫ ቃላትን ተናግረዋል እንዲሁም ይናገራለ።
በዚህ ጉባኤ ጌታ በመንፈስ ቅዱስ በኩል በግል እንደሚያነጋግረን ስለተሰጡት ምስክርነቶች ተነክቼ ነበር። ስንጸልይ እና የመንፈስን መነሳሻ ስናዳምጥ፣ ወደፊት በችግር እያደጉ ስለሚመጡ ቀናት የበለጠ ታላቅ እይታን እና በረከቶችን እናገኛለን።
የፕሬዘደንት ራስል ኤም ኔልሰንን ማስጠንቀቂያ እንደገና ሰምተናል፣ “በሚመጡት ቀናት ያለ መንፈስ ቅዱስ መመሪያ፣ ምሪት፣ መጽናኛ እና ቋሚ ከሆነ ተጽዕኖ በመንፈሳዊነት ተቋቁመን ለመቀጠል አይቻልም።”1
ያ ትንቢታዊ ማስጠንቀቂያ ልጆቼን፣ የልጅ ልጆቼን፣ እና የልጅ የልጅ ልጆቼን በመጪው አስቸጋሪ ቀናት ውስጥ ያንን ወሳኝ መመሪያ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ምን ማስተማር እንደምችል እንዳሰላስል አድርጎኛል።
ስለዚህ፣ ይህ የዛሬ መልእክት ወደፊት በሚመጡት አስደሳች ቀናት ውስጥ ከእነሱ ጋር በሌለሁበት ጊዜ ሊረዳቸው የሚችል ለዘሮቼ የተጻፈ አጭር ደብዳቤ ነው። እኔ ሊረዳቸው እንደሚችል የማውቀውን እንዲያውቁ እፈልጋለሁ።
በሚኖሩባቸው ቀናት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ዘላቂ የሆነ ተጽዕኖ እንዲኖረን ከእኛ ምን እንደሚጠይቅ በይበልጥ ለመረዳት ችያለሁ። ዛሬ መንፈስ ቅዱስ የቻልኩትን ያህል የዘወትር አጋር እንዲሆነኝ የመጋበዝ የራሴን የግል ልምድ እንድናገር በውስጤ አድሯል። ጸሎቴም እነርሱን ለማበረታታት መቻል ነው።
ስለሔልማን ልጆች፣ ስለኔፊ እና ሌሂ እንዲሁም አብረዋቸው ስለሚያገለግሉት ሌሎች የጌታ አገልጋዮች እንዲያሰቡ በማድረግ እጀምራለሁ። ሃይለኛ ተቃርኖዎችን ተጋፍጠዋል። ሓጢያተኛ በሆነ ቦታ ለይ እያገለገሉ ነበር እንዲሁም አስፈሪ ማታለያዎችን መጋፈጥ ነበረባቸው። የሔላማን በሆነው በዚህ መዝገብ አንድ ጥቅስ ውስጥ ድፍረትን አገኛለሁ፣ እና እናንተም ልታገኙ ትችላላችሁ።
“እናም በሰባ ዘጠነኛው ዓመት ኃያል የሆነ ጥል ተጀመረ። ነገር ግን እንዲህ ሆነ ኔፊና፣ ሌሂ፣ እናም ብዙዎቹ ወንድሞቻቸው ስለእምነቱ እውነት የሆነውን ነጥብ የሚያውቁት፣ በየቀኑ ብዙ ራዕዮችን ይመለከቱ የነበሩ፤ ስለሆነም ለህዝቡ ሰበኩ፣ በዚሁ ዓመት ሰዎቹ ጥሉን እንዲያቆሙ አደረጉ።”2
ይህ ታሪክ ያበረታታኛል፣ እናንተንም ሊያበረታታችሁ ይችላል። የሄለማን ልጆችተከታታይ በሆኑ ተሞክሮዎች በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ተምረዋል እንዲሁም ተመርተዋል። ይህ፣ የምንፈልገውን እና ከዚያም ዝግጁ ስንሆን ይበልጥ በመቀበል በመንፈሱ እና ከመንፈሱ በትዕዛዝ ላይ ትዕዛዝ ልንማር እንደምንችል ያረጋግጥልኛል።
በተመሳሳይ መልኩ ኔፊ የላባንን ሰሌዳዎች እንዲያመጣ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለስ በተጠየቀው ታሪክ ተበረታትቻለሁ። የመረጣቸውን አስታውሱ። እንዲህ አለ፣ “እሄዳለሁ እና ጌታ የዘዘኝንም ነገሮች አደርጋለዉ።”3
ካለፈው ልምዴ እና እንደ አቅሜ ካየሁት በላይ በሚመስሉ፣ ነገር ግን ከጌታ የተሰጡ ተግባራት እንደሆኑ በማውቃቸው ስራዎች ላይ ስሳተፍ፣ ኔፊ በዚያ ተልዕኮ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የነበረው ልምድ ብዙ ጊዜ ድፍረትን ሰጥቶኛል።
ኔፊ ስለ ልምዱ የተናገረውን ታስታውሳላችሁ፡ “እና ይህም በምሽት ነበር፤ እራሳቸውን ከግንቡ ውጪ እንዲደብቁ አደረኳቸው። እነርሱም ራሳቸውን ከደበቁ በኋላ እኔ ኔፊ ወደ ከተማው ሾለኩና፣ ወደ ላባን ቤት ሄድኩ።
እንዲህም በማለት ቀጠለ፡ “እናም ማድረግ ያለብኝን ነገሮች ቀድሜ ሳላውቅ በመንፈስ ተመራሁኝ።”4
ኔፊ በጌታ የተልእኮ ስራ ላይ በየደቂቃው በመንፈስ መመራቱን በማወቄ ተበረታትቻለሁኝ።
የመንፈስ ቅዱስ ቋሚ አጋርነት ያስፈልገናል፣ እናንተም ያስፈልጋችኋል። አሁን፣ እንፈልገዋለን፣ ነገር ግን ለማግኘት ቀላል እንዳልሆነ ከተሞክሮአችን እናውቃለን። መንፈስን የሚያስከፉ ነገሮችን ሁላችንም በየእለት ተእለት ህይወታችን እናስባለን፣ እንናገራለን፣ እናም እናደርጋለን።
ይህ በሚሆንበት ጊዜ፣ በጌታ ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለን ሊሰማን ይችላል። ብቸኛ እንደሆንን እንዲሰማን ልንፈተን እንችላለን። ንስሐ ስንገባ እና ቅዱስ ቁርባንን ስንቀበል በየሳምንቱ የምንቀበለውን “ሁልጊዜ መንፈሱ ከእነርሱ ጋር ይሆን ዘንድ”5 የሚለውን የተረጋገጠ ቃል ኪዳን ማስታወስ አስፈላጊ ነው።
የመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ ከተስማችሁ፤ የኃጥያት ክፍያው በህይወታችሁ እየስራ ስለመሆኑ እንደ አስደሳች ማስረጃ ውሰዱት።
ሽማግሌ ጄፍሪ አር. ሆላንድ እንዳሉት፡ “እነዚህ ከልክ ያለፉ ከባድ ጊዜያት በመጡ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ትቶናል ወይም ጸሎታችንን አይሰማም ለሚለው ፍራቻ መሸነፍ የለብንም። እርሱ ያዳምጠናል እርሱ ያየናል። እርሱ ይወደናል። ”6
ይህ ማረጋገጫ ረድቶኛል። ከጌታ እንደራቅኩኝ ሲሰማኝ፣ ለጸሎቶቼ የሚሰጡት መልሶች የዘገዩ ሲመስሉ፣ ንስሃ የመግባት እድሎች ይኖሩ እንደሆነ ህይወቴን እንድገመግም የፕሬዘደንት ኔልሰንን ምክር መከተልን ተምሬአለሁ። “የዕለት ተዕለት ንስሐ የንጽሕና እንደሆነ፣ ንጽህና ደግሞ ኃይልን እንደሚያመጣልን” ያስታውሱናል። 7
መንፈስ ቅዱስን መስማት ከባድ ሆኖ ካገኛችሁት፣ ንስሃ መግባት እና ይቅርታን መቀበል የሚያስፈልጋችሁ ነገር ካለ ልታሰላስሉ ትችላላችሁ።8 ለመንጻት ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ለማወቅ እናም ይበልጥ ቋሚ ለሆነ የመንፈስ ቅዱስ አጋርነት ብቁ ለመሆን በእምነት መጸለይ ትችላላችሁ።
የመንፈስ ቅዱስን አጋርነት መቀበል የምትፈልጉ ከሆነ፣ ለትክክለኛው ምክንያት ልትፈልጉት ይገባል። አላማዎቻችሁ የጌታ አላማዎች መሆን አለበት። ምክንያታችሁ በጣም እራስ ወዳድ ከሆነ፣ የመንፈስ ቅዱስን ማበረታቻዎች ለማዳመጥ እና ለመስማት ከባድ ሆኖ ታገኙታላችሁ።
ለእኔና እናንተ ቁልፉ አዳኙ የሚፈልገውን መፈለግ ነው። ምክንያታችን ንጹህ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር መነሳሳት አለበት። ጸሎታችንም “እኔ የምፈልገው ሁሉ አንተ የምትፈልገውን ነው። ፈቃድህ ይፈጸም” የሚል መሆን አለበት።
የአዳኙን መስዋትነት እና ለኔ ያለውን ፍቅር ለማስታወስ እሞክራለሁ። ከዚያም፣ ምስጋናን ለመስጠት ወደ ሰማይ አባቴ ስጸልይ፣ ፍቅር ይሰማኛል፣ ጸሎቴ እንደተሰማ እና ለእኔ እና ለምወዳቸው ምንም ምርጥ የሆነውን እንደምቀበል ማረጋገጫ አገኛለሁ። ምስክርነቴን ያጠነክረዋል።
መንፈስ ቅዱስ ከሚመሰክረው ነገሮች ሁሉ ለኛ በጣም ውዱ የሆነው፣ ኢየሱስ ህያው የእግዚአብሔር ልጅ፣ ክርስቶስ መሆኑን ነው። አዳኙ ይህን ቃል ገብቷል፣ ‘’፣“እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል። 3
ከአመታት በፊት፣ ከተበሳጨች እናት የስልክ ጥሪ ደረሰኝ። ሴት ልጇ ከቤት ርቃ እንደሄደች ነገረችኝ። ከሴት ልጇ ጋር ከነበራት ትንሽ ግንኙነት በመነሳት የሆነ ትልቅ ችግር እንደተፈጠረ ታወቃት። እንድረዳት ተማጸነችኝ።
የሴት ልጇ የቤት ለቤት አስተማሪ ማን እንደነበረ አወኩኝ። በዚያ ስም ይህ ከረጅም ጊዜ በፊት እንደሆነ ለማወቅ ትችላላችሁ። ደወልኩለት። ወጣት ነበረ። ሆኖም እሱ እና አብሮት ያገለግል የነበረው አጋሩ ሁለቱም ስለሴት ልጇ በመጨነቅ ብቻ ሳይሆን ሀዘን እና መከራን የሚያመጣ ምርጫ ልታደርግ እንደሆነ መገለጥን በማግኘት በምሽት ከእንቅልፋቸው እንደነቁ ነገረኝ። በዚያ የመንፈስ ቅዱስ ተነሳሽነት ብቻ እሷን ለማየት ሄዱ።
በመጀመሪያ፣ ስለ ሁኔታዋ ልትነግራቸው አልፈለገችም ነበር። በመንፈስ በመነሳሳት፣ ንስሃ እንድትገባና ጌታ ለሷ ያዘጋጀላትን መንገድ እንድትመርጥ ተማጸኗት። በመንፈስ አምናለሁ፤ ስለእሷ ሕይወት ያወቁትን ነገር ሊያውቁ የቻሉበት ብቸኛው መንገድ ከእግዚአብሄር የመጣእንደሆነ ተገነዘበች። አንዲት እናት ፍቅርየሚያሳስባትን ነገር ለሰማይ አባት እና ለአዳኙ አሳልፋ ሰጠች። ጌታን ለማገልገል ፈቃደኛ ስለነበሩ መንፈስ ቅዱስ ለእነዚያ የቤት ለቤት አስተማሪዎች ተልኮ ነበር። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ የሚገኘውን ምክር እና ቃልኪዳን ተከትለዋል፦
አንጀትህም ለሁሉም ሰው እና ለእምነት ቤተ ሰዎች በልግስና ይሞላ፣ እና ምግባረ በጎነትም ሳያቋርጥ አስተሳሰብህን ያሳምር፤ ከዚያም ልበ ሙሉነትህ በእግዚአብሔር ፊት እየጠነከረ ይሄዳል፤ እና የክህነት ትምህርትም በነፍስህ ላይ እንደ ሰማይ ጠል ትንጠባጠብልሀለች።
“መንፈስ ቅዱስም የዘወትር ባልንጀራህ ይሆናል፣ እና በትርህም የማይቀየርየፅድቅ እና የእውነት በትር ይሆናል፤ እና ስልጣንህም ዘለአለማዊ ስልጣን ይሆናል፣እና በማያስገድድ ዘዴም ይህም ወደ አንተለዘለአለም ይፈሳል።”10
ጌታ ቃልኪዳኑን እንደጠበቀ እመሰክራለሁ። መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ታማኝ የቃል ኪዳንን አባላት ለሆኑት እየተላከ ነው። አሁን፣ ልምዶቻችሁ ልዩ ይሆናሉ፣ መንፈስም ለእናንተ እንዲሁም ለምትወዷቸው እና ለምታገለግሏቸው ራዕይን እንድትቀበሉ ለእናንተ እምነት እና አቅም በሚመጥን በተሻለ መንገድ ይመራል። በራስ መተማመናችሁ እንዲያድግ በልቤ ሙሉ እጸልያለሁ።
እግዜአብሄር አብ ህያው እንደሆነ ምስክርነቴን እሰጣለሁ። ይወዳችኋል። እያንዳንዱን ጸሎታችሁን ይሰማል። መንፈስ ቅዱስ እንዲመራን፣ እንዲያጽናናን እና ስለ እውነት እንዲመሰክርልን ወደ እኛ፡ይልክልን ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አብ ጸልዩአል። አብ እና ተወዳጅ ልጁ በዛፎች ቁጥቋጦ ውስጥ ለጆሴፍ ሽሚዝ ተገልጠውለታል። ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ መፅሐፈ ሞርሞንን በእግዚአብሔር ሀይል እና ስጦታ ተርጉሟል።
የሰማይ መልእክተኞች የክህነት ቁልፎችን መልሰዋል። ፕሬዘደንት ረስል ኤም.ኔልሰን ለመላው ምድር የእግዚአብሔር ነቢይ ናቸው።
እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር፣ ህያው እንደሆኑ እና ቤተክርስቲያኗን እንድሚመሩ አውቃለሁ። እኔ እና እናንተ አዳኙን ባስታወስን እና በወደድን ጊዜ፣ ንስሃ ስንገባ፣ እናም ፍቅሩ በልባችን እንዲሆን በምንጠይቅበት ጊዜ ስለእነዚህ እውነታዎች ማረጋገጫ እናገኝለን እንዲሁም መንፈስ ቅዱስን እንደ ቋሚ አጋራችን የማግኘት እድሉ አለን። ያም በረከት እና የመንፈስ ቅዱስ ጋራነት በዚህ ቀን እና በህይወታችን ቀናት በሙሉ እንዲኖሩን እጸልያለሁ። እወዳችኋለሁ። በተቀደሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።